#የአይኔ_ማረፊያዬ_ጁነይድ
ከኢማም ጁነይድ ደቀ መዛሙርት አንዱ በሼይኹ አልተደሰተም ነበር፤ ከመድረሻው ላይ መድረሱን በማሰብ ጥሎቸው ሄደ ይባላል። አንድ ቀን ሸይኹን ለመፈተን ተመለሰ። ኢማም ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ በልቦናው ያለውን ያውቁ ነበር። ኢማም ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- “መደበኛ ወይስ መንፈሳዊ መልስ ትፈልጋለህ?” እሱም “ሁለቱንም እፈልጋለሁ” አለ።
ኢማሙ ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡- “የትኛውም ደረጃ ላይ ብትደርስ ኖሮ ልትፈትነኝ ባልመጣህ ነበር። መደበኛው መልስ ይህ ነው። መንፈሳዊው መልስ፦ ከዊላያ ( ቅዱሳን) ጓራ አባርሬሀለሁ የሚል ነበር። ይህን እንደተናገሩ ደረሳው ፊቱ ወደ ጥቁር ተለወጠና፡- “ጌታ ሆይ! ይቅርታ፣ የነበረኝን የኢማን (የእምነት) ጣፋጭነት አጣሁ። በደግነት ይቅር በሉኝ" ሲል ለመነ፤ ኢማሙ ጁነይድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡- “የአላህ አውሊያዎች የአላህ ፀጋዎች ጠባቂ መሆናቸውንና የነሱን ብስጭት መሸከም እንደማትችል ረስተሃል። በዚህም መሰረት በሙሪዱ ላይ ተነፈሱበት እና የጠፋውን ሁሉ ወዲያውኑ መልሶ አገኘ፤ ለሞኝነቱ በእጅጉ ተጸጸተ።
@abduftsemier

#ተገላቢጦሽ
ኢብራሂም አድሀም ወደ በስራ በሄዱ ጊዜ ሰዎች መስጂድ ተሰብስበው ተቀበሏቸው ሰዎቹም ኢብራሂምን ጥያቄ ጠየቁ "ዱኣ ብናደርግም ዱኣችን ምላሽ አያገኘም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ንገሩን" አሏቸው። ኢብራሂም አድሀም አስር ምክንያቶችን ዘረዘሩ።
1፦ አላህን እወዳለሁ ትላላችሁ ነገር ግን ትዕዛዙን አትታዘዙም።
2፦ ቁርአን ታነባላችሁ ነገር ግን አትኖሩትም።
3፦ ነብያችንን እንወዳለን ትላላችሁ ግን መመሪያ አድርጋችሁ አትከተሎቸውም።
4፦ ሸይጣን ጠላታችን ነው ትላላችሁ እናንተ ግን የእርሱ ወዳጆች ናችሁ።
5፦ ጀነትን ትመኛላችሁ ግን ለእሷ ብቁ ለመሆን አትጥሩም።
6፦ ጀሀነምን እንፈራለን ትላላችሁ ግን እዚያ የሚያደርስ ስራ ትሰራላችሁ።
7፦ ሞት እውነት ነው ትላላችሁ ግን ለእሱ አትዘጋጁም።
8፦ በሁሉም ሰው ላይ ስህተት ታያላችሁ የራሳችሁን ግን አታዩም።
9፦ አብዝታችሁ ትበላላችሁ ነገር ግን ለእዚያም አላህን አታመሰግኑም።
10፦ በየቀኑ ሬሳ ትቀብራላችሁ ነገር ግን አትማሩበትም።
ሰሉ ዐለል ሀቢብ💚💚
اللهم صل على سيدنا محمد!
ውብ የዱኣ ለይል

#የነቢዩ_ﷺ_ብርሃን
አሏህ (ሱ.ወ) የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) የፈጠረው ከፍጥረት ሳይሆን ከስሙ “አን-ኑር” ነው። “አን-ኑር” ከሚለው ቃል የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና የፍጥረት ምስጢር ነው። ለነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንደ ቃል ወይም ምንነት ታየ፣ ከዚያም ሌሎች ውብ ስሞችና ባህሪያት ሁሉ መጀመሪያና ፍጻሜ ሳይኖራቸው ተራ በተራ ተገለጡ። አላህ (ሱ.ወ) በሰጣቸው ብርሃን ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) የነዚህን ሁሉ ውብ ስሞችና ባህሪያት ሚስጢር ለማየት ችለዋል እና ኡማቸውን አልብሰውላቸዋል። የአውሊያን እና የሊቃውንቱን ብርሀን እንደ አቅማቸው ሰጣቸው። ሰዎች እነዚህን ምስጢሮች እንዲያዩ እንዲመሩ እና እንዲረዳቸው የአላህ ወሊዮች ተሰጥቷቸዋል፣ መደበኛ ሰው ደግሞ አቅሙ ስለሚቀንስ ትንሽ ተሰጥቷል።
በቂያማ ቀን የአላህን (ሱ.ወ) ውብ ስሞች እንደ ብርሃን የለበሱት! የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ወዳጆችና ተከታዮች በመባል ይታወቃሉ አላህም (ሱ.ወ) ሲያያቸው ያውቃቸዋል።

"አስታራቂው_አህመድ!"
ቢስሚላሂ ብዬ መድሁን ልጀምረው፤
ስለ ዘይኔ ላውራ ስለዛ ደግ ሰው፤
ታማሚ ናፋቂ በየሀገሩ ሞልቷል፤
በመናም ለማየት አንቱን ይናፍቃል፤
መዲና መርገጥን ሁሉም ተመኝቷል፤
አንቱ ያ ሙስጠፋ አሽረፉል ሹረፋ፤
ዝናዎት የጎላ ውዴታው የሰፋ፤
እኛም ለመጠጋት እርሷ ጋር ለመድረስ፤
በሳዳቶቹ በኩል ጉዞ ስንገሰግስ፤
ከአብሬት ጀምረን ሼኽ መህሙድ ድረስ፤
በነዚህ ሰዎች ነው የልባችን ሚደርስ።
መጀን በሰይዲ በገውስ አብዱልቃድር፤
ትንሹም ትልቁ ለሱ ገብቶ ሚያድር፤
መጀን በሀሰነል በስሪ መገን በቢያዚድ፤
አሳምረው ሰፉት የሱፊዩን መንገድ፤
መጀን በጋዛሊ መገን በሩሚው ጀላሉዲን፤
የእውቀት አብነት ያበጁ ኪታቡን፤
መጀን በረመዳን ቡጢ መገን በጁነይድ፤
የጠላትን መሰረት ገንድሶ የሚንድ፤
መጀን በሼህ ካባኒ መገን በሼህ ናዚም፤
ፈጥነው ያደርሳሉ ሀድራውን ለሚያልም፤
መጀን በቡራኢ መገን በሼህ መህሙድ፤
ሁልጊዜ እንኑር በሙሀባው ስንነድ፤
መጀን በኔው በአለቃዬ ዩኑስ ኤምሬ፤
የግጥሙ ሰዳሪ የቅኔ መምህሬ፤
ላንቱ ገብቻለው ባንቱ ነው ማማሬ።
መጀን በአልፈቂህ መገን በአባድር፤
የተቅዋቸው ፅናት ፆም የማያሳድር፤
መጀን በራያ ሙፍቲ መገን በጀማ ንጉስ፤
ሲጠሯቸው ጊዜ በቶሎ የሚደርስ፤
መጀን በወረዋዩ መገን በቃጥባሪዩ፤
ህይወታቸውን ሙሉ በዲኑ የሰዩ፤
መጀን በአህመድ በደዊ መገን በዳኖቹ፤
ሀድራቸው የሚያጠገብ ለሁሉ የሚመቹ፤
መጀን በሼህ አሊ መገን በጫሌ፤
ለአቅል የከበዳ ስራቸው አያሌ፤
መጀን በሼህ ኢልያስ መገን በኑርሁሴን፤
ስማቸው ሲነሳ ሸረኛ የሚያበን፤
መጀን በገዳባኖ መገን በአልከሶ፤
ሀይባቸው ያማረ ከላማቸው ለስልሶ፤
መጀን በዘመናችን ኡስታዝ ፈድሉ፤
የመውሊድ አጋፋሪ እውቀት የሚያበሉ፤
መጀን በአብሬቶች መገን በሚቅባስ፤
ከሙስጠፋ ዘንዳ በቶሎ የሚያደርስ።
መጀን በፋጢማ መገን በእናቴ አሚና፤
በጀነት አለቆች ሀሳባችን ይቅና፤
መጀን በአኢሻ መገን በረሱል ሚስቶች፤
ከፊልስጤም ምድር ይሰማ የምስራች፤
መጀን በአሲያ መገን በመርየም፤
ለጀነቱ ሰርግ ሁሉ ሰው ይታደም፤
መጀን በኔ ራቢዓ መገን በሰይዳ ነፊሳ፤
የአላህ ሙቀረብ ዱኣቸው በላዕ ሚያነሳ፤
መገን በአውገረድ ሀዋ መገን በዙለይካ፤
ልባችን በፍቅር ያብብና ይፍካ፤
መጀን በሴቶች ሁላ መገን በእንስቶች፤
ዱኣችን ይሰማ ያድርገን ማንሰለች።
መጀን በአባቶች መገን በእናቶች፤
አድርገን ጌታዬ ለሰይዲ ምንመች፤
መጀን በአውሊያው አለምን በሞሉት፤
ወራሾች ተደርገው ከላይ በተሰጡት።
በነዚህ ሁሉ ወዳጆቻችሁ ብለናል፤
ዛሬ ከሀድራችሁ መታደም ሽተናል፤
ከሰይዲ ሚቅባስ በኩል ለምነናል፤
በሼህ መህሙድም ደብዳቤ ልከናል፤
በሙፍቲ ዑመር ቶሎ አስከትለናል፤
ሰይዲ ለወዳጅ አያውቁምና እንቢ፤
እኛንም አዝልቁን ከመዲናው ግቢ፤
ከረውዷው እንፍሰስ ሁኑልን ዋቢ፤
ወዳጅ አድርጋችሁ ምረጡን እድሉን፤
ከሀድራችሁ ስብሰባ እኛንም ሰብስቡን፤
በባለከራማው ጠላት በሚያርዱት፤
በሙፍቲ ዑመር በኩል ቪዛ ይስጡት፤
እኛም እንደነሱ በከንቱ አንሙት፤
በዘንድሮው አመት ታሪክ ይመዝገብ፤
ሀጅ የምናደርግበት ይሁንልን ያረብ፤
ሌላ ወሬ የለን ስላንቱ ነውንጅ፤
እንዲው እንደናፈቀን ሳናይ እንዳናረጅ፤
በመካ መዲና አስጉዘን መውላና፤
ሁሉ ባንተ ነው የጠመመው ሚቃና።
አሚን!!!!
@abduftsemier
@abduftsemier
ቢስሚላሂ ብዬ መድሁን ልጀምረው፤
ስለ ዘይኔ ላውራ ስለዛ ደግ ሰው፤
ታማሚ ናፋቂ በየሀገሩ ሞልቷል፤
በመናም ለማየት አንቱን ይናፍቃል፤
መዲና መርገጥን ሁሉም ተመኝቷል፤
አንቱ ያ ሙስጠፋ አሽረፉል ሹረፋ፤
ዝናዎት የጎላ ውዴታው የሰፋ፤
እኛም ለመጠጋት እርሷ ጋር ለመድረስ፤
በሳዳቶቹ በኩል ጉዞ ስንገሰግስ፤
ከአብሬት ጀምረን ሼኽ መህሙድ ድረስ፤
በነዚህ ሰዎች ነው የልባችን ሚደርስ።
መጀን በሰይዲ በገውስ አብዱልቃድር፤
ትንሹም ትልቁ ለሱ ገብቶ ሚያድር፤
መጀን በሀሰነል በስሪ መገን በቢያዚድ፤
አሳምረው ሰፉት የሱፊዩን መንገድ፤
መጀን በጋዛሊ መገን በሩሚው ጀላሉዲን፤
የእውቀት አብነት ያበጁ ኪታቡን፤
መጀን በረመዳን ቡጢ መገን በጁነይድ፤
የጠላትን መሰረት ገንድሶ የሚንድ፤
መጀን በሼህ ካባኒ መገን በሼህ ናዚም፤
ፈጥነው ያደርሳሉ ሀድራውን ለሚያልም፤
መጀን በቡራኢ መገን በሼህ መህሙድ፤
ሁልጊዜ እንኑር በሙሀባው ስንነድ፤
መጀን በኔው በአለቃዬ ዩኑስ ኤምሬ፤
የግጥሙ ሰዳሪ የቅኔ መምህሬ፤
ላንቱ ገብቻለው ባንቱ ነው ማማሬ።
መጀን በአልፈቂህ መገን በአባድር፤
የተቅዋቸው ፅናት ፆም የማያሳድር፤
መጀን በራያ ሙፍቲ መገን በጀማ ንጉስ፤
ሲጠሯቸው ጊዜ በቶሎ የሚደርስ፤
መጀን በወረዋዩ መገን በቃጥባሪዩ፤
ህይወታቸውን ሙሉ በዲኑ የሰዩ፤
መጀን በአህመድ በደዊ መገን በዳኖቹ፤
ሀድራቸው የሚያጠገብ ለሁሉ የሚመቹ፤
መጀን በሼህ አሊ መገን በጫሌ፤
ለአቅል የከበዳ ስራቸው አያሌ፤
መጀን በሼህ ኢልያስ መገን በኑርሁሴን፤
ስማቸው ሲነሳ ሸረኛ የሚያበን፤
መጀን በገዳባኖ መገን በአልከሶ፤
ሀይባቸው ያማረ ከላማቸው ለስልሶ፤
መጀን በዘመናችን ኡስታዝ ፈድሉ፤
የመውሊድ አጋፋሪ እውቀት የሚያበሉ፤
መጀን በአብሬቶች መገን በሚቅባስ፤
ከሙስጠፋ ዘንዳ በቶሎ የሚያደርስ።
መጀን በፋጢማ መገን በእናቴ አሚና፤
በጀነት አለቆች ሀሳባችን ይቅና፤
መጀን በአኢሻ መገን በረሱል ሚስቶች፤
ከፊልስጤም ምድር ይሰማ የምስራች፤
መጀን በአሲያ መገን በመርየም፤
ለጀነቱ ሰርግ ሁሉ ሰው ይታደም፤
መጀን በኔ ራቢዓ መገን በሰይዳ ነፊሳ፤
የአላህ ሙቀረብ ዱኣቸው በላዕ ሚያነሳ፤
መገን በአውገረድ ሀዋ መገን በዙለይካ፤
ልባችን በፍቅር ያብብና ይፍካ፤
መጀን በሴቶች ሁላ መገን በእንስቶች፤
ዱኣችን ይሰማ ያድርገን ማንሰለች።
መጀን በአባቶች መገን በእናቶች፤
አድርገን ጌታዬ ለሰይዲ ምንመች፤
መጀን በአውሊያው አለምን በሞሉት፤
ወራሾች ተደርገው ከላይ በተሰጡት።
በነዚህ ሁሉ ወዳጆቻችሁ ብለናል፤
ዛሬ ከሀድራችሁ መታደም ሽተናል፤
ከሰይዲ ሚቅባስ በኩል ለምነናል፤
በሼህ መህሙድም ደብዳቤ ልከናል፤
በሙፍቲ ዑመር ቶሎ አስከትለናል፤
ሰይዲ ለወዳጅ አያውቁምና እንቢ፤
እኛንም አዝልቁን ከመዲናው ግቢ፤
ከረውዷው እንፍሰስ ሁኑልን ዋቢ፤
ወዳጅ አድርጋችሁ ምረጡን እድሉን፤
ከሀድራችሁ ስብሰባ እኛንም ሰብስቡን፤
በባለከራማው ጠላት በሚያርዱት፤
በሙፍቲ ዑመር በኩል ቪዛ ይስጡት፤
እኛም እንደነሱ በከንቱ አንሙት፤
በዘንድሮው አመት ታሪክ ይመዝገብ፤
ሀጅ የምናደርግበት ይሁንልን ያረብ፤
ሌላ ወሬ የለን ስላንቱ ነውንጅ፤
እንዲው እንደናፈቀን ሳናይ እንዳናረጅ፤
በመካ መዲና አስጉዘን መውላና፤
ሁሉ ባንተ ነው የጠመመው ሚቃና።
አሚን!!!!
@abduftsemier
@abduftsemier
ቁርአንን የተመለከተ አጭር መረጃ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
=> ቁርአን የወረደው ለ23አመታት ነዉ።
=> ቁርአን በመካ ዉስጥ ለ13 አመታትወርዷል።
=> ለቁርአን መዲና ዉስጥ ለ10 ለአመታትወርዷል።
=> የቁርአን ክፍሎች(ጅዞች) 30 ናቸው።
=> የቁርአን ሂዝብ 60 ናቸው።
=> የቁርአን ምዕራፎች (ሱራዋች) 114ናቸው።
=> የቁርአን"ሩቡዕ" 240 ናቸው።
=> የቁርአን ስሞች ብዛት 77439 ናቸው።
=> የቁርአን አንቀፅ ብዛት 6236 ናቸው።
=> የቁርአን ፊደላት ብዛት 321250 ናቸው።
=> ከቁርአን ውስት ታላቁ ምዕራፍ (ሱራ)ሱረቱል አል-ፋቲሀ።
=> ከቁርአን ዉስጥ ትልቁ አንቀፅ (አያህ)አያተል አል-ኩርሲ።
=> ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ምዕራፍ (ሱራ)ሱረቱል አል-በቀራ ።
=> ረጅሙ የቁርአን አንቀፅ "አያተል ደይን"ሱረቱል አል በቀራ አንቀፅ 282 ነው።
=> ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ቃል"ፈአስቀይናሙሁ"የሚለው ነው።
=> ቁርአን አጭሩ ቃል "ጣሃ"የሚለው ነው።
=> የቁረአን ሲሶ የሆነውቃል ሱረቱል አል-ኢህላስ(ቁል ሁ ወላሁ አሃድ)ነው።
=> የቁርአን ቀልብ ነው ተብሎ የተነገረለት ሰራ(ሱረቱል ያሲን)ነው።
=> የቁራን ሙሽራ ነው ተብሎ የተነገረለት ሱራ(ሱረቱል -አል -አረህማን)ነው።
*አልሀምዱሊላህ *ስርዝ ድልዝ የሌለበትን ቁርአንን ለለገሰን አላህሱ•ወልናመሰግን ይገባል።
አላህ ሱ• ወ ቁርአንን እሱ እንዳወረደው እሱ እንደሚጠብቀው ተናግሯል።
ሰደቀላሁል ዐዚም

#ዘይኒ_ኩሊ_ዘይን
ክፍል አንድ
✍️አብዱ ኤምሬ
*የረቢዕ_መዳረሻ
በነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ህይወት ውስጥ የቀን ውሎ እናየለን
"በታሪክ ውስጥ በሃይማኖታዊም ሆነ በዓለማዊ ደረጃዎች ከፍተኛ ስኬት ያለው ብቸኛው ሰው ነበሩ."
ሚካኤል ሃርት ነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) “History 100: A Ranking of the Most Influential Persons” በሚለው መጽሐፉ ውስጥ ቁጥር 1 ላይ አስቀምጦቸዋል።
የኔ ነቢይ ልጅ፣ ባል፣ አባት፣ ጓደኛ፣ሰባኪ፣ ተመሪ፣ የሀገር መሪ፣ የጦር አዛዥ ነበሩ በህይወታቸው ውስጥ ባሳለፉት እያንዳንዱ ሚና ውስጥ ምርጥ ነበሩ። እነዚህን በርካታ ሚናዎች በሚያስደንቅ ሁኔታ እንዴት እንደሚመሩ ጠይቀህ ታውቃለህ? ምናልባት የእለት ተእለት ተግባራቸው ላይ ማስተንተን ብርሃን እንዲፈነጥቅ እና ለእያንዳንዳችን መነሳሳት ሆኖ ያገለግላል! የሚገርመው ነገር የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ህይወት ጥብቅ ልማድ አልነበረም። ይልቁንም ዓላማ ያለው እና የተባረከ ሥራ ነበር እናም የተደረገው ነገር በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጫ ነው። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእለት ተእለት ተግባር በጣም አስፈላጊው ባህሪ በአምስቱ የግዴታ የሰላት ሰአቶች ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር። የእሳቸው ቀናት እያንዳንዱ ክፍል ከፈጣሪ ጋር በሚያደርጉት መለኮታዊ ስብሰባዎች ላይ በሚያምር ሁኔታ የተቆራኘ ነበር። የበለጠ ለማወቅ እንሞክር!
#ፈጅር/ጠዋት
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በፈጅር አዛን (የሶላት ጥሪ) ከእንቅልፋቸው ተነሱ (በተለምዶ) የሌሊት ረዣዥም የተሀጁድ ሶላታቸውን ከሰገዱ በኋላ። ለጀመአዊ ፈርዶች ወደ መስጂድ ከመሄዳቸው በፊት የሱና ሶላትን በቤት ውስጥ ይሰግዱ ነበር።
ከፈጅር በኋላ ሰሃቦች እና እሳቸው አላህን (ሱ.ወ) ጀንበር እስክትወጣ ድረስ ያስታውሳሉ። አንዳንድ ጊዜ ወደ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) አጠገብ ይሰበሰቡ እና ከሳቸው ጋር ሞቅ ያለ፣ ውይይት ያደርጋሉ። በዚህ ወቅት ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ምክራቸውን ወይም ልምዳቸውን ያካፍላሉ ወይም አንዳንድ ጊዜ ሶሓቦች ከእስልምና በፊት ስላዩት ህልም ወይም ሕይወታቸው ይነጋገራሉ። በአጠቃላይ ከሶላት በኋላ ከባልደረቦቻቸው ጋር የሚያሳለፉት ጊዜ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር፣ ለማስተማር፣ ለመምከር፣ ለማስታወስ፣ ቅሬታቸውን ለመስማት እና በመካከላቸው ለማስታረቅ ይጠቀሙበት ነበር። ከዚህ በኋላ ለቁርስ ወደ ቤት ይመለሳሉ፤ ቁርስ ብዙውን ጊዜ ቀለል ያለ የተምር ወይም የወተት ምግብ ነበር እናም ይህ ከሌለ ይጾሙ ነበር።
የቀረውን የጠዋት ጊዜ በመስጂድ ውስጥ የእለቱን ዋና ዋና ተግባራትን ይፈፅሙ ነበር። እስልምናን ማስተማርን ይጨምራል። አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ለባልደረቦቻቸው ብዙ ጊዜ ረጅም ትምህርቶችን አይሰጡም ነበር። ይልቁንም የአድማጮቹን እውቀት እና ኢማን የሚያሳደጉ ውይይቶችን የሚያደርጉ ጥያቄዎች ያሏቸው አጫጭር ትምህርቶች ነበሩ። በኋላም ሴት ልጃቸውን ፋጢማ፣ ባልደረቦቻቸውን፣ የተቸገረን ወይም የታመመን ሰው ለመጠየቅ ይወጣሉ። በአንድ ሰው ከተጋበዙ ግብዣውን ተቀብለው ደስ እንዲላቸው እና ልዩ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ። ወይም በገበያ ውስጥ እየተዘዋወሩ በደስታ ለሰዎች ሰላምታ በመስጠት በዕለት ተዕለት ንግድ ላይ ፍትህ እንዲሰፍን ያደርጋሉ።
ይህ ከተደረገ በኋላ ለዱሃ ሶላት እና ለተወሰነ ጊዜ ከሚስቶቻቸው ጋር ወደ ቤት ይመለሳሉ። በዱሃ እና በዙህር አዛን መካከል ያለው አብዛኛውን ጊዜ ሚስቶቻቸው እሳቸውን ለማየት እና እርስ በርስ የመጋባት ግዴታቸውን የሚወጡበት አጋጣሚ ነበር። ይህን ተከትሎም ለጥቂት ጊዜ ትንሽ ቀትር ወስደው ከዙህር አዛን ይነቃሉ።
ይቀጥላል...

አይ ማማር
አይ ውበት
አይ ግዜ
አይ ዘመን....
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
''They bared their brains to heaven..'' ይላል allen የታላላቆቹን ሞት ማለፍ ከሰማ በኋላ!
የታላላቆቹ ማለፍ ምድር ላይ ለቀሩ ዋይታ
ለሰማይ ደግሞ ደስ የሚል ፈገግታ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ሚቀበሏቸውን ፣ ሚገናኟቸውን ማሰብ አካሄዳቸውን መከተል ያስመኛል።
እጆቻቸውን ይዞ ወደ ሚሄዱበት አብሮ መጎዝ...
ወደዛ ደስ ወደሚሉት ሰዎች...
የታላላቆቹ ማለፍ ታላቅ ሀዘን ብቻ ሳይሆን የሚጥልብን እነሱን የመከተል ፣ እነሱን የመፈለግ መሪር ናፍቆት ያሸክመናል።
ደጋጎቹ ሁሉ ጥለውን አንዲት ትንሽ ቦታ ይበሰባሉ።
እዚህ የኖሩትን ተሰብስበው ይደግሙታል።
ዘላለም የሚያምር ነገር መስራት አይደክማቸው እነሱ እንደሆነ...
እንደ ሰይዲ ሚቅባስ ያሉ ሰዎች በሰማይ እና በምድር መሀከል ያለውን ወግ የሚያገናኙ ድልድዮች ነበሩ።
ከእንግዲህ ስለ ትናንትና ማን ይነግረናል?
ስለ ደጋጎቹ ሰዎች ማን ያጫውተናል?
በህይወት ያሉት በአለፉት ይቀናሉ! ማለት ይሄ ነው።
😭 ላንቱ ሳይሆን ለራሴ ነው የማለቅሰው፤ ላንቱ እረፍት ለኔ ምሬት፤ ከእንግዲህ ሀበሻ ላይ የሚሆነው ነገር ያስጭንቀኛል... አላህዬ ተካልን😭
የታላቆች ልጅ ታላቅ ስብዕና፤
ሰይዲ ሚቅባስ የመድሁ መውላና፤
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሀገሩን ያቀና፤
በቀጣይ ሀገር ያስደሳችሁ አላሁ ረበና።

#ፖስታ_ቤት
ገበሬው ለማዳበሪያ መቶ ብር ቸገረውና ለአላህ ደብዳቤ ጽፎ ፖስታ ቤት አስገባ። የፖስታ ቤቱ ሠራተኛ የሁሉንም ደብዳቤ በየአድራሻው አስገብቶ የአላህ አድራሻ ቢጠፋው ፖስታውን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ። አንብቦም ከት ብሎ ሳቀ። በአጭሩ እንዲህ ይላል
"አንተ አላህ የማዳበሪያ ምንም የለኝም። ክረምቱ መጥቷል እስከዛሬ ወር መቶ ብር ላክልኝ። የማዳበሪያ ካላገኘሁ አላርስም ካላረስኩ አልዘራም ካልዘራሁ እኔም ቤተሰቤም በረሃብ እንሞትብሃለን ይህን ደግሞ አንተ አትፈልገውም።..."
የፖስታ ቤቱ ሠራተኛ ደብዳቤውን አንብቦ ካበቃ በኋላ እስቲ የዚህን የዋህ ገበሬ ጉድ ልይ ብሎ ከኪሱ 99 ብር አወጣና በፖስታ አሽጎ ገበሬው ሳጥን ውስጥ አስገባ። በወሩ ገበሬው አላህ እንደላከለት እርግጠኛ ሆኖ መጣ። ፖስተኛው ከሩቁ ተደብቆ ይከታተለው ጀመር። ገበሬው ፖስታውን ሲከፍት 99 ብር ሆነበት። መልሶ ሌላ ደብዳቤ ጻፈ።
"አንተ አላህ የላክልኝ ብር ደርሶኛል። አንተ የላከው መቶ ብር ነበር የፖስታ ቤት ሠራተኞች ግን አንድ ብር አጉድለዋል። ለወደፊቱ በነሱ በኩል አትላክልኝ ይሠርቁኛል።" ብሎ ጻፈ
😀😀😀😀

ክፍል ሁለት
✍አብዱ ኤምሬ
#ዙሁር/ከሰአት በኋላ
ከዙህር ሶላት በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጭርና ጥልቅ ንግግር ያደረጋሉ፤ ብዙ ጊዜ ከባልደረቦቻቸው ጋር ከእኩለ ቀን በኋላ እንቅልፍ ይተኙ ነበር። ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከባልደረቦቻቸው ጋር በነበሩበት ወቅት ሁሉ ከነሱ አንዱ ሆነው ይቆዩ እንደነበር ልብ ሊባል ይገባል። አንድ እንግዳ ሰው በእነዚህ ስብሰባዎች ውስጥ ነቢዩን መለየት አይችልም - በጎዳናዎች ውስጥ ሲራመዱ ከጓደኞቻቸው ቀድመው አይሄዱም ሲቀመጡም ተነጥለው አይቀመጡም። እያንዳንዱን ሰሀቦች ፈገግ ብለው እያናገሮቸው አስፈላጊ እና የተከበሩ ሆነው እንዲሰማቸው ያደርጉ ነበር።
ተግባራዊ ምክር ፡ ልክ እንደ ነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሁልጊዜም ትሑት መሆን እንልመድ። እያንዳንዱን ህዝባቸውን እንደ ልጆቻቸው ያውቃሉ። ለዚህም ነው የመካ ቃል አቀባይ የሆነው ኡርዋህ ኢብን መስዑድ ለቁረይሾች እንዲህ ያለው፡- “የቁረይሽ ሰዎች ሆይ፣ የዓለምን ነገስታት ከኪስራ እስከ ፋርስ ጎብኝቻለሁ፣ ወታደሮቻቸውንም አግኝቻለሁ። እንደ ሶሓቦች ለመሪያቸው ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያደሩ ግን በንጉስ ተከታዮች ዘንድ አንድም ታዛዥነት አይቼ አላውቅም!
#አስር/ምሽት
ከአስር ሰላት በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከውጪው አለም ጋር እምብዛም አይሳተፉም ነበር። ቀኑን ሙሉ ለሁሉም ጊዜ ይሰጡ ስለነበር፤ በዐስር እና በመግሪብ መካከል ያለው ጊዜ የቤተሰብ ጊዜ ነው። ቤት ውስጥ ቤተሰብ ያገለግሉ ነበር፡ ልብሶችን ያጥባሉ፣ ልብስ ይጠግናሉ፣ ጫማቸውን ይጠግናሉ። ሁሉም ቤተሰባቸው ለመነጋገር እና ስለማንኛውም ነገር ለመወያየት ይሰበሰቡ ነበር። በእነዚህ ውይይቶች ወቅት፣ ሁሉም ርዕሰ ጉዳዮች በጠረጴዛው ላይ ይነሱ ነበር ነገር ግን በግልጽ፣ እምነትን እና መሻሻልን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ።
ተግባራዊ ጠቃሚ ምክር ፡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ቢኖርም ቤተሰብህን ፈጽሞ አትርሳ። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በምድር ላይ የነበራቸውን መለኮታዊ ተልእኮ ቢያሟሉ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን ኢስላማዊ ግዛት ጉዳዮችን ቢያስተዳድሩም ለቤተሰባቸው ጊዜ ይሰጡና ይንከባከቡ ነበር። ስለዚህ በሥራ ጫና ወይም በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ቤተሰቦቻችንን ችላ ማለት አለብን?

#ዙል_ጀላል
ሙሳ (አ.ሰ) አላህን እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፦ "ጌታዬ ሆይ ደካሞች ከጠንካሮች እንዴት መብታቸውን ማስመለስ ይችላሉ?"
ኃያሉ አላህም "ከሰአት በሆላ እንደዚህ አይነት ቦታ በዚህ አይነት ቀን ሂድ... ደካሞች መብታቸውን ከጠንካሮች እንዴት እንደሚወስዱ ታያለህ!" አላቸው።
ሙሳም ወደ ስፍራው ሄዱ ከአንድ ተራራ ላይ ፏፏቴ ሲወርድ አዩ ሙሳም በአቅራቢያው ቁጭ ብለው መመልከት ጀመሩ፡ ከቆይታ ቡሀላ አንድ ፈረሰኛ ከፈረሱ ወርዶ ውሀ ፍለጋ ወደ ፏፏቴው አምርቷ ከጠጣና ከታጠበ ቡሀላ ይዞት የነበረውን ቦርሳ ረስቶ ሄደ...
ሙሳ ከቦታቸው አልተነቃነቁም ከቆይታ ቡሀላ አንድ ወጣት ባሪያ በአህያ ተጭኗ ወደ ፏፏቴው መጣ እስኪጠግብ ጠጣና ታጠበ ሁሉን ቻይ ለሆነው አላህም ምስጋና አቀረበ ሊመለስ ሲልም ከፏፏቴው አጠገብ አንድ ቦርሳ ተመለከተ ባሪያውም ቦርሳውን ከፍቷ ሲያይ ወርቅ ገንዘብና ውድ ጌጣጌጦች ይዟ ነበር ባሪያውም አላህን አመስግኗ ቦርሳውን ይዞ ሄደ።
ከትንሽ ቆይታ ቡሀላም አንድ ሽማግሌ ሊጠጣና ሊታጠብ መጣ እየታጠበም ሳለ ቦርሳውን የረሳው ፈረሰኛ እየሮጠ ወደርሱ መጣ ፈረሰኛው ለአዛውንቱ እንዲህ አላቸው፦ እዚህ የተውኩት ቦርሳ የት ነው ያለው? ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ "እኔ አላውቅም ቦርሳ አላየሁም.." ፈረሰኛውም ምንም ሳይናገር በንዴት ወዲያው በሰይፍ አንገታቸውን ቀላው።
ሙሳ (አ.ሰ) ይህን ሁሉ ከተለመከቱ ቡሀላ "ጌታዬ ሆይ ፈረሰኛው ሽማግሌውን በድሏል አሉ?" አላህም እንዲህ አለ: "ሙሳ ሆይ ሽማግሌው ከረጅም ጊዜያት በፊት የፈረሰኛውን አባት ገድሎ ነበር : የባሪያው አባት ደግሜ ለፈረሰኛው አባት ለሀያ አመታት አገልግሎ ምንም ክፍያ አላገኘም። ስለዚህ *ፈረሰኛው የአባቱን ገዳይ ሽማግሌውን በመገደል ሀቁን አገኘ : ባሪያውም አባቱ ሃያ አመት የለፋበትን ከፈረሰኛው አገኘ!"
"*ሊበድልህ አይችልም፤ ፍላጎቱም የለውም፤ ስትበደልም አያስችለውም... በቃ ከምትገምተው በላይ ይወድሀል።"

#የልብ_መድሀኒት 🌹
*ልባችን ለምን ይታወካል?”** አንድ ሙሪድ ጠየቀ።
ሼክ ናዚም መለሱ;
"ከጌታህ ጋር ያለህን ግንኙነት ስትረሳ፣ ምህረቱን ስትዘነጋ ነው የምትረበሸው። ሰዎች በምህረት ውቅያኖስ ውስጥ መሆናቸውን ሲዘነጉ ረብሻ እና መከራ ወደ ልባቸው ይገባል። ከውኃ እንደ ወጡ ዓሦች ናቸው። ደስተኛ ለመሆን ሁልጊዜ በምህረት ውቅያኖስ ውስጥ መሆንህን ማስታወስ አለብህ።"

ክፍል ሶስት
#መግሪብ/ጀምበር ስትጠልቅ
የመግሪብ ሶላትን ከሰገዱ በኋላ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እራት የሚበሉበት ጊዜ ነበር፤ ይህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የእሳቸው ሁለተኛውና ዋናው ምግብ ሰአት ነበር። ሰሀቦች አንዳንድ ጊዜ በቤታቸው ለእራት እና ውይይቶች ይሰበሰቡ ነበር። ምግብ በነብዩ ህይወት ውስጥ ቀላል ነገር ብቻ ነበር። ምግብን በጭራሽ አይነቅፉም፤ ካልወደዱት ምንም አይናገሩም። ቀለል ባለ መልኩ እንግዶቻቸውን ለጋስ አስተናጋጅ ነበሩ። በአቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) ሀዲስ ላይ እንደታየው ቡኻሪ እንደዘገቡት፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወተት አቅርበው እንግዳው፡- “በእውነት በላከህ እምላለሁ ለእርሱ ምንም ቦታ የለኝም” እስከሚል ድረስ እንዲጠጣ አዘዙት።
ተግባራዊ ጠቃሚ ምክር ፡ በዚህ ዘመን ምግብ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። መጥፎ የአመጋገብ ልማድ ለብዙ በሽታዎች መንስኤ ነው! ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለኡማዎቻቸው በመብላትና በመጠጣት ከሚመጡ በሽታዎች የሚከላከል ነገር አስተምረዋል። እንዲህ አሉ፡- “የአደም ልጅ እስኪጠግብ አይመገብ። ሲሶውን ለምግብ፣ ሲሶውን ለመጠጥ፣ ሲሶውን ለአየር።" ይህንን ትክክለኛ ሀዲስ በየቀኑ ለመከተል እንሞክር

ክፍል አራት
ኢሻ/አዳር
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የዒሻን ሰላት ያዘገዩት ነበር። ወደ ቤት በሚመሱስበት ወቅት በአንዳንድ ምሽቶች አስፈላጊና ፖለቲካዊ የሆኑ ነገሮችን ለመወያየት ሶሓቦቹን አቡበክርና ዑመርን ይጎበኛሉ፤ አልያም ወደ ቤት አቅንተው ከቤተሰባቸው ጋር ውይይት አድርገው ይተኛሉ። በመንፈቀ ለሊት ይነቁና የተሀጁድ ሶላትን ይቀጥላሉ። በሌሊቱ መገባደጃ አካባቢ ሚስታቸውን 'ዊትር' እንድትሰግድ ከእንቅልፍ ከቀሰቀሱና ከሰገዱ ቡሀላ እስከ ፈጅር አዛን ድረስ ትንሽ ያርፋሉ።
ተግባራዊ ጠቃሚ ምክር፡ ከኢሻ በኋላ በተቻለህ ፍጥነት ብትተኛ፤ በለሊቱ ክፍል ቢያንስ ሁለት የተሀጁድ ሶላትን ለመስገድ ሞክር። ሽልማቶቹ አስደናቂ ናቸው!
በዚህ ዘመን የተለያዩ የስራ ሰአቶችን እንደሚያጣብቡን ምንም ጥርጥር የለውም ተግባራችንም ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) በነዚያ ጊዜያት ከነበሩት የተለየ ነው። ያ ግን የእሳቸው፦ ምሳሌ ላለመከተል ሰበብ አይሆንም! ዛሬም ቢሆን በእለት ተእለት ተግባራቸው ውስጥ ነብያዊ ሱናን ማካተት የቻሉ እና ድንቅ፣ ስኬታማ እና ውጤታማ ህይወት የሚመሩ በርካታ ስኬታማ ሰዎች አሉ። ከእነዚያ ሰዎች አንዱ ለመሆን እንሞክር ኢንሻ አላህ!

#እድለኛው_ዑማ
በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ ሰለዋት ማውረድ ካለው ታላላቅ ጥቅሞቹ አንዱ አላህ (ሱ.ወ) ጭንቀትን ሁሉ ያስወግዳል። አንድ የሥነ አእምሮ ሐኪም ጓደኛዬ እንደነገረኝ ሦስቱ የአእምሮ ሕመም ከተለያዩ የጭንቀት ደረጃዎች ጋር ይዛመዳሉ። እና ጭንቀትን በተለያዩ መንገዶች ለመከላከል እና ለማስወገድ እጅግ በጣም ተግባራዊ የሆነ መንገድ ካገኘኋቸው አንዱ... በነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ላይ የተትረፈረፈ ሰለዋት እንደማውረድ ደስተኛ የሚያደረግ ነገር አላገኘሁም፤ ሰለዋት አብዝቷ ደስተኛ ያልሆነ ሰው አይቼ አላውቅም። ከነብዩ (ሰላለሁ አለይህ ወሰለም) በረከቶች ውስጥ አንዱ ደስተኛ መሆን ነው።
- ሼክ ያህያ ሮዱስ
የደስታ ሁሉ ምንጭ ውዴ የተባለው፤
አለሙን ሰማዩን ለሱ ያደረገው፤
ከሙሀመድ አሚን አንድ ምፈልገው፤
ከመዲናዋ ጋር ኖሬ መሞትን ከዛ ከሀድራው።

#ከሰይዲ_ማዕድ
ሰይድ ሚቅባስ ወጣት ሳሉ የመንግስት ሥራ ጀምረው ነበር። ሥራው ግን የአዕምሮ እረፍት አልሰጣቸውም። ይሄ ሥራ ከነቢ መንገድ ጋር አብሮ ባይሄድስ ብለው ይሰጉ ነበር። አንድ ቀን ስጋታቸው ባስ አለና ጉድ እንዳልሆን በሚል ጭንቀት ሲያለቅሱ ዋሉ። የዛን እለት ማታ ታድያ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረጋቸው በህልማቸው እንዲህ ሆነ። አንድ ሰውዬ ይመጣና "ረሱል ይፈልጉሃል!" ይላቸዋል። በፍጥነት ብድግ ብለው "መርሐባ መርሐባ የት ናቸው?" ሲሉ ወደ አንድ ክፍል አመላከታቸው። እየተጣደፉ ሲገቡ ክፍሉ ባዶ ነበር። ሌላ ክፍል ከፍተው ሲገቡ አንድ ሰው ወንበር ላይ ተቀምጦ አዩ። ያ ሰው ሰይድ አቡበክር ሲዲቅ ረ.ዓ ናቸው። ወለላው ነቢ ደግሞ በተፈጠሩበት፣ በተወለዱበት መልክ አልጋ ላይ አረፍ ብለዋል። ውዱን ሰው በተኸለቁበት መልክ ማየታቸው ሆዳቸውን ቢያማታው እያለቀሱ በእንብርክክ፣ በዳዴ፣ በእንፉቅቅ ወደ አልጋው ይንደረደሩ ጀመር። ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው የኔ ነቢ አፈፍ አደረጓቸውና "ያንተ ጀነት’ኮ ከእኔና ከአቡበክር ጋር ነው!" አሏቸው። ሲነቁ ህልም ነው። ሲነጋ ለባለቤታቸው ወስያ መስጠት እንደሚፈልጉ ይነግሯቸዋል። ምክንያቱን ሲጠይቋቸውም "በቃ እኔ ልሞት ነው!" ብለው ከህልሙ የተረዱ የመሰላቸውን ፍቺ ይነግሯቸዋል። ያንን ቀን ከነቢና ከአቡበክር ጎን እንደሚሆኑ ከዛ ማር አንደበት የሰሙትን ብስራት እያሰቡ ሲስቁ፣ ወዲህ ደግሞ ከአባታቸው መለየትን እያስታወሱ ሲያለቅሱ ዋሉ። በሁኔታቸው የተደናገጡትና የእሜቴ አዒሻ ሞክሼ የሆኑት ባለቤታቸው ዱዓ ብለው በግ አስመጡ። ሁነኛ ሰውም አስጠሩ። ሰይድ ሙሒቡ መጡና ምን እንደተፈጠረ ጠየቋቸው። ይሄኔ እናት አዒሻ ሰይዲ ህልም ማየታቸውንና እሞታለሁ ብለው ማሰባቸውን ነግረው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው ጠየቋቸው። ሰይድ ሙሒቡ "ህልሙን ልስማው" ብለው አጥብቀው ያዟቸው። ሰይድ ሙሒቡ ህልሙን ሲሰሙ ሳቁ። "ታድያ የዚህ መናም ፍቺ’ኮ እርስዎ እንዳሰቡት የሞት አይደለም። የመንግስት ሥራ ቀጥተኛውን መንገድ ያስተኛል ብለው ሲሰጉ ስለነበር ቀንዎ ሲደርስ ኺታምዎ የሚሆነው ከነርሱ ጋር መሆኑን ነግረው አይስጉ እያሉዎ፣ እያባሸሩዎ ነው።" አሏቸው። ደስታ ሆነ። ለዱዓ የታሰበው በግ ለሹኩር ታረደ። ለካ የዋሻውን እግረኛ ሲዲቁል አክበርን "አትዘን አላህ ከ’ኛ ጋር ነው" እንዳሏቸው አብሽር አንተ ከ’ኛ ጋር ነህ ብለው ቀድመው እያባሸሯቸው ኖሯል። ለነገሩ ጌትዬውስ በወለላው ቃሉ "ላኸውፉን ዓለይሂም ወላሁም የህዘኑን!" ያለው እነሱን አይደል? በሁለቱም ዓለም ፍርሃት የለባቸው፣ ጭንቅ አያገኛቸው!
✍ሰይደቲ_አቲቃ
አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም💚💚💚

#ጥበቃ
ታዋቂው የሀዲስ ዘጋቢ እና የሰሃባ ተማሪ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በአንድ ወቅት ከሰዎች ጋር እየተጓዙ ሳለ መሸባቸውና በወንዝ ዳርቻ ላይ ለማደር ወሰኑ። ማደሪያ ሲያዘጋጁ የአካባቢው ሰዎች ወደ እነርሱ ቀርበው እንዲጅ አሏቸው “ከዚህ ቦታ ሂዱ እዚህ ለማረፍ የሚሞክር ሁሉ ይዘረፋል። ይህንን ሲሰሙ ቡድኑ በሙሉ ዕቃውን ጠቅልለው ወደ ሌላ ቦታ ሄዱ - ከመሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በስተቀር። እሳቸው ባነበቡት የጥበቃ አያት በሚሰጠው ደህንነት በመተማመን ብቻቸውን ምንም ሳይፈሩ ቀሩ።
ከዚያም ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) የተከሰቱትን ክስተቶች እንዲህ ብለዋል:- “ወንበዴዎቹን ሳይ ገና አልተኛሁም። የተመዘዘ ሰይፍ ይዘው ነበር። ከሰላሳ ጊዜ በላይ ሊቀርቡኝ ቢሞክሩም መቅረብ አልቻሉም። ደህናና ሰላማዊ ሆኜ እስከ ጠዋት ድረስ በደንብ ተኛሁ። ሲነጋ እቃዬን ሰብስቤ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ስጓዝ ከዘራፊዎቹ አንዱ ግዙፍ የሆመ ቀስት ተሸክሞ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ቁጥቋጦ ውስጥ አጋጠመኝ። ጠራኝና “አንተ ሰው ነህ ወይስ ጂን?” ሲል ጠየቀኝ። "ሰው - ከአደም (ዐለይሂ ሰላም) ዘሮች" ስል መለስኩለት። ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡- “ግን ሚስጥርህ ምንድን ነው? ከ70 ጊዜ በላይ ልናገኝህ ብንሞክርም በብረት ግንብ ተዘጋግተናል። እኔም መለስኩለት፡- “ምስጢሩ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ከነብይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የነገሩኝ ሐዲስ ነው፡- “በሌሊት ሰላሳ ሶስት የቁርኣን አንቀፅ ያነበበ ከሰው ሸር ፤ ከአዳኝ አውሬ፤ በቤተሰቡና በሀብቱ ከሚደርስ አደጋ ይጠበቃል እስከ ማለዳ ድረስ ፍጹም ደኅንነት እና ምቾት ይኖረዋል።” ሐዲሱን ዘግቤ ስጨርስ ውስጡ በጣም ተነካ ከፈረሱ ላይ ወርዶ ቀስቱን ሰበረ። "በአላህ ተአላ ስም ዳግም ወደ ዘረፋ ህይወት እንደማይመለስ ቃል ገባ።"
በሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አንቀጾች፡-
1. ሱረቱ በቀራህ (ቁጥር 1-5፣ 255-257፣ እና 284-286)
2. ሱረቱ አዕራፍ (ቁጥር 54-56)
3. ሱረቱ በኑ ኢስራኢል (ቁጥር 110-111)
4. ሱረቱ ሳፋት (ቁጥር 1-11)
5. ሱረቱ ረህማን (ቁጥር 33-35)
6. ሱረቱ ሐሽር (ቁጥር 21-24)
7. ሱረቱ ጂን (ቁጥር 3-4)

#የረቢዕ_ሽታ
ውዳችን ላይ የለይል ሰላት ፈርድ ነበር፣ ለሊቱን እግራቸው እስኪሰነጠቅ ይቆማሉ፣ ሲደክማቸው አንድ እግራቸውን ከፍ ያደርጋሉ፣ ድጋሚ ሲደክማቸው አንዱን አሳርፈው፣ ሌላውን ያነሱና ይቀጥላሉ። ይህን የሚመለከተው አላህ በቁርአኑ እንዲህ አላቸው ...
"ጧ . ሓ ....
ቁርአንን ባንተ ላይ አንድትቸገር አላወረድንም።" ጧሃ÷1
ከዛም ከለሊቱ ትንሽ ማረፍ ጀመሩ!
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይኢ!
❤️አህለን ወሳህላ ያ ሙሸሪፈ ረቢዒ❤️

#ረቢዑል_ኑር
'ወማ አርሰናልካ ኢላ ራህመታን ሊል-አለሚን (ቁርኣን 21፡107)፣ "(ሙሐመድ ሆይ) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አላክንህም።" ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለዓለማት እዝነት ላካቸው።
“የመውሊድ ወር የቅዱስነታችን ወር ነው። ይህ የተቀደሰ በረካ የተሞላ ወር ኢንሻአላህ የመልካምነት መጠቀሚያ ይሆናል። ዘንድሮ ትንሽ ከብዶ አልፏል። ባለፈው አመት ይህን ያህል ጭቆና አልነበረም። ጭቆና በበዛ ቁጥር። ከዚህ በተቃራኒ ግን አላህ አዛ ወጀላ የነብያችንን ﷺ ወር የእዝነትና የበረካ ወር አድርጓታል።
ስለዚህ በዚህ ወር ሰለዋት ባደረግን ቁጥር በነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ “ሰለዋት ባደረግክ ቁጥር ‹ወአለይኩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም› በማለት ይመልሳሉ። አስር፣ አምስት፣ መቶ ወይም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ሰለዋት ቢያደርግ አላህ አዛ ወጀላ ለሁሉም ምላሽ እንዲሰጡ አስችሏቸዋል።
ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚያከብር አላህ ያከብረዋል። ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን የማያከብር ሰው የቅንጣትን ዋጋ የለውም፤ አላህ ﷻ ይጠብቀን። አላህ ﷻ ይህን የተቀደሰ ወር በረካ የተሞላ ያድርግልን፤ የተጨቆኑትንም ያድናቸው። አሚን!

#ማመን
በአንድ ወቅት ግመሉን ይዞ ከገበያ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሰው ነበር፤ ጥሩ ቀን በማሳለፉ፣ በመንገድ ላይ መስጂድ ሲመለከት ለአላህ ምስጋናውን ለማቅረብ ወሰነ።
ግመሉን ውጭ ላይ ትቶ የሶላቱን ምንጣፍ ይዞ ገባ፤ ለሰአታት አላህን በማመስገን እየፀለየ እና ወደፊት ጥሩ ሙስሊም እንደሚሆን፣ ድሆችን እንደሚረዳ እና የማህበረሰቡ ምሰሶ እንደሚሆን ቃል ሲገባ ቆይቶ፤ ሲወጣ ሰማዩ ጨልሞ ነበር፤ ውጪ ላይ የተዋትን ግመል ወዲህና ወዲያ እያለ ሲፈልግ አጣት!
ወዲያው ሰውዬው በሀይለኛው ተናደደና እጁን ወደ ሰማይ እየጠቆመ: -
"አላህ ሆይ! ይህን እንዴት ልታደርገኝ ቻልክ? ሙሉ በሙሉ በአንተ ታምኜ ሳለሁ ግመሌ ለምን ጠፋ?”
የሚያልፍ ሱፊ ደረሳ ሰውዬውን ሲጮህ ሰምቶ ለራሱ ሳቀ።
"ስማ ወዳጄ አላህን እመን ግን ግመልህን እሰር!"
ሞኝ ከፍ ሲል ትልቅነት ይመስለዋል፤
አወዳደቁ መክፋቱን መች ይረዳዋል፤
እኛም እንታረቅ ከሰይደል ውጁድ፤
በረቢዐል አወል በሀድራው እንመድድ፤
ጊዜው ለኛ ይሁን ዑመቱን እንካድም፤
አንቱን የጠየቀ እምቢ አይባልም፤
ያሰብነው ኒያ ተቅዋ ተጨምሮ፤
ሁሉም ይፈረጅ ሰይዲ ዘንድሮ!
*አላህ ታማኝ ነው፤ ግን ታምነህ ከልብህ የሰጠህውን ነው።
*አላሁሙ ሷሊ አላ ሀቢቡሏህ፤ ወአላ ኡመቲ ረሱሊላህ!