#ዝምታ_ክብር_ያመጣል 💪 #ስራህ_ይናገር 🥰
( ✍️ አቤል ደመላሽ )
ለረጅም ጊዜያት ለሕይወቴ የጠቀመኝ አንድ ነገር ቢኖር በዝምታ ስራ በዝምታ ኑር የሚለው መርሄ ነው ። ለብዙ ሰዎች አንተነትህን ብቻ እየገለጥክ እና እኔ ይህ ነኝ እንዲህ አለኝ በዚህ ወጣሁ በዚህ ገባው የምትል ከሆነ እመነኝ ምንም ያሳካኸው ነገር የለም ማለት ነው...ለዚህ ነው አልሸጥ እንዳለ ዕቃ በሄድክበት የሚያስለፈልፍህ...ሁሌ ዝም በል በዝምታም ስራ አንተ ስላንተ አትናገር...ሁሌም ኑሮህን ብቻ ቀጥል...ዓላማህን ኑር...ሰዎች ጋር ለመታየት አትጣር...እመነኝ ያኔ ነፍስህ ደስተኛ ትሆናለች ። እኛ የምንፈልገው ድል ማድረግን ከሆነ ለምን እወቁልኝ እናበዛለን ። ለብዙ ሰዎች ግር የሚላቸው ነገር የኔ የዝምታ ሕይወት ነው ። ምንም መንገድን ብሄድ በዝምታ እጓዛለሁ...በዚያ ሲገምቱኝ በዚህ ነኝ...ምንም መንገዴ እወቁልኝ የለውም...ስለዚህ የኔ ድል በጊዜው አፍ አውጥቶ ያወራል ። ለዚህ ነው የሚያውቁህ ሰዎች እንዲገምቱህ ዕድል ስጣቸው በሕይወትህ ግን አስደንግጣቸው የሚባለው...ለዓመታት የጠቀመኝ ነገር ሰዎች እርምጃዬን እንጂ ሩጫዬን አለማወቃቸው ነው ። ዛሬም እላለሁ...በዝምታ ስራ...በዝምታ ኑር...ተራ አስተሳሰብ ካላቸው ጋር ወርደህ አትመካከር...እንደ ልጅ ከሚያስቡ የወተት ዘመን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር አትወያይ...መልስም አትሰጣጥ...ወርደው ከሚያወርዱ ጋር አትዋል...ስትወድቅ ትተውክ ይሄዳሉና ጌታ ምን ይላል እንጂ ሰው ምን ይለኛል አትበል...ራስህን እና እግዚአብሔር የሚልህን ስማ...እመነኝ ይሄንን ስታደርግ የእግዚአብሔር ሞገስ እና ድል አድራጊ ሕይወት ያንተ ይሆናል ።
#እግዚአብሔር_ይባርካችሁ 🙏🥰
#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ይብዛልን

#መርካቶ_አሁንም_እየነደደች_ነው 🥺😭
ብዙዎች የለፉበት ንብረት እየወደመ ነውና በፀሎታችሁ አስቧቸው !
1 ሰዓት ላይ ከሸማ ተራ የጀመረው ቃጠሎ በከባድ ሁኔታ እየሰፋ ቀጥሏል ።
#እግዚአብሔር_ሆይ_እርዳቸው... #ከአደጋ_ይጠብቃችሁ 🙏

#መለየት_ለተሻለ_ሕይወት ... #ከማይመጥናችሁ_ተለዩ
( ✍️ አቤል ደመላሽ )
- በሕይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሰው አዕምሮ በመጠንቀቅ እና እገሌ ይከፋው ይሆን በማለት በይሉኝታ የምንቆይባቸው የማይመጥኑን ስፍራዎች ወይም ደግሞ ሰዎች ናቸው ። በተለይ ሕሊናችን የማይመጥነው ስፍራ እና ቦታ ላይ እንዳለን እየነገረን እምቢ ትክክል ነኝ በማለት አልያም ደግሞ ከዚህ ስፍራ ብሄድ እና ከእገሌ ብለይ ይከፉብኛል ብለን ስናለሳልስ በሕይወታችን የስህተትን መንገድ እንለምደዋለን ። ከዚያ በመላመድ ውስጥ ባለ ለማጅነት ራሳችንን በዚያ አይመጥነንም ባልነው ስፍራ ያለውን ድባብ መስለን እንቀራለን ። ሕይወታችሁ ትርጉም እንዲኖረው ከፈለጋችሁ የማይመጥናችሁ ስፍራ ላይ ለአዕምሯችሁ አጉል የትህትና ካባ እያለበሳችሁ አትሰንብቱ...ምክንያቱም ሳታውቁት እናንተም የዚያ ተራ ስፍራ እና ሕይወት ተካፋይ ትሆናላችሁ ። በቃ ማለትን እንልመድ...በተለይ ደግሞ እናንተ ልትሆኑ የሚገባችሁ እና አሁን እየሆናችሁ ያላችሁት ነገር ካልተጣጣመላችሁ በሕይወታችሁ ይህ ስፍራ አይመጥነኝም ለማለት ይሉንታ አይያዛችሁ ። ምናልባት የእናንተ መገኘት የሚጠበቅበት እና የምትካቡበት ስፍራ እንኳን ቢሆን የማይመጥናችሁ ከሆነ በይሉኝታ አትሰንብቱ ።
በቃ ማለትን ያለመደ ሰው ሁሌ በጎተቱት ገመድ ሁሉ እየተጎተተ አንዴ ሼም ይዞኝ ነው አንዴ ደግሞ እገሌ ይደብረዋል እያለ ሲያለሳልስ ሊሰራ ካለው ታላቅ ነገር እና በሕይወቱ ሊገለጥ ካለው መልካም ነገር ጋር ይተላለፋል ።
ሞቅታ...ጭብጨባ...እና ውዳሴ አያታላችሁ...
ይቅርታ አልችልም...አልያም አይመጥነኝም ማለትን ልመዱ...ያኔ በሰው የሚመራ ተራ ሰው ሳይሆን በራሱ ቆራጥ የሆነ ትልቅ ሰው ትሆናላችሁ ።

#የወንድም_ዮሴፍ_ሰቆቃ_ቀጥሏል..😭
የዚህ ዮሴፍ ተካ የተባለ ወጣት በሊብያ ስደት ላይ እያለ መታገቱን ከቤተሰቦቹ ሰምተን ወደ እናንተ ካደረስን በኋላ ነገሩን የሰሙ ብዙ ሰዎች አዝነዋል። ዮሴፍ አሁን በሊብያ እጅግ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በቀናት ውስጥ ገንዘቡ (1,200,000 ብር) ካልተከፈለ ሊገድሉት እንደሆነ አጋቾቹ በየቀኑ ለቤተሰቡ እየተደወሉ እየዛቱባቸው ይገኛሉ። ልጁ የተያዘበት ሁኔታም በጣም አስጨናቂ ነው። እናም ይሄን የምትመለከቱ ቅዱሳን የአቅማችሁን በዮሴፍ ታላቅ ወንድም በተከፈተ አካውንት
CBE,1000131261218 Desalagn Teka Tufa እንድትለግሷቸው በታላቅ የልብ ሀዘን ይማፀናሉ።
ስለነገሩ በማንኛውም መንገድ ማጣራት የምትፈልጉ፣ በሊብያም ሰው የምታውቁ ልናግዘው እንችላለን የምትሉ ሰዎች በውስጥ መስመር የቤተሰቦቹን ስልክ እንሰጣችኋለን...
እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ