Telegram Web
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአረካ ከተማ ለሚገነባው የቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ !

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]


ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በወላይታ ሀገረ ስብከት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ቤተ ክህነት አረካ ከተማ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ለሚገነባው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል።

ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ አረካ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉ ሲሆን በበዓሉ የተገኙ በርካታ ምእመናንን ወንጌል አስተምረው አባታዊ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው አሁን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን በማርጀቱ ምክንያት አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት በማቀድ ሰበካ ጉባኤው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለግንባታው መሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ሁሉም አካል ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

#ዜና_ተዋሕዶ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
በሶርያ ምሥራቅ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የሽብር ጥቃት ደረሰ

ሰኔ 15 ቀን 2025 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ከደማስቆ በስተምሥራቅ በድዋይሌህ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢላማ የተደረገ ሲሆን በጥቃቱ ከ15 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በትንሹ 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የሶሪያ አረብ የዜና አገልግሎት (SANA) እና በርካታ አለም አቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

በሩሲያ የዜና አገልግሎት ኖቮስቲ የዘገበው የመጀመርያ ዘገባዎች እንዳመለከቱት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በጸሎት ወቅት ወደ ቤተክርስቲያኑ በመግባት በነበሩት ምእመናን ላይ ተኩስ በመክፈት ድንጋጤ ፈጥሯል። ከዚያም የሚፈነዳ ቀበቶ በማፈንዳት ከፍተኛ ፍንዳታ በማድረግ የቤተክርስቲያኑ ክፍሎች ወድሞ የበርካታ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

አል-ኢኽባሪያ ቲቪ እንደዘገበው የሀገር ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች የጥቃቱን መንስኤ ለማወቅ የወንጀል ምርመራ መጀመሩን ዘግቧል። ይህ በንዲህ እንዳለ የአምቡላንስ እና የሲቪል መከላከያ ቡድን ቁስለኛዎቹን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታሎች በማጓጓዝ ከፍተኛ የህክምና ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ነው የተገለጸው።

የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በደማስቆ እና በአካባቢዋ ከሚገኙት ታዋቂ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው። ከነቢዩ ኤልያስ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በጥንታዊ እና ታሪካዊነቱ ይታወቃል።

#ዜና_ተዋሕዶ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና      ወ.ዘ.ተ......
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥

🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █       

 
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
❤️በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ
በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም
የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ
መልሱ ይለቀቃል።
በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል
ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

         👇👇👇
@metehafe_kedusawi_teyake
@metehafe_kedusawi_teyake
@metehafe_kedusawi_teyake
🥷ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና👩‍⚕
         ⚫️ክፍል አንድ 🟡

ስለእውነት ነው  የምላችሁ በደንብ አንብቡ በስተመጨረሻ  የምታገኙት የመንፈስ ጥንካሬ እንዲህ ነው  ማለት አልችልም ብቻ  እንድታነቡ የእግዚአብሔር ፈቃደ በእናንተ ላይ ይሁን።

😄ምዕራፍ አንድ ማን ነበርኩ

ናህድ  ማሕሙድ ሙትዋሊ እባላለሁ። ሴቶችን ብቻ የሚያስተምረው የሄልሜት ኤል ዘይቱን ትምህርት ቤት ዲን ነበርኩ።

በካይሮ የታወቀ እና ትልቁ ትምህርት ቤት ነው። 4000 ልጃገረዶችን ያስተምራል። ከተማሪዎቹ ብዛት የተነሣ ት/ቤቱ የሚያስተምረው በጥዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነበር።

የት/ቤቱ ዲን እንደመሆኔ መጠን ሁለቱንም ፈረቃዎች መከታተል ነበረብኝ። ምንም እንኳን ከሁሉም ዲኖች በዕድሜ ታናሿ እና በቅርብ ከኮሌጅ የተመረቅኩ ብሆንም ይህንን ወንበር እንዳገኝ ግን ሁለት ነገሮች ረድተውኛል።

   እግዚአብሔር ብስለትን፣ በራስ መተማመንን፣ እንዲሁም ኃላፊ ነቴን በሚገባ የመወጣት ችሎታን አድሎኝ ነበር። የማንም ርዳታ ሳያስፈልገኝ የሚሰጠኝን ሥራ ሁሉ በአፋጣኝ የማከናወን ልምድ አለኝ።

ሰወች አንድን ነገር ሲሠሩ መመልከት ብቻ ለእኔ በቂዬ ነበር። ያንኑ ነገር ወዲያውኑ ልምድ እንዳለው ሰው አድርጌ ማከናወን እችላለሁ።

    በዚህ ችሎታዬ የተነሣ ይህንን ቦታ ያገኘሁት ቦታውን ላገኘው ከሚገባኝ ዐሥር ዓመታት ቀድም ነበር ከዚህ ችሎታዬ ጋር ተጨምሮ በት/ቤቱ የነበሩትን የሁለቱን ረዳት ዳይሬክተሮች ተግባር የማወቅ ዕድልም ገጥሞኛል። የተማሪዎችን ሰሞች በምሥጢራዊ ኮድ ካገኘኋቸው ዋና ዋና ልምዶች መካከል የሚጠቀሱት ናቸው።

እንዚህ ሁለቱ ተግባራት ደግሞ በት/ቤታችን ውስጥ ዋነኞቹ ሥራዎች ናቸው።
ምክንያቱም ሁለቱም ፍጹም የሆነ ምሥጢር ጠባቂነትን የሚጠይቁ ናቸውና።

  አንደኛው ረዳት ዳይሬክተር በ60 ዓመቱ ጡረታ ወጣ፣ ሌላው ደግሞ ወደ ሌላ የዓረብ ሀገር ለሥራ ሄደ።

ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም እነዚህን ሁለቱን ኃላፊነቶች ጠቀለልኳቸው። ይህም የት/ቤቱን ቁሌፍ ቁልፍ አስተዳደራዊ ኃላፈነቶች እንድቆጣጠር ዕድል ከፈተልኝ።

  እነዚህን ኃላፊነቶች ከጠቀለልኩ በኃላ ልክ የት/ቤቱ ንግሥት የሆንኩ ያህል ይሰማኝ ነበር።

በእነዚህ ነገሮች ሙሉ ሥልጣን እና ፍጹም የሆነ ኃላፈነት ነበርኝ። ሌላው ቀርቶ የእኔ የበላይ የሆነችው የት/ቤቱ ዳይሬክተር እንኳን በጣም ትቅርበኝ፣ የምትሠራውንም ነገር ሁሉ ታማክረኝ ነበር። የሚፈራ፣ ኃይለኛ፣ አድራጊ ፈጣሪ ሆንኩ።

   ለመኞቴ ወሰን አልነበረውም። ለዝቅተኛ ተማሪዎች የሚሰጠውን የትምህርት እገዛ እኔ ራሴ እንድከታለው ኃላፈነቱ እንዲሰጠኝ አስተዳደሩን ጠይቄ ተፈቀደልኝ። በዚህ የተነሣም በየወሩ ከእነዚህ ክፍሎች ለሚሰበሰበው ከ12ሺ-15ሺ ለሚጠጋው ገንዘብ ኃላፊ ሆንኩ። ለዚህ ኃላፊነቴ እንዲሁም ፈተና ለማዘጋጀት እና ለማባዛት ተግባሬ የሚከፈለኝ ገንዘብ ወራኃዊ ገቢዬን በሦስት እጥፍ አሳደገው።

ወደዚህ የሥልጣን እርከን ያሸጋገረኝ ሌላው ነገር ደግሞ የቤተ ሰቦቼ ታዋቂነት እና በመንግሥታዊ ቦታዎች ያላቸው ሥልጣን ነቀር።

ወንድሜ በማዕከላዊው የአስተዳደር እና የአመራር ሥርዓት ቢሮ ውስጥ ሥራ እስኪያጅ ነበር። አንደኛው ዋርሳዬ ደግሞ የማዘጋጃ ቤቱ ጸሐፊ እና የት/ቤቱ የወላጆች እና መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ነው።


የእርሱ ሁለቱ ሴቶች ልጆቹም የት/ቤቱ ተማሪዎች ነበሩ።
 
ሌላው ዋርሳዬ ደግሞ የቤተ መንግሥቱ ፓይለት ነው። እኅቴ የሄልዮፓሊስ አካባቢ የት/ቤቶች አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ ናት።

ባልዋም በማዕከላዊው  የመረጃ አገልግሎት ሹም ነበር።  እንዚህ ሁሉ ከእኔ ሰብእና እና በት/ቤቱ ከተፈጠረው ክፍተት ጋር ተደማምረው ከሥልጣን ወደ ሥልጣን አሸጋገሩኝ።

  ይህ ሁሉ በሀብት እና በሥልጣን ይጠቀመኝ እንጂ  ወስጤን  ግን ትዕቢተኛ ፣ ዕብሪተኛ እና ግብዝ አድርጎኛል።

   በሌላ በኩል ልቡናዬን ለሚያይ ደግሞ የተለየሁ ፍጥረት ነበርኩ። አምላኬን እወደዋለሁ የምል ቆዳ ስሱ  ሰው ነኝ። አዎን ጌታዬ ሆይ ምንም እንኳን ከአንተ ርቄ ብኖርም በፍጹም ልቤ እወድድህ እና እፈራህ ነበርኮ።

እግዚአብሔርን ስፈልገው ኖሬያለሁ፣ እነዚያ የሕይወቴ የተበላሹ ገጽታዎች ግን እርሱን እንዳላገኝው የመከለያ ግንብውቅም ነበር። አብዝቼ እጸልያለሁ፣ ቁርዐንንም አዘውትሬ አነባለሁ ፣ ይሁን እንጂ በውስጤ አንዳች የጎደለ ነገር መኖሩ ይሰማኝ ነበር።

ክርስቲያኖች እኔ የምወደውን አምላክ አይወዱትም ብየ ስለማስብ አብዝቼ እጣላቸው ነበር።

እግዚአብሔርን እኔ በማመልክበት መንገድ ለምን አያመልኩትም? እነርሱ ከእግዚአብሔር የኮበለሉ ናቸው እያልኩ እጅግ እጠላቸው ነበር።

   ክርስቲያኖችን ከመጥላቴ የተነሣ እነርሱን ለማዋድ፣ ለመጉዳት እና በእነርሱ  ላይ አንዳች ችግር ለመፍጠር ዘወትር እጥር ነበር።

ይህንን የማደርገው ግን በውስጤ ለሰው ክፋት ስላለኝ ሳይሆን የምወደውን እና የማመልከውን አምላክ ለምን አያመልኩም፣ ለምንስ አይወዱም? ብየ ነበር። በርግጥ ሁልጊዜ የሚገርመኝና የሚያሳስበኝ አንድ ነገር አለ።

እኔ ላገኘው የምጓጓለትን ውሳጣዊ ሰላም ክርስቲያኖች ገንዘብ አድርገውታል። እንዴት?

      😀ይቀጥላል
📱አቅራቢ፦#ድምፀ_ተዋሕዶ

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ‼️
    
📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+ታዛዥነትና  ተዘክሮተ  እግዚአብሔር+
~~~
አባ ዮሐንስ ኃፂር ከሚታወቅባቸው መልካም ምግባራት መካከል የሚጠቀሱለት ናቸው ታዛዥነትና  ተዘክሮተ  እግዚአብሔር፡፡ አንደ ቀን አባ ባሞይ ዮሐንስ ኃፂርን የደረቀ እንጨት ተክሎ ለምልማ እስክታፈራ ድረስ ውኃ እንዲያጠጣት አዘዘው፡፡ ያለማንገራገር በትኅትና ሆኖ አሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል ከሚርቅ ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ውኃ እያመላለሰ ያጠጣ ጀመር፡፡ በሦስተኛው ዓመት ያቺ በትር ለምልማና አብባ ያማረ ፍሬ አፈራች፡፡ አባ ባሞይ በዮሐንስ ታዛዥነት እጅግ ተደሰተ፡፡ ፍሬውን ለቅሞ ለገዳሙ መነኮሳት እንካችሁ ይህ የታዛዥነት ፍሬ ነው እያለ ሰጣቸው፡፡ መነኮሳቱም ይህን ተአምር ባዩ ጊዜ አደነቁ፡፡ ለቅን እና ታዛዥ ሰው ይህን ጸጋ የሰጠ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፡፡

"መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፡፡" ምሳሌ 12፤2

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
☦️መልካሙን ስለ መርሳት☦️


መልካም አድርግና እርሳው...
ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ።
መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን።
መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን።

መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።
እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል።

መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።

☦️ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ☦️

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
‼️
    
📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐
@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
        
👆🀄️🀄️ሉን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ተጠምቄ_ለመዳን_አስቀድሜ_ምን_ላድርግ⁉️
     
         
🔔 ክፍል ፫ ⬅️

በመጨረሻም ክብርይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልትድን ትወዳለህን? ሲለው ድውዩም መልሶ “አዎን ጌታ ሆይ ነገር ግን ውሃው በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው የሚያወርደኝ ሰው የለኝም እኔ በምመጣበት ጊዜ ሌላው
በመጨረሻም ክብርይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልትድን ትወዳለህን? ሲለው ድውዩም መልሶ “አዎን ጌታ ሆይ ነገር ግን ውሃው በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው የሚያወርደኝ ሰው የለኝም እኔ በምመጣበት ጊዜ ሌላው
ቀድሞኝ ይወርዳል” አለው የሐ 517 ወዲያው መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልጋውን እንዲሸከም ሲያዘው ያለምንን ጥርጥር አልጋውን ተሸክሞ እሮጠ።

ዛሬም በእግዚአብሔር ስም አምነን አይቻልም የሚባለውን እንችላለን ስለዚህ የትኛውም በፀበል መፈወስ የሚፈልግ ህመምተኛ ፀበልን ለሙከራ ሳይሆን ፀበልን ለመድሃኒትነት አምኖ መጠመቅ አለበት “እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ ተነቅለህ ሂድ ብትሉት ይፈልሳል የሚሳናችሁ ነገር የለምና" ተራራ የተባለው ዲያብሎስ ነው የሚሸነፈውም በእምነት ነው እምነት ያለው ሰው ሁሉንም ይችላል የሚሳነው ነገር የለም ስዚህ ፀበል ለመጠመቅ ወደ ጸበል ቦታ የሚሄድ ሁሉ አምነው ከሄዱ ተፈውሰው ይመጣሉና ወደ ጸበል ቦታ እንኳን አምነው የሄዱት ይቅርና ሳያምን በአጃቢዎቹ ግፊት የሄደው ንዕማን እንኳን ተፈውሶ ተመልሷል "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው" መ.ነገ ካልዕ 5፥13-14 ማር. 9፥23 ስሙ የተመሰገነ ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ሲያስተምር በለሲቷን ሲረግማት በፍጥነት ደርቃ እንዴት ከሥሯ ተነቅላ እንደወደቀች ተደንቀው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ሲመልስ “ማር 11፥21-24 ጴጥሮስም ትዝ አለውና “መምህር ሆይ እነሆ ያቺ የረገምካት በለስ ደርቃለች" አለው፡፡

ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “እግዚአብሔርን ማመን ይኑራችሁ እውነተ እላችኋለሁ ይህን ተራራ ተነስተህ ወደ ባህር ተወርወር ብትሉት በልባችሁ ባትጠራጠሩና ብታምኑም እንደተናገራችሁት ይሆናል ስለዚህ እላችኋለሁ አምናችሁ የምትፀልዩትና የምትለምኑትንም ሁሉ ታገኛላችሁ ይሆንላችሁማል"፡፡

ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የምንማረው እምነት የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን ፡ በምንሰራው ስራ ሁሉ የመከናዎኛ መሳሪያ እንዲሆን ነው የሚያምን ሁሉን ማድረግ ይችላል የማያምን ግን ምንም ማድረግ አይችልም ማለት ነው።

በተጨማሪም እምላካችን ከብር ይግባውና እንዲህ በማለት ያስተምራል ማር1615 እንዲህም አላቸው "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል ይህችም ምልክት በስሜ የሚያምኑትን ትከተላቸዋለች በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ በሐዲስ ቋንቋም ይናገራሉ እባቦችንም በእጃቸው ይይዛሉ የሚጎዳቸውም ነገር የለም የሚገድል መርዝ ቢጠጡም የሚጎዳቸው የለም ድውያኑ ላይም እጃቸውrg ይጭናሉ ድውያንም ይፈወሳሉ” በማለት የሚያምኑ ሰዎች እጅግ ታላላቅ ተአምራት እንደሚደረግላቸው አስተምሮናል በመሆኑም ከእግዚአብሔርአንድን ነገር ለመቀበል የሚለምን ሰው እግዚአብሔር ማድረግ እንደሚችል ምንም የሚሳነው ነገር እንደሌለ ማመን ይኖርበታል እንግዲህ ፀበል ተጠምቀ እንድድን ምን ላድርግ ብሎ የሚያስብ ሰው በመጀመሪያ እግዚአብሔርሕመምተኛውን ጤነኛ ጤነኛውን ሕመምተኛ ድሀውን ሀብታም ሀብታሙን ድሀ ደካማውን ብርቱ ብርቱውን ደካማ ማድረግ እንደሚችል አስቀድሞ አምኖ በፀበሉ ተጠምቆ እንደሚድን ጤናውን እንደሚያገኝ ማመን ይኖርበታል፡፡

ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የምትሆን እናታችን ቅድስት ሣራ ናት እናታችን ሣራ በዘጠና ዓመቷ ልጅ ትወልጃለሽ የሚል ብስራትን ስትሰማ ሳቀች ነገር ግን እግዚአብሔር ሳቅሽ ሲላት አልሳኩም በማለት ወደ ድንኳኗ ጥልቅ ብላ ገባች ጥርጣሬዋን በማመን አሸ ጅን አገኘች ዘፍ 18፥1-18 ዛሬም ቢሆን ብዙ ሰዎች በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዘው ሲሰቃዩ ፀበል እንዲጠመቁ ሲጠየቁ ስለማያምኑ የማያድን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ፀበል ተጠምቀው ያልዳኑ ሰዎች የሉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ መጠመቂያው የገቡ ሰዎች ሁሉም ድነው ወጥተዋል፡፡ ለምሳሌ ንዕማን 2ኛነገ 5፥13-14 መፃጉ የሐ 5፥8-16 ዕውር ሆኖ የተወለደው ሰው ዮሐ 9፥1-8

ዛሬም ቢሆን ፀበሉ ያድናል ነገር ግን የማያምኑ ሰዎች በፀበል ማዳን መዳን አይችሉም እንግዲህ እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር የምናገኝበት መሳሪያ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅብና ዕብ ዘካ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አማላጅነቷ ከእኛ ከልጆቿ ጋር ይሁንና ትልቅ መማሪያ የሚሆን አስደናቂ መሰረታችን ናት ያለ ወንድ ጸንሰሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ መላኩ ሲያበስራት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለው አምና ተቀበለች በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወለደች ሉቃ 1፡30-48 በዚህም ቅድስት ኤልሳቤጥ አማላጅነቷ ይደርብንና እንዲህ ስትል አመሰግናታለች "ከእግዚአብሔር ዘንድ የነገሩሽን ቃል የምታምኚ አንቺ ብፅዕት ነሽ" በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅበት ዘመን እመቤታችን ግን ይህን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልጃለሽ ሲላት እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ እንደሚች ስለምታውቅ ያለምንም ማቅማማት ተቀበለችው እሷም የፀጋ አባቷን የባሕሪ ልጁ አድርጋ ወለደችው እግዚአብሔርም ለድንግል ማርያም የጸጋ አባቷ የባሕሪ ልጇ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ስንመለከት ከእሷ በፊት በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችን ሴት ታሪክ ሰምታም አይታም የማታውቅ እናታችን ድንግል ማርያም መላኩ ገብርኤል ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ብሎ ስለነገራት ብቻ ምንም አብነት የሚሆናት ሰው ከሷ በፊት ሳይኖር አምና ተቀበለች፡፡ ሉቃ 1፡37 ዘፍ 18፥14

       
😀ይቀጥላል
📱አቅራቢ፦#ድምፀ_ተዋሕዶ

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያሳውቁ‼️
    
📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሠላሳ በዚህች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ ።

+++

ሰኔ ሠላሳ በዚህች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።

በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።

ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።

#ድምፀ_ተዋሕዶ

🔛ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ‼️
    
📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
         📣 ድምፀ_ተዋሕዶ📣
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/07/07 21:45:26
Back to Top
HTML Embed Code: