Telegram Web
ዘንድሮም እንዳምና ካቻምናው የሸዋልኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር ልንጓዝ ነው::

🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 )
የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር

🔹ባሳለፍነው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት / UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋልኢድ በዓልን ዘንድሮም ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ለማክበር ቀኑ አልደርስ ብሎናል::

እናንተስ ከእኛ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ናችሁ?

በዚህ የጉዞ መርሀ ግብር

🔸ከኢድ አልፈጥር በዓል 7 ቀናት በኋላ በሀረሪ ብሄረሰብ ተወላጆች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ተወዳጁ የሸዋልኢድ የአደባባይ በዓልን እንታደማለን።

በጀጎል ግንብ የሚከናወነው ይህ ልዩ ፌስቲቫል በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ታዳሚዎች እና እንግዶች አምረው ደምቀው በሚታዩበት ምሽት ይከበራል።

🔸እንዲሁም በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የሀረሪን ባህል እና ታሪክ የሚገልፁ ቅርሶች እንጎበኛለን::

🐎 ሌላው የዚህ ጉዞ አጓጊ ክፍል
በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኞቹ የዱር ፈረሶች ወደሚገኙበት ምስራቅ ሀረርጌ የኢትዮዽያ ክፍል በማምራት የቁንዱዶ ተራራ እና የቁንዱዶ የዱር ፈረሶችን እንጎበኛለን::

⛺️ የአንድ ቀን አዳራችንን ከባህር ጠለል በላይ 2,950 ሜ ከፍታ ላይ በማድረግ በቁንዱዶ ተራራ ላይ የማይረሳ ምሽት እናሳልፋለን::

🚂 ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የበርሃዋ ገነት ድሬድዋን ሳንጎበኝ በፍፁም አንመለስም::

ይህን አጓጊ ጉዞ ከእኛ ጋር ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች በአፋጣኝ ይደውልልን:: ወይንም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላክልን:: @guzoadwahiking @guzoad

+251942545470, +251964423971
እጅግ ውስን ቦታዎች ብቻ ቀርተውናል::

#ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #harar #shewaleid #unescoworldheritage
Guzo Adwa updates pinned «ዘንድሮም እንዳምና ካቻምናው የሸዋልኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር ልንጓዝ ነው:: 🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 ) የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር 🔹ባሳለፍነው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት / UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋልኢድ በዓልን ዘንድሮም ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ለማክበር ቀኑ አልደርስ ብሎናል:: እናንተስ…»
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቁንዱዶ የዱር ፈረሶች! (በኢትዮዽያ ብቸኞቹ የዱር ፈረሶች:: )
መገኛ 📌 ምስራቅ ሀረርጌ ጉርሱም ,ቁንዱዶ ተራራ

የዓመቱ ታላቅ ጉዞ ከጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ጋር !
ጉዞ ወደ ሀረር-ድሬድዋ-ቁንዱዶ ተራራ! (3ኛ ዓመት)

🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 ) ሊካሄድ ነው::

የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር

ለማንኛውም አይነት ተጨማሪ መረጃዎች ወይንም ማብራሪያዎች በተከታዮቹ የስልክ ቁጥሮች ያገኙናል::

+251942545470, +251964423971
ወይንም በ ቴሌግራም @guzoadwahiking , @guzoad
መልካም ቀን ይሁንልን !
Guzo Adwa updates pinned «ዘንድሮም እንዳምና ካቻምናው የሸዋልኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር ልንጓዝ ነው:: 🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 ) የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር 🔹ባሳለፍነው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት / UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋልኢድ በዓልን ዘንድሮም ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ለማክበር ቀኑ አልደርስ ብሎናል:: እናንተስ…»
Guzo Adwa updates pinned «ዘንድሮም እንዳምና ካቻምናው የሸዋልኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር ልንጓዝ ነው:: 🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 ) የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር 🔹ባሳለፍነው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት / UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋልኢድ በዓልን ዘንድሮም ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ለማክበር ቀኑ አልደርስ ብሎናል:: እናንተስ…»
ማሳሰቢያ❗️
የክፍያ ቅናሽ ዕድሉ በነገው ዕለት ያበቃል::
ለተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ አድራሻዎች ያግኙን:: @guzoadwahiking , @guzoad ወይንም በስልክ +251942545470
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀጣዩን የተራራ ላይ ካምፒንግ እርስዎም ይቀላቀሉ! ⛰️⛺️🐎

አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል!

ለተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ አድራሻዎች ያገኙናል!
+251942545470 , +251964423971
@guzoadwahiking @guzoad

መልካም ቀን ተመኘን!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ።
ዒድ ሙባረክ!

👉ዛሬ ጨረቃ በመታየቷ ምክንያት በነገው ዕለት የዒድ አልፈጥር በዓል ይከበራል:: በዚህም መሰረት በቀጣዩ ሳምንት አርብ የሚጀመረው የሀረር-ድሬድዋ-ቁንዱዶ ተራራ ጉዟችን መርሀ ግብር ይህን ይመስላል::

______________________________________

የጉዞ መርሀግብር (ከቀን 1-4)

ቀን 1:- አርብ መጋቢት 26

✈️ ከአዲስ አበባ - ድሬድዋ የአውሮፕላን በረራ ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ ከጠዋቱ 2:05 የሚያበቃ

በጉዟችን የመጀመሪያ ቀን ላይ የድሬዳዋ ከተማ ጉብኝት : በመቀጠል በተመሳሳይ ቀን ወደ ሀረር ከተማ ማምሻችንን እናቀናለን (ከ ድሬድዋ ከተማ የ 2:30 ሰዓት መንገድ)::

ሀረር ከተማ እንደደረስን ወደ ተዘጋጀልን የሆቴል ማረፊያ በማምራት ከአጭር የሻወር እረፍት በኃላ ማምሻችንን የሀረር ከተማ መታወቂያ ከሆኑት የአደባባይ ትዕይንቶች ዋነኛ ወደሆነው ጅቦችን በምሽት ስጋ የማብላት የትዕይንት ስፍራ በማምራት ይህን ድርጊት እንመለከታለን:: ከእራት ፕሮግራም በኃላ የቀኑ ማጠናቀቂያ ይሆናል::

ቀን 2:- ቅዳሜ መጋቢት 27

ይህ ቀን የሀረር ከተማን ይበልጡንም ጀጎልን እና በውስጡ የሚገኙ በርካታ የሀረሪን ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል ፣ ማንነት ወዘተ...የሚገልፁ አኩሪ ቅርሶችና ሙዚየሞች የምንጎበኝበት ዕለት ይሆናል:: እጅግ ውብ ውብ የሚሆኑ የሀረር ማስታወሻ ፎቶዎችን እንነሳለን:: በዚሁ ቀን ከአመሻሽ ጀምሮ (ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ) ሌሊቱን በሙሉ በአደባባይ በዓል የሚደምቀውን የሸዋልኢድ በዓልን እንታደማለን::

ቀን 3:- እሁድ መጋቢት 28
ጉዞ ከሀረር ወደ ቁንዱዶ ተራራ

የቁንዱዶ ተራራ ከሀረር ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባቢሌ እና የጉርሱም ከተማን አልፎ የሚገኝ ግዙፍ ተራራ ነው ::
ቁንዱዶ ተራራ ለእግር ጉዞ እና ተራራ ወዳጆች በሁሉም አይነት የተራራ መመዘኛ ''አንጀት አርስ'' ሊባል የሚችል ተራራ ሲሆን በዚህም ጉዞ
በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኞቹ የዱር ፈረሶችን "የቁንዱዶ የዱር ፈረሶችን" እንጎበኛለን::

የአንድ ቀን አዳራችንን ከባህር ጠለል በላይ 2,950 ሜ ከፍታ ላይ በማድረግ በቁንዱዶ ተራራ ላይ በካምፋየር የደመቀ የማይረሳ ምሽት በጋራ እናሳልፋለን::

ቀን 4 :- ሰኞ መጋቢት 29
ከቁንዱዶ ተራራ መልስ : ከምሳ ሰዓት እረፍ በኃላ
ቀጥታ ወደ ድሬድዋ ከተማ ኤርፖርት በማምራት (ቁንዱዶ ተራራ ከሚገኝበት ቦታ ወደ 170 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ) ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን የምንመለስ ይሆናል::
የበረራ ሰዓት ከምሽቱ 12:25

የጉዞ ማጠቃለያ!

ለማንኛውም አይነት ተጨማሪ መረጃዎች ወይንም ማብራሪያዎች በተከታዮቹ የስልክ ቁጥሮች ያገኙናል::

+251942545470 , +251964423971
@guzoadwahiking , @guzoad

በድጋሚ መልካም በዓል!
Guzo Adwa updates pinned «ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ! 👉ዛሬ ጨረቃ በመታየቷ ምክንያት በነገው ዕለት የዒድ አልፈጥር በዓል ይከበራል:: በዚህም መሰረት በቀጣዩ ሳምንት አርብ የሚጀመረው የሀረር-ድሬድዋ-ቁንዱዶ ተራራ ጉዟችን መርሀ ግብር ይህን ይመስላል:: ______________________________________ የጉዞ መርሀግብር (ከቀን 1-4)…»
2025/03/31 02:48:16
Back to Top
HTML Embed Code: