Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#የእመቤታችን 120 ስሞች !
ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም 120 ስሞችን እንዲህ በማለት ትጠራታለች።
1. ሰአሊተ ምሕረት
2. ድንግል
3. እመ ብዙሃን
4. አቁራሪተ መዓት
5. የገብርኤል ብስራት
6. ንፅህተ ንጹሐን
7. ሃገረ እግዚአብሔር
8. ቅድስተ ቅዱሳን
9. ማህደረ ሰላም
10. መዓርገ ሕይወት
11. ማኅደረ ስብሐት
12. ማኅደረ ትፍስሕት
13. ቤተ ሃይማኖት
14. ብጽዕት
15. ሕሪት
16. ክብርት
17. ልእልት
18. ውድስት
19. የሰማዕታት እናት
20. የመላዕክት እህት
21. የነቢያት ትንቢት
22. የሐዋርያት ሞገስ
23. እመ ብርሃን
24. ርሕርሕተ ልብ
25. እመ አምላክ
26. የሲና እፀ ጳጦስ
27. የአዳም ተስፋ
28. የአብል ይውሕና
29. የሴት ቸርነት
30. የሔኖክ ደግነት
31. ሙጻአ ፀሐይ
32. ታቦት ዘዶር
33. እግዝትነ ማርያም
34. የቅዱስ ኤፍሬም ባራኪ
35. ምልዕተ ውዳሴ
36. ቡርክት
37. የደስታ መገኛ
38. ምእራግ
39. አዳም ቆማ
40. ጽርሕ ንጽሕት
41. ማሕደረ መለኮት
42. እሕቱ ለሙሴ
43. ገራሕቱ ለአብርሃም
44. ወለቱ ለዳዊት
45. እሙ ለአማኑኤል
46. ነያ ሰናይት
47. እምነ ጽዮን
48. መዝገበ ብርሃን
49. ጽጌ ሃይማኖት
50. ደብተራ ፍጽምት
51. ማርያም ቅድስት
52. አክሊለ ንጹሐን
53. ብርሃነ ቅዱሳን
54. ወለተ ሐና ወኢያቄም
55. መድኃኒተ ይእቲ
56. ሐመልማለ ገነት
57. ሙዳዬ መና
58. ርግበ ጸአዳ
59. ሐመልማላዊት
60. መንፈሳዊት ሃገር
61. የኖህ መርከብ
62. የሴም ምርቃቱ
63. የሴም እድል ፈንታዉ
64. የአብርሃም ዘመድ
65. ሶልያና
66. እሙ ለፀሐይ ጽድቅ
67. ምስራቀ ምስራቃት
68. በትረ አሮን
69. የገነት ኮል
70. የይስሐቅ ሽቱ
71. የያዕቆብ መሰላል
72. የዮሴፍ አረጋጊ
73. ቤዛዊተ ዓለም
74. የእሴይ ሥር
75. ወለተ ዳዊት
76. የሙሴ ጽላት
77. የአሮን ካህን ጸናጽል
78. የኢያሱ የምስክር ሐውልት
79. የጌዴዎን ጸምር
80. የሳሙኤል ሽቱ
81. የአሚናዳብ ሰረገላ
82. የዳዊት መሰንቆ
83. የሰሎሞን ቀለበት
84. የኤልያስ መሶበወርቅ
85. የኤልሳዕ ልሕኩት
86. የኢሳይያስ ትንቢት
87. የሕዝቅኤል አዳራሽ
88. ዕፀ ሕይወት
89. የሚኪያስ ኤፍራታ
90. የናሆም ፈዋሽ
91. የዘካርያስ ደስታ
92. ወለተ ጽዮን
93. ንጽሕት ጸምር
94. ደብተራ ዘትዕይንት
95. ሀገረ ክርስቶስ
96. ኪዳነ ምሕረት
97. በአታ
98. መሰረተ ሕይወት
99. ናዛዚተ ሕዙናን
100. እሕትነ ነያ
101. አንቀጸ አድሕኖ
102. መዓዛ እረፍት
103. ርግብየ ሠናይት
104. ሐረገወይን
105. አንቀጸ ብርሃን
106. ተቅዋም ዘወርቅ
107. መቅደስ
108. ሐመልማለ ወርቅ
109. ብርሃነ ሕይወት
110. ሆሕተ ምስራቅ
111. መዝገቡ ለቃል
112. ፍኖተ ሕይወት
113. ምስጢረ ስብሐት
114. መዝገበ ብርሃን
115. ምልእተ ክብር
116. ምልእተ ፍስሐ
117. ምልእተ ፀጋ
118. ጽላተ ኪዳን
119. ጽላተ ሕግ
120. ዳግሚት ሰማይ
#ክብር_ለእናታችን
#ዕርገተ_ማርያም - (#ነሐሴ_16)

ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ ።

የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው ። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ።

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው ። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።

ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።

በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ።

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
"ሥጋ በዝሙት እንደሚረክስ ኹሉ፥ ነፍስም በሰይጣናዊ አሳቦች፣ በእኩይ ሃይማኖትና በእኩይ ግብር ትረክሳለች፡፡ አንድ ሰው "በሥጋ ድንግል ነኝ" ቢል፥ ነገር ግን በወንድሙ የሚቀና ከኾነ እርሱ ድንግል አይደለም፡፡ ከቅናት ጋር ሩካቤ ስለ ፈጸመ ድንግልናውን አጥቷል፡፡ ውዳሴ ከንቱን የሚወድድም እርሱ ድንግል አይደለም፡፡ የቅናት ስሜት ክብረ ድንግልናውን አሳጥቶታል፡፡ ስሜት ወደ ውሳጤው ዘልቆ ገብቶ የነፍሱን ድንግልና አፍርሶበታልና። ወንድሙን የሚጠላም እርሱ ድንግል ከመኾን በላይ ነፍሰ ገዳይ ነው። በአጠቃላይ እያንዳንዱ ሰው በተገዛለት ክፉ ስሜት ድንግልናውን ያጣል። ስለዚሁ ምክንያትም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ኹሉ መቀላቀሎችን አራቀ የነፍሳችን ጸር የኾኑ ማናቸውንም አሳቦች ወደን ፈቅደን ባለመቀበል ደናግል እንድንኾን አዘዘን።

እንግዲህ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ልንናገረው የሚገባን ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ምሕረት ልንቀበል የምንችለው እንዴት ነው? ልንድን የምንችለውስ እንዴት ነው? ጸሎትንና የጸሎት ፍሬዎች የኾኑትን እነርሱም ትሕትናንና የውሃትን ዘወትር ለራሳችን እንያዝ ብዬ እነግራችኋለሁ። እርሱ “ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ" ብሎአልና (ማቴ.11፥29)። ክቡር ዳዊትም፦- “የተሰበረን መንፈስ ለእግዚአብሔር ሠዋ፤ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” ብሎአል (መዝ.50፥17)። እግዚአብሔር ከተሰበረ፣ ትሑት ከኾነና ከሚያመስግን ልብ በላይ አጥብቆ የሚወድደው የለምና።

ስለዚህ ወንድሜ! አንተም ያላሰብከውና የሚያናውጽ መከራ ቢገጥምህ መጠጊያ ይኾኑህ ዘንድ ሰዎችን እንዳትመለከት፤ ዘላቂና ቋሚ ያይደለ እርዳታን እንዳትፈልግ ተጠንቀቅ። ይልቅ ኹሉንም ናቃቸው፤ በአሳብህም መድኃኒተ ነፍሳት ወደ ኾነው ወደ እግዚአብሔር ተፋጠን። ልባችንን መጠገን (መፈወስ) የሚቻለው ልባችንን ብቻውን የሠራ (የፈጠረ) እና ግብራችንን ኹሉ የሚያውቅ እርሱ ብቻ ነውና (መዝ.32፥15)። ወደ ሕሊናችን ጓዳ መግባት፣ አሳባችንን መመርመር ልባችንንም ማጽናናት ሥልጣን (ኃይል) ያለው አርሱ ብቻ ነውና። እርሱ ልባችንን ካላጽናና ሰዎች ኹሉ የሚያደርጉልን ነገር ትርፍና ረብ የለሽ ነውና። እግዚአብሔር ሲያጽናናንና ሲያረጋጋን ግን እንደ ገና ሰዎች ቍጥር በሌለው መከራ ቢያውኩንም በፍጹም እኛን መጉዳት አይቻላቸውም፤ እርሱ ልባችንን ጽኑዕ ሲያደርግ ማንም እኛን ለማነዋወጽ ኃይል የለውምና።"

(ንስሓ እና ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 73-74 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

ለሌሎች ያካፍሉ!
ወዳጆቼ ሆይ !

"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምንነው #ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው #ጽዋ ላይ አታገኙትም
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እባካችሁን ሼር አድርጉ
ክርስቲያን

💒 ክርስቲያን ማለት ቀጥታ #ክርስቶስ ከሚለው የፅዕር/ግሪክ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም____
• የክርስቶስ ተከታይ
• የክርስቶስ ወገን
• የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማለት ነወ፡፡፡

@ an English Oxford define the word #Christian as " the one who is based on or believing the teaching of Jesus christ."

💒 ስለዚህ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የሆኑ ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው በክርስቶስ ምክንያት በዘመኑ ከነበሩ ህዝበ አይሁዶች ተለይተው ተጠርተውበታል፡፡፡

እውነቱ ይህ ሆኖ እያለ ግን ማንም በዘፈቀደ በመነሳት ይህን ስያሜ ለራሱ ቢያደርገው ስሙን ለራሱ ከማድረጉ በስተቀር መጸሐፍ ቅዱሳዊ አንድምታ አይኖረውም፡፡፡፡፡፡፡፡
በዘመኑም የምናያቸው የምዕራቡ ዓለም /አሜሪካ ፡ ሩስያና አውሮፓውያን ጀርመን ፡ ፖርቹጋል ፡ እንግሊዝ ፡ ፈረንሳይ እንዲሁም ምስራቃውያን ግሪክ/ ---- ክርስቲያን ባዮች እንዲሁ ናቸው፡፡
©ከአምስቱ እህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገራት ማለትም፦
1.ግብፅ
2.ሶሪያ
3.አርመን
4.ህንድ
5.ኢትዮጵያ + ኤርትራ ውጭ _ክርስቲያን ቢባሉም የስም ብቻ ነው፡፡፡፡፡

💒 ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን ያሉዋቸው በዘመኑ የነበሩ ትምህርታቸውንም የማይቀበሉ ህዝበ #አይሁዶች ናቸው፡፡፡
እንዲህ ሲባሉ ግን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ይስማማናል ይገባናል ብለው አምነው ተቀብለውታል፡፡፡፡፡፡፡፡

💒 ክርስቲያን የተባሉበት ምክንያት የክርስቶስ ተከታይ ስለሆኑና እርሱንም ስለአመኑና ስለመሰሉ ትምህርቱንም ስለተቀበሉ ነው ፡፡

⛪️ አይሐዶችም ይህን ብለው ያወጡላቸው ለሐዋርያት ብለው ሳይሆን የክርስቶስ ትምህርት ስለማይቀበሉ ስለእርሱም እንዳይሰብኩ ከእነርሱ ወገን ለይተው ለማሳደድና ለማሰር እንዲመቻቸው ነው፡፡፡፡፡

💒ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው #ክርስቲያን የተባሉበት ቦታ በጊዜው የሶሪያ ዋና ከተማና የክርስቲያኖች መናኸሪያ በሆነችው #በአንጾኪያ ነው፡፡፡

<<<... ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።>>>>>
{{{[የሐዋ 11: 26]}}}

💒 አንድም በአዲስ ኪዳንም በአብ ወለድ መንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቀ የክርስቶስ አማኝ ወይም በስሙ/ክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ማለት ይሆናል፡፡፡፡
ትርጉሙም፡ የመሱሁ/የንጉሱ ተከታዮች/ባሪያዎች እንባላለን ፡ ክርስቶስ ማለት መሲህ ማለት ነውና ፡፡፡

ይህ ከሆነ እርሱን/ ኢየሱስ ክርስቶስን/ ተከተለንና መስለን ክርስቶሳውያን የተባልን እኛ ክርስቲያኖች እርሱን መስለን የምንከተልበትና የምናምንበት መንገድ /እምነት #__ክርስትና ይባላል።
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈••✥

​​እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም
🙏 አደረሳችሁ አደረሰን 🙏

✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈••✥


💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot
💠 https://www.tgoop.com/+U8lHYm3xtPo4Njhk
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥


    ​​ እንኳን ለታላቁ የዐቢይ ጾም 
   በሰላም እና በጤና አደረሳቹ አደረሰን
          🙏  አሜን (፫)  🙏


✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥


💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot
💠 https://www.tgoop.com/+U8lHYm3xtPo4Njhk
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
✥┈     የንስሀ መዝሙሮች     ┈✥


የሊቀ መዘምር ይልማ ኃይሉ መዝሙሮች

© ቤተ ዕንዚራ


✥┈ ┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈ ┈✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur 💠

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot
💠 https://www.tgoop.com/+U8lHYm3xtPo4Njhk

✥┈ ┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈ ┈✥
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍት ስብስብ 📚
💒 የአለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት 📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

➱ 1, እመጓ
➱ 2, ዝጓራ
➱ 3, መርበብት
➱ 4, ሰበዝ
➱ 5, ሜተራሊዮን
Forwarded from 💠 EOTC 💠
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽
‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

▰ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ማውጫ 🔔
https://www.tgoop.com/+o4Lx0cg9quI0ZTZk

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

▰ ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍ ማውጫ 📖
https://www.tgoop.com/+bmWacGGbXvJjOTQ8

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

▰ ኦርቶዶክሳዊ ፊልም ማውጫ 🖥
https://www.tgoop.com/+2xn741d3nc81OTNk

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

▰ ኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪ ማውጫ ☎️
https://www.tgoop.com/+LGQNqBY_V0pjM2U0

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ኦርቶዶክስ ኖት ?

📚 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ
ይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት
መፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ 📖


🔰 መጽሐፍ ቅዱስ
🔰 ድርሳናት 
🔰 ገድላት  
🔰 ተዓምራት
🔰 መልከዐት
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 መዝሙረ ዳዊት
🔰 ህማማት
🔰 መፅሀፈ ቅዳሴ                     
🔰 የሰዶም መጨረሻ                      
🔰 ባህረ ሀሳብ         
🔰 የሳጥናኤል ጎል               
🔰 አንድሮሜዳ
🔰 እመጓ ዝጎራ
🔰 መርበብት ሰበዝ
🔰 መጽሐፈ ሄኖክ 
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 የወጣቶች ህይወት
🔰 ኦርቶዶክስ መልስ አላት
🔰 የዋልድባ ገዳም ታሪክ
🔰 መጽሐፈ አክሲማሮስ
🔰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት   
🔰 ሐይማኖተ አበው
🔰 ራዕየ ማርያም 
🔰 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ
🔰 ፍካሬ ኢየሱስ
🔰 መርበብተ ሰሎሞን
🔰 የቶ መስቀል ትርጉም
🔰 ባሕረ ሐሳብ 
🔰 ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኦርቶዶክስ ኖት ?

📚 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ
ይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት
መፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ 📖


🔰 መጽሐፍ ቅዱስ
🔰 ድርሳናት 
🔰 ገድላት  
🔰 ተዓምራት
🔰 መልከዐት
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 መዝሙረ ዳዊት
🔰 ህማማት
🔰 መፅሀፈ ቅዳሴ                     
🔰 የሰዶም መጨረሻ                      
🔰 ባህረ ሀሳብ         
🔰 የሳጥናኤል ጎል               
🔰 አንድሮሜዳ
🔰 እመጓ ዝጎራ
🔰 መርበብት ሰበዝ
🔰 መጽሐፈ ሄኖክ 
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 የወጣቶች ህይወት
🔰 ኦርቶዶክስ መልስ አላት
🔰 የዋልድባ ገዳም ታሪክ
🔰 መጽሐፈ አክሲማሮስ
🔰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት   
🔰 ሐይማኖተ አበው
🔰 ራዕየ ማርያም 
🔰 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ
🔰 ፍካሬ ኢየሱስ
🔰 መርበብተ ሰሎሞን
🔰 የቶ መስቀል ትርጉም
🔰 ባሕረ ሐሳብ 
🔰 ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍት ስብስብ 📚
💒 የአለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት 📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

➱ 1, እመጓ
➱ 2, ዝጓራ
➱ 3, መርበብት
➱ 4, ሰበዝ
➱ 5, ሜተራሊዮን


➲ ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍ ማውጫ 📖
https://www.tgoop.com/+bmWacGGbXvJjOTQ8
.
🔔  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች  🔔

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ
የብዙ ዘማሪያንን መዝሙሮችን አዘጋጅተናል
በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው ያድምጡ‼️

🔔➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔔➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🔔➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🔔➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🔔➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🔔➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🔔➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🔔➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🔔➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🔔➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🔔➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🔔➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🔔➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ


በቻናላችን ላይ የእነዚህን ድንቅ ዝማሬ እና ሌላ
ብዙ መዝሙሮችን ያገኙበታል ይ🀄️🀄️ሉን።
➲ @Orthodox_mezemur

መዝሙሮቹን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
2025/01/07 10:41:00
Back to Top
HTML Embed Code: