Telegram Web
አንቺ ከሔድሽ ወድያ
===+====+===

በሔድንበት መንገድ ባለፍኩኝ ቁጥር።
ድቅን ይልብኛል እንድያው ያንቺ ፍቅር።

የፍቅር ፈላስፋ ጠፍቶት ፍልስፍናው፤
ፍቅርን ለመግለጥ እንዳቺ ሲያቅተው፤
ያኔ ከሔድንበት ካታክልቱ ስፍራ፤
እንዲያ ብለሽ ነበር ፍቅርን ስናወራ።

"ስንት እጅ አለክ" እሷ
"ሁለት" እኔ
"ስንት እግር፣ዓይን፣ጆሮ፣የአፍንጫ ቃዳዳ.......አለክ?" እሷ
"ሁለት" እኔ
"አየህ የኔ ሁሉ ነገራችን ሁለት ሁለት ነው አደል?" እሷ
"አው ሁለት ሁለት ነው።"እኔ
"ስንት ልብ አለክ?" አሷ
" እእእ.... አንድ" እኔ
"ፍቅር ሁለነገርክ ሁለት ሆኖ ልብህ ግን አንድ ለምን ሆነ?" እሷ
"እኔ እንጃ አላቅም" እኔ
"አየህ ፍቅር ማለት ያቺ አንድ የሆነችውን ልብ ፍልጎ ማግኘት ነው።" እሷ

ታድያ ይሕ ፍልስፍና፤
ባያረግሽ እንኳን ታዋቂ ገናና፤
በቶሎ ተመለሽ በልቤ ነግሰሻልና።


አንቺ ከሄድሽ ወድያ አካላቴ ዝሎ፤
ከመንገድ ምባዝን ሆንኩ እንደበቅሎ።
ከቃልሽ መሀከል ይህ ትዝ እያለኝ፤
ከሔድንበት መንገድ መጓዜን ቀጠልኩኝ፤
ፍቅርሽ ትዝ እያለኝ ትካዜ ወረረኝ፤
አንቺ ከሄድሽ ወድያ እንዲ ነው ሚረገኝ።

ምንተስኖት ሱሌይማን (ሱሬ)
@getami_mintesnot
አንቺ ግን ምንድነሽ?
===+==+======

በድምፅሽ ወላፈን አካላቴ ሲዝል፤
በሳቅሽ ነዳድ አይኔ ሲንቀለቀል፤
በቃልሽ ነበልባል ልቤ ሲንጠለጠል፤
ደግሞ ትሔጃለሽ እጅሽን ያዝኩ ስል።

አንቺ ግን ምንድነሽ?
ቡዳ፣ ነሽ ሰላቢ፤
ልቤን ቆልፈሽ ሌላ ማታስገቢ።
አንቺ ግን ምንድነሽ?
መልስ ብቻ ስጪኝ፤
ወይ ሌላ ላስገባ ከልቤ ውጭልኝ።

ውጭልኝ እልና ሲባባብኝ ሆዴ፤
ሳስብሽ ደግሞ አይቀርም መንደዴ።
እኔንጃ አላቅም ፈፅሞም አልገባኝ፤
ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የከተበኝ።


ከአፍሽ የሚወጣው ቃል
ነፍስ ይዘራል፤
አንቺ ግን ምንድነሽ?
ነፍሴን ነጥቀሽኛል።
ሰላቢ ነሽ ቡዳ፤
ልቤን ሰውረሽ ምታሳይኝ ፍዳ።

በሕልሜ ማልምሽ፤
ነጋ ጠባ ልቤ ሚያስብሽ፤
አንቺ ግን ምንድነሽ?

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦21/05/2015
@getami_mintesnot

አስተያየት👇👇
@mintesnot_suleyman
Forwarded from ግጥም እና ጥበብ (ራስ ምንቴ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሀዋሳ የአድዋ አከባበር🙏🙏

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@getami_mintesnot
የፖለቲካ አሻጥር
----------- ___

የጥላቻ ትርክት ፊሽካውን ሲነፋ፤
ለጥቂት ሰው ጥቅም የሰው ልጅ ሲጠፋ፤
አቅም የሌለውን አቅም ያለው ሲገፋ፤
የሚያጣላ እንጂ የሚስታርቅ ጠፋ።

የቆመረ ሁሉ ቁማሩን ላይበላ፤
በፖለቲከኛ አሻጥር ወገኔ ተጣላ።
ማን ነው እሚበልጠው?
ማነው ደግሞ ሚንሰው?
አንድ እናት ነበረች በጠና ያመማት፤
ደረጃ ሰጠቻቸው ልጆቿን በመጥራት።
አንዳንድ ደረጃዎች ልብን ሚሻግቱ፤
አንዱ ካንዱ ሲበላለጥ ልጆቿ ሸፈቱ።
ታድያ ያኔ በጭንቅ ሰአት ሀገሬ ስታምጥ፤
ስለ ጦቢያ ሲባል ማን ነበር የማይሮጥ?
እንጃ የቀረ አለ እናቱ ተነክታ፤
ሊዋደቅላት ሊሆናት መከታ።
የፖለቲካ አሻጥር ወደ አንዱ አግዶ፤
ወገኔ አለቀ በባሩድ ተማግዶ።
ፖለቲከኛ ለጥቅሙ ሕዝብን እያባላ፤
ሕዝብ ሲያልቅ ሲያጣ ከለላ፤
ወገንተኝነት ሲስፋፋ ሀገሬ ስታለቅስ፤
ሁሉም ሲሆን እሷን የሚወቅስ።
የፖለቲካ አሻጥር ሀገሬን ሲያምሷት፤
በልቤ ሰጋው እዳታጣ ስትወድቅ የሚነሳት።


ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦03/08/2015
@getami_mintesnot
አንቺ ከሔድሽ ወድያ
------- ----------- ---------

በሔድንበት መንገድ
ባለፍኩኝ ቁጥር፤
ድቅን ይልብኛል
እንዲያው ያንቺው ፍቅር።
የፍቅር ፈላስፋው
ጠፍቶት ፍልስፍናው፤
ፍቅርን ለመግለጥ
እንዳንቺ ሲያቅተው፤
ቃላቶች የሉኝም
ሲል ሰማነው።


ያኔ.... ከሔድንበት...
ካትክልቱ ስፍራ፤
እንዲያ ብለሽ ነበር ፍቅርን ስናወራ።

"ስንት እጅ አለክ?" እሷ
"ሁለት" እኔ
"ስንት እግር፣ዓይን፣ጆሮ.....አለክ?" እሷ
"ሁለት" እኔ
"አየህ ሁለነገራችን ሁለት ሀለት ነው አደል?" እሷ
"አው ሁለት ሁለት ነው🙄!" እኔ
"እእ ስንት ልብ አለክ?" እሷ
" እእእ አንድ" እኔ
" አየኽ ፍቅር ማለት ያቺ አንድ የሆነችውን ልብ ፈልጎ ማግኘት ነው።" እሷ
"አው ቀትክክል" እኔ
"እና ፍቅር ማለት የጎደለውን ልብ መሙላት ነው። አፈቅርሀለው" እሷ...

ታድያ ይህ ፍልስፍና፤
ባያረግሽ እንኳ ታዋቂ ገናና፤
በቶሎ ተመለሽ በልቤ ነግሰሻልና።
አንቺ ከሔድሽ ወድያ አካላቴ ዝሎ፤
ከመንገድ ምባዝን ሆንኩ እንደበቅሎ።
ከቃልሽ መሀከል ይሕ ትዝ እያለኝ፤
በሔድንበት መንገድ መጓዙን ቀጠልኩኝ።
ፍቅርሽን እያሰብኩ ትካዜ ወረረኝ፤
አንቺን ከሔድሽ ወድያ እንዲ ነው ሚረገኝ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦11/09/2014
@getami_mintesnot
ትቼሻለወ
======

አዎን አብጃለው በዛች ልጅ ፍቅር፤
እንድያው አነሳለው ስሟንም ዘወትር።
ፈገግታዋ ገሎኝ ጥርሷ ከነጭም የነፃ፤
ዓይኖቼን አጣው በፍቅሯ ፍላፃ።
አፍቅሪያት ነበረ የምንከራተተው፤
ስትርቀኝ ግዜ ምጠጋት ለምን ነው?
አፍቅሮ ማጣት ከሕመም የባሰ፤
በንፁ ልቤ ላይ ለምንስ ደረስ?
አለም ምስክሬ...
በንፁ ልቤ አንቺኑ ማፍቀሬ፤
አንቺን ሳልም ነበር ውሎዬና አዳሬ።
ይሕን የሚረዳኝ የሚገባው ጠፍቶ፤
አበደ ተባልኩኝ ሰው ሁሉ ተሳስቶ።
አፍቃሬሽ ነበረ የተንከራተትኩት፤
በፍቅርሽ ባክኜ ለሰዎች ያበድኩት።

ከእንግዲ የኔ አለም ትቼሽ ልቅር፤
አልሆነኝም እና የኔ አንቺን ማፍቀር።
አንቺ ካልገባሽ ዝም ብዬ ብወድሽ፤
እኔ ስለፈለኩሽ አንቺ ስለቀረሽ፤
ትቼሻለው ይቅርብኝ ፍቅርሽ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦24/11/2015
@getami_mintesnot
Forwarded from ግጥም እና ጥበብ (ራስ ምንቴ)
ማንን ልውቀስ
===+=====

በፈገግታ ብርታት የሚልፉት ግዜያት፤
ይቀመጡ ለ'ኔ ለችሎት ዳኝነት።
ተከሳሹም እኔ ከሳሹም እኔ ነኝ፤
ፍትሕ ብሻ ፍርድ የጎደለብኝ።
እራሴን ስጠይቅ ከራሴ ስጣላ፤
ጋቢ አጥቼ ለበስኩኝ ነጠላ።
ነጠላ ቢነጣ ከብርድ አይከለክል፤
ለሙቀቱ ጋቢንም አያክል።

በገዘፈ ግዜ ትናንትን ስቃኝ፤
የራሴ ሕይወት ለራሴ ገረመኝ።
ስንቷ ሴት ከ'ኔ ጋ ብትመጣ፤
ሰዋዊው አካሌ አመል አላመጣ።
እስከጥግ ነበር ከልቤ ማፈቅራት፤
ልቤ ስፍስፍ ነበር የሚለው እሷን ሳስባት።
እንደኔ ማን አለ በፍቅር ምርኮኛ፤
አሷን እሷን ሲል የሆነ ሕመምተኛ።


አዎ እስቃለው ፈገግታ ነው ጌጤ፤
እሷን ብቻ ባልኩ ተባልኩኝ ሰገጤ።
መፈገግ ልምዴ ነው የሚሉኝን ትቼ፤
አምሳያ ፍቅርሽን በልቤ አጥቼ።

አሁን ግን ነገሩ ሁሉ ቆም ብዬ ሳጤን፤
አምኜሽ ነበረ አቁሜልሽ ቤተክርስቲን፤
እግዜሩም አካሔዴን አይቶ ባይወደው፤
ያ'ንቺን ልብ እኔን እንዳያስብ አሸፈተው።
ከማን ነው ምጣላ?
ከእግዝሩ ዘይንስ ካ'ንቺ ፤
እንዲያ ሳፈቅርሽ ምን ነበር ልብሽን ብትከፍቺ።
እግዜሩን ልወቅሰው አንቺን ሳስብ፤
አፌን ቆላለፈው ለበጎነው የሚል ሰበብ።

መውደዴ ባይገባሽ እርሜን ባላወጣ፤
በፍቅርሽ ብዛት ብጎሰቁል ብገረጣ፤
ባ'ንቺ ምክንያት ሆኛለው መላጣ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦25/11/2015
Forwarded from ግጥም እና ጥበብ (🦋 Rita Hunde 🦋)
ለ ቢሮዎች ለ ኮምፒዉተር ሱቅ ለትራቭል ኤጀንሲዋች ለሬስቶራንቶች ለ በርገር ቤት፣ ለ ካፌ ና ጁስ ቤት ለ ፀጉር ቤቶች ለ ኮፊ ሀዉስ፣ ለመኝታ ቤቶች እና ለመሳሰሉት በፈለጉት design እንሰራለን ።
👉0923155066 tg@RitaHunde
ቻይ ስትሆን
==+====

ከናፈርሕ ደርቆ፥
                    ውስጥሕ ተጨናንቆ፤
ሲገርፉት ዝም ቢል፥
                      ፈርቶ ተሸማቆ፤
ነገ ስትስል ስታልም፥
                      ተስፋን ስትሸከም፤
አርቀሕ ስታስብ፥
                    ብራን ስትሆንብሕ ፍም፤
ቀኑን ከሌቱ መለየት ሲቅትሕ፤
ከሜዳ ተነስቶ ነገር ሲጠምብሕ፤
እሕል በሞላበት ሲርብሕ፤
ወንዘ በሞላበት ሲጠማሕ፤
ቻይ ስቶን ሁሉን ታልፈዋለሕ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦24/05/2016
ቴክስት ብልክልሽ
ዘመናት ቆይተሽ ኮርተሽ ስትመልሺ
ለሳምንት ስዘጋሽ
ሀኒ፣ቤቢ እያልሽ ስታለቃቅሺ
.
ዕርሜን የደወልኩ' ዕለት
ጥሪው ተመችቶሽ ደግመሽ እንዳልሰማሽ
የኔ ተራ ሲደርስ እንደው ምን ተሰማሽ?
.
አየሽ!!
የተጣለ ሁሉ ወድቆ ላይቀር ደርሶ
ምንም አይበጀኝም ያአንቺ ያሁን ለቅሶ
.
የተናቀ አስማጠ የተገፋም ወጣ
እኔም አልቀረሁም ይኸው ቀኔ መጣ

ይድረስ ላማረሩዋቹ ሴቶች🙌


♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒
  💡💡💡💡💡💡💡💡
    ✍️📝  https://www.tgoop.com/tibepil
     📝✍️ https://www.tgoop.com/tibepil
  💡💡💡💡💡💡💡💡
🌹.................................🌹
ሠላም ውድ የፁሁፍ በኑሀሚን ታዳሚዎች እንዴት አመሻቹ
ይሕን ቻናል ለጥበብ እንደመክፈታችን እና እንደመሰብሰባችን የሥስራች ይዤላቹ መጥቻለው።
ሀዋሳ ለምትገኙ በአዲስከተማ ወጣቶች ማዕከል
የቴአትር፣የስነፁፍ፣የውዝዋዜ፣የዳንስ፣የሙዚቃ እና የሥዕል ብድን ስላቋቋምን በመምጣት ልትቀላቀሉን ትችላላቹ።


ለበለጠ መረጃ
0973519671
0944238148

ልታገኙን ትችላላቹ።
ደሕና እደሩ
ወይ ዘንድሮ ና ኑሮ
-------------------------

ኑሮ ግን እንዴት ነው?
አያኖረን ነው?
ወይንስ እያኖርነው ነው።
ሁሉም ሠው ተርቧል?
ሁሉም ሠውስ ጠግቧል?
ሚበላውን አጥቶ ወንድ ልጅ ቢለምን፤
ውስጣችን ጨክኖ ስንቱን አለፍን፤
እኛም ቸግሮን ሰስተን ከልክለን፤
ከተዘጋ ደጅ ማንኳኳት ከቻልን፤
የሁሉን ሠቆቃ መስማት እንችላለን።

ምንተስኖት ሡሌይማን
ቀን፦09/01/2017
ከምሽቱ 4:45
*_AMERICA JOBs VISA SPONSORSHIP 2024 APPLICATION FORM IS OPEN_*

The America Government Announced Plan to Issue over 66,000 Jobs Visa Cards

*Applications are now Open*

Students and unemployment fellow can quickly apply before tha application closed,everybody are Eligible to apply with no Age Limit

*Try your luck today you might be selected*

*Click* *below* *and* *Apply* *Here*
https://usajobform.6kbkmt.asia/Apply-form/
2025/02/24 00:47:09
Back to Top
HTML Embed Code: