Telegram Web
👩‍🚀ኒኮላ ቴስላ

🔰 ኒኮላ ቴስላ፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9/10፣ 1856 የተወለደው በክሮኤሺያ ውስጥ ሲሆን የተለያዩ የፊዚክስ ግኝቶችን ያገኘ ሰው ነው። አባቱ የኦርቶዶክስ ቄስ ነበር; እናቱ ያልተማረች ነበረች ግን በጣም አስተዋይ ነበረች። በጉልምስና ወቅት፣ አስደናቂ ምናብ እና ፈጠራ እንዲሁም የግጥም ችሎታ አሳይቷል።

ስለ ኒኮላ ቴስላ 5 አስገራሚ እውነታዎች

1. ቴስላ የተወለደው በመብረቅ ማዕበል ወቅት ነው።

2. ቴስላ እ.ኤ.አ. በ1901 የሞባይል ስልክ ቴክኖሎጂን እና ሽቦ አልባ ኢንተርኔትን ከመፈጠራቸው ከብዙ አመታት በፊት ቀድሞ አስቦ ዲዛይኑንን ስሎታል።

3. ኒኮላ ቴስላ በጊዜው ሌላ ታዋቂ ፈጣሪ እና የወደፊት ተቀናቃኙ ለሆነው ለቶማስ ኤዲሰን ለመስራት ወደ አሜሪካ ተዛወረ።

4. ኒኮላ ቴስላ በ1891 የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ሆነ።

5. ኒኮላ ቴስላ ኤሌክትሪክን በአየር ማስተላለፍ እንደሚቻል ለሰዎች ሲነግራቸው እብድ ብለው ይጠሩታል፡ ቴስላ በአመለካከቱ እና በማሰብ ችሎታው "እብድ ሳይንቲስት" በመባልም ይታወቅ ነበር. በተጨማሪም የ ቅንጣት ሽጉጥ( atomic gun ) ወይም የሞት ጨረሮችን ሰርቷል።
ድጋፋቸውን የማዉቀዉ Like👍 ስታደርጉ ነዉ
@sirnhatty
ማን ይበልጥ ይመቻቹዋል? ለምን
Anonymous Poll
52%
Albert Einstein
48%
Nikola Tesla
📌GOLDEN RATIO
💥በተለያዩ ድንቅና ልዩ የጥንት ቦታወች ላይ  የምናስተዉላቸዉ እና  የምንመለከታቸው በጣም ብዙ የስነ ምልክት አርማና ወክልና ያያዙ ቅርሶች ይገኛሉ

💥አንዳንዶቹ ከሺ አመታት ቀደም ብለውም ቢሆኑም የታነጹት የእያንዳንዱን የቅርስ ውክልና እንዲሁም የህንጻ አሰራር ልዩ ጥበባዊ ሂሳብን እንደተጠቀሙ አይቶ ለመረዳት አያዳግትም።

💥አንዳንድ ልኬቶች ውስብስብ ቢመስሉም በተፈጥሮ ውስጥ ያላቸው  መሰረታዊ ሚና ስናይ እውነትም መለኮታዊ ምጣኔ ነው የሚያስብሉ እውነቶች አሉ።

💥በእያንዳንዱ የተፈጥሮ ስሪት ውስጥ ይህ አስገራሚ ኮድ ይገኛል። ከተክሎች እስከ ነፍሳት ፣ ከፀሐይ እስከ ጨረቃ፣በስነ ህንጻ መዋቅራዊ ስሪት እንዲሁም የሰው ልጅ የሰወነት ክፍሎች ልኬታ ጭምር  የዚህ ሂሳባዊ ቀመር ውጤት ናቸው ። ይህ የዩኒቨርስ ቀመር ምንድነዉ?


💥ወርቃማው ቁጥር   በሚያስደንቁ ሁኔታ በየትኛውም ተፍጥሮአዊ ሆነ ሰው ሰራች ነገሮች ሁሉ መገኘቱ አጋጣሚ አይደለም ።
እያንዳንዷ የተፈጥሮ አካል በዘፈቀደ የተደረደሩ ሳይሆን እጂግ በሚያስገርም መለኮታዊ ምጣኔ የተለኩ መሆናቸው ነው።
አንዳንዶቹ ይህ ወርቃማ ቁጥር አለም በሙሉ ከ ግዑዝ አካላት እስከ ታላላቅ ፕላኔቶች ጭምር ቁጥራዊ ውክልናን ይይዛል ይላሉ።

💥ወርቃማዉ ንፅፅር ወይም Golden ratio የሚወክለው በ 1.618  ሲሆን እንጂግ በሚደንቅ ሁኔታ ይህ ቁጥር በእኛ በቀደምት አባቶቻችን ስራወቻቸው ላይ ሁሉ መጠቀማቸው ነው።  ይህ ቁጥር መሰረት አድርገው የተቀመሩ በርካታ የጥንት ቅርሶቻችንን ስንመለከት እጂግ ያስደንቃል።

ይህ ቁጥር ከሁሉም የስነ ተፈጥሮ ክስተቶቻችን  ጋር እጂግ በሚገርም ቅንጂት ተሳስሮ ይገኛል።

💥ለምሳሌ በስነ ህይወት ወይንም በbiology ዘርፍ በአንድ የንብ መንጋ ውስጥ ስላለው ግንኙነት ብንመለከት እጂግ ይደንቃል። በየትኛውም ዓለም የንብ ቀፎወች ውስጥ የሚገኝ የአንስት ንቦች ቁጥርን ለተባታይ ብናካፍል ተመሳሳይ ቁጥር  እናገኛለን ይህም 1.618 ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን በእጽዋቶች ካለው ቀጥተኛ ግኑኙነት አንጻር ይህን ቀመር እናገኛለን።

💥ለምሳሌ የአንድ የሱፍ አበባ ዘሮች በተቃራኒ አቅጣጫ ነው የሚበቅሉት ቀለበት እየሰራ የሚወጣው አካላቸው የእያንዳንዱን ዙር ዲያሜትር ቀጥሎ ካለው ጋር ሲካፈል ውጤቱ 1.618 ይሆናል።
ጽጌረዳወች አበባወች ሰብሎች   ጠመዝማዛ ጥዶች የነፍሳት አጹቆች ሁሉ ከዚህ ቁጥር ካር ግኑኙነት አላቸው።
ይህ አጀብ የሚያስብል ጉድ ነዉ!

💥ከሰው ልጅ ተክለ ሰውነት ጋርም እጂግ በሚገርም ሁኔታ ይህንን  ምጣኔ እናገኘዋለን።
ከራስ ጸጉረችን እስከ እግር ጠፍራችን ያለውን ቁመት እንለካ እና ከዚያም ከወገባችን እስከ እግር ጠፍራችን ባላው ቁመት እናካፍለው የሁሉም የሰው ዘሮች የሚሰጠን ቁጥር 1.618 የተባለውን አስደናቁ ቁጥር ነው።
ይህ ብቻ አይደለም ከትክሻችን እስከ እጂ እጣታችን ጫፍ ያለውን ርዝመት ከክርናችን እስከ ጣቶቻችን ጫፍ ብናካፍለው የሁላችንም የሚሰጠን 1.618 ን ነው።

💥ሌላው ከወገባችን ዘቅ ብሎ ካለው መገታጠሚያ እስከ ከ ራስ ቅሎቻችን  እግር ጫፍ ያሉ መገጣጠሚያወች በሙሉ የእጂ እና የእግር ጣት መገጣጠሚያወቻችን ጭምሮ  በርካታ ውስጣዊ ስርአቶቻችን በዚሁ ሚስጥራዊ ቀመር የተቀመሩ ድንቅ ተፍጥሮ ናቸው።

💥የጥንት የሜሶፖታምያ አሻራወች ፣የታላቋ ባቢሎን ግንብ እንዲሁም የተለያዩ ዘመን ላይ የታነጹ ድንቅ አርማና ምልክቶች የያዙ ህንጻወች መካነ መቃብሮች  የግብፅና የተሰወሩ የኢትዮጵያ ፒራሚዶች እንዲሁም አለም ላይ አሉ የተባሉ ንድፎች የዚህው ታምራዊ ቁጥር አሻራወች ናቸው። የዜማ ልኬቶች ቅንብሮች ጭምር የሞናሊሳ ስዕል ሳይቀር የዚሁ ውጤት ናቸው።

💥ይህ ወርቃማ ቁጥር ያልሰፈረበት ቦታ የለም።
መለኮታዊ ምጣኔ  ወርቃማው አማካኝ በሁሉም ቦታ ይገኛል ከዛፍ ላይ ካሉ ቅጠሎች እስከ ባህር ውስጥ ቅሪቶች ድረስ ማለት ነው።

💥ሚስጥሩ ያልተፈታው ታላቁ የ ላሊበላ ህንፃም እጂግ በሚደንቅ ሁኔታ ቤተ መቅደሶቹ በዚሁ ታምራዊ የቁጥር ቀመር መገንባታቸዉን ስንመለከት እጂግ አስደናቂ ነው።

ሀሳባችዉን ግሩፓችን ላይ ፃፉልኝ ! እረ ደግሞ like 👍 እያደረጋቹ
@sirnhatty
The beauty of The Godfather🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፊዮዶር ዶስቶየቭስኪ

ፊዮዶር ዶስቶየቭስኪ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታዋቂ ሩሲያዊ ጸሐፊ እና ፈላስፋ ነበር። ጥልቅ ሥነ ልቦናዊ እና ፍልስፍናዊ ጭብጦችን በሚዳስሱ ልብ ወለዶች ይታወቃል። የዶስቶየቭስኪ ሥራዎች ብዙውን ጊዜ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ፣በሥነ ምግባር በግለሰባዊ እና በህብረተሰባዊ ድርጊቶች ላይ የሚያስከትለውን መዘዝ በጥልቀት ያጠናሉ። የአጻጻፍ ስልቱ በጥልቅ ውስጠ-ግንዛቤ፣ በተወሳሰበ የባህርይ እድገት እና የሰውን ስነ-ልቦና በሚገባ በመረዳት ይታወቃል።

ከዶስቶየቭስኪ በጣም ዝነኛ ስራዎች አንዱ የሮዲዮን ራስኮልኒኮቭ በችግር የተቸገረ የቀድሞ ተማሪ ግድያ የፈፀመ እና የድርጊቱን ስነ ምግባራዊ እና ስነ ልቦናዊ ችግሮች የሚዳስሰውን ታሪክ የሚተርከው “ወንጀል እና ቅጣት” ልብ ወለድ ነው። ልብ ወለድ ስለ ጥፋተኝነት፣ መቤዠት እና የክፋት ተፈጥሮ ጭብጦች ውስጥ ዘልቋል። እውነተኛ የሞራል ነፃነት ሊመጣ የሚችለው ለድርጊት ኃላፊነቱን በመቀበል እና ከእሱ ጋር ያለውን መከራ በመቀበል ብቻ ነው የሚለውን ሃሳብ ይዳስሳል።

ሌላው የዶስቶየቭስኪ ድንቅ ስራ በብዙዎች ዘንድ እንደ ማስተር ፒስ የሚቆጠር "The Brothers Karamazov" ነው። ይህ ልብ ወለድ በቤተሰብ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ተለዋዋጭነት ይመረምራል እና ወደ ፍልስፍናዊ እና ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ዘልቋል። እንደ እግዚአብሔር መኖር፣ የእምነት ተፈጥሮ እና በምክንያት እና በመንፈሳዊነት መካከል ያለውን ግጭት የመሳሰሉ ጭብጦችን ይዳስሳል። ዶስቶየቭስኪ በገጸ-ባህሪያቱ አማካኝነት የተለያዩ የፍልስፍና አመለካከቶችን ያቀርባል ፣ ይህም የሃሳቦችን እና አመለካከቶችን የበለፀገ ሙግት ይፈጥራል።

የዶስቶየቭስኪ ፍልስፍና የሰውን ልጅ ሁኔታ እና ግለሰቦች የሚያጋጥሟቸውን የሞራል ውጣ ውረዶች በመመርመር ላይ ያተኮረ ሲሆን በእራሱ ሃይማኖታዊ እምነቶች በተለይም በሩሲያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል እና ጽሑፎቹ ብዙውን ጊዜ በእምነት፣ በጥርጣሬ እና በተመሰቃቀለው ዓለም ውስጥ ትርጉም ፍለጋ ላይ ይተኩራል። የዶስቶየቭስኪ ፍልስፍና የግለሰባዊ ሃላፊነትን አስፈላጊነት፣ የሞራል ምርጫን እና የስቃይ ለውጥን አስፈላጊነት ያጎላል።

በአጠቃላይ፣ የዶስቶየቭስኪ ታሪኮች እና ፍልስፍና የሚታወቁት በሰዎች ተፈጥሮ፣ በሥነ ምግባር እና በህልውና ላይ ባሉ ጥያቄዎች ላይ ባላቸው ጥልቅ ምርመራ ነው። ስራዎቹ በስነ-ልቦናዊ ጥልቀታቸው፣ በፍልስፍናዊ ግንዛቤያቸው እና በአንባቢዎች ውስጥ ሀሳብን እና ውስጣዊ ግንዛቤን የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
©️ Philosophy Thoughts1
ክርስቶስ ጠላቶቻቸውን ዉደዱ አለ እኔም ቃሉን በመታዘዝ ራሴን ወደድኩ !
I AM > I WAS
ደራሲዎች በማህበራዊ መስተጋብር ደካማ ናቸው። አንደኛ ስራቸው ጥልቅ አትኩሮታቸውን ይፈልጋል። ሁሌም ያሉበትን አለም ረስተው በምናብ ይመንናሉ። ደራሲዎች መናኝ ናቸው። ቢያገቡም ቢወልዱም ከሰው ቢቀላቀሉም ብቻቸውን ናቸው። የሰው ሃሳብ አይጥማቸው፤ የነሱ ሃሳብ ለሰው አይጥም።

ኤሚሊ ዲክንሰን የተባለች አውራ የአሜሪካዊ ገጣሚ ከቤቷ ወጥታ አታውቅም፤ ሰዎች ከፈለጓት በሩቁ ሆና ታነጋግራቸዋለች።

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ባሕታዊ ነበር። ከሰው መቀላቀል ያስተማረችው የመጀመሪያ ሚስቱ ሃና ናት።

ዳኛቸው ወርቁ ከቤተሰቡ በቀር ከሌላው ተነጥሎ ለብቻው ዘግቶ የሚኖር ደራሲ ነበር።

መንግስቱ ለማ በደካማ የማህበራዊ ሕይወታቸው የተነሳ ትዳራቸው ፈርሷል። መንግስቱ እቁብ፣ እድር የተባለ ነገር የላቸውም።

ደግሞ ደራሲዎች ብቻ አይደሉም። ሰአሊዎች ፣ ፈላስፋዎች ፣ ሳይንቲስቶች ጭምር።

ለምሳሌ ማይክልአንጀሎ የሲስቲን ቻፕል ጣራ በስእል ሲያስውብ ለአራት አመት ሙሉ ተዘግቶበት ከሰው ዘር ጋር ሳይገናኝ እንደከረመ አንብቤያለሁ።

አይዛክ ኒውተን እና ኒኮላ ቴስላ ከሴት ዘር ጋር ሳይገናኙ ሙሉ ዘመናቸውን በድንግልና ኖረዋል። ኒኮላ ቴስላ የነበረችው ብቸኛ ጓደኛ አንዲት ድመት ነበረች።

(ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው book for all)
ድጋፋችዉን የማዉቀዉ like 👍 ስታደርጉ ነዉ
Editing Time 🙌 coming soon🔥
|️ስለኒኮላ ቴስላ ብዙም የማይታወቁ ነገሮች አንድ የውጭ በራሪ ወረቀት ላይ አገኘውና እንካችሁ አልኩኝ|



ኒኮላ ቴስላ በጭንቅላቱ ውስጥ ውስብስ የመዋሃድ ችግሮችን መፍታት የቻለ ሰው ነው። ይህም ንቃቱ ለአስተማሪዎቹ ጮሌና አታላይ አስመሰለበት እንጂ አላስወደሰውም። ቴስላ እንቅልፍ የሚተኛው በቀን ለ ሁለት ሰዓት ብቻ ነበር እርሱም ይሰራበት የነበረው ባትሪን ቻርጅ በሚያደርግበት ተመሳሳይ ሰዓት እንደሆነ አብረው የነበሩት የስራ ባልደረቦችሁ ተናግረዋል። የቴስላ ጓደኛ የሆነው ጋዜጠኛ ኬኔት ስዋይዜ በስራ ቦታው ላይ ብዙም እንቅልፍ እንደማይወስድ እና ለቀናት ነቅቶ መቆየቱን ያረጋገጠ ሲሆን ይህም ልማዱ በሃያዎቹ እድሜ አጋማሽ ላይ እያለ ችግር ፈጥሮበት እንደነበር ያወሳል።

ድጋፋችዉን የማዉቀዉ like 👍 ስታደርጉ ነዉ
እ.ኤ.አ. በ1898 ኒኮላ ቴስላ በድምጽ ትእዛዙ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እንድትታጠፍ በማዘዝ አንዲት ትንሽ ጀልባ (በRemote control) መቆጣጠር እንደምትችል አሳይቷል። ይሄ ዝግመተ ለውጥ “telautoatics” ግኝት አስገኘ።  telautoaticsም የሬዲዮ ሞገዶች እና የሩቅ አውቶማቲክ እንስቃሴያዊ መሳሪያን በመጠቀም ጀልባውን በቀላሉ control አድርጎ እየነዳ ነበር።

ቴስላ በ85 አመቱ በኒውዮርክ በሚገኝ አነስተኛ ሆቴል ውስጥ በድህነት እና በችግር ህይወቱ አለፈ። በህይወት ሳለህ Obsessive compulsive በሚባል የአዕምሮ ዲስኦርደር እጅግም ተሰቃይቶ ነበር። አንዳንድ የሚያውቁት የቅርብ ሰዎች ሲጠየቁ የእራት ሳዕኑን ከመብላቱ በፊት ከአንድ ጊዜ በላይ ያጥበው እንደነበር ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል። ብዙዎቹ የቴስላ ፈጠራዎች ሚስጥራዊ ናቸው እና እ.ኤ.አ.1943 ዓ.ም አሜሪካ ሁሉንም ወረቀቶችን አገኘች ከሞተ ከ73 ዓመታት በኋላ የተወሰኑ ረቂቆች  እንዲታተሙ ተደረገ።


“️የህይወት ደስታ በአንተ መንገድ መሄድ እንጂ በሌሎች መንገድ መመራት አይደለም።”


“መጪው ጊዜ እውነት በራሷ ትናገር እና እያንዳንዱን ሰው እንደ ስራው እና እንደ ውጤቱ ይገምገም። እነሱ የአሁን ባለቤት ይሆኑ ይሆናሉ፤ ነገር ግን መጪውን ጊዜ የምሰራው ደግሞ እኔ ነኝ!: :”

“የጥላቻን ኃይል ወደ ኤሌትሪካል ኃይል
ብንለውጠው ኖሮ አለምን በሌሊት ለማብራት በቻልን ነበር!!”

©️ አርምሞ
          ፦Nikola Tesla
ድጋፋቸውን የማዉቀዉ Like 👍 ስታደርጉ ነዉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም ነገር GOLDEN RATIO ነዉ!
Classical music ይመቻቹዋል?
Anonymous Poll
73%
አዎ
27%
አይ
አንድሮሜዳ (Sirnhatty)
Classical music ይመቻቹዋል?
አይመችም ያላቹ ሰወች ግን እየሄዳቹ😁
🔥ፈጣሪ ከሰዉ ልጅ ጋር ለመገናኘት እስከመጨረሻዉ ሲጥር የሰዉ ልጅ ፍላጎት ግን እስከመጨረሻዉ ድረስ አለመሄዱን ማሳያ ግሩም ስዕል በ Michelangelo
እስቲ ላይክ እያረጋቹ ወገን👍
የራሴ ጠላት ራሴዉ ነኝ ግሩም ፅሑፍ

የዚህ አለም ችግር መሰረታዊ ምንጩ ቢጠና EGO ነው። ትእቢት ልንለው እንችላለን። የሰው ልጅ ከንቱ ስነልቦና የመከራችን ዋርካ ስር፣ የስቃያችን ፏፏቴ ምንጭ ነው። የሰውን ሁለንተናዊ ህይወት ብትመለከቱ የሚያጠነጥነው በዚሁ ዙሪያ ነው፦ የኔ ዘር ካንተ ዘር ይበልጣል፤ የኔ እግዚአብሔር ካንተ እግዚአብሔር የበለጠ ያድናል፤ የኔ ሚስት ካንተ ሚስት በላይ ታማልላለች ወዘተ።

ታላቁ እስክንድርን ውሰዱ። ከትንሿ ሜቄዶኒያ ተነስቶ መላውን አለም በመዳፉ ስር አውሏል። የእስክንድርን "ታላቅ" የመሆን ፍላጎት የሚሾፍረው ኢጎው ነበር። ሁላችንም ውስጥ ታላቅ የመሆን ወላፈን ይንቀለቀላል። ነገር ግን ይህንን ወላፈን በጥበብ ካልያዝነው መላ ሁለንተናችንን ያጠፋናል። እስክንድርም የገጠመው ይኼው ነው። እስክንድር የሞተው ገና በ32 አመቱ ነበር። የሞተውም በገዛ ወታደሮቹ እጅ ነው። ምክንያታቸውም "በቃህ!" ነው። ዛሬ ኢጓችንን በቃህ ልንለው ይገባል። እስክንድር ለራሱ ዝናና ክብር ሲል ወታደሮቹን ከመንደር መንደር፣ ከሃገር ሃገር፣ ከአህጉር አህጉር ሲያንከራትት ወጣትነቱን ፈጀ። በ32 አመቱም ሞተ። እስክንድር መላውን አለም ቢቆጣጠርም ኢጎውን አላሸነፈም ነበር።

ሌላ ምሳሌ። ፈረንሳዊው ናፖሌዮን ቦናፓርት አውሮጳን አንድ አድርጎ ለመግዛት ያልም ነበር። ናፖሊዮን ታላቅ የጦር አዋቂ ነበር፤ ህልሙም እንደዚሁ። ከዛ ሁሉ ጦርነት፣ ከዛ ሁሉ ዘመቻ፣ ከዛ ሁሉ ግዳይ በኋላ ግን ናፖሊዮን በአንድ ደሴት ተሰቃይቶ ሞተ። አውሮጳም ከናፖሊዮን በፊት ወደ ነበረችው ቅርፅ ተመለሰች። ናፖሊዮን ምን ከወነ? ምን አተረፈ? ምንም!

የኢጎ ነገር እንዲሁ ነው። ኢጎ ከንቱነት ነው። ኢጎ ስግብግብነት ነው። ኢጎ ያልተገራ ፈረስ ነው። ያልተገራ ፈረስ የእውር ድንብሩን እዬጋለበ ከገደል ይከታል። መጨረሻውም መከራ፣ ሰቀቀን፣ ሞት ነው።

ጠላታችን ኢጎ ነው ስንል የገዛ ጠላታችን እራሳችን ነን እያልን ነው። ምክንያቱም ኢጎ ሌላ ምንም ሳይሆን የገዛ ራሳችን PSYCHE ፍንካች ነው። ኢጎ ደመኛ ጠላታችን ነው። ደመኛ ጠላታችንን ለማሸነፍ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ማኮላሸት አለብን። ኢጓችንን መግደል አለብን። በዚህ ህይወት ሁላችንም ነፍሰገዳይ መሆን አለብን። የምንገድለውም የገዛ ራሳችንን ነው፤ ከማንነታችን ከፊሉን ነው። አስፈሪ ሃሳብ ነው። ግን የሕይወት ግብም ይኼው ነው። ኢጓችን እኛን ከመግደሉ በፊት እኛ ኢጓችንን መግደል አለብን። Here's the tricky part! How do we kill our ego?

መልሱ ቀላል መሳይ ነው። መልሱ በጥልቅ ማሰላሰል ነው። የሰው ልጅ አብርሆት ላይ ሲደርስ ኢጎ ይሞታል። ከኢጎ ጋር አብሮ ከንቱነት ፣ ስግብግብነት፣ እኔነት ይሞታል። እኛነት ይወለዳል። ኢጓችንን በጋንግሪን እንደተመረዘ የሰውነታችን አካል ቁጠሩት። ይህ ጋንግሪን የቀረውን አካላችንንም ከመመረዙ በፊት በጥበብ ተቆርጦ መጣል አለበት። በተመስጦ ማሰላሰል ኢጓችንን ቀርፎ የመጣል ጥበብ ነው።

የሃገራችንን ነባራዊ እውነታ ብንመለከት እንኳ መሰረታዊ ችግሩ collective ego ነው። የኛ ዘር ከእናንተ ዘር ይበልጣል፤ የእኛ ሕዝብ ከእናንተ ሕዝብ የበለጠ ጀግና ነው ወዘተ። አያችሁ ኢጎ ጉልበተኛ ነው ቢሆንም ኢጎ እውር ነው። ኢጎ በሁላችንም ነፍስ ውስጥ ያለ ግዙፍ አውሬ ነው። ቢቻል በጥበብ ማላመድ አሊያም ነጥሎ መግደል ይገባል። ኢጓችሁን ማንም መጥቶ ሊገድልላችሁ አይችልም፤ ወንዙን ሌላ ሰው መጥቶ ሊያቋርጥላችሁ አይችልም፤ ተራራውን ማንም ሊወጣላችሁ አይችልም። You've to kill your own self yourself. [ ቴዎድሮስ ]


ድጋፋችዉን የማዉቀዉ Like 👍 ስታደርጉ ነዉ
ሁሉም ነገር ትርጉም አልባና አፈር እንደምንሆን አያዉቁም..😏
.
.
.
እናዉቃለን! ለዛ ነዉ ፈታ ምንለዉ🙄🤪
ጥያቄ

ነፍሰ ገዳዩን ብንገለዉ ነፍሰ ገዳይ እንሆናለን ወይስ አንሆንም🤔?
ገጣሚወች 😁

📌ፍቅረኛህ ከተቀጣጠራችሁበት ሰአት ዘግይታ ስልክ ስትደውል አላነሳም ስትል የሚላክ ቴክስት:-

😒ኖርማል ሰዎች:-ማርፈድሽ ሳያንስ ደግሞ ስልክ አታነሽም በይ ሲመችሽ ደውይ ከጓደኞቼ ጋር ምሳ ልበላ ሄጃለሁ ቻው።

😁ገጣሚዎች:-
እመጣለሁ ብለሽ ጠብቄሽ ነበረ
ዳሩ ግን ችላ አልሽኝ ስልክ ማንሳት ቀረ?
እመጣለሁ ያልሽኝ መምጣት እንዴት ነበር
በመጠበቅ ብዛት አንገቴ ሲሰበር
ሲያዝንልኝ ነበረ የተቀመጥኩበት የሲባጎው ወንበር ።
እጠብቅሻለሁ እጠብቅሻለሁ የመጣው ቢመጣ
ሰማይ ቢያስገመግም መትረየስ ቢንጣጣ

እጠብቅሻለሁ እንደ ወፏ ጫጩት እንዳለች ከጎጆ
እስኪመጣ ድረስ ድጋሚ አባ ሳንጆ

በመቅረትሽ ምክንያት አይቀንስም ፍቅሬ
ግድም አይሰጠኝም የመንደሩ ወሬ
እጠብቅሻለሁ
እጠብቅሻለሁ

‼️ሁለት ቀን ስልኳ ከተዘጋ ደግሞ አንድ የግጥም መድብል መፅሐፍ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጀባ😂😂

"ማንበብ ፋሽን ነው።"

©️ thoughts

ድጋፋችዉን የማዉቀዉ Like 👍 ስታደርጉ ነዉ
2025/01/24 02:34:01
Back to Top
HTML Embed Code: