Telegram Web
Speak when ur opinions matter...
@art_and_lit
አርግዣለሁ

መቼም እንዴት? የሚለውን ጥያቄ አትጠይቁኝም ብዬ አስባለሁ ፤ ብቻ አርግዣለሁ። ለማንም ሳልናገር ብዙም ሳልቆይ ምሳ ጋብዤ ለጓደኛዬ ነገርኳት። እሷም "እንዴት? ፣መቼ ?፣ከማን?፣ቆይ እንዴት ?.." ብዙ እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ደርድራለች። ግን የድንጋጤ ነገር ሆኖ ነው እንጂ እንዴት? ተብሎ አይጠየቅም። ለጥያቄዎቿ ባይሆንም መልስ ሠጥቻታለሁ። ስጀምር "ልጅነቴ ናፈቀኝ" አልኳት። ትንሽ አየር ስቤ "ታውቂያለሽ ልጁ ሆነሽ ሚያሳስብሽ ነገር ቢኖር መጫወት ፣ማይመስሉ ታሪኮችን በኮልታፋ አፋችን ማውራት ፣ሁሉም ነገር ደስ እያለን ምንመኝበት፣መልሶ መጫወት እና በቃ ዝምብሎ ማደግ። ልብ መግዛት ስትጀምሪ ግን መኮላተፉ ይቀራል ፣ጨዋታው ይቀንሳል ፣ ቀስ በቀስ የልጅነት ድፍረትሽ ይጠፋል። ምን ቢያጋጥመን ነው ግን እንደዚ ምንለዋወጠው?"።
ጓደኛዬ ግራ ገብቷት "ይሄ ነገር እርግዝና ብቻ ነው? አስፈራሽኝ እኮ" አለችኝ። "ሰክሪያለው ጓደኛዬ ፤ መለወጥ በማልችለው ስጨነቅ ማየት ያለብኝን ሳላይ ብዙ ባክኛለሁ። ወጣትነት ቃሉ ለራሱ ይከብዳል ወጣ- ትነት የወጣ ነገር አይደል የሚመስለው ብቻ እዚ እድሜ ላይ ስደርስ ለብ ያልን ውሀ ነን። ለብ ስልሽ ወይ በደንብ አልሞቅን ወይ በረዶ አልሆንን መምረጥ የማንችል ድብልቆሽ ነን። መንገዱ ሲጠፋብን ገዳምን የምንመርጥ፣ መኖር ሲያቅተን ሞትን የምንመኝ፣ መስራት ሲሰለቸን ተስፋ የምንቆርጥ ፣ ሣይሆንልን ሲቀር በሰው የምናሳብብ፣ግዚያዊ ስሜት አዳማጮች ና የአይን ፍቅር ሲሳዮች እንሆናለን ።

የምናምነው ስናጣ ፣የሚክደን ቢበዛ ፣ ምንጨብጠው ብናጣ በቃ እንሄዳለን ጃንቦ ልንጠጣ። ከዛማ ሚከበንን ሳናስተውል ፤ ስንስቅ ብንመስል ደስተኛ ምንከፋ አይመስላቸውም በቃ ስንዝናና። ስቃያችን መደበቂያ አላጣ ፌዝ ያለበት ግዜ ማጥፊያ ፤ ድንጋይ ማሞቅያ ቦታ ይፈልጋል። ችግርን አፍኖ አፋፍኖ መያዝን እንፈልጋለን። ለምን ግን አልጮህንም? አዎ! ኡኡኡ! ብንልስ ኖሮ? የዛኔ የሚሰማን ብናገኝ ለራሱ 'በቃ አበደች! ለየላት' በተባልን ነበር። ውስጣችን ተዳፍኖ የቀረው ንዴት፣ ሀዘን፣ ብቸኝነት፣መቅበጥበጥ፣መንቀልቀል እና ስቃይ እስቲ ብናወጣው ፍንጣሪው ምን ያህል ቦታ እንደሚያፈርስ ገምቺ ፤ብቻ ተዘርዝሮ አያልቅም። ቢገባንማ ኖሮ እንደሚሉት ወጣትነት የሠጠን እሳት መጥፊያችን ብቻ ሣይሆን መብሰያችንም ነበር። አንዴ ሙቅ አንዴ በረዶ ስንል ግን የብስል ጥሬ ሆነን እንቀራለን።

ምናለ የዛኔ የጠፋን ሲመስለን ሚነግረን ብናገኝ ብቻችንን እንዳልሆንን። የዛኔ ተስፋ ስንቆርጥ ነገ አዲስ የህይወት 'ሊዝ' መሆኗን ቢነግሩንስ ኖሮ ። ልባችን ፣ አእምሮአችን ሲሻግት መነፀራችንን ሚቀይርልን ሰው እንዴት እንጣ? መንገዱ ግራ ሲያጋባን መንገዱን በመፈለግ ውስጥ መኖርን፤ እንዴት እንጣ ሚነግረን በስቃይና ህመም ውስጥ ማለፍን። ጨለማ መደበቂያ ቢመስል እንዴት ከሰው ርቆ ፤ ከብርሀን ተላቆ። የሚነግረን ካገኘን እድለኞች ነን። ማስተዋል ቢሠጠን አመስጋኞች በሆንን። በወጣትነት ያለን ፀጋ ፣ሀይል፣ውበት፣ጥንካሬ ፣ብሩህ አእምሮ አለምን በቀየረ ይሄ እስኪገባን ድረስ ብዙ ቦታዎችን እናተራምስ ይሆናል። "

ጓደኛዬ ቀልዴ በዛባት መሰለኝ "አርግዣለሁ ብለሽ አስደንግጠሽ የምን ዝባዝንኬ ነው!" እኔም " ከዚህ በላይ ምን እርግዝና አለ። አናቴ ምን ትላለች መሠለሽ 'የተረገዘ መወለድ አለበት!' እኔም ወስኛለሁ እወልደዋለው" አልኳት።"አንቺ አብደሻል! በይ ቻው ! ለዚ ነበር ስራ ያስፈታሽኝ?" ብላ ስማኝ መውጣቷን ቀጠለች። "አየሽ አንቺ ጓደኛዬ ለራሱ አበድሽ አልሽኝ እኮ! በይ ለክርስትናው እንዳትቀሪ ጠርቼሻለሁ።" አልኳት በፈገግታ። ቢገባት ኖሮ የተናገርኩት ለሧም ነበር ይሄ ምክር አደለም ግን ከምናቡ አለም ውጪ ሌላ ታሪክ የለንም ታሪካችንን እኛ እናስተካክለው። አሁን እንውለደው!

B.
@art_and_lit
እሱ

የጨለማው ንጉስ ነው። የዳንኪራ ቤቶች ዝነኛ ፣የመጠጥ ቤቶች ቋሚ ተሰላፊ ፤ እሱ ነው። እሱን ማያቅ አለ ማለት ዘበት ነው። በቀን "አይቸዋለሁ " የሚል አይገኝም። ፀሀይ ጠልቃ ጨለማ ሲተካ ግን በቃ መዞር ይጀምራል ወደ ቢራ ጋጋታ። ታድያ የሚያቁት ፤ ብዙ ሠይመውታል በጣም የወደዱት። የአዝማሪ ቤት ዳንኪራ ወዝ አይኖረውም እሱ ከጠፋ።

ለመጠጣት ሲያስብ "አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ የሠጠኸኝን ሙሉ ጤንነት ይዤ በራሴ ተነሳሽነት ላረክሰው እነሆ ልጠጣ ልሄድ ነው" ይላል እጁን ጠምዝዞ በግድ የሚያስጠጣው ሀይል ያለ ይመስል። ጥግብ ብሎ ከሰከረ በኋላ ደግሞ "አምላኬ እንደው መራመድ ቢከብደኝ ብርሀን ሆነህ ምራኝ ፊት ለፊቱን እያየህ ፤ልጅህ አጥፍቷል ዛሬ መጠጥ በዝቶበታል " እያለ ይቀባጥራል። ንግግሩን ለሠማ ሁሌ ከአምላኩ ጋር ነው። ምን ዋጋ አለው ከንቱ ! ብኩን ሆኖ ቀረ።

እሱን ከሚመስሉ ጋር አብሮ ቢጠጣ ስንቱን ያስተናግዳል የውሸት ጋጋታ ። አንዱ ስልኩን ያነሳውና "ውዴ ስራ ይዜ ነው እራት ብይ አጠብቂኝ "፣"እየመጣሁ ነው ታክሲ ውስጥ ነኝ" ልጁ እኮ ገና የመጀመሪያ ቢራውን አስከፍቶ እየጠጣ ነው። ከውሸት የዘለለ ሚስቱን "ምን ፈለግሽ!" ብሎ የሚቆጣውን ሲያይ ደግሞ አንገቱን ወደ ሠማይ ቀና እያረገ "አቤቱ ሆይ ይሄን ክህደት ልታሳየኝ ነው እዚ የጋበዝከኝ" እያለ አንገቱን ይነቀንቃል። በጫጫታ ውስጥ ያሉ አጣጮቹ "እንዴ ምን ነካህ! እዚህማ አምላክህ ሳይሆን ሰይጣን ነው የጋበዘህ ዝምብለህ ጠጣ !" እያሉ ይሳለቁበታል።

አንዳንዴ ነሸጥ ሲያረገው ለብቻው ይጠጣል። መጫወቱን ይቀንሳል፣ራሱን ማዳመጥ ሲጀምር ግን እብደት ይመስለዋል፤ ድንጋይ የተሸከመ ያህል ትከሻውን ይከብደዋል። አምላኩን ማናገር ሲጀምር "አምላኬ ማሰቡን ላንተ ልተውልህ አንተው አስተካክለው የውስጤን ውጥንቅጥ ፤ እስከዛ ልጠጣ ሌቱ እስኪነጋ " እያለ የያዘውን ብርሌ ይጎነጫል።

እሱ ብዙ ሰው ነው። አንዴ አስታራቂ አንዴ ሁከት አስጀማሪ በተተራመሰው አለም ውስጥ የራሱን "ትንሿን ሁከት" የሚፈጥር ሰው ነው። አምላኩን ቀና ብሎ" እኔን ብቻ ነው ወይስ ሁሉንም ሠው ነው እንደኔ አስተዋይ ያረከው " ይላል በምፀት። " ልብሴን ባልቀይርም ፣ ስታይ ዝርክርክ ብመስልም ፣ብሬን ብበትንም ፣ትናንትን ብረሳም እኔ ለራሴ ጥሩ ሰው ነኝ። አዎ! እያጠፋው ነው ግን ምን ላርግ ከእኔ በፊት አለሜ ጠፍታለች ፤ከእኔ በፊት ብርሀኔ ትታኝ ሄዳለች" እያለ መቀባጠሩን ይቀጥላል።

ሲገጥም ሲያስገጥም ያድርና በማሲንቆው ዜማ ነቀፋው አልቀረም ስህተትን ካየማ። ድንገት ብድግ ብሎ " ይሄ መልእክት ለእናንተ ነው አዳምጡኝ አንዴ " ይልና "ብር ተበድሮ ለሚጠጣ ሁሉ ፣ ቀለበቱን አውልቆ ለገባ ሁሉ፣ ሳይከፍል ለመውጣት ላሠበ ሁሉ፣ጓደኛን ለመመረዝ የተዘጋጀ ሁሉ ፣ቀኑን ለማበላሸት የሚጠጣ ሁሉ እባካችሁ አንዴ ለራሳችሁ አጨብጭቡ በዚህ ውድቀት ውስጥ ለመቆየት ፈቃደኛ ስለሆናችሁ። አስቡት እስቲ ከ24 ሰዐት ውስጥ ቀናቹን ስትሰርቁ ፤እዚ ስትባክኑ እናንተ ሌቦች ናችሁ። ምታባክኑት ግዜና ገንዘብ የእናንተ ብቻ ሳይሆን የልጆቻችሁንም፣ የራሳችሁን ብር ብቻ ሳይሆን የቤተሰባችሁንም ፣የካዳችሁት እምነት የሚወዷቹን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የአምላካችሁንም ነው። ዛሬ ልንገራችሁ እናንተ ሌቦች ናችሁ..........ሌቦች..........አው......ሌቦች" አያለ መንዘባዘቡን ይቀጥላል።

ቀና ብሎ አምላኩን ማናገሩን ሁሌም አይተውም " አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ለምጠጣበት ስላላጣሁ አመሰግናለሁ ማታ እየጨቀጨኩ ባስቸግርህ አንተ ትግስተኛ እኔን ከመስማት አልተቆጠብክም። ምናለ አንተ እንዳለህ መጠጥ ሳልቀምስ በቀትር ብረዳ ገና ሳይጨልምብኝ ፤ሀጥያቴ ሳይበዛ.....ምናለ......ምናለ" እያለ መንገዱን
ይቀጥላል።

እሱ ሁላችንም ምናቀው ሰካራም ነው። አምላኩን በከፊሉ ያልረሳ፤ ብሶቱን የሚሰማለት ያጣ ብቸኛ ሰው ነው።

B.
@art_and_lit
they call it 'being on the same page' ; i call it avoiding unnecessary argument...
@art_and_lit
Don't waste your time on people who miscalculate ur intentions...
@art_and_lit
'things might have gone far more worse but here we are thinking about things that didn't'...
@art_and_lit
' its not what u should've been doing ; yet what u are doing to where u want to go that matters'
@art_and_lit
Let ur life reaction say ' i made it and i'm proud of the decisions i made '
@art_and_lit
"የሠው ልጅ በራሱ ሀሳብ መሸነፍ ሲጀምር; ዱላ ማንሳት ይጀምራል።"
@art_and_lit
mute those screams that doubts ur every move when going towards something good...
@art_and_lit
Maybe u prefer being alone because you haven't found your circle first, maybe you are vibing with the wrong people that's why u feel lost or out of game, maybe you are not getting the right people to have that productive conversations. So maybe the time is not here yet just till u find your person draw ur circle, build ur boundaries, creat the vibe u desire and that same energy will attract everything you desire most...keep growing
@art_and_lit
'This life is way too precious i dont want to waste any time sleeping and not exploring ; worrying and not experiencing'
B.
#stay_kind
@art_and_lit
A man made of pain and suffering is the most dangerous creature and no limit can holdback the birth of a vicious angry man and no law can cease the birth of vulnerable fearful soul cuz we ended up how the chaos carved us into...and we didn't know it...
@art_and_lit
' i aM tHE TYpe whO iS frIeNDly tO eVErYboDy yet NoT tHe onE wHo mAkEs anYbODy A FriEND...'
#choose_wisely
@art_and_lit
If u ask me how am doing
I could only tell this moment
A moment that has no words
Words that can't fill a sentence
Emotions unspeakable
And a silence that speaks its pain
If u ask me what am thinking
The voice in my head Keep screaming
i can't shut it up
IT dont want me to think
Questioning my action
Mirroring my reflection
Confusing my decision
Incarnation would be the word
A different kind of pain
Caging a soul inside
Praying for a fresh start
Making me over think this will not stop....
#the_demons_inside
@art_and_lit
Its funny how some experience feel different for two people experiencing it at the same time...
@art_and_lit
Loving urself doesn't mean doing things for selfish reasons. Its about building ur character ,attitude and personality in the best possible way that for some reason u just feel ultimately complete ,enough and nothing less...
#love_urself
@art_and_lit
Imagine ur life as a business and the air ur breath, the health u have, the happiness u get out of the good things u do is paid for from ur monthly salary. Some people have more than others so how many of us will keep paying for the air we breath and still smoke? , how many of us will pay for a good health and still be alcoholics? How many of us will continue to pay for a good feelings while choosing to stay in chaos. I guess we have to be rich enough to keep paying for our needs yet we choose to play around and stay lazy. I want u to imagine this too. What do u think will happen if u can't pay no more? Stuck in a dying business and thats just ur life....most of the free things in life are pricless...never forget that
@art_and_lit
Ur commitment to the extent of sacrifice ur willing to make to stay in a certain scenario determines how important something is to you...so if ur effort is not enough then its better to let go than a reckless dedication...
@art_and_lit
We will keep losing and losing if we can't see where we are failing. Inorder to achieve something whether its greed, hatred, anger and fear by itself we have to know and eliminate factors cuz if we can't do it then our insecurities will do the job for us manipulating our decision , projecting our shame and the worst thing is; it will make us so denial that we don't know its our fault all along...
@art_and_lit
2025/02/20 21:33:40
Back to Top
HTML Embed Code: