Telegram Web
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመሩት ልኡክ ቡድን አባላት በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ጎበኙ፡፡

በ2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ከ900 ሚልየን ብር በላይ በጀት ተመድቦላቸው እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ማለትም የተማሪዎች መማርያ፣ መኝታ እና የልብስ ማጠብያ ህንፃዎች፣
የውሃ፣ መብራት፣ መንገድ እና ፍሳሽ ማስወገጃ ስራዎች፣ የአጥር ግንባታ እንዲሁም የስብሰባ አዳራሽ እና የተማሪዎች መመገብያ ባንድ ላይ የያዘ ዘመናዊ አዳራሽ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክተር በተከበሩ አቶ መስፍን ነገዎ የተመራ ልኡክ ቡድን አባላት ዛሬ ሰኔ 09/2016 ዓ/ም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች በጋራ ለማየት እና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ላይ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው፡፡

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን መስሪያ ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች እና የግንባታ ባለሙዎች ተሳትፈዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለልኡካን ቡድኑ አባላት ዩኒቨርሲቲው እንዲገነባ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠለት ከየካቲት 08/2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች አጭር ሪፖርት እና ገለፃ አቅርበዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ መሰጠት ይቀጥላል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ዛሬ ያልተሰጠ ሲሆን፤ ፈተናው ነገ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም መሰጠት እንደሚቀጥል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ነገ የፊዚክስ ትምህርት ፈተና እንዲሁም ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ደግሞ የኬሚስትሪ ፈተና ይሰጣል።

[ዘገባው የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ነው]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
በአረፋ በዓል ምክንያት በቀን 9/10/2016 ዓ.ም ሳይሰጥ የዋለው የሬሜዲያል ፈተና ሰኞ (በ10/10/2016 ዓ.ም) በፊዚክስ እና ማክሰኞ (በ11/10/2016 ዓ.ም) በኬሚስትሪ ፈተና እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡ (ትምህርት ሚኒስቴር)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
አዲስ አበባ በ35 ትምህርት ቤቶች ላይ ዕገዳ ተጣለ

በአዲስ አበባ የሚገኙ 35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሂዱ ማገዱን የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሰታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛዉ ገብሩ፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን ባደረገዉ ቁጥጥር የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙና የትምህርት መመሪያዎችን ያላሟሉ 35 የግል ይዞታ ያላቸዉ ትምህርት ቤቶች ላይ እገዳ እንደተጣለ ገልፀዋል።

ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች መካከልም የካ፣ ልደታ ጉለሌና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች፣ የቅዱስ ሚካኤል አምስት ትምህርት ቤቶች፣ የካ አፖሎ ትምህርት ቤት ይገኙበታል ተብሏል።

ዕገዳ በተጣለባቸዉ ትምህር ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በመኖረያ አቅሪያቢያቸዉ በሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንዲስተናግዱ ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የተዘጉት ትምህርት ቤቶችም የተሟላ የተማሪዎችን ማስረጃ እንዲሰጡ እንደሚደረግ አስረድተዋል። (ኢፕድ)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
የ41 ትምህርት ቤቶች ፈቃድ መሠረዙን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ፈቃዳቸው የተሠረዘው የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶችን እና ፈቃዳቸው የተሠረዘ የትምህርት ተቋማትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1 ሺህ 332 ሲሆኑ÷ የማስተማር ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው ተሠርዟል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ መሆኑና ወደፊት እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ፈቃዳቸው መሠረዙን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
በ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት አገልግሎት እንዳይሰጡ የታገዱ የትምህርት ተቋማት ዝርዝር

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
2024/06/27 01:50:41
Back to Top
HTML Embed Code: