Telegram Web
በ14ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የፋሽን ሾው ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው 14ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የፋሽን ሾው ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በከሰዓቱ መርሀግብር የአራዳ ማኑፋክቸሪግ ኮሌጅ ፋሽን ሾው ውድድሩን ያካሄዱ ሲሆን በቀጣይም የቂርቆስ ማኑፋክቸሪግ ኮሌጅና እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

ለውድድሩ የቀረቡ የተለያዩ የአልባሳት አይነቶች በኮሌጁ ተማሪዎችና አሰልጣኞች ዲዛይን ተደርገው የቀረቡ ሲሆን አልባሳቶቹ አፍሪካዊነትን የሚገልጹና የተለያየ መልዕክት ያላቸው ናቸው።

በአውደርዕዩ በከተማው የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችና ወጣቶች ምርትና አገር በቀል ሥራዎች ለእይታ ለእይታ እየቀረቡ ይገኛሉ።

አወደርዕዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ለቀጣይ ሶስት ቀናት ይቆያል።(ኢ ፕ ድ)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ትምህርት ሚኒስቴር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም ጉዞ ላይ ውይይት አካሄደ።

Read More 👉 Click
ATC NEWS
Photo
ትምህርት ሚኒስቴር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም ጉዞ ላይ ውይይት አካሄደ።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር የተቋሙን የለውጥ ጉዞ በተመለከተ የግማሽ ቀን ውይይት በዋናው ግቢ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ባሉበት ወቅት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሃገርአቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እንዲተገበር የተዘጋጀውን የለውጥ እቅድ ተቀብሎ ለማስፈጸም እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሐኑ ነጋ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የታሰበው ሪፎርም አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ለመገምገም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በውይይት ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። ትም/ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ተቋማቱን የመደገፍ፣ የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ በመስራት ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን እያስቀመጠ እንዳለ የጠቀሱት ሚኒስትሩ "ዩኒቨርሲቲዎች በእውነትና በእውቀት ላይ ተመስርተው ሀገርን የመጠበቅ ልዩ ኃላፊነት ስላለባቸው ዓለም እየመጣባት ካለው የለውጥ ወጀብ ሀገራችንን ለመታደግ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት በመፍጠር መመከት እንድንችል የፊት መሪ መሆን ይኖርባቸዋል" ብለዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው የትምህርት ዘርፍ በሃገር ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ከሚገኙ የለውጥ ስራዎች መካከል ዋነኛው መሆኑን ጠቁመው የከፍ/ትም/ተቋማት እንደ ሀገር ማምጣት ለምንፈልገው ለውጥ ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደር ናሲሴ "ችግሮችን ለመቅረፍ 'እንዴት እዚህ ደረስን?' ከሚለው ጥያቄ በላይ 'ወዴት እየሄድን ነው?' በሚለው ላይ አትኩረን ዩኒቨርሲቲዎቻችን አካዳሚክ የልህቀት ማዕከላት እንዲሆኑና ትውልድን በብቃት እንዲቀርፁ ብዝሃነትን የሚያስተናግድና ለለውጥ ዝግጁ የሆነ አመራር፣ ዓለምአቀፋዊ ይዘት ያለው እና ሰላማዊ የመማር ማስተማርና የምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ማስቻል እንፈልጋለን" ብለዋል:: ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከእነዚህ መስፈርቶች አንፃር በጥንካሬ የሚነገርለት ጎን እንዳለው ሁሉ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሄ ማስቀመጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል::

'ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ለመሆን በመሰረታዊነት የተረጋጋ የፋይናንስ ሥርዓት እና ብቁ የአስተዳደር መዋቅር ያስፈልጋቸዋል' ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ኮራ ጡሹኔ የታቀደውን ሪፎርም ለመተግበር ያለፈውን አሰራር ለመኮነን ሳይሆን የተሻለ ጥራት ያለው አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ስለሆነ ከሁሉም የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ እንጂ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተለየ ችግር ስላለበት አይደለም ብለዋል::

በትም/ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች አደረጃጀትና አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ እንዳሉት መሰል ውይይት በሌሎችም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀጥል እንደሆነና አላማውም ዩኒቨርሲቲዎች ካሉባቸው ውስስብስብ ተግዳሮቶች የሚወጡበትን መንገድ በማመላከትና የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው ለማስቻል አሁን ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር ያላቸውን ቁመና በጋራ ተወያይተን መስመር ማስያዝና ብቃታቸውን ለማረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል::

በውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች በርካታ ሃሳቦች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል::


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድረሻ አከላት ጋር መክሯል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ሥርዓቱ ን ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፈተናው የተሳካ እንዲሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው÷የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ተቋሙ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎችና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን÷በቀጣይ ሁሉንም ተማሪዎች በኦንላይን ለመፈተን ሙከራ ይደረጋል መባሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#share

በዛሬው ዕለት የመውጫ ፈተና የተፈተናቹህ የኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ተማሪዎች የዛሬው ፈተና ተሰርዞ ነገ በድጋሚ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደምትፈተኑ ተረጋግጧል‼️

ስለሆነም የትምህርት መስኩ ተፈታኞች ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን።

Today afternoon exit-exam is(electrical and computer engineering )cancelled in #national level. So please prepare your self according to the above schedule and program.

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#Update #WachamoUniversity

የ2016 ዓ.ም የምረቃ መርሃግብር በተመለከተ

የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የ2016 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የምረቃ መርሃግብሩ ከዚህ ቀደም ይፋ ከተደረገው ተሻሽሏል።

👉 የተማሪዎች ምረቃ በ Main campus 25/10/2016 EC ስሆን 
👉በ Durame campus ደግሞ 26/10/2016 EC  እንድሆን ተብሏል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ለሁሉም የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተፈታኞች
*//**
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ድጋሚ የምትወስዱት ዛሬ ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ መሆኑን እንድታውቁ::

To All Electrical Engineering GC Students
//
June 25, 2024
All Electrical Engineering Students sitting for exit exam, you will re-sit for the exam today afternoon starting at 2:00 pm (8 o'clock). Please share the same information with all examinees and invigilators.

©ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ #ይፋ እንደሚደረግ ተሰምቷል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ሲል ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የጠየቃቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ብለው መልሰውልኛል በማለት ዘግቧል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

©ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
Electrical and Computer Engineering.xlsx
14.3 KB
#AASTU

Electrical engineering room placement for the exit exam


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ Management የመውጫ ፈተና በተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት መሰረት አልተዘጋጀም በሚል በርካታ ተፈታኞች ቅሬታ አቀረቡ።

ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠውን የ Management የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ፈተናው የተሰናዳው ትምህርት ሚኒስቴር እንድንዘጋጅበት ባቀረበልን ብሉ ፕሪንት መሰረት አልነበረም በሚል ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ተፈታኞቹ አያይዘውም የ management ዲፓርትመንት ለብቻው (ለዲፖርትመንቱ) ጥያቄ ተዘጋጅቶ መፈተን እየተቻለ አራት ዲፓርትመንቶችን ማለትም Management, Business management, Business administration እና Business management and entrepreneurship የሚባሉ ዲፓርትመንቶችን አንድ ላይ በመጨፍለቅ ፈተናው ተዘጋጅቷል በሚል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ለወልቂጤ ዩንቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች

ዛሬ (18/10/2016 ዓ.ም) ጠዋት 5፡00 ሰዓት ሊሰጥ የነበረው የመውጫ ፈተና #ለከሰዓት👉 8፡00 የተቀየረ መሆኑን አውቃችሁ በተመደባችሁበት የፈተና ቦታ 7፡30 እንድትገኙ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

💥በተመሳሳይ Electrical and Computer Engineering ተፈታኝ ተማሪዎች የመፈተኛ ቦታ ወደ ICT ህንጻ Lab-16 የተቀየረ መሆኑን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#Ad

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ( Entrance Exam) ተፈታኝ ለሆናቹህ ተማሪዎች በ100ብር ብቻ #Old_Curriculum Mathematics Text Book የገፅ ለገፅ ቲቶርያል ቪዲዮ አቅርበንላቹሃል።

በ100ብር ⬇️
የድሮውን የሂሳብ መማሪያ መፅሀፍ ከ9-12 የሁሉንም ቻፕተሮች የገፅ ለገፅ ቲቶርያል እና የተለያዩ ዓመታት የፈተና ጥያቄዎች የቪድዮ ማብራሪያን ማግኘት ትችላላችሁ።

[ይህ ቅናሽ ለዘንድሮ ተፈታኝ ለሆናቹህ ተማሪዎች ብቻ ነው ]

ለመመዝገብ👉 @muedu
በሁለቱም ቅርንጫፎቻችን (ሜክሲኮና መገናኛ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች ከሁሉም ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Interior Design
🎯 Digital Marketing
🎯 Adobe photoshop
🎯 Website Design
🎯 Programming Language
🎯 Video Editing
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares (Peachtree/ Queeck books)
🎯 Engineering Softwares (Autocad,Etabs, Civil 3d,Reviet, solid work, bill of quantity, software engineering courses)
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign (English, Arebic, German, Chinese, French, Italy, swedish, Norway, Spanish, Turkish..) & Local (Amharic, Oromiffa, Tigrigna, Geez..) Languages

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

አድራሻ:-1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)
            2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛዉን ሊፍት(ትንሹ ኬኬር)

☎️ 0910317675/0991929303/0991929304
@Top_trainings

Join our telegram channel
https://www.tgoop.com/topinstitutes
#AAU

አንጋፋው አዲስ አበበ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ለ74ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት ያስመርቃል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ25ኛ ጊዜ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሀሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም. ያስመርቃል።

⚡️Looking forward to July 4, 2024 starting @ 8:00 am

⚡️Venue: HU International Stadium

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
2024/09/29 02:54:54
Back to Top
HTML Embed Code: