ወንጌል ስለ ልጁ ነው። (ሮሜ. 1፥4) ልጁ ደግሞ ስለ ሁሉም ነው። “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው” እንዳለ ሐዋርያው። (ኤፌ.1፥10)
ቅዱሳት ምሥጢራት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመዳን ትምህርት፣ ነገረ ምጽአት እና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዘርፎች መክብባቸው ነገረ ክርስቶስ ነው። "ሁሉ በእርሱ ለእርሱ" የተፈጠረ ነውና፤ “ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።” (ቆላ. 1፥17)
ስለዚህ፦
1. ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ የክርስቶስን ክብር (ፍቅር) ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የምልጃ ክርክር ይህን የማስጠበቅ ያለማስጠበቅ ነው። ክርስቶስ "ይማልዳል" የሚለውን ንባብ በእግዚአብሔር ቀኝ ከመቀመጡ እና የትህትና አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን compromise ሳያደርግ መተርጎም የሚችል ከኦርቶዶክሳዊት አስተምህሮ አይጣላም፤ ካልሆነ ግን ችግር ይሆናል። (የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሮሜ 8፥34 ትርጓሜ እና የጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሐተታ ድንቅ ነው።)
2. አንዳንዶች እነርሱ የክርስቶስ እኛ የቅዱሳን ጠበቆች እንደሆን ምስል መፍጠር ይፈልጋሉ። በእኛ በኩል ግን ለነገረ ቅዱሳን ጥብቅና ስንቆም ለነገረ ክርስቶስ እየቆምን ነው። የቅዱሳን ጉዳይ የክርስቶስ አካል (የቤተ ክርስቲያን) ጉዳይ ነው። ክርስቶስን ከቅዱሳኑ ለይቶ መናገር አይቻልምና። በሥጋና በደም የተካፈላቸው እና ከራሱ ጋር አንድ ያደረጋቸው የአካሉ ብልቶች ናቸውና። እነርሱም የእሱን መልክ ይይዙ ዘንድ በጸጋው ጸንተው የተጋደሉ ናቸውና። ከቅዱሳን የተለየ እና ለእርሱ ያለውን ለቅዱሳን በጸጋ ያልሰጠ ክርስቶስን አናውቅም፤ እንዲህ ያለውን ክርስቶስ ቅዱሳት መጻሕፍት አልነገሩንምና።
3. ይህን አንድነት ተረድቶ ማስረዳት የማይችል ሰው በተለይ በእቅበተ እምነት ላይ ባይሠማራ ጥሩ ነው። ቅንዓት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ለመረዳት የምናያቸው ምልክቶች በቂ ናቸውና። ጥሩ ያልሆነ ምስል በቤተ ክርስቲያን ላይ ይፈጠር ዘንድ ምክንያት እንዳይሆን። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ነባቤ መለኮት እንዳለው ሁሉም ለጽድቅ ቢጠራም ሁሉም የነገረ መለኮት አብራሪ ሊሆን አይችልምና። መሠረታዊው የክርስትና አኗኗር (practice) ወሳኝ ነው። በንስሐ እየተዘጋጁ የሚቀበሉትን "ለማንበብ እና ለመተርጎም ያነቃቸዋል" ከተባለለት ቅዱስ ቁርባን አለመራቅን ይጠይቃል። ቀጥሎም ጊዜ ወስዶ መማር፣ ብዙ ማንበብ፣ ኦርቶዶክሳዊውን የአበው ልቡና ገንዘብ ለማድረግ በብርቱ መድከም ይጠይቃል። "Theology is not for all."
✍️መምህር በረከት አዝመራው እንደጻፈው

https://youtu.be/xKrEvhkzQ4s?si=t8zvghIdtOYoO2dt
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ በወንድም አክሊል።
በአጭር ደቂቃ ሰፊ ትምህርት 👈
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ በወንድም አክሊል።
በአጭር ደቂቃ ሰፊ ትምህርት 👈
YouTube
May 18, 2025
የቆያችኋባቸው መናብርት ከእናንተ በፊት በተራ የሚዳረሱና ማንም ጉዳይ የማይላቸው "የዙር ወንበሮች" ነበሩ። ከእናንተ በኋላ ያ ተቀይሯል። በገሐድም፣ በኅቡዕም፣ በመልከ ብዙ ግንባር (alliance) ከያዛችሁት ርቱዕ መንገድ እንድትናጠቡ የሚደረገውን ያልታዘብን አይደለንም። ያልተደረብንላችሁ እውነት ተደራቢ ስለማትሻ ነው። ባሰባችሁበትና ባሰብነው ልክ ተቋሙን ለመለወጥ እንዳልቻላችሁ እናውቃለን። ያንን የኃላፊነት ቀንበር ግን ብቻችሁን አትሸከሙትም። እንጋራችኋለን። በሦስት ዓመት የሠላሳ ዓመት ሰቆቃ የሚመዝን ድካም ውስጥ እንደ ነበራችሁ እንረዳለን። በዚህም "አባቶቻችን" ስንል አናፍርባችሁም። እናመሰግናለን። ቤተ ክርስቲያን ታመሰግናችኋለች።
አዳም "አትብላ" ለሚለው የመጀመሪያ ድምጽ ቢታዘዝ ኖሮ፣ "አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ" የሚለውን ሁለተኛውን ድምጽ ባልሰማ ነበር።
"ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍና (pig philosophy) እንተው።
"ነገ እንሞታለንና እንጹም!"
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

#ከእግዚአብሔር አባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋ እና ሰላም በሁላችን ለይ ይሁን
#ዛሬ አንድ አድስ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ነው አጋፔ ቻናል ይባላል በቅርብ ጊዜ የተከፈተ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን የሆኑ ትምህርት የሚሰጥበት ቻናል ነው
#እንቁ እና የቤተክርስቲያናችን ቀኝ እጅ በሆኑ መምህራኖቻችን እና ወንድሞቻችን እህቶቻችን አንድ በመሆን የከፈቱት ቻናል ነው በቅርብ ቀን አገልግሎት ይጀምራል
#1,በመንፈሳዊ ትምህርት
#2,በህይወት ትምህርት
#3,በዜና ቤተክርስቲያን
#4,በመዝሙር ግጥም
#5,መጽሀፎችን በpdf
#ሌሎችንም ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ትምህርቶች ይሰጥበታል የቤተክርስቲያን አስተምሮ የሚከተል ቻናል ነው
#ትንሿን ቤተ ክርስቲያንን ተቀላቀሉ👇👇
https://www.tgoop.com/Agape_Orthodox
1000 የመግባት ቻሌንጅ ሼር አርጉ ተወዳጅ ባለ ማህተቦች ይሄን ቻናል ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን እንደግፍ እንደግፍ 🙏☦