Telegram Web
የማይበድል ባርያ
የማይምር ጌታ የለም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እብሉይ የተባለ በግ ጠባቂ ነበር ከኃጥያት ስራ የቀረው የለም። ያመነዝራል፣ ይሰርቃል ይገድላል በዚህም የሰይጣንን ሥራ እየፈጸመ ፵ (40) ዓመት ኖረ።

በአንዲት ዕለትም ከቀኑ እኩሌታ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ እርጉዝ ሴትን አየ ሰይጣንም በልቡ ክፉ ሃሳብን ጨመረበት እንዲህም አለ ሆዷን ሰንጥቄ ህጻኑ እንዴት እንደሚተኛ ማየት አለብኝ ብሎ ጸጉሯንም ጎትቶ ከመሬት ጣላት ሆዷንም በቢላ ሰንጥቆ ልጁንም እናቱንም ገደላቸው።

በግ አርቢውም የሰራውንም ኃጥያት ተመልክቶ እጅግ አዘነ የማይበድል ባርያ የማይምር ጌታ የለም ብሎ አምርሮም እያለቀሰ ወደ በረሀ ሄዶ ፵(40) ዓመት ስለበደሉ አለቀሰ አጋንንትም ተገልጸው ከአንተ ዲያቢሎስ አባታችን ይሻላል እያሉ ያፌዙበት ነበር። እሱ ግን በተጋድሎ በረታ።

የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጾ ስለ ሴቲቱ ደም ጌታ ይቅር ብሎሃል ስለ ልጁ ግን ይቅር አላለህም አለው አባ እብሉይም ተጨማሪ ፵ (40) ዓመት ተጋደለ ጌታም ይቅር አለው። (ስንክሳር የካቲት ፭)


ክርስቲያን ሆይ እግዚአብሔር ይቅር ባይ መሐሪ አምላክ ነው እንደ ቸርነቱ ነው እንጅ እንደኛ በደልማ በጠፋን ነበር። ስለዚህ ንስሐ ከመግባት አንቦዝን።
✞ግነዩ ለእግዚአብሔር✞

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር
እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም(፪)

በዓለ ሃምሳ በሃምሳኛው በዚያች ቀን
በእሳት አምሳል ሰጣቸው ቅዱስ መንፈሱን(፪)

ሐዋርያትም ተቀበሉ ይህን ሥጦታ
እስከ ፍጻሜው በኃይል የሚያበረታታ(፪)

በብዙ ቋንቋ ሲናገሩ ተርጉመው
ጉሽ ጠጥተው ነው እያሉ አፌዙባቸው(፪)

የኢዩኤል ቃል ተፈጸመ ያ ትንቢት
ሲያፈስባቸው መንፈሱን አምላክ በዚያ ዕለት(፪)

ዞረው አስተማሩ ቅዱስ ቃሉን ትምህርት
ከክፉ አድኖ ዓለም አገኘ ሕይወት(፪)

እንግዲህ እንፍጠን ወደ እቅፍ ቤተክርስቲያን
እንድታድለን በአንድነት ቅዱስ መንፈስን(፪)

በጽርሐ ጽዮን የወረደው ቅዱስ መንፈስ
ይውረድ ይባርከን ያጽናናን ሁላችንን ይቀድስ(፪)

መዝሙር
በዲያቆን ሳሙኤል ልሳነወርቅ
አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
+ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ +

“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20

"ከእኛ ወገን ክርስቲያን እየተባሉ በገዛ መንገዳቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ... የእንስሳ ሥጋ ከመብላት የሚከለከሉ የሰውን ሥጋ ለመብላት ግን የሚተጉ እነዚህ ናቸው"

"ስምዖን ጴጥሮስ ከሐዋርያት ሁሉ አብልጦ ክርስቶስን ወደደው:: ክርስቶስ ግን ከሐዋርያት ሁሉ አልቆ ወንጌላዊው ዮሐንስን ይወድደው ነበር::
ስለወደደው ግን አለቃ መሆንን ለዮሐንስ አልሠጠም:: እርሱ ከወደደው በላይ እርሱን የሚወደውን አለቃ አደረገው እንጂ"

"ክርስቶስን መውደድ ከወንድሞቹ ይልቅ በጴጥሮስ ላይ በዛ:: ከወንድሞቹ ይልቅ ወደ ጌታ ኢየሱስ ለመድረስ ቸኩሏልና ከመርከቢቱ ዘልሎ ወደ ባሕር ተወረወረ እንጂ በመርከብ ለመጎተት አልቆየም::
ወደ ወደደው ለመድረስ ቀደማቸው:: ከመርከቢቱ ላይ ያዘለለችው ወደ ጥልቁም ባሕር የወረወረችው ፍቅር እርስዋ የክህደቱን መጽሐፍ ደመሰሰችለት::
ራሱን ወደ ጥልቁ የጥብርያዶስ ባሕር በወረወረ ጊዜ የዕዳው መጽሐፍ ሰጠመ:: እርሱ ግን በብዙ ጭንቅ በብዙም ፍለጋ በዋናተኞችም በብልጠታቸው ጥበብ እንደሚገኝ እንደሚያበራ ዕንቁ ሆኖ ከባሕር ውስጥ ወጣ"

#ከመጽሐፈ ምሥጢር ውብ ገጾች


"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ሐምሌ 22 በዚህች ዕለት ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በአደራነት የሰጠቻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸው እየደገፉ በትምህርታቸው እያበረቱ በማስተዳደር ላይ እንዳሉ በ1928 ዓ.ም በአረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ የተገደሉበትና ሰማዕትነት የተቀበሉበት ዕለት ነው።
አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ በ1875ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ።ብፁዕነታቸው ጴጥሮስ የሚለውን ስመ ጵጵስና ከማግኘታቸው በፊት መምህር ኃይለማርያም ይባሉ ነበር።ወላጆቻቸውም በትምህርት እንዲያድጉ ልዩ ፍላጎት ስለነበራቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ወስደው ባህታዊ ተድላ ለተባሉ አባት ሰጧቸው።ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በዚያው አጠናቀቁ።የቅኔ ትምህርታቸውን ለማስፋፋት ወደ ዋሸራ ተሻገሩ፣በዚያም በመምህርነት ተመረቁ።የዜማውንም ትምህርት በሚገባ ለመማር ወደ ጎንደር ተጓዙ። እሱንም እንዳጠናቀቁ ወደ ወሎ ቦሩ ሜዳ በመሄድ ደግሞ ከመምህር አካለወልድ የመጽሐፍት ትርጓሜ ትምህርቶች ብሉያትን፣ ሐዲሳትን እና ሊቃውንትን በብቃት አጠናቀቁ።

በ1900 ዓ.ም በምስካበ ቅዱሳን በመሄድ ወንበር ዘረጉ።በዚያም ለዘጠኝ ዓመታት ያህል ቅኔና መጥሐፍትን አስተማሩ።በ1909ዓ.ም ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም በመሔድ ምንኩስናን ተቀበሉ።ሥርዓተ ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ በምሁር ኢየሱስ ገዳም፣በዝዋይ ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት አገልግለዋል። በ1919 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አበ ንስሐ ሆኑ።

ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የራሷን ጳጳሳት ለመሾም ስትነሳ ከተመረጡት አምስት አባቶች መካከል አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ።በዚህም መሠረት ከሌሎች አባቶች ጋር ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መዓርገ ጵጵስና ተቀበሉ።ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ” ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ።

1928 ፋሽስት ወደኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ በመጀመሪያ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር አርበኞቹ ለማበረታታት ተጓዙ። ከዚያም ከተመለሱ በኋላ ወደ ወደ ደብረሊባኖስ በመሄድ የመጣውን ችግር ያሥታግስ ዘንድ እየጸለዩ ለሀገርና ለነጻነት መሞትም ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ያተጓቸው ነበር።ይሁን እንጂ በሦስት በኩል እየተመራ የመጣው ጦር እል ባለማጥቃቱ ወደየመጣበት ሲመለስ ብፁዕነታቸው ግን “ብችል ጠላት በኢትዮጵያውን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሳ አደርገዋለሁ ካልሆነ እዚሁ እሞታለሁ” ብለው ከአርበኞች ተነጥለው በአዲስ አበባ ቀሩ። ጠላት በከተማዋ ባሰማራቸው ባንዳዎች ምክንያት እንደልባቸው መንቀሳቀስም አልቻሉም ነበርና እዚሁ ከተማ ተሰውሬ መኖር አልፈልግም ብለው ሐምሌ 22ቀን 1928 ዓ.ም በወቅቱ የኢጣሊያ እንደራሴ ለነበሩት ለራስ ኃይሉ እጃቸውን ሰጡ።ራስ ኃይሉም ወዲያው ለግራዚያኒ አሳልፈው ሰጧቸው።

ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ "አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ" ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቆአቸው እርስቸውም የሚክተለውን ተናግረዋል።
"አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝ ቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ክተቱት። ወዲያው ወታደሮች በሩምታ ተኩስው ገደሉ ዋቸው። ይህ እንደሆነ አስገድዶ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።

ማታ ከአስገዳዩ ኮለኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት 'በዚህ ቄስ መገደል አኮ ሕዝቡ ተደሰቷል' እለኝ እንዴት?' ብለው 'አላየህም ሲያጨበጭብ' አለኝ። እኔም 'ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጤበጭባል' አልኩት። 'እንዴት?' ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት። እሱም አሳየኝ። ከዚህ በኋላ " የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቼአለሁ" ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ስዓታቸውን ጭምር አሳየኝ። መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተስንጥቋል።”ብለው ያዩትን መስክረዋል።

ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የብፁዕነታቸውን አኩሪ ተግባር ትውልድ ሲያዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ16 ቀን 1938 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሐውልት ቆሞላቸዋል።
የሐቀኛው አባታችን በረከት ይደርብን!
ምንጭ:- ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣
አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
አቡነ ጴጥሮስ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት 'ኮርየር ዴላሴራ' (corriere della sera) የተባለው ጋዜጣ ወኪል እና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው 'ፖጃሌ' የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓም አዲስ አበባ በነበረ ጊዜ ሂደቱን ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽሑፍ አቅርቦ ነበር:-

"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸውም ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሠየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል 'ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም አንዲያምፁ አድርገዋል' የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ አርስዎ ለምን ዐመፁ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?' ሲል ጠየቃቸው ፡፡
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መልስ መለሱ...

“አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ አኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ከርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ከርስቲያኔ አቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣረዬ ብቻ የምናገረውን አናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ” አሉ፡፡
ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእከት አስተላለፉ፡፡

''አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ።ነጸነታችሁን ከሚረክስ ሙታቹህ ስማችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪየ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።''
ጋዜጠኛው ይቀጥላል

“እኒህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣሊያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርጎም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሃቀኛ ንግግር አላስተረጎመም፡፡ እኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበበ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ኃላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቢ ተቀምጦ ስለ ነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለ ገለጠልኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተስበስቡት ጣሊያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበበ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰማ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር"። ሞት የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲቀመጡም ፈቀደላቸው፣በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው።ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር።”
ምንጭ፡ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን
ከክብርሽ ሰማይ ስር
💚💚💛💛❤️

“ድንገት ባየ ጊዜ
ደምቆ ሶስቱ ቀለም
ፈርቶም ይሁን ወዶ
የማይደነግጥ የለም”



#Ethiopia| 💚💛

#ሰላም_ፍቅር_ብልጽግና
#ይቅርታ_ፍቅር_ደስታ
#ኦርቶዶክስ እናቴ ለዘላለም ኑሪ
#የምሕረት_ዘመን_ይሁንልን


እንዴት አደርሽ እማማ ኢትዮጵያ?!💚💛

እንደ ትንሿ ወር
ልክ እንደ ጻጉሜ
ይጠርልሽ #ጦቢያዬ
የመከራ የሀዘንሽ እድሜ

መልካም አዲስ አመት😍😍
💚💛

#ፍቅር_ፍቅር_ፍቅር
#ኦርቶዶክስ_ለዘላለም_ትኑር
#ሰሰላም የመረጋጋት
#የምሕረት_ዘመን_ይሁንልን
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልትረዳ የምትችለው ሁልጊዜ አንተ በምትፈልገው መንገድ ብቻ እንዲሠራ ባለመጠበቅ ነው። አንዳንዴ በአንተ እና በአምላክህ ሐሳብ መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊኖር ይችላል። ራሱ ባለቤቱም "ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው" ብሎናል።(ኢሳ 55፥9) "ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ከጸለይህ በኋላ "የምትፈልገውን ብቻ በመጠባበቅ" ፈጣሪህን የፈቃድህ አገልጋይ አታድርገው። በጸሎትህ አምላክ የሚወደውን ወይም ፈቃዱን ማወቅ ከፈለግህ "አንተ የምትወደውን" እንደ ብቸኛ መልስ አትጠባበቅ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ኅዳር 17/ 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ቴሌግራም
መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://www.tgoop.com/atronss
+++ ልሸፈንላችሁ? +++

ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ከሕዝቡ ጋር ሲገናኝ የፊቱን ማንጸባረቅ አይተው "ተሸፈንልን" ያሉት ሕዝቡ ናቸው። እርሱ "ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ቆይቼ እኮ አሁን መውረዴ ነው? ምነው የፊቴ ብርሃን አስቸገራችሁ? ልሸፈንላችሁ እንዴ?" አላለም። እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ "ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር" ነው የሚለው።(ዘጸ 34፥29) ለቅዱሳን እግዚአብሔር በፊታቸው የሚሥለው የክብር ብርሃን እነርሱን ለሚመለከታቸው እንጂ ለራሳቸው አይታወቃቸውም። እውነተኞቹ ቅዱሳን  "ተሸፈኑልን" የሚባሉ እንጂ "ልሸፈንላችሁ" የሚሉ አይደሉም።

ጥቂት በጎ ሥራ ሠርተህ ጻድቅነትህን በግድ ለማሳየት አትሞክር። ሌሎች ተሸፈንልን ይበሉህ እንጂ፣ አንተ ራስህ "ልሸፈንላችሁ" እያልህ የዋሐንን አታስጨንቅ።

በአገራችን የሚታወቅ ተረት አለ። አንድ ጊዜ ትንኝ በሬ ቀንድ ላይ ቆመችና "ከብጄህ እንደ ሆነ ንገረኝና ልነሣልህ" አለችው። በሬውም "እንኳን ልትከብጅኝ መኖርሽንም አላወቅሁም" አላት።

"ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው"   ሉቃስ 18፥9

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://www.tgoop.com/atronss
ምጽዋት በአበው አንደበት

"አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው።"
#ቅዱስ_ባስልዮስ

"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል።"
#ቅዱስ_አምብሮስ

"አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን።"
#ቅዱስ_አግናጥዮስ

መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://www.tgoop.com/atronss
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ያላትን ግንኙነት ልታቋርጥ እንደምትችል ገለጸች።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦታው ቢገኙም ከካቶሊክ እምነት ተወካይ በስተቀር የሌሎቹ ቤተ እምነት ተወካዮች ባለመገኘታቸው መግለጫው ሳይደረግ ቀርቷል።

ነገር ግን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በትናንትናው ዕለት ታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ስብሰባ ተገኝተው የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እንደገለጹት የውይይቱ አጀንዳ 'በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተካሄደ ያለው ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ታሪካዊ ጥቃት ' በሚል እንደነበር የጠቀሱ ሲሆን በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች የሰላም ጥሪና መግለጫ እንዲሰጥ ወስነው እንደነበር አስረድተዋል። ነገር ግን በዛሬው ስብሰባ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተወካይ በቀር የሁሉም ቤተ እምነት ተወካዮች በአለመገኘታቸው መግለጫው ሳይሰጥ ቀርቷል ብለዋል። ይህም የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ሆኖ አግኝተነዋል በማለት ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበኩላቸው ለሀገር የቆመ የሃይማኖት ተቋም ተሰባስቦ ችግር መፍታት ሲገባው ከካቶሊክ እምነት ተወካይ በስተቀር ሁሉም ተናበው በመቅረታቸው በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ያዩበት አተያይ ጤናማ እንዳልሆነ ተገንዝበናል ብለዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያላት ግንኙት ይቋረጣል። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያንን ሲፈልጉ የሚያከብሯት ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚያዋርዷት እንድትሆን አንፈልግም ሲሉም ተናግረዋል።

በመጨረሻም ወጣቶች ጉዳዩ ስሜታዊ ቢያደርግም ሰዎች በሚፈልጉት መንገድ እንዳንጓዝ ያስፈልጋል። ቤተ ክርስቲያን ጸብ እንድታጭር የሚፈልጉ አሉ ስለዚህም መጠንቀቅ ያሻል ሲሉም አሳስበዋል
አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ይህንም ንጉሠ ፋርስ ከሠለስቱ ደቂቅ ጋራ አራተኛ ሆኖ በእሳት ውስጥ ሲመላለስ አይቶ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል ብሎ የገለጸበት ስም ነው፡፡ በግዕዙ ‹‹ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብኤር ይመስል›› እንዲል (ዳን ፫፡፳፭)፡፡ ንጉሡ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል እንጂ ቅዱስ ገብረኤል መሆኑን አልገለጸም፡፡ ይህንን የገለጸው ቅዱስ ያሬድ ነው፤ "ዝኬ ውእቱ ገብርኤል ዘባጢሁ ለእሳት -የሚነደውን እሳት ያጠፋው ገብርኤል ነው" ድጓ ገጽ ፻፸፡፡

በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል፤ ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፤ ጥሬ ትርጉሙ ወልደ እግዚአብሔር ይባላል አለ እንጂ በቁሙ መላእኩ የእግዚአብሐር ልጅ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል "መጋቤ ሐዲስ፣ አብሣሪው መላእክ" ይባላል፡፡ የተባለብትም ምክንያት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም "ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ" ብሎ በስሙ ትርጓሜ ምሥጢረ ሥጋዌን በመናገሩ መጻሕፍት "ወልደ እግዚአብሔር" ሲሉ ይጠሩታል፡፡ መተርጉማን ሊቃውንትም "ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ፣እግዚእ ወገብር" ብለው ተናግረዋል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" እንዲል (ሉቃስ ፩፡፲፱)፡፡ በተራዳኢነቱና በአማላጅነቱ በምእመናን ዘንድ ፈጣን ነው፡፡ ያዘኑትን ለማፅናናት የምስራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን የሚላክና ፈጥኖ የሚደርስ መላእክ ነው፡፡

በጣዖት ፍቅር እጅግ ያለመጠን ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣዖት ሰገዱ፡፡ እውነተኛ አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ንጉስ ሆይ "አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣዖት አንሰግድም" አሉት ሦስቱ ወጣቶች፡፡ ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሱ አገልጋዮች አናንያ፣ አዛርያን እና ሚሳኤልን ወደ እቶነ እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ ከእሳቱ ኃይል የተነሣ የንጉሡ አገልጋዮቹም በእሳቱ እየተጠለፉ ነደዱ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት ‹‹እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቃጠላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡፡›› አለ፡፡

ንጉስ ናብከደነፆር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን ወጣቶች የነደደውን እሳት አብርዶ በሃይማኖታቸው እንደአፀናቸው በግልጽ በነብዩ ዳንኤል ተገልጿል፡፡

የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት እኮ ጥንት የነበረ ብቻ ሳይሆን እስከ አለንበት ዘመን ደርሶ የመልአኩን አማላጅነት በዓይን የተመለከትነው ተጨባጭ ድርጊት ነው፡፡ የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን መልአኩን ልናከብረውና ልናመሰግነው ይገባል፡፡ አምላከ ቅዱሳን በረከቱን ያሳድርብን አሜን፡፡
2025/07/03 21:10:05
Back to Top
HTML Embed Code: