የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬ
በትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25) በሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀተ ክርስትና ተፈጽሞለት በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ።
ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሜዳልያ (Medal of St. Ephrem the Syrian) የተባለውን በክብር አበርክታለታለች።
እነዚያን ወርቅ የሆኑ አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚወጉ የማር ኤፍሬምን ድርሳናት ከውጭ (በሃይማኖት) ሆኖ መተርጎሙ ሁሌ ያሳዝነኝ ነበር። ታምሞ ግን የሚድንበትን መድኃኒት ተሸክሞ እንደሚቸገር ምስኪን ሰው አድርጌም አስበው ነበር። ድርሳናቱ መቼ ነው ወደሚድንበት መርከብ እየመሩ የሚያስገቡት ብዬ ብዙ ጊዜ እጠይቅ ነበር።
ያለፈው ቅዳሜ ግን ይህን ኀዘን የሚሽር የምሥራች ሰማሁ። ለካስ ቅዱሱ የቀጠረለት ቀን ነበር?! ይኸው የኤፍሬም ቀለም የበላውን (ያቃጠለውን) ምሁር ከኦርቶዶክሳዊው ካህን ስር በትሕትና በርከክ ብሎ አየሁት።
ይህ መመለስ የቅዱሱ ምልጃ እና በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ያለቀሱ የብዙ የዋሃን ምእመናን እንባ ውጤት ነው።
የአበው ድርሳን አሁንም በሥራ ላይ ነው!!!
ዲያቆን አቤል ካሣሁን

"የክርስቶስ ቤዛነት ይህ ነው፦ እርሱ ስለተሸከማቸው ዘግናኝ ሕማሞች እና ኃጢኣቶች እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ይናገራል። ኃጢኣት የማያውቀውን እርሱን እግዚአብሔር አብ ስለእኛ ሲል 'ኃጢኣት እንዲሆን' አደረገው። አመንዝራው፣ ስድ ሆኖ የሚበድለው፣ ቆሻሻ በሆኑ ተግባራት አረንቋ ውስጥ የሚዛቅጠው እና ኃፍረት አልባ በሆኑ ተግባራት የሚበላሸው ሁሉ ከክርስቶስ ሲሸሽ ድምጹ በኋላው ይከተለዋል። ይኸውም 'የተወደድህ ልጅ ሆይ፥ ና! ኃጢኣቶችህ ከእኔ ጋር
ናቸው፤' እያለ የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ደም ነው! ገና የሠራሃቸው ዕለት ነው በምልዓት የተሸከምኳቸው። ካሣውን ከፍያለሁ፦ ሐፍረት ተጭኖብኛል፤ ተገርፌያለሁ፤ ደቅቄያለሁ፤ ተሰቅያለሁ፤ እንዲሁም መርገምን ተሸክሜያለሁ። ለአንተ የይቅርታ እና የንጽሕና ተግባራትን እንዲሁም ይገባኛል የምትልበትን ጸጋ አዘጋጅቼልሃለሁ። ና! ለአንተ መከራ የተቀበልኩትን ያህል በአንተ ደስ ይለኝ ዘንድ ና! የመዳንን ዘውድ እደፋልህ ዘንድ፣ ፍቅሬን እና መንፈስ ቅዱስን
በአንተ ላይ አፈስስ ዘንድ፣ እንዲህ አድርጌ ወደ አባቴ አቀርብህ ዘንድ ና! አንተ ከበጎቼ ሁሉ እጅግ ውዱ ነህ፤ እኔ ደሜን እስከመክፈል ደርሼ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥቼሃለሁና።"
***
የክርስቶስ ስሞች፣ ገጽ 135-36።

----------------- ምእመናን ግን !!! አንድ ነገር ልብ -------- አድርጉ ።
ምእመናን ኾይ!! እኛ ዲያቆናቶቻችሁ እና እኛ ካህናቶቻችሁ እኛ መምህሮቻችሁ ቁራሽ ሰጥታችሁ ፣ ድግስ አካፍላችሁ አሥራት በኲራት ሰጥታችሁ እንዳስታማራችሁን እናውቅላችኋለን። አኹንም ሕልውናችን ከፈጣሪ በታች በእናንተ ድጋፍ ነው። ነገር ግን ይህንን የእኛን ንትር ክ አይታችሁ ከቤታችሁ ስንዝርም ኾነ ሴንቲ ሜትር ወደ ኋላ አትበሉ ።ቤታችሁ እማ ቅድስት ናት ክብርት ናት ንጽሕት ናት ብጽፅት ናት ። የጸጋ ግምጃ ቤት የክብር ሙዳይ ናት ፣ ኹልጊዜም ይህንን ታሪክ አስታውሱ
በዐለመ መላእክት በቅዱሳኑ መሀከል ዲያብሎስና ሠራዊቱ ፣ በዕብራውያን ሕብረት መካከል ሰለጵአድና አካን፣ በጌታ ጉባኤ መሀከል ይሁዳ፣በሐዋርያት ጉባኤ ግኖስቲኮች፣ በኤልሳእ ጉባኤ ግያዝ፥ በጳውሎስ ጉባኤ ዴማስ ።፤ በ፫፻ጉባኤ መሀከል አርዮስና ግብር አበሮቹ በ፪፻ ሊቃውንት መሀከል ንስጥሮስና ግብር አበሮቹ ፣ በ፩፻፶ ሊቃውንት መሀከል መቅዶንዮስ ግብር አበሮቹ ፤ እስከ ዕለተ ምጽአት በሚነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሀከል እስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሱ እኩያን መምህራን ሰባክያን ኤጲስቆጶሳት ጳጳሳት እንደሚነሱ መረዳት አለባችሁ። ይሁዳን ብቻ አይታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ከይሁዳ አጠገብ ተስፋ የምታደርጉት ክርስቶስና ቅዱሳን ሐዋርያት አሉና ። አርዮስን ብቻ አይታችሁ የርሱን ዜና ሰምታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ።
ተስፋ የማንቆርጥባቸው አትናቴዎስና እለ እስክንድሮስ አሉንና ። መቅዶንዮስን ብቻ አይታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ተስፋችሁን የሚያጸና ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትም አለላችሁና። አይዟችሁ ምእመናን እናንተን ያለ አንድ ቄርሎስ፣ ያለ አንድ አትናቴዎስ ፣ ያለ አንድ እለ እስንድሮስማ ያለ አንድ ተክለ ሃይማኖት አይተዋችሁም ። በእውነቱ አይታዋችሁም እናት ልጇን ሙሽራ ጌጧን ትረሳለችን????
ምእመናን ኾይ! ታድያ የኛ ጌታስ እናንተን ይረሳልን?? ልጁ ዳቦ የሚለምነው ፣ አባቱ ድንጋይ የሚያጎርሰው ማን ነው? ይልቁንስ የዳቦውን ልብ ልቡን አውጥቶ ያበላው የለምን? ልጁ እንቁላል የሚለምነው አባቱ እምቧይ የሚሰጠው ማን ነው? አስኳል አስኳሉን አውጥቶ ይሰጠው የለምን???
ታድያ የእናንተ የሥጋው አባት እንደዚህ የሚራራ ከኾነ አባታችሁ እግዚአብሔርማ እንደምን አይራራልችሁ ???
ምእመናን ኾይ!! ይህ የነበረ ያለ የሚኖር ነው። ይህንን ሰምታችሁ በካህኑ እጅ ከመቀበል በመ/ሩ አንደበት ከመሰበክ ፣ በጳጳሱ እጅ ከመባረክ ወደ ኋላ አትበሉ ።
ገንዳ ለራሱ እየደረቀ በጎችን ግን ያጠጣል።ሻማም ለራሱ እየቀለጠ ለሌላው ግን ያበራል። ካህናትም እንደደዚሁ ናቸው ነን ። ሻማውን ትታችሁ ብርሃኑን ተጠቀሙ ።ገንዳውን ሳይኾን ውሃውን ገንዘብ አድርጉ። ጌታ በወንጌል እንዲህ ብሏል ። ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በጌታ ወንበር ተቀምጠዋል።ስለዚህ ያዘዟችሁን ኹሉ አድርጉ ጠብቁትም።ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ። እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳን ሊነኩት አይወዱም ማቴ ፳፫ ፥ ፪ ከላይ የተቀሰውን ጥቅስ ኹላችሁ መለስ ጊዜ አስቡት። ቤ/ክርስቲያንን በግለሰቦች መለካት መመጠን ታላቁ ስህተት ነው። ቤ/ክርስያናችሁ ዐለቷ ክርስቶስ ነው፤ የትምህርት የሃይማኖት ዐለቷ ቅ/ጴጥሮስና ሐዋርያት ናቸው። እና ነፋሳት በነፈሱ ቁጥ ማዕበላት በወረዱ ቁጥር ጎርፎች በጎረፉ ቁጠር አትነቃነቁ ። እኛ እናሻግራለን እንጅ እኛ እናሻግራለን እንጅ አንሻገርም የተባለውን ምሳሌ አልሰማችሁምን?? ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ወንጌል ስለ ልጁ ነው። (ሮሜ. 1፥4) ልጁ ደግሞ ስለ ሁሉም ነው። “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው” እንዳለ ሐዋርያው። (ኤፌ.1፥10)
ቅዱሳት ምሥጢራት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመዳን ትምህርት፣ ነገረ ምጽአት እና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዘርፎች መክብባቸው ነገረ ክርስቶስ ነው። "ሁሉ በእርሱ ለእርሱ" የተፈጠረ ነውና፤ “ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።” (ቆላ. 1፥17)
ስለዚህ፦
1. ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ የክርስቶስን ክብር (ፍቅር) ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የምልጃ ክርክር ይህን የማስጠበቅ ያለማስጠበቅ ነው። ክርስቶስ "ይማልዳል" የሚለውን ንባብ በእግዚአብሔር ቀኝ ከመቀመጡ እና የትህትና አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን compromise ሳያደርግ መተርጎም የሚችል ከኦርቶዶክሳዊት አስተምህሮ አይጣላም፤ ካልሆነ ግን ችግር ይሆናል። (የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሮሜ 8፥34 ትርጓሜ እና የጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሐተታ ድንቅ ነው።)
2. አንዳንዶች እነርሱ የክርስቶስ እኛ የቅዱሳን ጠበቆች እንደሆን ምስል መፍጠር ይፈልጋሉ። በእኛ በኩል ግን ለነገረ ቅዱሳን ጥብቅና ስንቆም ለነገረ ክርስቶስ እየቆምን ነው። የቅዱሳን ጉዳይ የክርስቶስ አካል (የቤተ ክርስቲያን) ጉዳይ ነው። ክርስቶስን ከቅዱሳኑ ለይቶ መናገር አይቻልምና። በሥጋና በደም የተካፈላቸው እና ከራሱ ጋር አንድ ያደረጋቸው የአካሉ ብልቶች ናቸውና። እነርሱም የእሱን መልክ ይይዙ ዘንድ በጸጋው ጸንተው የተጋደሉ ናቸውና። ከቅዱሳን የተለየ እና ለእርሱ ያለውን ለቅዱሳን በጸጋ ያልሰጠ ክርስቶስን አናውቅም፤ እንዲህ ያለውን ክርስቶስ ቅዱሳት መጻሕፍት አልነገሩንምና።
3. ይህን አንድነት ተረድቶ ማስረዳት የማይችል ሰው በተለይ በእቅበተ እምነት ላይ ባይሠማራ ጥሩ ነው። ቅንዓት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ለመረዳት የምናያቸው ምልክቶች በቂ ናቸውና። ጥሩ ያልሆነ ምስል በቤተ ክርስቲያን ላይ ይፈጠር ዘንድ ምክንያት እንዳይሆን። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ነባቤ መለኮት እንዳለው ሁሉም ለጽድቅ ቢጠራም ሁሉም የነገረ መለኮት አብራሪ ሊሆን አይችልምና። መሠረታዊው የክርስትና አኗኗር (practice) ወሳኝ ነው። በንስሐ እየተዘጋጁ የሚቀበሉትን "ለማንበብ እና ለመተርጎም ያነቃቸዋል" ከተባለለት ቅዱስ ቁርባን አለመራቅን ይጠይቃል። ቀጥሎም ጊዜ ወስዶ መማር፣ ብዙ ማንበብ፣ ኦርቶዶክሳዊውን የአበው ልቡና ገንዘብ ለማድረግ በብርቱ መድከም ይጠይቃል። "Theology is not for all."
✍️መምህር በረከት አዝመራው እንደጻፈው

https://youtu.be/xKrEvhkzQ4s?si=t8zvghIdtOYoO2dt
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ በወንድም አክሊል።
በአጭር ደቂቃ ሰፊ ትምህርት 👈
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ በወንድም አክሊል።
በአጭር ደቂቃ ሰፊ ትምህርት 👈
YouTube
May 18, 2025
የቆያችኋባቸው መናብርት ከእናንተ በፊት በተራ የሚዳረሱና ማንም ጉዳይ የማይላቸው "የዙር ወንበሮች" ነበሩ። ከእናንተ በኋላ ያ ተቀይሯል። በገሐድም፣ በኅቡዕም፣ በመልከ ብዙ ግንባር (alliance) ከያዛችሁት ርቱዕ መንገድ እንድትናጠቡ የሚደረገውን ያልታዘብን አይደለንም። ያልተደረብንላችሁ እውነት ተደራቢ ስለማትሻ ነው። ባሰባችሁበትና ባሰብነው ልክ ተቋሙን ለመለወጥ እንዳልቻላችሁ እናውቃለን። ያንን የኃላፊነት ቀንበር ግን ብቻችሁን አትሸከሙትም። እንጋራችኋለን። በሦስት ዓመት የሠላሳ ዓመት ሰቆቃ የሚመዝን ድካም ውስጥ እንደ ነበራችሁ እንረዳለን። በዚህም "አባቶቻችን" ስንል አናፍርባችሁም። እናመሰግናለን። ቤተ ክርስቲያን ታመሰግናችኋለች።
አዳም "አትብላ" ለሚለው የመጀመሪያ ድምጽ ቢታዘዝ ኖሮ፣ "አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ" የሚለውን ሁለተኛውን ድምጽ ባልሰማ ነበር።
"ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍና (pig philosophy) እንተው።
"ነገ እንሞታለንና እንጹም!"
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

#ከእግዚአብሔር አባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋ እና ሰላም በሁላችን ለይ ይሁን
#ዛሬ አንድ አድስ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ነው አጋፔ ቻናል ይባላል በቅርብ ጊዜ የተከፈተ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን የሆኑ ትምህርት የሚሰጥበት ቻናል ነው
#እንቁ እና የቤተክርስቲያናችን ቀኝ እጅ በሆኑ መምህራኖቻችን እና ወንድሞቻችን እህቶቻችን አንድ በመሆን የከፈቱት ቻናል ነው በቅርብ ቀን አገልግሎት ይጀምራል
#1,በመንፈሳዊ ትምህርት
#2,በህይወት ትምህርት
#3,በዜና ቤተክርስቲያን
#4,በመዝሙር ግጥም
#5,መጽሀፎችን በpdf
#ሌሎችንም ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ትምህርቶች ይሰጥበታል የቤተክርስቲያን አስተምሮ የሚከተል ቻናል ነው
#ትንሿን ቤተ ክርስቲያንን ተቀላቀሉ👇👇
https://www.tgoop.com/Agape_Orthodox
1000 የመግባት ቻሌንጅ ሼር አርጉ ተወዳጅ ባለ ማህተቦች ይሄን ቻናል ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን እንደግፍ እንደግፍ 🙏☦