tgoop.com/bahiretibebat/8167
Last Update:
✝ስለ እርሱ አንብቡ !
እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለ እርሱ አብዝታችሁ አንብቡ 🌱
▸እርሱን ለማወቅ ስለ እርሱ አንብቡ ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ ❓
▸ ስለ እርሱ አንብቡ ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ ። ነገር ግን ወደ #እርሱ_ጥልቀት_ለመግባት ወይም እርሱ #ወደ_እናንተ_ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ .. ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ ❗️ በጽሑፎች ውስጥ ስለ እርሱ " ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ..." [ መዝ 44*2] የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት☀️ ታውቁ ዘንድ አንብቡ ።
▸ #እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለ እርሱ አንብቡ ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ ።
▸ ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰለሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "...እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው " [ መኃ 5*16] ትላላችሁ ።
▸ ከወደዳችሁት ስለ እርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ ። እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚያነቡትን ስለ እርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል ። ስለ እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ #እንደምትወዱት🥰 ታውቃላችሁ ። "
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ☀️
BY የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥናትና ምርምር መጽሔት ስራዎች
Share with your friend now:
tgoop.com/bahiretibebat/8167