Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
8164 - Telegram Web
Telegram Web
፲፪. ይቅርታ

ሰምተን ለመዳን ያብቃን - ይቆየን
የየካቲት 4 ዕለቱ ወንጌል ንባብ!

ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር። ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ምልክት ይፈልጋል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል።ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች👩‍⚖️፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ። የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ። መብራትንም አብርቶ በስውር ወይም በእንቅብ በታች የሚያኖረው የለም፥ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ🕯 ላይ ያኖረዋል እንጂ።

የሉቃስ ወንጌል 11:29-33
'"ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ➾ ሰው በልቡናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ። "'

ስርዓተ ቅዳሴ

➾አንዳንዴ በሰዎች ተቀይማችኹ ልክ ቅዳሴ ገብታችኹ ስትሰሙት 🤲 ... ከዛ ትውት ቅያሜያችኹን ተፈውሳችሁ ወደ ቤታችኹ
💫በቅዱሳን ጸሎት እኛንም ይማረን 🤲
“በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።”
መዝ 18፥6
የሰማይን አምላክ አመስግኑ

መዝ 135/6፥26
" እግዚኦ ኢትጸመመኒ ስእለትየ
እስመ 'አፈ ዐማፂ'፥ 'ወአፈ ኃጥእ' አብቀዉ ላዕሌየ።
ወነበቡ ላዕሌየ በልሳነ ዐመፃ። "
          መዝ ፻፰ ÷ ፩

አቤቱ ባርያህን ቸል አትበል🤲
▸◂ " ጌታዬ አምላኬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ #የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ #ምስጢሬን አዋይሃለሁ።

▸◂ ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል #ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ😭 ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር #ብቻ ስሆን ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን #ባዶነቴ ያስጨንቀኛል።

▸◂ ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ #ነፍሴ ከዓለምና በዓለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን #ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"

     ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

#በሰማይ_የሀሉ_ልብክሙ 🤲
አምላክ ሆይ፥ ምሥጋናዬን ዝም አትበል፥”
መዝ 108፥1
'' አቤቱ፥የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ❗️
በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ➠ #ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት። አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። ''

መዝ ፫÷፩
2025/02/27 06:43:40
Back to Top
HTML Embed Code: