Telegram Web
"ለመወለዱ ጥንት በሌለዉ አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮቱ ከአብ በተወለደ ዳግመኛም እኛን ለማዳን ቡሃላ ዘመን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በእግዚአብሔር ልጅ እናምናለን ።የቀኑ ቀጠሮ ሲደርስ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከድንግልም ተወለደ።"
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
እሰይ ነጋ!ቀኑን ሙሉ ክፋትን በመስራት አንተን ስናሳዝን እንዳንውል ጠብቀን::

ከራሳችን ጠብቀን
ከክፉ ሐሳቦቻችን ጠብቀን
ከጠላት ወጥመድ ጠብቀን
እረኛችን ሆይ ጠብቀን

መልካም ቀን
በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡
      ሥርዓተ ቅዳሴ
           @behlateabew
ጌታችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወደው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከቅድስት ማርያም መወለዱንም የማያምን ሰው ሁሉ እንግዳ እስከሚሆን ምጽአቱ ድርስ ጳውሎስ እንደ ተናገረ የተለየ ይሁን፡፡
        ሥርዓተ ቅዳሴ
          @behlateabew
"መብላትና መጠጣት ብቻውን ጓደኝነት አይስብለውም፣እንዲህ ዓይነቱ ጓደኝነትማ ዘራፊዎች እና ነፍሰ ገዳዮች እንኳ አላቸው። ነገር ግን ወዳጆች ከሆንን፣ እርስ በርሳችን ከልብ የምንተሳሰብ ከሆነ፣ እርስ በርሳችን በመንፈሳዊነት የምንረዳዳ፣ ጓደኞቻችንን ወደ ገሃነም የሚወስዱ እንቅፋት አናድርገው።
      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አቤቱ አንተን ደስ ከማያሰኝ ሐሳብ እንለይ ዘንድ መለየቱን ስጠን....አቤቱ የእውቀት ዓይኖችን ስጠን፤ ዘውትር አንተን ያዩ ዘንድ ፤ጆሮቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ።"

ቅዳሴ እግዚእ
“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡ ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
የጥምቀት ገሃድ እና ሰንበት

✥እንደ ሥርዐተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ማንኛውም ክርስቲያን ሊጾማቸው
የሚገቡ የአዋጅ አጽዋማት 7 ናቸው፡፡ እነዚህም ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ፍልሰታ፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድ፣ ጾመ ነነዌ እና ጾመ ድኅነት (የዓርብና ረቡዕ ጾም) ናቸው፡፡ የገሃድ ጾም ከ7ቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው ማለት
ነው፡፡
✥ገሃድ ማለት “ለውጥ፣ ልዋጭ” ማለት ነው፡፡ … ወይም እንደ ዘይቤው “ግልጥ”ማለት ነው፤ “ይፋ” ማለት ነው፡፡ የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ስለሆነ ገሃድ ይለዋል
በተጨማሪም ዕለቱን
ፍትሐ ነገስት ጾመ ድራር እያለም ይጠራዋል

✥ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ
ሲውሉ በሌሊት ስለሚቀደስና ስለሚበላ በለውጡ በዋዜማው ሐሙስና ማክሰኞ
ይጾማል፤በሌላም ቀን ቢውል የጥምቀት ዋዜማ ቅዳሴው ለሊት ስለሆነ ይጾማል ይህም ጾም በያመቱ እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኗል፡፡

✥ነገር ግን የዘንድሮን 2017 ዓ.ም ለየት የሚያደርገው ጥር 10ቀን ቅዳሜ ሰንበት ላይ ስለዋለ የምንጾመው ከጥሉላት (ከፍስግ) ምግቦች ብቻ ይሆንና አርብን እስከ 12 ሰአት እንጾማለን ማለት ነው
ከብርሃነ ጥምቀቱ በረከትን ያድለን
በዓሉን የሰላም በዓል ያድርግልን አሜን
✟"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቁ ምክንያት ከብሉይ ወደ ሐዲስ፥ ከኦሪት ወደ ወንጌል አሻገረን፤ የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ከፈተልን፤ ወደ ሀገራችን (ወደ ሰማይ) ይጠራን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ሊነገር በማይችል ክብር ያከብረን ዘንድም ቅዱስ መንፈሱን ላከልን፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
መልካም በዓል!!!
❝ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን። ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ። ... መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች። ❞
ቅዱስ ኤፍሬም
ካህን ለተጋቢዎች ከሚጸልየው ጸሎትና ከሚሰጣቸው ቡራኬ ውስጥ አንዱ እንዲህ ይላል፦

"በቃና ዘገሊላ ሰርግ የወረደች የእግዚአብሔር በረከት ትደርባችሁ። በመካከላችሁም ስምምነትን ታድርግላችሁ፤ ፍቅርን በልቡናችሁ ታሳድርባችሁ፤ ብዕላችሁን ያብዛላችሁ፤ ቤታችሁን ያንጽላችሁ፤ ረጅም ዕድሜ ጸጥ ያለ ኑሮ ይስጣችሁ፤ የተባረኩ ልጆችንም ይስጣችሁ። አሜን!"

ከገ/እግዚአብሔር ኪደ ፌስቡክ ገጽ
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ በአሁኑ "አሐቲ ቤተከርስቲያን" አለን ? "በአሁኑ ሰዓት ቅዳሴ ከአለ በሥጋ ወደሙ"።

ይድረስ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ና ሰባኪያን

የከተማ ለአንድ ክብረ በዓል ለdecoration ብቻ በሚሊዮኖች ብር ይመደባሉ። ገጠር በአገልጋይ ፣ በጧዋፍ እና ዕጣን ዕጥረት ዓመት ሙሉ ያለአገልግሎት ዘመኑን አሻግረሉ።

ልክ ጌታችን ሐሙስ ማታ ከሰዱቃውያን እና ከፈሪሳውያን ፈተና በፊት ወደ ጌቴሴማኒ ሄዶ ብቻውን እንደ ቆመ ሁሉ የገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ባለፉት ዓመታት በትልቅ እና ውስብስብ ፈተና ውስጥ ወድቀው፣ የድኅነት በሮች ተዘግተው፣ ከአውደ ምህረቷ በትምህረቷ ልጆቿን ስትሰበስብበት የነበሩ አደባባዮቿ ዛሬ የከብቶች ግጦሽ ሆነው የቀሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ቅዳሴና ማህሌትን መሳተፍ ሳይሆን ሰምተው ለመደሰት እንኳን በናፍቆት ሲጠባበቁ የነበሩ ምዕመናን ተስፋ ወደ መቁረጥ ተቃርበዋል፡፡ ተስፋም ጨልሞአል።

በዓመታዊ ክብረ በዓላትና በጥምቀት እንኳንስ ከመንበሩ ወጥቶ ህዝቡን ባርኮ የማያውቁ፣ ቅዳሴና የውስጥ አገልግሎት የማያገኙ ታቦታት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በሥጋ ተወልደው በመንፈስ ግን በጥምቀት ከእግዚአብሔር ያልተወለዱ፣ ክርስቲያኖች ሆነዉ የድኅነት በራቸው ተዘግታባቸው ንስሃ አባት አግኝተው ከኃጥያታቸው ተፈትተው የንስሃ ሕይዎት እንኳን እንዳይኖሩ እናታቸው በተ ክርስቲያን የአገልግሎት መካን ሆናባቸዋለች፡፡

ከዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን በአገልጋዮች ችግር ምክንያት ታቦት ከመንበሩ ተነስቶ ሳይወጣ ቀርቶ፣ የቤተ ክርስቲያን፣ም ደጅ ተዘግቶ ማየት ምን ያህል ልብ ያደማ ይሆን? መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማግኘት መናፈቃቸውስ እስከ መቼ ይሆን? ማንስ ይድረስላቸው? ቅዱስ ጳውሎስ " እኛ ሁላችን ወንድማማች ነን፡፡ አንድ ህብስትም ተካፍለናል፡፡

በአንድነትም ክርስቶስን እንመገባለን፡፡" ያለውንስ አስበን እኛ ለምን በወንድማማችነታችን አልደረስንላቸውም?
የከተማ አድባራትና ካቴድራሎች ከ10 ያላነሱ ሰባኪያነ ወንጌል አሏቸው፡፡ የገጠር አጥቢያዎች ግን እንደ ወረዳ አንድ እንኳን ሰባኬ ወንጌል የሌላቸው፣ የከተማ አድባራት የአንድ ሰባኪ ደመወዝ በወር እስከ 20ሺህ ሲሆን የአንድ ገጥር አጥቢያ ዓመታዊ በጀት ግን 8ሺህ የማይሆን፣ መሪጌቶችና ሊቃውነት በከተማ በአንድ አጥቢያ ከ20 እስከ 100 ሲሆኑ በገጠር ግን እንደ ወረዳ አንድ እንኳን በሌለበት እንድ ሐዋርያት በጸሎት ሃይማኖት "ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡" ስንጸልይ እንዴት አውነት ሊሆንልን ይችላል?

የከተማ አቢያተ ክርስቲያናት ብዙ ሊቃውንት፣ ሰባኪያነ ወንጌል እንዲሁም በርካታ የሚያስተምሩ አባቶችን ይዘው አውደ ምህረታቸው ሁሌም በወንጌል፣ የውስጥ አገልግሎትም፡- በማህሌት፣ በሰዓታት፣ በኪዳን፣ በቅኔ፣ በቅዳሴ አሸብርቆ በገጠር ያሉ ወንድሞቻቸው ደግሞ ይህን ሁሉ አገልግሎት አጥተው በነፍስም በስጋም ተርበው ሳሉ ነገ ጌታ ሲመጣ " ተርቤ ኣላበላችሁኝም፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም" ብሎ ሲጠይቀን ምን ብለን እንመስለት?
ታርዤ አላለበሳችሁኝም ለሚለውም ጥያቄ የገጠር ምዕመናን ቤተ ክርሰቲያነቸው ተዘግቶባቸው በጥምቀት ክርስቶስን ሳናለብሳቸው ቀርተን ምን አይነት መልስ እንሰጥ የሆን?

የሰማያዊው ህብስት እና የሕይወት ውኃ ምንጭ የሆነው የክርስቶስ እናትና ሙሽራ ቤተ ክርስቲያን ተዘግታ ከማየት የሚበልጥ ምን ኀዘን አለ? አንድ ሰው ለምድራዊው ሀገሩና ወገኑ ተቆርቁሮ አክቲቪስት እንደሚሆን ገንዘቡንና ያለውን ነገር ለዚህ ጉዳይ እንደሚያውል ሁሉ ለሰማያውያን ወይም መንፈሳውያን ወንድሞቹስ ለምን አይቆረቀርም? አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እናቶቻች፣ እህቶቻችን፣ ጓደኞቻችን እና ልጆቻችን በችግር ውስጥ እያሉ እኔ ክስርቲያን ነኝ ለማለትስ ምን ሞራል ይኖረናል? ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ሲመጣ ለምታልፈው ዓለም ሌትና ቀን እየደከምክ፣ የሐብትና የደም መስዋዕትነት እየከፈልክ ለማታልፈው ለሰማያዊ ርስትህ ለቤተ ክርስቲያንህስ እጅህ ወዴት ነው? መችስ ጊዜ ይኖርሃል? ሀብትህስ የት አለ? ሁሉን ለሰጠህ ለመስጠት የተከፈተ የልብ የስቶታ በር አለህን? ወላጅ እናትህ፣ አሳዳጊህ በአገልግሎት የወላድ መካን ስትሆን ምን ይሰማህ ይሆን?
ስጋዊ ቤትህ ጸድቶ የሕይዎት እንጀራ ቤት የጌታ ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም የሚፈተትባት መንፈሳዊ ቤትህ የገጠሯ ቤተ ክርስቲያን በመካነ መቃብር ተከባ እንዲህ መስላ የቅዳሴ እና የሌሎች አገልግሎት ድምጽ ጠፍቶት የአሞራዎች ድምጽ ከቧት ያየ አይንና የሰማ ጆሮ ምን ይበል?

የምዕመናን የመዝሙራቸው ድምጽ ሲስተጋባባት የነበረች የቤተ ከርስቲያን ደጅ በአራዊት እና በእንስሳት ፈርሳ ክርስቲያኖች በችግራቸው ጊዜ እረፍት የሚያገኙባት የነበረች ቀን የከብቶች እና የሌሎች እንስሳት ማረፊ ሌሊት የአራዊት መዝናኝ ሆና ስናገኛት ሂሊናችን ምን ያህል ይረበሽ? ጌታ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም እንዳለው ከስጋና ከነፍስ መከራ መፍትሄ ለማግኘት ወደሷ የመጡት እልፍ ክርስቲያኖች ተዘግታ ሲያገኟት በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨምሮባቸው ውስጣቸው ቆስሎ የሚያጽናናቸውንም አጥተው የሰላም በር በሆነችው በቤተ ክርስቲያን ፊት ቆመው ሲያለቅሱ ከማየት በላይ እንባ ለምን ይውረድ?
ደዌ ስጋ ታመው በየሆስፒታሉና በየፀበል ስፍራዎች ከወደቁት በላይ አገልግሎት በማጣት የተዘጋችውን ቤተ ክርሰቲያን አይተው በመንፈሳዊ ቅናት የታመሙትን ማን ይጠይቃቸው? ድውያነ ስጋን ገንዘብና ምግብ ይዘን እንጠይቃቸዋለን፡፡ አገልግሎት በማጣት ታመው ዐይናቸው በእንባ የልባቸው ሀሳብ ስለ ቤተቨ ክርስቲያን በማሰብ የታመሙትን በምን እንጠይቃቸው የሆን? ትናንት ዳዊትና ጽና ይዘው ቤተ ክርስቲያንን በዜማ ሲያገለግሉ ቆይተው በእርጅና ምክንያት በቤት የቀሩት አባቶች በእርጅና ድካም ላይ የቤተ ክርስቲያናቸውን መዘጋት ሲያዩ ይህን ከማየት ይልቅ ሞትን አይመርጡምን?

ትላንት መጾረ መስቀልን ይዘው ተንስዑ ሲሉ የነበሩ ዲያቆናት ዛሬ እጃቸው ባዶ ቀርቶ በልባቸው ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው እያንጎራጎሩ ሲሄዱ የማን ጆሮ ሰምቶ አለንላችሁ ይበላቸው? እናቶችና አባቶች በእርጅና ዘመናቸው ንስሃ ገብተው ከክርስቶስ ጋራ መኖር እየተመኙ ምኞታቸው ሳይሳካ ቀርቶ ሌሊት መንጣፋቸውን በእንባ የሚረጥቡትን፣ በተዘጋችው ቤት ክርስቲያን ደጅም እንባቸውን እየፈሰሱ እንደ ራሄል ወደ ሰማይ የሚረጩትን ማን አይቶ እኔ ደረስኩላችሁ ይበላቸው?

ግን ለምን ክርስቲያን በመንፈሳዊ ወንድሙ ላይ ልቡ ጨከነ? አንዲት ቤተ ክርስቲያን አለችን የሚል ወገንስ ለወገኑ አለሁልህ የሚል ድምጹ ለምን ጠፋ? ይህ ትውልድ ሌላው እንኳን ቢቀር አለሁልህ ብሎ አእምሮውን የሚያረጋጋለትን ሰው ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስያኔ ተዘጋች ብሎ አካሉና ሀሳቡን ለዓለም አሳልፎ የሰጠውን ትውልድ ማን ከተኩላ መካከል ይመልሰው? ማንስ በኀዘን የተሰበረውንና የፈረሰውን የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ቀና ያድርገው? ሕዝቅ 22 እንደ ተባለው በፈረሰው በኩል ለመጠገን ዪቆመው ማነው? በመንፈሳቸው ታመው ወድቀው የቆሰሉትን መንፈሳዊ ወገኖቹን ዘይት ቀብቶ ደግፎ የሚያነሳ ደጉ ሳምራዊ ማነው? እንደ ሐዋርያው ፊሊጶስ ባልንጀራውን በበጎ የሚያስበው የት አለ?
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
ጌታችን ይቺ ከሁሉ አብልጣ ሰጠች ብሎ እነዳመሰገናት ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ጉልበቱን ገንዘቡን፣ ሙያውን በመስጠት ጌታውን ለማስደሰት የተዘጋጀ ማነው? የክርስቶስ አካል የሆነችዋ ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ ድረሱልኝ ብላ አሰምታ ስትጣራ ድምቷን ሰምቶ እናቴ አለሁልስ የሚላት እውነተኛ ልጇ የመስቀሉ ስር ዮሐንስ ታዲያ ማነው?

የምድር አቀማመጥ እና በሁሉም የፈተና ሰይፍ እየተወረወረባት ልጆቿን ለማትረፍ የምትቾኸዋን የገጠር ቤተ ክርስቲያን ማን እኔ አለሁልሽ ይበላት? በአቡነ ተክሃይማኖት ለይ ሲወረወር የነበረው የፈተና ሰይፍ በመንፈሳዊ የሀይማኖት አገልግሎት ደካሞች የሆኑትን የገጠር ክርስቲያኖችን ምን ያህል ያቆስላቸው ይሆን? የተክልዬ አምላክ ድረስልን! የሀይማኖት ጽናትን እንዲሰጠን ተክልዬ በአምላክህ ፊት ቁምልን እያሉ እጃቸውን ወደ እግዚአብሔር ለሚዘረጉት የቱ መንድም አለሁላችሁ ይበላቸው?
ስነ ልቦናቸው የተሰበረውን ካህናትና አገልጋዮችንስ ማን የጠግናቸው? ለፈርሰው ህንፃ አብያተክርስቲያናት ደግሞም ኃጢአትን በማብዛት በቁም ለሞቱት ህንፃ ሥላሴ የሆኑት የሰው ልጆች እንደ ዲያቆን ፊሊጶስ በቅልጥፍና አስተምሮ አጥምቆ በደስታ ለመመለስ ለመንፈስ ቅዱስ ምርጥ እቃ ለመሆን የተዘጋጀ ማነው? እውነተኛ ፌቨን በመሆን ለክርስቲያን ወገን የምትስብ ሴት ማናት? የተራበውን ሕዝብ ጌታ አበርክቶ እንዲመግባቸው ሁለት አሳና አምስት እንጀራን ወደ ጌታ የሚያቀርቡ እነማን ይሁን ?

የአባቶች አይን በእንባ ብዛት ፈዞ ብሌናቸው ፈዟል፡፡ ከንፈሮቻቸውም ድረሱልን በማለት እየጮሁ እና እየወተወቱ ደረቀ፡፡ በመከራው ጊዜ ርዝመት ምክንያትም አንገታቸው ተሰብሮ አቀረቀሩ፡፡ አንጀታቸው በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ተረጋግቶ አልቀመጥ በሏቸዋል፡፡

ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ስለ ድንግል ማርያም ሲናገር እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር እንዳለው አወሷም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል እንዳለችው የተባረከ ዘር በመሆን በተለያየ መልኩ በዘመናዊ ፈተና ተጠላልፎ ለፍርድ እሳት ተላልፎ እየተሰጠ ያለውን ትውልድ ከዚህ በኋላ ደርሶለት ከጥፋት የሚያድነው የተመረጠ ትውልድ ማነው? እንደ ዘሩባቤል መቅደሱን መልሶ በማነጽ እስራኤላቅያን ዘነፍስን ከጥፋት የሚታደግ ሰው ከወዴት እንጥራ? እንደ ነሂሚያ የፈረሰውን የእየሩሳሌምን ግምብ እና ቅጥር መልሶ ለመሥራት ከገኖቹ ጋር አንድ ልብ በመሆን ወደ ሥራ የሚገባ ከወዴጥ እናምጣ?
ጌታችን ያቺ አመንዝራ የነበረች ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ጥሩ መዓዛ ያለው የከበረ ሽቱ ይዛ እሱ ወዳለበት ወደ ስምዖን ቤት ስትሄድ ሌሎቹ ሲነቅፏት ከመሞቴ በፊት ለቀብሬ አዘጋጅታኛለችና ተዉአት እርሷ ያደረገች ይህ ነገር ይህ የመንግስት ወንጌል በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ እሷ ያደረገች ዳግሞ ለመተሰቢያ ይሆንላት ዘንድ ይነገርላታል እንዳለው ምንም እንኳን ሰውነታችን በኃጥያት ቢቆሽሽም መልካም መዓዛ ያለው ሽቱ በመያዝ የክርስቶስ አካል ወደ ሆነችው ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን ማን ይሂድ? በስጋ ከዚህ ዓለም ሳንሰናበት ምን አይነት በጎ ነገር ሠርተን በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ ይሁንልን?

ሞቼ ከዚህ ዓለም ላይ ከማለፌ በፊት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያኔ አገልግሎቷ እንዲሰፋ ምን ይዤ ልቅረብ? ምን ሠርቼም በመንፈስ የወለደችኝን መንፈሳዊ እናቴን ቤተ ክርስቲያንነን ላስደስት?
"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም። ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
2025/01/27 03:36:04
Back to Top
HTML Embed Code: