Telegram Web
የይሁዳ መሳም ውጤቱ ጌታን አሳልፎ መስጠት ነው። የለንጊኖስ መውጋት ውጤቱ ልጅነት የምናገኝበትን ማየ ገቦ ማስገኘት ነው። እንዲህ ከሆነ ከይሁዳ ሰላምታ የለንጊኖስ መውጋት ይሻላል።
ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ፣ ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፣ አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ

➥|እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል (ዐሠርቱ ቃላት) የተጻፉብሽ የሙሴ ታቦት (ጽላት) ነሽ፡፡ (ጊደሮች) ርግቦች ከልጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደወደዱ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ፈጽሜ አፈቅርሻለሁና ረድኤትሽ አይለየኝ፡፡
ባዘንኩም በተቆረቆርሁ ጊዜ የኃዘኔ መፅናኛ ነሽ። ባለቀስኩም ጊዜ የለቅሶዬ መተዊያ ነሽ። በዘመርሁ ጊዜ ለእጄ እንደ መሰንቆ ለጣቶቼም እንደበገና ነሽ። በተራብሁ ጊዜ ለሆዴ ትመግቢኛለሽ በተጠማሁ ጊዜ እኔን ለማርካት የሕይወት ውሃን የተመላሽ ነሽ። በተጨነቅሁ ጊዜ ጭንቀቴን ታርቂያለሽ። በቆሰልኩም ጊዜ ቁስሌን ታጠጊያለሽ። በበደልኩም ጊዜ ኃጢያቴን ታቀልያለሽ። በርኩሰቴም ጊዜ ንጹሕ ታደርጊኛለሽ። የደኸየሁም ጊዜ ለድህነቴ ባለጸግነት ሀብቴ ነሽ።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የመድኃኒት ብልቃጥ ድንግል ሆይ ጸሎቴ በልጅሽ ፊት የተወደደ ይሁን የሙሴ መሥዋዕት በምድረ በዳ የአሮን መሥዋዕት በምስክሩ ድንኳን የተወደደ እንደ ሆነ፡፡
አርጋኖ ዘረቡዕ
ወዘእንበለ ንስአሎ ይሁብ ፍትወተነ|ሳንለምነው የምንሻውን ይሰጠናል::
ኪዳን ዘነግህ
“ጸቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ፤ ሀሊበ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፤ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስሂን"
ቅዱስ ያሬድ

እንኳን አደረሳችሁ
በዓታ ለማርያም
“የክርስቶስ ፍቅር እንደምናውቀው እና እንደምንጠብቀው “እንደሆነው የሚቀበል(accept as who they are)” አይነት ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር ሰዎችን እንደሆኑት የሚቀበል እና ‘አዲስ፣ዋጋ የሚታጣለት፣ታላቅ’ አድርጎ የሚለውጥ ነው።”

አበምኔት አይሪኒ
ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ

| ከአንተ ሌላ (ከአንተ በቀር ሌላ) አምላክ እንደ አለ አልሰማንም አላየንም አባቶቻችንም አልነገሩንም ።
መፅሐፈ ሰዓታት
ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?)” (ማቴ. 16:24 )
አኀዊነ በኵሉ አስተፋጠንኩ ከመ እጽሐፍ ለክሙ በእንተ ሕይወተ ኵልነ እስመ ጥቀ እጽሕፍ ለክሙ ጽሑቀ ወአስተበቍዐክሙ ከመ ትትቀነይዋ ለእንተ ተውህበት ለቅዱሳን ሃይማኖት።| ወንድሞቻችን ስለ ሁላችን ሕይወት አጽፍላችሁ ዘንድ በሁሉ ቸኰልኩ እንድጽፍላችሁ አጅግ ጓጕቼ ነበርና ለቅዱሳን የተሰጠችውንም ሃይማኖት እንድ ታገለግሏት እማልዳችኋለሁ ።
የይሁዳ መልክት 1-3
“በከየት ወለሀወት ገዳምከ፤
ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ... “

እንኳን ለአባታችን አባ ሳሙኤል የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
"ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት የማኅፀንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድንዋልና። ከእኛም እርግማንን አጠፋልን። "
ቅዱስ ኤፍሬም
“በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰዉ ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፣ ስለተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋህዷልና ቅድምና የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት”
ቅዱስ ኤፍሬም
 “ይህች ቤተልሔም መንግሥተ ሰማያትን መሰለች”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፤ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው፤ እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡”
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ናጣሊስ
"ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤
እርሱም እናቱን ፈጠረ፤
የፈጠረውንም ሥጋ መልሶ ተዋሐደው።"
ቅዱስ ኤፍሬም
"በቀዳማዊት ሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ሞት በሰው ላይ ሰለጠነ፤ በዳግማዊት ሔዋን (ድንግል ማርያም) መታዘዝ ምክንያት ሕይወት ወደ ዓለም መጣ፡፡ ሞት ኃይሉን አጣ፡፡"
ቅዱስ ሄሬንዮስ
ከአብ የተወለደ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሚሆን የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ በመለኮቱ መዋረድ ሳይኖርበት በፈቃዱ ተዋርዶ የተገዥ ባሕርይን ተዋሐደ።

ሰው ሆይ ሥጋ ያልነበረው እርሱ ለአንተ ብሎ ሥጋን ተዋሐደ፤ ሰው ሆይ በመለኮቱ አይዳሠሥ የነበረ ነፍስን ሥጋን የተዋሐደ ቃል ለአንተ ብሎ ተዳሠሠ፤ በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍጹም ሥጋ ተዋሐደ።

አይታይ የነበረው የሚታይ ሥጋን ተዋሐደ፤ የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ሥጋ ተዳሠሠ፤ የማይለወጥም አደረገው።

ባዕል እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለ፤ የነገሥታት ንጉሥ በበረት ተጣለ።


ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አጢፎስ
ምዕራፍ ፰

👉 @behlateabew 👈
"ከዛሬ ጀምሮ ስላምን እንከተላት ክርስቶስ በዚህች ዕለት ተወልዷልና።"
ቅዱስ ያሬድ
2025/02/05 07:16:26
Back to Top
HTML Embed Code: