Telegram Web
ልጄ ሆይ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን፤ በድኃ ላይ አትጨክን፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን፤ ስትበለጥግ ድኅነትን፤i ስትሾም ሽረትን፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት፡፡

ልጄ ሆይ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል፡፡

ለአፍህ መሐላ አታልምደው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ፡፡

ልጄ ሆይ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም፡፡

ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡

ልጄ ሆይ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና፡፡

ልጄ ሆይ፤ ጠላት በዛብኝ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ እጽፍልሃለሁ፡፡ በፍየል ነብር፤ በበግ ተኩላ፤ በአህያ ጅብ፤ በላም አንበሳ፤ በአይጥ ድመት፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው፡፡ ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡ ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት & የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡

ልጄ ሆይ፤ ቀን በሥራህ ላይ፤ ሌሊት በአልጋህ ላይ፤ የሚጠብቅህ እግዚአብሔር ነውና ማታ ስትተኛ፤ ጧት ስትነሣ እግዚአብሔርን አምላክህን መለመንና ማመስገን አትተው፡፡

(ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር)
የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤

የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤

የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤

የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤

የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤

የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤

የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤

የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤

የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#ጠቃሚ_ምክር_ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ባልንጀራህን ልትገሥጽ ብትፈልግ፣ ልትመክር ብትሻ፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ልታደርግ ብትፈቅድ ይህን ያለ ቍጣና ከስሜታዊነት ወጥተህ አድርገው፡፡ የሚገሥጽ፣ የሚመክር ሰው ባለ መድኃኒት ነውና፡፡ ነገር ግን ለራሱ ባለ መድኃኒትን የሚሻ ከኾነ ሌላውን ሰው እንደ ምን መፈወስ ይቻለዋል? ራሱ ቁስለኛ ኾኖ ሳለ ሌላውን ለመፈወስ ከመኼዱ በፊት የራሱን ቁስል የማያሽረው ለምንድን ነው? ባለ መድኃኒት ሌላ ሰውን ለማዳን በሚኼድበት መጀመሪያ የራሱን እጅ ያቆስላልን? የሌላውን ዐይን ለማዳን የሚኼድ ባለ መድኃኒት አስቀድሞ የራሱን ዐይን ያሳውራልን? እንዲህ ከማድርግ እግዚአብሔር ይጠብ ቀን፡፡

ስለዚህ አንተ ሰው! ሌላውን ከመገሠጽህና ከመምከርህ በፊት የራስህ ዐይኖች አጥርተው የሚያዩና ንጹሃን ይኹኑ፡፡ ሕሊናህን አታቆሽሸው፡፡ እንዲህ ከኾነ ግን ሌላውን ማንጻት እንደ ምን ይቻልሃል? በቍጣ ውስጥ መኾንና ከቍጣ ንጹህ መኾን የሚሰጡት ውስጣዊ ሰላም በጭራሽ የሚነጻጸር አይደለም፡፡ እንዲህ ከኾነ ታዲያ ሰላም የሚሰጥህን ጌታ [ነፍስህን] አስቀድመህ ከዙፋኑ ላይ ጥለህና ከጭቃው ጋር ለውሰኸው ስታበቃ፡ ከእርሱ እርዳታን የምትሻው እንዴት ብለህ ነው? ዳኞች የዳኝነት ሥራቸውን ሊያከናውኑ ሲፈልጉ አስቀድመው ካባቸውን ደርው ከፍርድ ዙፋናቸው ላይ እንደሚቀመጡ አላየህንምን? አንተም ነፍስህን የዳኝነት ልብስን አልብሰሃት በተገቢው ቦታዋ ልታስቀምጣት ይገባሃል፡፡ እርሱም የማስተዋል ልብስ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 62-63)
ALERT

ሊባኖስ የምትኖሩ ካላችሁ

(ሼር በማድረግ በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች እንዲደርስ እናድርግ!)


በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ
ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ
በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል።

ጽህፈት ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል።

ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተከታተለ እንደሚገኝም አሳውቋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዜጎች እንድትወስዱ ሲል አሳስቧል።

1. በአብዛኛው የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይቻላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ቦታዎች እራስን ማራቅ፣

2. ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን እና አቅጣጫዎችን መተግበር ወይም ማከበር፤

3. አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የበለጠ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ በቀጣይ የምንወስዳቸውን እርምጃዎችን ይፋ ስለምናደግ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የፌስ-ቡክ ፔጅ የሚለቀቁ መረጃዎችን በየጊዜው መከታተል፣

4. ማንኛውንም የከፋ ሁኔታ በሚገጥማችሁ ወቅት በቆንስላው ቀጥታ የስልክ መስመር +9615467166 እና በWhatsapp ቁጥር ማሳወቅ ጠቃሚ ይሆናል።


(መረጃው ከቲክቫህ ማጋዚን የተገኘ ነው)
"ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም ይስተካከላል!"

አንድ የመዋዕለ ህፃናት ርዕሰ መምህር እሁድ ጠዋት የሚያስተምሯቸውን ህፃናቶች እና ወላጆቻቸውን ሰብስበው እየተናገሩ እያለ አንድ ህፃን ልጅ ሲያስቸግራቸው የሚጫወትበት ተገጣጣሚ መጫወቻ (puzzle Game) ይሰጠዋል። ጨዋታው የተበታተነውን የአለም ካርታ ገጣጥሞ የተስተካከለ ዓለም ማምጣት ነበር። የዓለም ካርታው ውቅያኖስ እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ህፃኑ ለማስተካከል ቸገረው። ነገር ግን የካርታውን ክፍልፋዮች ሲገለበጥ የሰው አካል ቁርጥራጭ ስእሎችን አገኘ። ይህ የሰው ስእል የአለሙ ካርታ በትክክል ሥፍራውን ከያዘ በኋላ በእስኪብርቶ የተሳለ ስእል ነበር። ህፃኑ ታድያ ስዕሉን እንዲሁም አባቱን እየተመለከተ የተሳለውን የሰው ስእል ቦታ ቦታውን ያሲዘውና ገልበጥ ሲያደርገው የዓለሙ ካርታ ተስተካክሎ አገኘው።

ወዲያው ለአባቱ ያሳየዋል። አባትየውም በመገረም እንዴት እንዲህ በፍጥነት አስተካከልከው ቢለው ህፃኑም ሰውየውን ሳስተካክለው የዓለም ካርታውም ተስተካከለልኝ አለው። ያም ርዕሰ መምህር በነጋታው ጠዋት ባልደረባዎቹን ሰብስቦ ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም ይስተካከላል ሲል ተናገረ።

(ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)
#መንፈሳዊ_የግጥም_መደብል_ለኢሉ_ኪዳነምሕረት

ገቢው በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ ለምትገኝ ለኢሉ ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ህንጻ ማስፈጸሚያ የሚውል በአረብ አገር (ሳኡዲ አረብያ) የሚኖሩ እህቶች የተዘጋጀ መንፈሳዊ የግጥም መደብል ነው።

መጽሐፍን እየገዛን የበረከቱ ተካፋይ እንሁን... ሼር እያደረግን ላለደረሰው እናድርስ መጽሐፉ ተሽጦ ለታሰበበት አላማ እንዲውል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

➛ የመጽሐፍ የጀርባ ዋጋ 250ብር
➛ መጽሐፉን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች እየደወላችኹ ማግኘት ይቻላል።

➛ 0912868821
➛ 0914140681
(ቀጥታ በመደወልና እና በቴሌግራም ቢያዙን ካሉበት ቦታ እናደርሳለን)

የገዳሙ አካውት ቁጥሩ ገቢ ማድረግ ካሰቡ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000 26 68 75 348
ኢሉ ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ህንጻ ኮሚቴ

በእንተ ንስሐ በቅዱስ ኤፍሬም

እርሱ ለገበሬው ዝናብና ጠልን በነፃ ስለ ሰጠ ገበሬው ማረስና መዝራት ትቶ አይተኛም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ኃጢአተኞችን የሚያድን መድኃኒት (ንስሐ) በእጃችን ስላለ ለኃጢአት ሥርየት መለመንን አንተው፡፡ ዘወትር መጸለይንም አንስነፍ፡፡

አንድ ገበሬ ዘር ባይዘራ ዝናቡ መዝነቡ ምንም ጥቅም እንደማይሰጠው ሁሉ ኃጢአተኛም ስለ ኃጢአቱ ተጸጽቶ ምሕረትን ካልለመነ ንስሐም ካልገባ ንስሐ መኖሩ ብቻ አያድነውም። ይልቅስ እርሱ ‹‹ቊስላችሁን አሳዩኝ እኔም አድናችኋለሁ›› ይላልና እንለምነው ዘንድ ይገባል፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱ በምሕረቱ ይጎበኘናል፤ በቸርነቱም ያድነናል፡፡

እንግዲህ በወዳጅነት መጸጸታችሁን ንገሩት፡፡ እርሱም ይቀበላችኋል፡፡ ‹‹ወደኔ ተመለሱ እኔም ወደእናንተ እመለሳለሁ›› ብሎ በነቢዩ ነግሮናልና፡፡ እንዲህ ልቡናችሁን ወደ ጸሎት መልሱ፤ ቸርነቱም ሊቀበላችሁ ወደ እናንተ ይመለከታል፡፡ በንስሓ መንገድ ተመላለሱ ያን ጊዜ ቸርነቱ ያበራላችኋል፡፡

ነገር ግን አንድ ቀን ተጸጽታችሁ በሌላ ቀን ደግሞ ኃጢአተኞች አትሁኑ፤ አንድ ቀን የኃጢአተኞች ተባባሪ ሌላ ቀን ደግሞ ተነሳሒ አትሁኑ፡፡ ለቅሶአቸሁና ጸጸታችሁ አንድ ቀን ብቻ አይሁን፡፡ አንድ ቀን ‹‹በድያለሁ፣ ወድቄአለሁ› ብላችሁ ሌላ ቀን ደግሞ ‹‹ነገ እንሞታለንና ዛሬ እንብላ እንጠጣም›› አትበሉ፡፡

ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ እንጂ ሁል ጊዜ በጥፋት መንገድ አትመላለሱ፤ ሞት ሳታስቡት በድንገት ይመጣባችኋልና፡፡ የሥጋ ምቾትም ንስሓን አይፈልግምና ለጥፋት ይዳርጋል፡፡

የመጨረሻው ቀን መጥቶ ሳያገኘን በንስሓ መንገድ እንመላለስ፡፡ የማይቀረው ሞት ሲመጣ ሁለተኛው ሞት እንዳያገኘን በቅድስና ሆነን እንጠብቅ፡፡ በሃይማኖት መጽናትም የድካማችንን ፍሬ እናግኝ። በዚህች ዓለም መልካሙን ሥራ ሠርተው ካለፉ ቅዱሳን ጋር የክብር አክሊል እንቀዳጅ ዘንድ፡፡ ሰው ታይቶ የሚጠፋውን የዚህን ዓለም አክሊል ለመቀዳጀት በወታደር እና በሠረገላ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ጊዜአዊ የሆነ የዚህን ዓለም ደስታና ሐዘን ለመቅመስ ነው፡፡

ይቀጥላል....

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - በእንተ ንስሐ በዲያቆን መዝገቡ የተተረጎመ - ገጽ 31-34)

በእንተ ንስሐ በቅዱስ ኤፍሬም

እንግዲህ የዚህን ዓለም ዘውድ ለመቀዳጀት ሩጫው ይህን ያህል ከሆነ ዘላለማዊውን ክብር፣ ሰማያዊውን አክሊል ለመቀዳጀት ውድድሩ ምንኛ ታላቅ ይሆን? ስለዚህ ሐዋርያው ‹‹የሚታገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታገሣል፤ እነርሱስ የሚጠፋውንና የሚያልፈውን አክሊል ያገኙ ዘንድ ይበረታሉ፤ እኛ ግን የማያልፈውን አክሊል ለማግኘት እንታገሣለን›› (1ቆሮ. 9፥25-26) አለን፡፡

እንግዲህ እርጉም በሆነው ጠላታችን ላይ ድል እስክናገኝ ድረስ ከተንኮል ሥራውም እስክናመልጥ ድረስ የተጋድሎአችንን መሣርያ ንጽሕና ማድረግ ይገባናል፡፡ ክፉ የሆነው ጠላታችን እኛ ትኁታን ስንሆን ይቀናብናልና ይዋጋናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ከጠላት ቀስት የምንድንበት የበለሳን መድኃኒት ሰጠን፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ያስተማረን የንስሓ መድኃኒት ነው፡፡

በእውነት ለቀረበ፣ ከልቡም ተጸጽቶ ለተመለሰ ይህ መድኃኒት ፍጹም የሚያድን ነው፡፡ ነገር ግን መድኃኒቱ የተሰረቀ በደል ያለበትን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው፣ የረከሰ ሰውነታቸውን እየወደዱ በአፋቸው ብቻ ‹‹አድነን›› ለሚሉት አይደለም፡፡

ዳግመኛ በቀደመ ርኵሰታቸው የሚወቀሱትን የወቀሳ ድምፅ ስሙ፡፡ እንደዚሁም በመተላለፋቸው እራሳቸውን እየወቀሱ ዳግመኛ ወደ ጥፋት እንዳይመለሱ የሚጠነቀቁትን ስሙ፤ በግብርም እነርሱን ምሰሉ፡፡ ሕሊናን ሁሉ ወደሚመረምረው ወደ እርሱ ሁለት ልብ ሆናችሁ አትቅረቡ፡፡ የተሰወረውን ሁሉ ያውቃልና በሁለት መንገድ አትመላለሱ፡፡

እንግዲህ ንስሓ ለመግባት ፍጠኑ እንጂ ወደ አረንቋ አትመለሱ፡፡ በቸርነቱ ፍቅር ታጥባችሁ ንጹሐን ሁኑ እንጂ ዕዳችሁ ከተሰረዘላችሁ በኋላ ገንዘቡ እንደ ወደመበት ሰው ዳግመኛ ወደ ዕዳ አትግቡ፡፡

ከምርኮ የተለቀቀ ሰው በምንም መልኩ ዳግመኛ መማረክ፣ ወደ ምርኮው ቦታ ተመልሶ መሔድ አይፈልግም፡፡ ወይም ከግዞት ሥቃይ ከወጣ በኋላ ዳግመኛ መገዛት አይፈልግም፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ ወደ ግዞት እንዳይገባ ይጸልያል፡፡ እንግዲህ እናንተም ከገዳይ ቀንበር ከወጣችሁ በኋላ ዳግመኛ እንዳትገዙ ጸልዩ፤ በጥልፍልፉ ወጥመድም እንዳትያዙ ትጉ፡፡

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - በእንተ ንስሐ በዲያቆን መዝገቡ የተተረጎመ - ገጽ 31-34)
በሊባኖስ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

በሊባኖስ በተለይም በደቡብ እና በምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መጥቷል፤ በዚህ ምክንያት ለጊዜው በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ዜጎቻችንን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም ከታች በተቀመጠው መሰረት ስማችሁን( ፓስፓርት ላይ አንደተፃፈው)፣ የፓስፓርት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራችሁን በመደወል አንድታስመዘግቡ፡፡

1 በደቡብ ሊባኖስ ( ታየር ፣ ሱር፣ ቢንት ጅቤል፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የምትገኙ ዜጎቻችን በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89

2. በምስራቅ ሊባኖስ (በአልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የምትገኙ ዜጎቻችን በስልክ
ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 እንድታሳውቁ ጥሪ ቀርቧል።

(መረጃው በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲደርስ እናጋራው)
#መንፈሳዊ_የግጥም_መደብል_ለኢሉ_ኪዳነምሕረት

ገቢው በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ ለምትገኝ ለኢሉ ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ህንጻ ማስፈጸሚያ የሚውል በአረብ አገር (ሳኡዲ አረብያ) የሚኖሩ እህቶች የተዘጋጀ መንፈሳዊ የግጥም መደብል ነው።

መጽሐፍን እየገዛን የበረከቱ ተካፋይ እንሁን... ሼር እያደረግን ላለደረሰው እናድርስ መጽሐፉ ተሽጦ ለታሰበበት አላማ እንዲውል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

➛ የመጽሐፍ የጀርባ ዋጋ 250ብር
➛ መጽሐፉን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች እየደወላችኹ ማግኘት ይቻላል።

➛ 0912868821
➛ 0914140681
(ቀጥታ በመደወልና እና በቴሌግራም ቢያዙን ካሉበት ቦታ እናደርሳለን)

የገዳሙ አካውት ቁጥሩ ገቢ ማድረግ ካሰቡ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000 26 68 75 348
ኢሉ ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ህንጻ ኮሚቴ
መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው።
መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው።
መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው።
መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው።

መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው።
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው።
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው።

መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
"የክርስቶስ መስቀል እግዚአብሔር ፍቅሩን ለዓለም የሰበከበት አትሮንስ ነው፡፡"

#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
ንግሥት እሌኒን እናወድሳት ዘንድ ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግሥትነቷን በዓለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም፤ ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡
2024/09/27 00:40:38
Back to Top
HTML Embed Code: