Telegram Web
ቢላሉል ሐበሺ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አካሄደ
=========================
ቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር በህጋዊነት ከተመሰረተበት ከ 1996 ዓ/ል ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት የማህረሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች እየፈታ የሚገኝ ሀገር በቀል ዘመናዊ እድር ነዉ፡፡
በመሆኑም እነዚህን ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል የቢላሉል ሐበሺ መስራቾች እና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት በቀን 19/12/2016 ዓ/ል በ አማና ሞዴል ት/ት ቤት አዳራሽ የአመት ኣፈፃፀሙን ለመገምገም አመታዊ ስብሰባዉን አካሂዷል ፡፡
በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዉ ወቅት በ2016 ዓ/ል የተሰሩ ስራዎች፣ ያገጠሙ ችግሮች እና ያሉን መልካም እድሎች በዝርዝር ተለይተዉ ዉይይት ከተደረገባቸዉ በኋላ የ 2017 ዓ/ል እቅዶች እና በ 5 ዓመታት ዉስጥ ሊሰሩ የታቀዱ ትላልቅ ፕሮክቶች እንዴት እና በምን መልኩ እንደሚሰሩ ዉይይት በማድረግ የ 2017 ዓ/ል እቅዶችን በማፅደቅ ስብሰባዉን አጠናቋል ፡፡
ቢላሉል ሐበሺ ለ2017 የት/ት ዘመን ለየቲምና የመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ።
=======================

ቢላሉል ሐበሺ ከ20 አመት በላይ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ የበጎ ስራዎች አንዱ የሆነው ለየቲምና የመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ።

የተማሪዎቹ ወላጆች የተደረገልን ድጋፍ የብዙ ወላጆችን ችግር የቀረፈ እና በተለይ ደግሞ ተማሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ላይ እንዲያደርጉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

ስለሆነም እነዚህን እና መሰል ስራዎችን ለመደገፍ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦1000468418863
ዘምዘም ባንክ፦ 1762810301
ሒጅራ ባንክ፦ 1000677130001
ሕብረት ባንክ፦ 1959711933992028
ንብ ባንክ፦ 7000009204337
አቢሲንያ ባንክ ፦ 84338214
አዋሽ ባንክ ፦ 01322043751400

በስልክዎ ድጋፍ ለማድረግ
****
በ6833 ላይ ok ብለዉ በመላክ የሚስኪኖች ወገኖቻችን ድጋፍ በማድረግ ከአላህ ዘንድ አጅርን ያግኙ!
አድራሻ፦ ሳርቤት አደባባይ ወደመካኒሳ በሚወስደዉ መንገድ ወረድ ብሎ ከአባድር መስጂድ አጠገብ ያገኙናል
ለበለጠ መረጃ፦ 09-72-79-79-79
09-72-78-78-78 ብለዉ ይደዉሉልን።
“ ኑ ወደ ደግነት“
የዳሽን ባንክ አመራሮች የቢላሉል ሐበሺ ማዕከልን ጎበኙ
=======================
ከወለድ ነፃ /IFB/ የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ቢላሉል ሐበሺ እየሰራቸዉ ያሉትን ስራዎች መካኒሳ አባድር በሚገኘዉ ማእከላችን በመገኘት የቢላሉል ሐበሺ የቦርድ አመራሮች እና አባላት በተገኙበት ሁሉንም ስራዎቻችንን ጎብኝተዋል፡፡
የባንኩ አመራሮቹ በቢላሉል ሐበሺ ማእከል ዉስጥ የሚገኙትን የልብስ ስፌት፣ የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች፣ የቪዲግራፊና ፎቶግራፊ ማሰልጠኛ ማእከልን እንዲሁም በእድሳት ላይ የሚገኘዉን ሙዝየም የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ ጊዜ ቢላሉል ሐበሺ የማህበረሰቡን ችግሮች ተቋማዊ እና ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ ለመቅረፍ እየተከተላቸዉ ያሉ መርሆች እና ስትራቴጁክ ስራዎች በስራ አስኪያጁ በአቶ ጀማል መሐመድ አማካኝነት ገለፃ ተደርጓል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ በተደረገዉ አጭር ዉይይት ላይ የቢላል የቦርድ አመራሮች ቢላሉል ሐበሺ ላለፉት 20 ዓመታት እየሰራቸዉ ያሉትን አንኳር አንኳር ስራዎች እና ለወዲፊቱ በስትራቲጅክ እቅዱ ሊሰራቸዉ ያቀዳቸዉን እቅዶች
ያብራሩ ሲሆን የባንኩ አመራሮች ባዩት ነገር በጣም እንደተደሰቱ ከመግለፃቸዉ ባሻገር ተቋሙ ሙሉ ትኩረቱን ዘለቄታዊ መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በማድረግ በት/ት፣ በአጫጭር ስልጠና፣ በጤና፣ በማቋቋም እና በሌሎች መሰረታዊ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች ዘላቂ እና ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ ማህበረሰቡን ለማገዝ እየከወነ ያለዉ ስራ ይበል የሚያሰኝ እና ሊበረታታ የሚገባዉ እንደሆነ ሃሳባቸዉን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ዳሽን ባንክ አቅሙ በፈቀደ መጠን ዘላቂ እና ማህበረሰቡ ላይ ሁነኛ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ ስራዎች ላይ ከዚህ በፊት ከነበረዉ በተጠናከረ መልኩ ከቢላሉል ሐበሺ ተቋም ጋር በመስራት የማህበረሰቡን ዘርፍ ብዙ ችግሮች ለማቃለል የበኩላቸዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አመላክተዋል፡፡
ቢላሉል ሐበሺ የምስጋና ሰርቲፌኬት ተበረከተለት
=========================
ቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር ህጋዊ ሰዉነት ካገኘበት ከ 1996 ዓ/ል ጀምሮ እንደ ሃገር ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራት ስራዎችን በመስራት የተለያዩ የማህረሰብ ክፍሎችን እና ተቋማቶችን የመርዳት እና የመደገፍ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በትግራይ ክልል በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራ የሚገኘዉ ማሕበረ ገበርቲ ሰናይ ዳሩል ሂጅረተይኒ (Darul Hijreteyni Charity Association) እና ፉርቃን የቁርኣን እና ተርቢያ ት/ቤት ለቢላሉል ሐበሺ የምስጋና ሰርቲፊኬት አበርክተዋል፡፡
በሰርቲፊኬቱ ርክክብ ወቅት ማሕበረ ገበርቲ ሰናይ ዳሩል ሂጅረተይኒ (Darul Hijreteyni Charity Association) አስቸካይ እርዳታ በመስጠት፣ ቋሚ እርዳታ በማድረግ፣ ዉሃ ችግር ያለባቸዉን ዉሃ በመቆፈር እንዲሁም እከናወናቸዉ ያሉትን የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በተሻለ ሁኔታ እንድንሰራ ቢላሉል ሐበሺ ከጎናቸዉ በመቆም ላደረገዉ አስተዋፅኦ የምስጋና ሰርቲፌኬት ያበረከቱ ሲሆን በተመሳሳይ ፉርቃን የቁርኣን እና ተርቢያ ት/ቤት ህፃናት እና ሴቶች ላይ ዉጤታማ ስራ እንድንሰራ ከጎናችን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን ሲሉ የምስጋና ሰርቲፊኬቱን ለቢላሉል ሐበሺ መስራች እና የበላይ ጠባቂ ኡስታዝ ሙሐመድጀማል ጎናፍር አበርክተዋል፡፡
በመጨረሻም ሁለቱም ድርጅቶች በቀጣይ ከቢላሉል ሐበሺ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት በማጠናከር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰሩ እና ቢላሉል ሐበሺ በዚህ ረገድ ከጎናቸዉ እንዲቆም አስገንዝበዋል፡፡
2025/02/19 05:32:46
Back to Top
HTML Embed Code: