Telegram Web
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላችሁ🙏

📌 ቃላት እንደቁልፍ ናቸው። ትክክለኛውን ቃል በትክክለኛው ቦታ መጠቀም ከቻልን የክፉ ሰውን ልብ የመክፈትና አፍን የመዝጋት አቅም አለው። ከአፋችን ለሚወጣው እንጠንቀቅ።

📌 አእምሮክ ከስሜቶችክ በላይ ጠንካራ እንዲሆን አለማምደው። ያ ካልሆነ በየቀኑ እራስክን እያጣክ ትኖራለክ።

📌 ብዙዎች ፍቅር ይጎዳል ይላሉ። እውነታው ግን ይሄ አይደለም። የሚጎዳው ብቸኝነት ነው፤ የሚጎዳው መከዳት ነው። እውነታው ግን ፍቅር የተሰበረን ልብ ጠግኖ እንደአዲስ ልዩ ሰው እንደሆንን እንድናምን የሚያደርገው ብቸኛው ነገር ነው። በዚህ አለም ብቸኛው የማይጎዳ ነገር ቢኖር ፍቅር ነው።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌
ብዕር ያለው ያውጋ/bir yalew yawga pinned «🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላችሁ🙏 📌 ቃላት እንደቁልፍ ናቸው። ትክክለኛውን ቃል በትክክለኛው ቦታ መጠቀም ከቻልን የክፉ ሰውን ልብ የመክፈትና አፍን የመዝጋት አቅም አለው። ከአፋችን ለሚወጣው እንጠንቀቅ። 📌 አእምሮክ ከስሜቶችክ በላይ ጠንካራ እንዲሆን አለማምደው። ያ ካልሆነ በየቀኑ እራስክን እያጣክ ትኖራለክ። 📌 ብዙዎች ፍቅር ይጎዳል ይላሉ። እውነታው ግን ይሄ አይደለም። የሚጎዳው ብቸኝነት…»
የካቲት 12 ቀን የሰማዕታት ቀን
የካቲት ሚካኤል መቼ ተከበረ
ዶማ ይዞ ዋለ ሰው እየቆፈረ!!

<< ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሰላምና በፍቅር ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ተሰበሰቡ።ጥቂት ቆይቶ ግራዚያኒና መኳንንቱ ከተቀመጡበት ጠረጴዛ አጠገብ ቦምቦች ተወረወሩ። ቦምቡ እንደተጣለ ግራዚያኒ ጠረጴዛው ስር ተደበቀ።ሌሎች ኢጣሊያኖች ግን ከመሬት ተኙ። ቦምቡን የጣለው በኢጣሊያኖቹ ዘንድ በአስተርጓሚነት የሚሰራ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ተወላጅ ነው።

<< ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለ።ኢጣሊያኖቹ ሌላ የሚወረወር ቦምብ እንደሌለ ካወቁ በኋላ ከተኙበት ተነሱ። ወዲያው ካርቴሲ ወደ ኢትዮጵያውያን መኳንንት ሽጉጡን አነጣጥሮ የመጀመሪያዋን አንድ ጥይት ተኮሰ። ካራቢኜሪዎችም ምሳሌውን ተከተሉ። በጥቂት ጊዜ ውስጥም በዚያ ግቢ 300 ሬሳዎች ተከመሩ።

<< ኃይለኛና ተገቢ ያልሆነ ጭፍጨፋ ነበር። ሽማግሌዎች፣ እውሮች፣ እግር የሌላቸው ለማኞች፣ ድሆች እናቶች ከነልጆቻቸው ነበሩበት። ባለጥቁር ሸሚዞች በግቢው እየተሯሯጡ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ይፈልጉ ነበር።ከሬሳዎቹ መሀልም የሚተነፍስ እንዳለ እያሉ እየመረመሩ ይገድሉ ነበር። . . .<< ምን ዓይነት አጨካከን ነው? ደም እንደ ውሃ ሲፈስ በየመንገዱ ላይ ያየሁት የዚያን ጊዜ ነው። የወንዶች፣ የሴቶች፣ የልጆች ሬሣ በያለበት ተኝቷል።

ወዲያውም ከባድ የቃጠሎ ጭስ ተነስቶ ከተማዋን አጨለማት። የሕዝቡ ቤት ከተፈተሸ በኋላ ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ ቤቱ በእሳት ይቃጠላል። ቃጠሎው ቶሎ እንዲያያዝም በቤንዚንና በዘይት ይጠቀሙ ነበር። ሰዉ እሳቱን እየሸሸ ከቤቱ ሲወጣ በመትረየስ ይገድሉታል። ሌሊቱንም ሲገድሉና ሲያቃጥሉ አደሩ። . . .

<< መኪናዎች እየዞሩ ሬሣ ያነሳሉ። ባለጥቁር ሸሚዞች ወደ ኢጣሊያ ባንክ እየገቡ ሌሊት የሰረቁትን ብርና ወርቅ ያስቀምጣሉ። ዘረፋው በቤት ውስጥ ብቻ አልነበረም። ከሚገድሏቸው ሴቶች አንገትና ጆሮ ላይ የሚገኘውን ወርቅ ሁሉ ይወስዱ ነበር። << ሕክምና በምሰራበት ቦታ ብዙ ኢጣሊያኖች ይመጡ ነበር።

እያንዳንዱ ኢጣሊያም ምን ያህል ሰው እንደገደለ በኩራት ይናገራል። አንዳንዶቹ 80 ገደልኩ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ መቶ እንደገደሉ በኩራት ይናገራሉ። አንድ ኢጣሊያዊ ብቻ እያዘነ "እኔስ የገደልኩት ሁለት ብቻ ነው" ብሎ ሲናገር ሰምቻለሁ። ... የማልረሳው ነገር ግድያው እንዲቆም በተደረገበት ጊዜ "ታላቁ ግራዚያኒ ለሕዝብ በማዘን ግድያው ይቁም ብለዋል" ተብሎ የተነገረው ነው። ግሩም አዘኔታ፥ ...>>. . . . .

(ይህ በወቅቱ አዲስ አበባ የነበረው ሀንጋሪያዊ ሐኪም ዶክተር ላዲስላስ ሳቫ የዓይን ምስክርነት ነው።) የካቲት 12 ቀን በተጀመረው እልቂት በሶስት ቀን ውስጥ 30,000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በኋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እሥር ቤቶች ተላከ።

የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት( ጳውሎስ ኞኞ)
@biryalew
@biryalew
#ዓድዋ_የምኒልክ_እጅ_ሥራ  !!! 
             በIsho Bir

…ምኒልክን ልትጠላው ትችላለህ፤ ደግሞም ልትወደው ትችላለህ። ነገር ግን ምኒልክ ተራ ስብዕና እንዳልነበረ ለመረዳት አይከብድም።

… ምኒልክ ውስብስብ ሰው ነው። ረቂቅ ነው። ደግሞ አድማጭ ነው።

… ምኒልክ እንደ ገሞራ  እሳት የሚፋጅ ነው። ደግሞ እንደ ምንጭ ውኃ ገር ነው። ሚኒልክ ሀገር መመስረት፣ ግዛት ማስተዳደር ያውቃል። ተራ የታሪክ ሰው አይደለም። ጉልህ ነው።

… የምኒልክን ነገር ለማጉላት ብዬ ከሌሎች ማወዳደር አልፈልግም። ዳግሞም ማሳነስ ሊሆን ይችላል።

… ውጫሌ ውል የዓድዋ ጦርነት መነሻ ነው ይላሉ። ፈፅሞ ስህተት ነው። የዓድዋ ጦርነት መነሻ የበርሊኑ የቅኝ ገዢዎች ውል ነው።

… አውሮጳ አፍሪካን ለመቀራመት የተስማማው በበርሊን ስምምነት ነው። ያን ለማስፈፀም አውሮጳውያን በውድም፣ በውልም፣ በግድም አድርገውታል። በውል ወደ ቅኝ ግዛት የገቡ ብዙ ናቸው።

… ጣሊያን ለምኒልክ የውጫሌን ውል ስታቀርብለት፣ ምኒልክ ሳይገባው ቀርቶ፣ ተሸውዶ፣ ወይ ገር ሆኖ ነው ማለት ደካማ የታሪክ ተማሪ ከመሆን የሚመጣ ነው።

…የውጫሌ ውል የተፈረመው አፄ ዮሐንስ በሞቱ በ 10 ቀናት ውስጥ ነው። የዓድዋ ጦርነት የተካሄደው ደግሞ አፄ ዮሐንስ ከሞቱ ከ 7 ዓመት በኋላ ነው።

… ምኒልክ የውጫሌን ውል በመፈረም የራሱን ጉልበት እስኪያጠናክር ግዜ መግዣ ነው ያደረገው። ሚኒልክ ከፍ ለማለት ዝቅ ማለትን ያውቃል።

… እንደ ጣይቱ የሚፋጅ እሳት፣ እንደ  ልብ ወዳጁ ራስ መኮንን የረጋ ውኃ ብቻ ቢሆን፣ ሀገርም አይሠራም፣ መንግሥቱንም አያፀናም ነበር።

… ውጫሌ በተፈረመበት ወቅት ምኒልክ፣ ብዙ ጠላቶች ነበሩት። ተጨማሪ ጠላት ጣሊያንን ማድረግ ስላልወደደ የፈረመው ነው።

… የውጫሌ ውል ኖረ አልኖረ ጣሊያን እንደሁ ኢትዮጵያን መውረሯ እንደማይቀር የሚታወቀውማ፣ የትግራይና የኤርትራን መኳንንት ጥሩ አድርጋ ስትክድ በማየት ነው። ምኒልክ ግን ጦርነቱን ቢያንስ እሱ በመረጠው ግዜ እንዲሆን ማድረግ ችሏል።

… ሚኒልክ ሁሉን ያዳምጣል። በቅንም ይረዳል። ዓላማውን አይስትም። ብልሃተኛም ነው።

… የአምባላጄ ጦርነት፣ የመቀሌ ከበባን በአሸናፊነት ሲያልፍ፣ በምኒልክ ውሳኔ የሚቆጡ ብዙ ነበሩ። ጣሊያኖችን ቢማርክም መልሶ እንደውም ከመጋዣ (ፈረስና በቅሎ ) ጋር ላካቸው እያሉ የሚወቅሱት ነበሩ። ምኒልክ ግን ጦርነት የሚገጥምበትን ቦታ እየመረጠ ነበር። የሱ መኳንንት የሚያውቁትን ምኒልክ ጠፍቶት አይደለም። ከባድ ስትራቴጂስት ስለነበረ ነው።

… ምኒልክ ያሰለፈውን ኃይል ያውቀዋል። ከቴድሮስ እስከ ራስ ውቤ፣ ወርቂትና ተዋበች፣ እስከ ዮሐንስና ጎበና የነበሩ ጦርነቶችን፣ በአይኑ ያየና የሰለጠ ንጉሥ እና ብልህ ጦርነት አዋቂ ነው።

… የቻይናው ታዋቂ የጦር ጀነራል - ሱን ሱ " ኃይል እንዳለህ ስታዉቅ፣ ደካማ ምሰል" ያለውን ምኒልክ ፈፅሞታል።

… ጣሊያን ዓድዋ ላይ የዘላለም ውርደት እስክትከናነብ በዚህ የሚኒልክ ብልጠት ተሸውዳለች። ምኒልክም ዓድዋ እስኪደርስ ድረስ የሚፋጅ ነብር መሆኑን ደብቆ ቆይቷል።

… አምስት ወር የተደረገ ጉዞ፣ የስምንት ሰዓት አጭር ጦርነት የሆነው፣ በዚህች አስደናቂ የምኒልክ ብልሃት ነው።

… ምኒልክ ያደረጋቸው ነገሮች፣ የፈፀማቸው ታሪኮች፣ የሰበሰባቸው ሸንጎዎች፣ የወሰናቸው ውሳኔዎች በእርግጠኝነት የምኒልክን ልህቀት የሚያገኑ ናቸው።

… ዓድዋ - በምኒልክ ተመርጦ፣ በምኒልክ ታቅዶ፣ በምኒልክ ተመርቶ፣ የተፈፀመ ጀብዱ ነው።

… ለዚያም ነው ምኒልክ የሀገር መሪ ብቻ ሳይሆን ሀገር መሥራች ነው የሚባለው።

… ከዚህ መለስ ስላለው የታሪክ ፋይዳ፣ ውጤት፣ ጥቅምና ጉዳት እንነጋገር እንጂ ሁነቱ ዳግም ላይመለስ፣ በምኒልክ ተፈፅሟል ።

***

ይገርምሃል ሸዋ !!!
💚💛❤️

#ዓድዋ_125
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ኢትዮጵያ

@biryalew
@biryalew
Forwarded from ,
እስቲ እሁድ የገባውን የ ኮሮና ክትባት የሚከተብና የማይከተብ እጁን ያሳይ እስካኩን የለቀኩትን መረጃ እያየ መቼም እከተባለው ሚል አይጠፋም????
Anonymous Poll
13%
እከተባለው
75%
አልከተብም
23%
እኔንጃ አሳማኝ መረጃ እፈልጋለው
እስቲ እሁድ የገባውን የኮሮና ክትባት የሚከተብና የማይከተብ እጁን ያሳይ
Anonymous Poll
73%
አልከተብም
27%
እከተባለው
"በየትኛውም ዕድሜ እና ቦታ ማንኛዋም ሴት ልጅ በወር አበባዋ ምክንያት ፍጽሞ ወደ ኋላ መቅረት የለባትም"

በሚል መሪ ቃል መራሂት ከ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 16/2013 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ከሰዓት 8፡00-10፡00 ልዩ የኤግዚቢሽን ፕሮግራም ላይ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
#መራሂት
ሁላችንም የኦርቶዶክስ ልጆች ይሄን ፕሮፋይል እናድርግ
Forwarded from Drunk mood®
sa|`| gallery

"You can never cross the ocean unless you have the courage to lose sight of the shore."

join @samgallery19

©@saM_galler_y📸
Forwarded from Drunk mood®
sa|`| gallery

''Success is getting what you want. Happiness is wanting what you get. ''😇🤝

join @samgallery19

© @saM_galler_y📸
Forwarded from ዋልያ cast agent
ለ ነገ (ማክሰኞ)ጥኋት 1:00 አያት መድረስ የምትችል እድሜ 22-24 የሆነች አንድ ወጣት ሴት ለናፍቆት የዴስቲቪ ድራማ ስለምንፈልግ መድረስ የሚችል ይደውልልን
0934187226
Forwarded from Drunk mood®
sa|`| gallery

'' The amount of happiness that you have depends on the amount of freedom you have in your heart. ''

join @samgallery19

© @saM_galler_y📸
2025/03/29 09:06:28
Back to Top
HTML Embed Code: