፩
[ከማሰብ ነፃ አይደለንም]…
ማሰብን ትልቅ ቁምነገር የሚያደርገው ማሕበረሰባዊ ግንዛቤያችን ሰውን ከማሽን ለይቶ አያይም… በቀን ውስጥ ከሰባ ሺህ በላይ የሃሳብ ሰበዝ አዕምሮአችንን ሲያባትል እንደሚውል ስናስብና ስንቱን ሃሳብ ፈቅደን እንደምናስብ ስንጠይቅ የነፃነት ነገር ይገባናል…
የሃሳብ ፈለጋችን ሲሶው እንኳ በገዛ ፈቃዳችን አይተለምም… እግረ - አዕምሮአችን በደረሰበት የምንደርስ እንጂ የፈቀድነውን የምናስስ አይደለንም… ሰው በትክክል የሃሳብ ማሽኑ ባሪያ ነው… በአዕምሮችን ላይ እንሰለጥን ዘንድ ገና ነፃ አልወጣንም!!... ነፃ ከሆንክ አዕምሮህን ፀጥ አድርገው…
___
@bridgethoughts

፪
[ከስሜት ነፃ አይደለንም]…
በሚግለበለብ የስሜት እሳትና ከስሎ ሲያበቃ በሚያምድ ፀፀት መሃል ስንታኘክ የምንውለው ለዚህ ነው… ለበርካታዎቹ የስሜት ጥያቄዎቻችንን የእምቢታ ድፍረት የለንም… ስሜት ግዘፍ ነስቶ ከክፉ ግብረ መልሱ ጋር ሲያጋትረን ነው ልክ ያለመሆን እምነት ሆድ ሆዳችንን የሚበላው…
ስሜቱን በሚያስተናግደውና በስሜቱ ምላሽ በሚቆጨው እኔነት መሃል ልዩነት ኖሮ አይደለም ሰበብና ድርጊት የተለያየ አቀባበል የቆያቸው - እኛ በስሜት ላይ ስላልሰለጠንን እንጂ…
ከስሜቱ አንድ ስንዝር የቀደመ ሰው ከስሜቱ ምስ ከሚለጥቁ እልፍ ኪሎሜትሮች ድካም ይድናል…
____

፫
[ከመፈለግ ነፃ አይደለንም]…
ከእጅህ ያለው አልማዝ ቀሎ የሌለህ የመሰለህ ሸክላ ከረቀቀ በፍላጎት ባርነት ውስጥ ነህ… እስኪኖርህ ልብህን አቁሞት የኖረህለት ያነሰብህ ነገር ካለ ችግር አለ… እርካታ ስትፈልገው የምትኖረው እንጂ የሚኖርህ አይሆንም…
ባለህ ደስታን ሳትፈጥር በሌለህ መኖር ደስታህ ሊከሰት አይችልም… ደስታህ በፈላጊነትህ ላይ ባለህ ስልጣን እንጂ በአገኘሁ ባይነትህ ማግስት ውስጥ ሊኖር አይችልም…
ስግብግብነት ጉድለት በሚመስለው ነገር ላይ የሚያተኩር ሰው ሕመም ሲሆን እርካታ ምልዓቱን ማየት የሚችል ሰው ትርፍ ነው…

፬
[ከፍርድ ነፃ አይደለንም]…
በየዕለቱ ለሚገጥሙን ሁነቶች ሁሉ ሚዛን እናኖራለን… ልክ እንሰይማለን… ስም እናወጣለን… ለምናየው፣ ለምንሰማው፣ ለምንዳስሰው… የስሜት ሕዋሳቶቻችን ለሚያቀብሉን ነገር ሁሉ ደረጃ እንመድባለን፣ ጎራ እንፈጥራለን፣ ፈርጅ እናበጃለን…
የሚዛን ማበጂያችን ምንጩ ደግሞ የተቃኘንበት አውድ ነው… ቤተሰብ፣ ማሕበረሰብ፣ ሚዲያ፣ ጓደኛ፣ ስርዓት… ወዘተ…
ልክህ ሲያንስብህ ልክ ታዛባለህ… ልኬት ሲገባህ ግን ልክ መስጠት ታቆማለህ…

፭
[ከነኝታ ነፃ አይደለንም]…
‘እንዲህ ነኝ’ – ‘እንዲያ ነኝ’ ስትል የምትውለው ከነኝታህ ተጽዕኖ መላቀቅ ባለመቻልህ ነው… ነኝታህ ከመሆንታህ ይበልጥብሃል… የሆንከው ግን ነኝ ከምትለው የማይናጸር ጥልቅ ነው…
ነኝታህ የመሆንታህን ብርሃን ያደበዝዛል… ነኝታህ ከጎሳህ፣ ከስራህ፣ ከችሎታህ፣ ከሃብትህ፣ ሐይማኖትህ… ወዘተ ይመነጫል… መሆንታህ ግና የአማናዊው ተፈጥሮህ መሰረት ነው… The essence of who you are in the deepest level... አግዮስ፣ ንዑድ፣ ክቡር፣ ጽሩይ…
ነኝ የምትለውን ሁሉ አውልቀህ ብትጥል ምን የሚቀር ይመስልሃል?… ምንም!... መሆንታው ላይ የቆመ ግና ያልሆነው ስለሌለ ነኝ የሚለው አይኖረውም… የሚያጣው ስለሌለው ባዶነት አይሰማውም…

፮
[ከትርጉም ነፃ አይደለንም]…
በኑረት ሃዲድ ላይ እርምጃዎቻችንን የሚወስኑ ትርጉማ ትርጉሞችን የያዘ ኮሮጆ አለን… ለነገሮች የሚኖረን ምላሽ ትርጉማችን ላይ ይንጠለጠላል… በትክክል ከትርጉም እስራት ነፃ አይደለንም…
ለሕይወት ያለህ ትርጉም ነው - የእልፍ በረከቷን ጓዳ አልያም የንፉግነቷን ጎድጓዳ የሚያሳይህ… ለፍቅር ያለህ ትርጉም ነው - የዓይናማነቱን ድምቀት አልያም የእውርነቱን ጽልመት የሚያቆይህ… ለስራ ያለህ ትርጉም ነው - የወዝህን ሲሳይ አልያም የሌሎችን ፍሬ ብካይ የሚያስመኝህ… ሌላውም ሁሉ እንዲሁ ነው…
ትርጉም ከሰጠህ በኋላ ሌላ ተዓምር መጠበቅ የለብህም… መዝገቡን ከዘጋህ በኋላ ሌላ ምዕራፍ ሊኖር አይችልም… ትርጉም ያበጀህለት ታስረሃል - ነገርህንም ቋጥረሃል… ከልብ ደስተኛ የሆነ አንድ ሰው ታውቅ እንደሁ ለነገሮች ያለውን አተያይ ጠይቀው… ወይ የትርጉም ሜኑ የለውም - ሁሉን እንዳመጣጡ ተቀብሎ ይኖራል… አልያም በጎ በጎዎቹ ትርጉሞች የኑረቱ አካል ናቸው…

፯
[ከቂም ነፃ አይደለንም]…
ስለት የቆረጠው ጣትህ ደም እስከመች ነው ይፈስ ዘንድ የምትተወው?... ነገር የጓጎጠው ልብህስ ገላ እስከመች ነው ይቆስል ዘንድ ችላ የምትለው?...
የጣትህ ደም ፍሰት አንተ ችላ ብትለውም በደምህ ውስጥ ያሉት ፕላትሌትስ ከየቦታው ተጠራርተው በሚሰሩት ግድብ /Blood clotting/ ይቋረጣል… የልብህ ቁስል ግን ፈቅደህ በምትሰጠው ይቅርታ እንጂ በሌላ መንገድ አይጠግም…
ይቅርታ ከሚደረግለት በላይ ለአድራጊው የሚሰጠው ሰላም ትልቅ ነው… ቂመኛ ስትሆን በዳዬ ያልከውን ባየህ አልያም ባሰብክ ቁጥር በደሉ ካደረሰብህ የአንድ ጊዜ ሁነት በላይ ደጋግመህ ትታመማለህ… ይቅር ስትል ግና ከመጀመሪያው ቁስልም ትፈወሳለህ…
ያልኖርክበትን ዘመን ጠቅሰህ የለውጥን እርሾ ነው የክፋትን ቁርሾ የምታሻትተው?… የትናንትን በደል ቆጥረህ በግመል ሽንት ነው በቀስት አቅጣጫ ጉዞህን የምትቃኘው?…
ቅድመ አያትህ ለአያትህ ያሻገረውን ክፋት ትተህ ጥበቡን ቀምር፣ አያትህ ለአባትህ የተወውን ጠብመንጃ ጥለህ ሞፈሩን አንሳ፣ ከአባትህ የፍቅር ታሪክ ለልጅህ ጦማር አዘጋጅ… ‘ስታልፍ’ የሚነበበው ታሪክህ እርሱ ብቻ ነውና…

፰
[ከጥበቃ ነፃ አይደለንም]…
በአገኘዋለሁ ተስፋ ውስጥ እንደታሰርን አለን… በይመጣል ጥበቃ ውስጥ እንደታበትን አለን…
ለኑረት አንዳች አበርክቶ የሌለው ሁሉ ቁጭ ብሎ ይጠብቃል… ከሰማይ ይጠብቃል… ከምድር ይጠብቃል… ከወዳጁ ይጠብቃል… ከመንግስት ይጠብቃል…
ከጥበቃ ነፃ ስላይደለ ግምቱ ፍርሽ ሲሆንበት ይበሳጫል… ከሌሎች የሚጠበቀውን ልክ አበጅቶ “ከአንተ አይጠበቅም” ይላል…
ደግሞ ወዲህ የሚጠብቀውን የማያውቅም አለ… ሳሙኤል ቤኬት አንድ ጊዜ “Waiting for Godot” የሚል አብሰርድ ድራማ ጽፎ ነበር… በድራማው ውስጥ የሚታዩት ሁለት ገጸባሕሪያት ካሉበት ጭንቅ ያወጣቸው ዘንድ In the middle of nowhere ቆመው የማያውቁትን አንድ ነገር ሲጠብቁ ይታያል… ተጠባቂው ሲመጣ ባይታይም እነርሱ ግን ጥበቃቸውን አያቋርጡም…
አንደኛው ገጸባሕሪ በመሰላቸት:
“Nothing happens, nobody comes, nobody goes, it's awful!” ይላል…
ያም ሆኖ ቀረ ብለው አይንቀሳቀሱም… ምክንያቱም 'ጎዶትን' እየጠበቁ ነው…
ESTRAGON - Let's go.
VLADIMIR - We can't.
ESTRAGON - Why not?
VLADIMIR - We're waiting for Godot. …
የድራማው ፀሐፊ አንድ ጊዜ በጋዜጠኛ ተጠየቀ፡ “ጎዶት ማን ነው?”…
ቤኬት መለሰ፡ “እኔም አላውቀውም”

ማሳረጊያ
___
[... ነገሩን በደንብ ከተመለከትነው የሰው ልጅ እንኳንና ከሌላ ከራሱም ነፃ አይደለም...]
____
[እንዲያው ግን ነገሩን ወደ መሬት ለማውረድ ያህል...]
🌿 ማድረግ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ ነፃነት አይደለም… ከአድራጊነትህ ጋር ኃላፊነት አለ… ተግባርህ የሌሎችን ጉዳት ካስከተለ ከፀፀት አትነፃም…
🌿 እንዳሻህ መናገር ወይም መፃፍ ነፃነት አይደለም… ቃልህ የአብሮ መኖር ሚዛን ካዛባ አልያም ጎራ ለይቶ ደም ካቃባ ከተጠያቂነት አትድንም…
🌿 ነፃነት ብቻነትም አይደለም… ኑረት ለሌሎች ባለን አበርክቶት እንጂ በራስ ደሴት ጡዘት ከቴም አትሞላም…
🌿 ነፃነት እንደልቡ መኖርም አይደለም… እንደ ደንቡ መመላለስ እንጂ…
____
[እህስ…]
🌼 ኦርጅናሌው ነፃነት የልጅነት ንጽሕና ይመስለኛል!! እንደልጅ ልጅነት - እንደ ሕፃን ‘ጅልነት’ የመኖር ድፍረት… የልጅነት ዓለም ከራሱ ከ’ነፃነትም’ ነፃ ያወጣል… ነፃ ነኝ ከሚለው ባዶ እምነትም ጭምር…
🌼 ልጅነት ነፃነትን ይኖራታል እንጂ አያነፃጽራትም… ነፃ ነኝ አይደለሁም ውዝግብ የሌለበት ኑረት ነው ‘ነፃ ነፃነት’… የሚኖሩት ግን የማያስቡት… ከራስ ውስጥ የሚወልዱት… ፈቅዶ የሚቸርህ አልያም ከፍቶ የሚነሳህ የሌለበት እውነት ነው ነፃነት…
🌼 ይህን ነፃነት ከሰንሰለት እስርም ሆነ ከግዞት ተከርቸም መሃል ሆነህ ልታጣጥመው ትችላለህ… ከደቋሽ ክንድና አደፍራሽ ሁከት ሳትርቅም ልትኖረው ትችላለህ…
🌸 ምክንያቱም ‘ነፃ’ ነፃነት ነውና… 🌸
____
ብዙ ፍቅር!! 🌷🌷🌷

ጥበቃ... [Expectation]
___
["Blessed is he who expects nothing, for he shall never be disappointed." — Alexander Pope]
___
መጠበቅን መሰላል እንደመውጣት ነው የማስበው፤ በጣም ትጠብቃለህ ማለት በመሰላሉ ከፍተኛ እርካብ ላይ አለህ ማለት ሲሆን ጥበቃህ ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ነው ማለት ደግሞ የመሰላሉን ተመሳሳይ ቦታ ይዘሃል ማለት ነው...
እንግዲህ መሰላል የወጣ ሰው ዕጣፈንታ ሁለት ነው... ወይ እንዳወጣጡ ይወርዳል፣ አልያም ከደረሰበት ነጥብ እርካብ ከድቶት ይወድቃል...
[የመጠበቅ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው መሰላሉ ላይ በሰቀለህ እውነታ ነው... ብዙውን ጊዜ ግን ጥበቃ ከእጅ ካለው የታወቀ ሁኔታ ይልቅ ባልተጨበጠ ተስፋ ላይ የሚመሰረት ይሆንና መውደቅን ውጤቱ ያደርጋል...]
በመስተጋብራችንም ሆነ በግል ልምምዳችን ውስጥ እጅግ አደገኛው ስሜት መጠበቅ ሲሆን አስከፊ ውጤቱ ደግሞ የጠበቁት ሳይሆን ሲቀር የሚፈጠረው ስብራት ነው...
ይህ ጥበቃ የታክሲ ሰልፍ ወይም የቦኖ ወረፋ አይደለም... ጊዜ ሲደርስ የምትደርስበት ወይም የመሆን ዋስትና የጨበጠ አይደለም... የስሜት ዕዳ ነው... የቅጽበት ክስተት... ቀጥሎ ምን እንደሚሆን የማይታወቅባት ዓለም ዕዳ...
እኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከሕይወት ጋር በጸጥታ የምንገባው ውል አለን... ኮሽታ ሳናሰማ በተስፋ፣ በህልም፣ በምኞት በመፃኢ ላይ የተመሰረተ ስምምነት እንፈጽማለን... በአዕምሮአችን ውስጥ ጥንቅቅ ብለው የተሰደሩ በርካታ ውብ ስዕሎች አሉን... ጠንክረን ስለሰራን፣ አጥብቀን ስላፈቀርን፣ ተግተን ስለጠበቅን ሕይወትም በዚያው መሰረት ምላሽ እንደምትሰጠን እናስባለን - እናምናለንም... ግና ምኞትና እውነታ ሁሌ አይሰምሩም... ያንጊዜ ደግሞ የመንፈስ ስብራት ይገጥመናል...
ስብራት ያልሰመረ ጥበቃ ውጤት ነው... ብዙ የለፉለት ግንኙነት ምላሽ ሲያጣ፣ ለረጅም ጊዜ የጠበቁት ዕድል ቅዠት ሲሆን፣ እንደ ጣልንባቸው ተስፋና እንደ ሰጠናቸው ቦታ ሰዎች ሳይከውኑ ሲቀሩ ህመም ይገጥመናል... ህመሙ ግን ስለ እጦታችን ብቻ አይደለም... ከእጃችን በሌለ ነገር ላይ የገነባነው ተስፋ ከፊታችን ብን የማለቱ ሃቅ ብሎም ለርሱ ብለን ያጠፋነው ጊዜ የሚፈጥረው ቁጭትም እንጂ...
“Disappointment is a sort of bankruptcy—the bankruptcy of a soul that expends too much in hope and expectation.” — Eric Hoffer
[ነገሩን በምሳሌ እናፍታታው...]
ያፈቀርካት ልጅ ከልብህ የቀለስክላትን ጎጆ አክላ እንድትከሰትልህ ትጠብቃለህ - በእርሷ ልብ ውስጥ ዳስ የተጣለለት ተፈቃሪ ሊኖር መቻሉን ግን ትዘነጋለህ...
[እናም - 'አይሆንም' አለችኝ በሚል ሰበብ ልብህ እንክት ትላለች...]
___
ሃሳብህን ሰው ሁሉ እንዲረዳልህ ትጠብቃለህ - ግና ሁሉም ሰው በየራሱ ንሸጣ፣ በየራሱ መንገድ እንጂ ባንተ መንገድ ብቻ ነገርህን ሊገነዘብ እንደማይችል ትዘነጋለህ...
[በዚህ ምክንያት ድብርት ትከናነባለህ...]
___
ሰዎች ሁሌም በበጎ ቃልና በፈካ ፊት እንዲቀበሉህ ትጠብቃለህ - ሆኖም በብዙ ዓይነት የስሜት መዋዠቅ ውስጥ እንደሚያልፉ፣ ያም ቀናነታቸውን እንደሚያደበዝዘው ትዘነጋለህ...
[በዚህ ምክንያት ቀንህን አስረክበህ ትውላለህ... አንዳንዴም ቂም ቋጥረህ ግንኙነትህን ታበላሻለህ...]
___
ሎተሪ እንዲደርስህ ትጠብቃለህ - ሆኖም ከብዙ ሚሊዮኖች ጋር የሚደረግ ውድድር መሆኑን ትዘነጋለህ...
[በዚህ ሰበብ ዩኒቨርሱን በአድሎ ፈፃሚነት ትከሳለህ...]
___
በድካምህ ልክ ሹመት፣ በጥረትህ ልክ ሽልማት ትጠብቃለህ - የሰዎች ሚዛን ያለው ራሳቸው ጋ መሆኑን ግን ትዘነጋለህ...
[እናም ይህን ሰበብ አርገህ የስራ ሞራልህን ትገድላለህ...]
___
ብዙ ድካምና ሃብት ያፈሰስክበት ቢዝነስ ፈጥኖ ውጤታማ እንዲሆን ትጠብቃለህ - የጊዜና የሁኔታዎችን ምቹነት የማጤን አስፈላጊነት ግን ትዘነጋለህ...
[በዚህ ምክንያት የሚያድግ ወረትህን ትቀብራለህ፣ ሌላ የመጀመር ድፍረትህንም ትሰዋለህ...]
___
በችግራቸው ጊዜ አለሁ ያልካቸው ሁሉ ኑሮ ሲፈትንህና ምርግ ሆኖ ሲጫንህ እንዲደርሱልህ ትጠብቃለህ - ከጓዳቸው ያደፈጠ፣ ከገመናቸው የተሻጠ ምስቅልቅል ሊኖር እንደሚችል ግን ትዘነጋለህ...
[አዎን - በዚህ ተቀይመህ ሰው ትርቃለህ... የልብህንም ሰዎች ታጣለህ...]
___
ወዳጆችህ በሃዘንህ ጊዜ ጎንህ ተገኝተው እንባህን እንዲጠርጉ፣ በክፉ ጊዜህ ገመናህን እንዲሸሽጉ፣ በደስታህ ጊዜ ድግስህን እንዲያደምቁ ትጠብቃለህ - ከእነርሱ ታዛ ሰው የማይደርስበት ለቅሶና ምሬት፣ በሳቅ የሚከልሉት ችግርና ብሶት ሊኖር እንደሚችል ግን ትዘነጋለህ...
[እናም በዚህ ሰበብ ሰው የምታይበት ዓይን፣ የምታቀርብበት ወሰን፣ የምታርቅበትም ሚዛን ይዥጎረጎራል...]
___
"We are all prisoners of our expectations." — Georges Bernanos
___
[ታዲያስ?...]
እንግዲህ ጥበቃ የአዕምሮ ቅኝት ነውና ይቆጣጠሩታል እንጂ አያስቀሩትም... ይመጥኑታል እንጂ አልቦ አያደርሱትም...
ማግስቱን ለድብርት፣ ከርሞ ለስብራት ምክንያት እንዳይሆን ግን ብዙ ነገር ማድረግ ይቻላል...
___
[ሦስት መላዎች ይታዩኛል...]
___
፩) Flexibility - 'ይህን ካላገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ' ከማለት ይልቅ 'ይህ ባይሆን ያንን አሳካለሁ' ብሎ ማሰብ... ችክ አለማለት... አማራጮችን ማየት... አንዳንድ ጊዜ ያጣነው በመሰለን አንድ ነገር ፈንታ ያልጠበቅነው እልፍ ስጦታ ሊደርሰን ይችላል... የጠበቅነው የሚጎዳን፣ የሚሰጠን የሚያስደስት ሊሆንም ይችላል...
፪) እንዲሆን የሚፈልጉት ነገር ላይ what if መቀላቀል... ባይሆንስ ብሎ ማሰብ... ቢቻል የጉዳዩን ተጨባጭነት ማጤን፣ አልያም ጥበቃን ማመጣጠን...
[በመሰላሉ ግርጌ ላይ መቆየት... ነገሩን የሚያመጣው ወይም የሚያስቀረው ጥበቃው ሳይሆን የጉዳዩ ተጋጋዥ ሁኔታዎች ሕብር ነው... ሊመጣ ያለን - ባለመጠበቅ አታጣም፣ የማይመጣንም በመጠባበቅ አትወልድም...]
፫) መቀበል... የሆነውን እንደመሆኑ ማስተናገድ... ስለ ጉዳዩ ከመብሰልሰል ይልቅ ክስተቱን እንደሁኔታው ተቀብሎ ወደፊት መጓዝ... ባለፈው ጎርበጥባጣ የባከነ ጉልበትህን ሳይሆን ቀሪው አቅምህ የሚያስወጣህን አቀበት ማስተዋል... Let it go!
___
"We must accept finite disappointment, but never lose infinite hope." — Martin Luther King Jr.
___
መልካም አሁን!!