Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኡማ
የ አላህ ሰላም እና ረድኤት በናንተ ላይ ይሁን በአብዛኛው እኛ ሙስሊሞች ላይ የሚስተዋል ቃል አለ እሱም አንድ ኡማ ነን የሚል ነው።

ግን ኡማ ሚባል ነገር አለን? ቢላልን ከሀበሻ ሰልማንን ከ ፉርስ ድሀን ከ ሀብታም እንዳሰባሰበው አይነት ኡማ አለን?
ስንቶቻችን ነን ሰፈራችን ካለው ሙስሊም ጋር ምንተዋወቀው ምን ያህልስ እንቀራረባለን እውንን እንቅስቃሴያችንን እስልምና ይወደዋል?
እነዚህ ተራ በተራ ስሩን ነቅለን ሀሳብን አብላልተን በስፋት እንመለከተዋለን
ŤŘÜȚĤ Reavealed pinned «ኡማ የ አላህ ሰላም እና ረድኤት በናንተ ላይ ይሁን በአብዛኛው እኛ ሙስሊሞች ላይ የሚስተዋል ቃል አለ እሱም አንድ ኡማ ነን የሚል ነው። ግን ኡማ ሚባል ነገር አለን? ቢላልን ከሀበሻ ሰልማንን ከ ፉርስ ድሀን ከ ሀብታም እንዳሰባሰበው አይነት ኡማ አለን? ስንቶቻችን ነን ሰፈራችን ካለው ሙስሊም ጋር ምንተዋወቀው ምን ያህልስ እንቀራረባለን እውንን እንቅስቃሴያችንን እስልምና ይወደዋል? እነዚህ ተራ በተራ…»
إنّا لله وإنا إليه راجعون
تُوفِّيَ شيخنا الحبيب أبو إسحاق الحويني
نسأل الله أن يرحمه رحمة واسعة ويسكنه ታላቁ አሊም አብ ኢስሀቅ አልሁወይኒ ወደ አኺራ ሄደዋል አላህ ይርሀማቸው
ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ የመጽሀፉን ኒያ በራሱ አስጀምሮታል። የ100 መጽሀፍ 5,000 ብር በማስገባት ጀምሮታል። በተጨማሪም ኡሙ ዳኑ የ10 መጽሀፍ 500 ብር ገቢ አድርጋለች። ሌሎችም ቀጥለዋል።

የመጽሀፉን ብዛት ኒያችሁን ከዚህ በታች ባለው አካውንት በማስገባት ደረሰኙን ከታች ባለው የቴሌግራም አካውንት ማስቀመጥ ትችላላችሁ፦

1000572021029
Hayat Seid

https://www.tgoop.com/Yahyabook
እኔ ምለው ለዛ ፖለቲከኛ መልስ ይሰጠው እንዴ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ዓመት 12 ወር ነው። ለይለቱል ቀድር በዓመት አንዴ ስትሆን እርሷን ያገኘ ከ 1000 ወር በላጭ ናት። 1000 ወር 83 ዓመት ይሆናል። 1000÷12= 83። አንድ ሰው 10 ዓመት ሙሉ ተከታትሎ ለይለቱል ቀድርን ያገኘ 830 ዓመት በላይ እንደኖረ ይሆናል። 83×10= 830። ይህ ትልቅ ጸጋ ነው። ከሺሕ ወር በላጭ የሆነችውን ይህቺን ሌሊት ለማግኘት ሙሥሊሙ ኢዕቲካፍ ይገባል። “ኢዕቲካፍ” اعتكاف‌‎ ማለት “መቀመጥ” ማለት ሲሆን የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ላይ በመስጂድ ውስጥ ለመዘውተር በመነየት የተወሰነ ጊዜ መጠነ-ሰፊና ዘርፈ-ብዙ ዒባዳህ በማድረግ መቀመጥ ነው፦
2፥187 *”እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”*፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُون فِى ٱلْمَسَٰجِد

በመሥጂድ ኢዕቲካፍ ለማድረግ የሚቀመጠው “ዓኪፍ” عَاكِف ሲባል፥ እነዚህ አንቀጽ ላይ “ተቀማጮች” ለሚለው ቃል የገባው የዓኪፍ ብዙ ቁጥር “ዓኪፉን” عَٰكِفُون መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ እሳቤ በሐዲስም ላይ ተቀምጧል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 2
የነቢዩ”ﷺ” ባልተቤት ዓኢይሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” እስኪሞቱ ድረስ ከረመዷን መጨረሻ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከእርሳቸው በኃላ ባልተቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَعْتَكِفُ الْعَشْرَ الأَوَاخِرَ مِنْ رَمَضَانَ حَتَّى تَوَفَّاهُ اللَّهُ، ثُمَّ اعْتَكَفَ أَزْوَاجُهُ مِنْ بَعْدِهِ‏.‏

የሚያጅበው በዚህች ሌሊት መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፥ እስከ ፈጅር ሶላት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፦
97፥4 *”በእርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ*፡፡ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ
97፥5 *እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት*፡፡ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ

ለይለቱል ቀድርን በኢማን እና በኢሕቲሣብ ያገኘ ሰው ከአላህ ዘንድ የሚኖረው ምንዳና ትሩፋት ያለፈው ኃጢአቶቹ ሁሉ ይቅር መባል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 28
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በለይለቱል ቀድር በኢማን እና ከአላህ አጅር አገኛለው ብሎ ሶላት የቆመ ያለፈው ኃጢአቶቹ ሁሉ ይቅር ይባልለታል”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ يَقُمْ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ

በለይለቱል ቀድር ጊዜ የሚባለው ዱዓ፦ “አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅርታንም ትወዳለህ፥ ይቅር በለኝ” ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 48 ሐዲስ 144
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ እኔም፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! የትኛው ሌሊት ለይለቱል ቀድርን እንደሆነ ባውቅ ምን ማለት እንዳለብኝ ንገሩኝ” ብዬ ጠየኳቸው፥ እርሳቸውም፦ “አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅርታንም ትወዳለህ፥ ይቅር በለኝ” የሚል ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَرَأَيْتَ إِنْ عَلِمْتُ أَىُّ لَيْلَةٍ لَيْلَةُ الْقَدْرِ مَا أَقُولُ فِيهَا قَالَ ‏ “‏ قُولِي اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ كَرِيمٌ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي ‏”‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ ‏

ምንኛ መታደል ነው? ኢሥላም ዐቂደቱ አር-ረባኒያ ነው ስልን በዕውር ድንብር ጸለምተኛ ሙግት”Pessimistic approach” ሳይሆን በእማኝና በአስረጅ ሙግት”Optimistic approach” ነው።
አላህ ለይለቱል ቀድርን በኢማን እና በኢሕቲሣብ ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁርአን ለመሸምደድ
...

፩) መሸምደድ የፈለግነውን ገጽ በአንድ ሙጀዊድ ቃሪእ ለ5 ደቂቃ ማዳመጥ

፪) የገጹን ተፍሲር ማጥናትና ቃላቱን መረዳት

፫) ለመሸምደድ የፈለግነውን ገጽ 2 ጊዜ ማንበብ

፬) ገጹን ለኹለት ከፍለን ግማሹን 3 ጊዜ ደጋግሞ ማንበብ

፭)ቀጥለን የገጹን 1/4 አንድ አንድ አያት እየቀራን መሸምደድ

፮) ሸምድደን እንደጨረስን ቢያንስ 3 ጊዜ መደጋግም

፯) የሚቀጥሉትንም የገጹ ክፍሎች በተመሳሳይ መልኩ መሸምደድ

፰) የተሸመደዱትን አያቶች አገጣጥሞ ሙሉ ገጹን መደጋገም
...

ወዳጄ ቁርአንን ለመሸምደድ ሌሎችም በርካታ መንገዶች እንዳሉ ልብ ይሏል። እርሶ በተመቸዎ መንገድ መሞከሩ ግን የተገባ ነው።
ዕቅበተ-ኢሥላም
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
ዕቅበት-ኢሥላም ማለት እስልምናን መከላከል ማለት ነው ::መከላከል በሁለት ይከፈላል አናደኛው ቀጥተኛ የሆነ መከላከል ወይም የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ላይ መልስ በመስጠት ማቀብ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ በተዘዋዋሪ ጥቃት በመሰንዘር ማቀብ ነው::ይህ የእቅበት አይየነት ተወዳጅና የተመረጠ ነው ለዚህም አንድ ምሳሌ ልስጣቹ::
ካንተ በተቃራኒ አቅጣጫ ያለን ሰው በከፍተኛ ሙመንተም ጥያቄዎችን በማንሳት ተቃራኒውን አካል የሚነሱ ጥያቄዎችን ከመመለስ ውጪ ሌላ ነገር እንዳያስብ ማረግ ነው::አሁን ባለው አቁዋም ይህንን መስራት የሚችለው ሙስሊሙ ብቻ ነው ምክንያቱ ወገኖች ያረጀ እና የተመለሰ ጥያቄ ስለሚያነሱ ከዛ ውጪ ግን ይህንን ስራ ጠንቅቆ መስራት የሚችል የለም::
ግን እየተጠቀምንበት ነውን? በፍፁም አይደለም
ሌላው ነጥብ ወገኖች የሚያነሱት እያንዳንዱ ጥያቄ የ ሺዐህ ሙግት ነው ለዚ ነው አንድ ሰው ወደ ንፅፅር ከመግባቱ በፊ የሺዕህ በይነመረብ መምታት ይጠይቃል ከነሱ አርጊመንት መካከል ሰሞኑን ምሰሟቸውን ላካፍላቹ::
-እስልምና ራስን በራስ ማርካት ፈቅዱዋል(ተጀምሯል)

-እስልምና እናትና ማግባት ፈቅዱዋል(አልተጀመረም)
-እስልምና ሴትን ለግንኙነት መለዋወጥ ፈቅዱዋል
-ለጋብቻ ሴትን ባዶ ቆት ማየት ይቻላል
-በወንድ ምራቅ መርካት.....ወዘተ
በእርግጠኝነት አብዛኛውን አታቋቸውም ግን አታስብ ወደዚ ከመምጣታችን በፊት ሺዕዎች ዲባንክ ያደረግንበት ነጥብ ነው😎
Channel photo updated
ቢረፍድም ኢድ ሙባረክ
ከረመዷን በኋላ ...
...

ዓይን የልብ በር ነው።ዓይን የጎመጀውን ልብ ይመኘዋል። ከዚያም ርካሽ ፈላጊው ገላ በሩካቤ ያረጋግጠዋል።

መረሳት የሌለበት ከሩቅ የምናየው ወራጅ አግዳሚው ኹሉ የደም ገንቦ ነው።

አህያ ለራሱ ለባሌበቱ ከሩቅ ሲታይ ሰጋር በቅሎ ይመስላል።

ብዙዎች በዓይናቸው ሰበብ ምናባዊ ቅዠት ወይም የዝንተ-ዓለም ጸጸት ያለበት ሓራም ውስጥ ወድቀዋል።

በረመዷን የተሰበሰበው ዓይናችን ከረመዷን ውጭም እንዲሰበሰብ ዱዓ ማድረግም መጣርም ያስፈልጋል።
Forwarded from ĴËM-X¥
ማስታወቂያ
            በአላህ ፍቃድ፣ አዲስ ጅማሮ!

ከሰሂህ ቡኻሪ እና ሙስሊም የተመረጡ

ሀዲሶችን በአማርኛ እና በአረብኛ ይከታተሉ።

  * "የሀዲስ እውቀትዎን ያሳድጉ! [የቴሌግራም

ሊንክ] https://www.tgoop.com/jemanu1

✔️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉ

ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያድርሱ!"
Subscribe አርጉ
2025/04/03 19:03:53
Back to Top
HTML Embed Code: