Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Audio
ጀናዛ እና ህግጋቶቹ

        ክፍል 12

የተዳሰሱ መልእክቶች ፦

☞ ለሕድ እንዴት እና በምን መዝጋት እንዳለብን

☞ ቀብርን ከፍ ስለማድረግ

☞ የቀብርን መሐል መቆለል

☞ መቃብር ላይ ምልክት ማድረግ

☞ የቀብር ስርአቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ለሟቹ ዱዐ ማድረግ
Audio
ጀናዛ እና ህግጋቶቹ

        ክፍል 13

የተዳሰሱ መልእክቶች ፦

የመቃብር ኣዳቦች

☞ቀብር ላይ ስለ መቀመጥ

☞ወደ ቀብር ዞሮ ስለመስገድ

☞ቀብር ላይ መስጂድን መገንባት

☞"ፋቲሓ ቅሩልኝ" እያሉ ቀብር ላይ መፃፍ

☞ ለቀብር ዚያራ ብሎ ጉዞን መጓዝ

☞የሞተን ሰው ስለመሳደብ
Audio
ጀናዛ እና ህግጋቶቹ

        ክፍል 14(የመጨረሻው ክፍል)

የተዳሰሱ መልእክቶች ፦

☞የቂርኣት እና ሶለዋት አጅርን ስጦታ ስለመስጠት

☞የተዕዚያ ምንዳ

☞የተዕዚያ ቃላት

☞ተዕዚያ ላይ የተለመዱ ሙንከራት

☞ "ዐብዱል ጀሊል" መቅራት

☞በለቅሶ ወቅት የጎረቤትና ዘመድ ሚና

☞በለቅሶ ወቅት ለመብላት እና ለመጠጣት መሰባሰብ

☞ለሟች የሚጠቅሙ ስራዎች
ረመዷን እና ተውበት

እንደሚታወቀው ታላቁ የረመዷን ወር ሊገባ የተወሰኑ ቀናት ብቻ ቀርተውታል።እናም መቃረቡን አስመልክቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይህንን ወር ካጠፋናቸው ጥፋቶች ወደ አሏህ በፀፀት ተመልሰን በንፁህ ልብ መቀበል እንዳለብን በሰፊው ትምህቶች ሲሰጡ ይስተዋላል።ይሁን እንጂ እነዚህን ትምህርቶች በቅጡ ያልተረዱ ወንድሞችና እህቶች ስህተቶችን ሲፈፅሙ ይታያል።ከነዚህ ስህተቶች መካከል አንዱን ብቻ ለማሳያነት ልጥቀስ

\\  ረመዷን ሲመጣ ሁሉም በሚባል ያህል ሙስሊሙ ኡማ ባለቺው እውቀት ልክ ይዘጋጃል።ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል በተውበት ወደ አሏህ መመለስ አንደኛውና ዋንኛው ነው።ነገር ግን ተውበታችን ተውበታችንን በሚያበላሽ እሳቤ( ኒያ) ላይ ተመስርቶ ይታያል።ይህ እሳቤ ምንድነው ካላቹህ ? መልካም !! ነገሩ ወዲህ ነው, ገና ተውበት ስናደርግ ለተውበታችን የመነሻና የመድረሻ ጊዜ ገደብ እናበጅለታለን።

ለምሳሌ፦ አንድ ሶላት የማይሰግድ ሰው ረመዷንን ከዚህ ጥፋቱ ተመልሶ መቀበል ይፈልጋል።ነገር ግን ሶላቱን የሚጀምረው የረመዷን የመጀመሪያው ቀን  ወይም ከሱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ይሆናል፤ይህም ብቻ አይደለም ረመዷን መጨረሻ አካባቢም በነሻጣ የጀመረውን ሶላት አቋርጦ ፆሙን ብቻ ያስቀጥላል። የዚህን ሰው ተውበት ስናይ የተውበትን መስፈርት ያሟላ አይደለም።ምክንያቱም ተቀባይነት ያለው ተውበት በጥቂቱ ሶስት መስፈርቶችን ያሟላ መሆን አለበት።እነርሱም

➊ ተውበት ለማድረግ ከወሰነበት ሰዓት ጀምሮ ከወንጀሉ ተነቅሎ መውጣት

➋ በሰራው ወንጀል መፀፀት

➌ ዳግም ወደዛ ወንጀል ላለመመለስ ቁር፞ጥ ያለ ውሳኔ መወሰን

★ ከላይ ለምሳሌነት ያነሳነው ሰውዬ ግልፅ በሆነ መልኩ የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን መስፈርት ያሟላ አይደለም።ምክንያቱም ተውበት ለማድረግ የወሰነው ምናልባት ረመዷን ሳምንት ሲቀረው ይሆናል ነገር ግን ሶላቱን የሚጀምረው ረመዷን ሲገባ ነው።ይህም ማለት ተውበት ለማድረግ ከወሰነበት ሰዓት ጀምሮ ከወንጀሉ ( ሶላቱን ከመተው) አልወጣም ማለት ነው።በዚህ መሰረት የመጀመሪያውን መስፈርት አጓድሏል።ሌላኛው ደሞ ረመዷን ሲወጣ አብሮ ሶላቱንም ይተዋል።ይህ ከሆነ  ደሞ ተውበት ስናደርግ ዳግም ወደዛ ጥፋት ላለመመለስ ቁር፞ጥ ያለ ውሳኔ መወሰን አለበት ብለን ሶስተኛ ላይ ያሰቀመጥነውን መስፈርት ያላሟላ ሆኖ ይገኛል ማለት ነው።ተውበታችን ደሞ ተቀባይነት የሚኖረው ሁሉንም መስፈርት ስናሟላ ነው።ያለበለዚያ ተውበታችን አሁን አፏን ጠርጋ ምንም ሳትቆይ ዳግም ቆሻሻ ለመልቀም እንደመትመለሰው ዶሮ ነውና የሚሆነው ልንጠነቀቅ ይገባል።ሶላቱን ካሁኗ ሰዓት ጀምረን ላለማቋረጥ ወስነን መጀመር አለብን። ለምሳሌ ብለን ሶላትን መተው አነሳን እንጂ ከሌሎችም ጥፋቶቻችን ስንመለስ በዚህ መልኩ መሆን ይኖርበታል።

እናስተዉል!!

ተውበት ማለት ካሳለፍናቸው የወንጀል ቆሻሾቻችን የምንፀዳበት የአዛኙ ጌታችን ትልቅ ስጦታ መሆኑን ማስተዋል ይጠበቅብናል።ተውበት ማድረግ ባይኖር እና በእያንዳንዱ ወንጀላችን አሏህ ቢተሳሰበን  ምን ይውጠን ነበር!? የትስ እናመልጥ ነበር? ስለዚህ ወንድም እና እህቶች የተውበትን ፀጋነት አስተውለን ይህንን ድንቅ የአሏህ ስጦታ እሱ ባዘዘን እንዲሁም መልዕክተኛው ( አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ባሳዩን መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል እንጂ እንደ ቀልድ የምናስመልጠው እድል መሆን የለበትም።ከዚህ በተጨማሪ ተውበት ማለት ልክ እንደ ሶላት ፣ ፆም ፣ ዘካና መሰል የሆኑ ኢባዳዎች እራሱን የቻለ ዒባዳ መሆኑን ጠንቅቀን አውቀን በተገቢው መልኩ ልንፈፅመው ይገባል።

በመጨረሻም አሏህ

َّ (وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ)

(ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ።)
【አል—ኑር 31】

ብሏልና  ይህንን የተከበረውን እንግዳ  አድርሶን ፤ እሱ በሚፈልገው መልኩ ወደሱ በፀፀት ተመልሰው ይህንን ታላቅ ወር የሚቀበሉ እና በውስጡም መልካሙን ሁሉ ገጥሟቸው የውመል ቂያማ በፆማቸው አጅር ምክንያት ከሚደሰቱት ያድርገን ።


                   አሏሁመ አሚን!!
Audio
" ዚክረ ረመዷን "

ክፍል 1

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

🗝 የሸዕባንን ወር እንጠቀምበት

🗝 ሸዕባን 15 የሚከበረው የአልከሶ መውሊድ

🗝 ሸዕባን 15 ምንም የተለየ ነገር የለውም

🗝 ረመዷን 10 ቀን ሲቀረው የሚጀመር ፆም የለም
🗝 የፆም መስፈርቶች

\\ ለአካለ መጠን ሚደረሰው መች ነው??

// የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ሆኖ
መፆም ሐራም ነው

በድጋሚ የተለጠፈ

🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
Audio
" ዚክረ ረመዷን "
     
      ክፍል 2

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

🗝 የሕፃናት ፆም

🗝  የጃጀ ሽማግሌ ፆም

🗝 በህመም እና እድሜ ምክኒያት መፆም የማይችሉ ሰዎች

በድጋሚ የተለጠፈ


                🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
Audio
" ዚክረ ረመዷን "
     
      ክፍል 3

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

🗝 የአዕምሮ እክል ያለበት ሰው ፆም

🗝  ይሻለዋል ተብሎ ተስፋ የማይደረግ ህመምን የታመመ ሰው ፆም

🗝 መንገደኛ ሰው እና የረመዷን ፆም

በድጋሚ የተለጠፈ


                🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
Audio
" ዚክረ ረመዷን "
     
      ክፍል 4

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

🗝 የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ፆም

🗝  የእርጉዝና አጥቢ ሴት ፆም

🗝 ያለፈው ረመዷን ቀዷእ ሳይከፍል ቀጣዩ ረመዷን የገባበት ሰው

🗝 የረመዷን ቀዷእ እያለበት የሞተ ሰው


በድጋሚ የተለጠፈ

                🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
Audio
" ዚክረ ረመዷን "
     
      ክፍል 5

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

  ## ፆምን የሚያጠፉ ነገሮች

🗝 መብላትና መጠጣት

🗝  መብላትና መጠጣትን ሊተካ የሚችል ነገርን መጠቀም

🗝 በረመዷን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም

🗝 በረመዷን የቀኑ ክፍለ ጊዜ በራስ ፍላጎት የዘር ፈሳሽ እንዲፈስ ማድረግ

በድጋሚ የተለጠፈ


                🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
Audio
" ዚክረ ረመዷን "
     
      ክፍል 6(የመጨረሻው ክፍል)

የተዳሰሱ ነጥቦች፦

  ## ፆምን የሚያጠፉ ነገሮች

🗝 ሒጃማ/ ዋግምት መስሰራት

🗝 ሆን ብሎ ማስመለስ

🗝 የሐይድ ደም መምጣት

በድጋሚ የተለጠፈ



                🎙ሙሐመድ ኸይሩ

https://www.tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group
ማስታወሻ

መልዕክተኛችን( ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ) እንዲህ ይላሉ

- ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ  ﻗﺎﻝ : ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪ
ﷺ : ‏«ﻻ ﺗﻘﺪﻣﻮﺍ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺑﺼﻮﻡ ﻳﻮﻡٍ ﻭﻻ ﻳﻮﻣﻴﻦ،
ﺇﻻ ﺭﺟﻞٌ ﻛﺎﻥ ﻳﺼﻮﻡ ﺻﻮﻣًﺎ ﻓﻠﻴﺼُﻤْﻪ ‏» . ﻣﺘﻔﻖٌ
ﻋﻠﻴﻪ

"ረመዷንን ሁለት ወይም አንድ ቀን በመፆም አትቅደሙት፤ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው ካልሆነ በስተቀር፤ (ያስለመደ)ከሆነ ግን ይፁም።"

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው ረመዷን ሁለት ወይም አንድ ቀን ሲቀረው መፆም የተከለከለ መሆኑን ነው።ነገር ግን የተከለከለው ያለምንም ምክንያት ከመሬት ተነስቶ ( ለምሳሌ የረመዷን መቀበያ እያሉ) መፆም እንጂ  እዚው ሐዲስ ላይ እንደተብራራው ከዛ በፊት ያስለመድነው ሸሪዓዊ ምክንያት ያለው ፆም ከሆነ ግን ሁለትም ይሁን አንድ ቀን ሲቀረው መፆም የተፈቀደ መሆኑን ነው።ሸሪዓዊ ምክንያት ሲባል ለምሳሌ  ረመዷን ማክሰኞ  የሚገባ ቢሆን ሰኞና ሐሙስ ያስለመደ ሰው ረመዷን አንድ ቀን ሲቀረው መፆም አይቻልም ተብሏልና ሰኞን ቀን አትፁም አንለውም ምክንያቱም ሐዲሱ ላይ ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው ካለ ግን ይፁም ተብሏልና።

አስተውሉ

ማስተላለፍ የፈለኩት መልዕክት ካለፈው ረመዷን ቀዷ ኖሮብን በተለያዩ ምክንያቶች ሳንፆም የቀረን ወንድሞችና እህቶች ካለን የሐዲሱ ክልከላ እኛን አይመለከተንምና ረመዷን አንድ ቀን ብቻ ቢቀረው እንኳን ያለብንን ቀዷ መክፈል ይቻላል ብቻ ሳይሆን ግዴታችን ነው።ምክንያቱም ሐዲሱ ላይ መልዕክተኛው ( ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ)  ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው  ካለ ግን  ይፁም ብለው ፍቃድ ሰጥተዋልና።ያስለመድነው ሱና ፆም ካለ እንድንፆም ከተፈቀደለን ዋጂብ የሆነን ፆም ( ያለብንን ቀዷ) መፆም ደሞ ይበልጥ የተፈቀደና ከዛም አልፎ ግዴታ ይሆንብናል።ስለዚህ ቀዷ ያለብን ወንድምና እህቶች ሐዲሱን በስህተት ተረድተን ወይም ያለ አግባብ የተረዱት ሰዎችን ንግግር ሰምተን ጊዜውን ማስመለጥ የለብንምና ያለብንን ቀዷ ካልጨረስን የተቀሩትን ጥቂት ቀናት ተጠቅመን ቀዷችንን እንፁም።

አሏህ ለመልካሙ ሁሉ ይግጠመን
Forwarded from ابن أمان الوراقي
ታላቅ የሰለፊያ ደዕዋ ዝግጅት በግዴ ና አቦራት ቀበሌ በሞሬ ሎብሬራ አካባቢ
እነሆ የፊታችን እሁድ የካቲት 23/6/2017 ዓ/ል
ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ወቅታዊ እና አንገብጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ ኡስታዞች እና ዱኣቶች ተሰናድቶ ይጠብቆታል።
ፕሮግራሙ በአይነቱ ለየት ያለ በመሆኑ አይደለም መቅረት ማርፈድም ያስቆጫል።
አድራሻ ከጀማል ሳይድ ወደ ሞሬ በሚያስገባዉ መንገድ 400ሜ ገባ ብሎ  በስተግራ በኩል አት-ተዉባ መስጂድ።
ዛሬ የረመዷን ጨረቃ በመታየቷ ነገ ማለትም ቅዳሜ (22/06/2017)የረመዷን የመጀመሪያው ቀን ይሆናል::

አሏህ በሰላም ደርሰው ከሚጠቀሙበት ያድርገን!!
2025/03/01 08:50:59
Back to Top
HTML Embed Code: