Telegram Web
🍂 ጻድቁ አባታችን #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
ታህሳስ 9 በዓለ ልደታቸው

አባታቸው መልዓከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም
ይባላሉ፡፡የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር
ዳውንት ይባላል፡፡

ጻድቁ አባታችን በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ
ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ
ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው
በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን
በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡

ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን
የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን
የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ
እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡

🍂 ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ጆሮውን ወደ
ልመናቸው አዘነበለ እንዳለ መዝ 33፤29 እግዚአብሔር
አምላክ በዓይነ ምህረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም
ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ቀን
ተጸንሶ #ታህሳስ_9 ቀን ተወለደ፡፡በተወለደ እለትም ተነስቶ
በእግሩ ቆሞ 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ ጣዕም ባለው አንደበቱ
ተናገረ፡፡ 9 ጊዜም ህጻናትን ለሚያናግሩ ገዥ ለሚሆኑ
ለአጋይዝተ አለም ስላሴና ለእመቤታችን ለመስቀሉም
ሰገደ፡፡እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ብዙ ሰዎች ከህጻኑ
አንደበት የስላሴን ምስጋና ሰምተው ፈጽመው አደነቁ
ዳግመኛም በዚህ ህጻን ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ
አድሮበታል ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ሀገራቸው ገቡ፡፡

አባቱና እናቱም መጀመሪያ ስለመወለዱ ዳግመኛም
የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ምስጋና በማቅረቡ ደስ
አላቸውና እግዚአብሔር ይህን ህፃን ሰጠን እኛ በአብ
በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስዕል ፊትና ለፍጥረት ሁሉ
ለምትራራ ከሁሉ በላይ በሆነች አምላክን በወለደች
በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ቁመን እንደለመንን
ልመናችንን ሰምታ የተመረጠ ልጅ ሰጠችን ብለው
አመሰገኑ፡፡የመንጻት ወራት በተፈጸመ ጊዜ በ40 ቀን
አባትና እናቱ በጸራ ወርቅና ብር ንጉስ ይኩኖ አምላክ ወደ
አሰራው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ወስደው አዳም
በ40 ቀኑ ወደ ገነት እንደገባ በቤተክርስቲያን ስርዓት
ተጠመቀ፡፡

አዳም በአርባ ሄዋን በሰማንያ ቀን ወደ ገነት
እንደገቡ ኩፋሌ 4፤9 ካህናትም መንፈስ ቅዱስ
እንዳናገራቸው ስሙን እስትንፋሰ ክርስቶስ ብለው ሰየሙት ስጋ ወደሙን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ የስሙም ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቀው አደገ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቦናውን ብሩህ አድርጎለት በ5 ዓመቱ የቅዱሳን መጽሐፍትን፣ ቃላትን ፣ብሉያትንና
፣ሐዲሳትንም፣ድርሳናትንም አወቀ፡፡ ከመምህር ኪራኮስ
የመፅሐፍትን ትምህርት ከነትርጓሜው በ7 ዓመቱ ጨረሰ፡፡

🍂 በማስተዋል ሲመለከት አባቱንና እናቱን ዘመዶቹን የተወ ቃሌን ይጠብቃል መንግስተ ሰማያትን ይወርሳል ይህን ያላደረገ ሊያገለግለኝ አይችልም የሚለውን አገኘ ማቴ
10፡37 ይህንንም ቃል በልቦናው ይዞ የምነናውን ስርዓት
ይጠብቅ ነበር፡፡ 7 ጊዜ በመዓልት 7 ጊዜ በሌሊት
በየዕለቱ 150 መዝሙረ ዳዊትን ሲያደርስ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊቱን በትምህርተ መስቀል አማትቦ
ጸሎት በጀመረ ጊዜ እጆቹን ሲዘረጋ ወጥመዳቸውን
ያጠመዱ አጋንንት በነፋስ ፊት እንዳለ ጢስ ተነው ይጠፋሉ

እየተሯሯጡም ፈጥነው ይሸሻሉ፡፡ ከዚህ በኃላ ስሙ
ማርቆስ ከሚባል ጳጳስ ድቁናን ተቀበለ፡፡ ልጄ
ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ
ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ እንዳለ ሲራክ 2፤1 ይህንን
አለም ናቀ፡፡ ልዩ ክብር የሚሆን የምንኩስናን ልብስ
ይቀበል ዘንድ በተወለደ በ 14 ዓመቱ ወደ ደብረ ሐይቅ
ገዳም ሄደ ከባህር ዳር ቆሞ የሙሴን ጸሎት ወደ
እግዚአብሔር ጸለየ ያለመርከብ ባህሩን ተሻግሮ ወደ
ቤተክርስቲያን ገባ፡፡የኢየሱስ ሞዐ ልጅ የሚሆን አበምኔቱ
በመነኮሳት መጽሐፍ እንደተፃፈ 3 ዓመት ፈተነው፡፡ በኃይቅገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት ያገለግል ነበር፡፡ከአባ ህንጻ ደብረ ድባ ከሚባል ቦታ የቅስና ስልጣን ተቀበለ፡፡

🍂 አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ለማስተማር ወደ
አባቶቹ ሀገር ወደ አባቱ መቃብር በገባ ጊዜ እዚያው ደርሶ
ቤተክርስቲያን ሰራ እለቱን ስንዴ ዘርቶ፣ወይን
ተክሎ፣ጽድንም ወይራን ግራርን ተክሎ በአንዲት ቀን
ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እለቱን አድርሷል፤ስንዴውን
ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሷል፡፡
ከእለታት በአንድ ቀን አባታችን በጸሎት ላይ ሳለ መልአኩ
ቅዱስ ሚካኤል ከብሩህ ደመና ጋር ወደ እርሱ መጥቶ
በደመና ጭኖ ከፈጣሪው ዘንድ አደረሰው፡፡ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱሳኖቹ እንዲባረክ
ካደረገ በኃላ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘው ወደ
ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ አድርሰህ አሳየው
አለው፡፡መላዕኩም እንደታዘዘው አደረገ፡፡መልሶም ወደ
ኢትዮጵያ ምድር ደብረ ዛብሒል ወደ ምትባል ቦታ
አደረሰው፡፡ ከዚያም ደርሶ ድንቅ ታምራትን አደረገ ውሃም
ከአለት ላይ እያመነጨ ህሙማንን ፈወሳቸው፡፡

በባህር ውስጥ ጠልቆ ዘወትር በሄደበት ሀገር ሀሉ
ሲጸልይየሚያርፍበትን ቦታና ስጋዬ የሚቀበርበትን ቦታ ግለጽልኝብሎ በጸለየጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተልኮ መጥቶ የአባትህ አባት ከሸዋ ሀገር መጥቶ ታቦተ እግዚአብሔር አብን ወደ አስተከለበት ወደ አባ ሙሴ ደብር ወደ አባትህና እናትህ ቦታ ዳውንት ምትባል ሀገር ሂድ ብሎ የእረፍት ቦታውን ነገረው፡፡ከዚያም ወደ ብዙ ገዳማት በመሄድ ቡራኬን ተቀበለ፡፡ ከአራት ዓመት በኃላ አረጋውያን መነኮሳትንተሰናበታቸው መርቀውት ተለያዩ፡፡

🍂 የኢትዮጵያን ገዳማትተዘዋውሮ እየጎበኘ ጎዣም ደረሰ ፤በዚያ እያስተማረ፣ እያጠመቀ የታመሙትን
እየፈወሰ፣የእውራንን አይን እያበራና ሙታንን እያስነሳ በዚያ ተቀመጠ፡፡ በባህር ውስጥም ገብቶ 9 ዓመት ለኢትዮጵያ ጸለየ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኃላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ይህችን ሀገር እና የኢትዮጵያን ህዝቦች ምሬልሃለሁ ከዚህች ባህር
ውጣ አለው፡፡ አባታችንም ከባህር ውስጥ ወጥቶ ተንበርክኮ ለጌታችን ሰገደ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማረፊያህ ቦታ ምስራቅ ወደ ምትሆን ወደ ዳውንት ሂድ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ አባታችንም በአስራሰባት ዓመቱ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄድበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ደረሰች፡፡ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸለየ አለቀሰ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ አላት ጸሐይም ወደ ኃላ ተመልሳ በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃል ቆመች ደብረ አሰጋጅ እንደገባ ጸሐይም አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ
እገባ ዘንድ ፍታኝ አለችው እግዚአብሔር ይፍታሽ ባላት
ጊዜ ገባች፡፡

🍂 እድሜው ሰላሳ ሦስት በሆነ ጊዜ ወደ ደብረ ድባው
አበምኔት መጥቶ ሚያዝያ ዘጠኝ ቀን ምንኩስናን ተቀበለ፡፡በዚያ ደንጋይ ፈልፍሎ ዋሻ አዘጋጀ፡፡ ሉቃስ የሳላት ከግብፅ የመጣች የድንግል ማርያምን ስዕል አስገብቶ የዋሻውን በር ዘጋ፡፡ ያለ ደቀመዝሙሩ ልብሰ ክርስቶስ
በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር አይገናኝም፡፡በዚህ ድንቅ ድንቅ
ታምራትን እያደረገ ሁለት መቶ አርባ ሺ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣ፡፡

ያባታችን የረፍት ጊዜ በደረሰ ሰዓት ጌታችን ለአባታችን
ቃልኪዳን መታሰቢያህን ያደረገ ዝክርህን የዘከሩ
የገድልህን መጽሐፍ የጻፉ ያጻፉ ቤተ ክርስቲያንህን የሠሩ
ያሠሩ የሠሩትን ኃጢአት ይቅር እላቸዋለሁ።

ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ገድልህን የጻፈውን ያጻፈውን
ያነበበውን የተረጎመውን ጽፎም በቤቱ ያስቀመጠውን ሰው የተለያዩ በሽታ የሚያመጡ ሰውን የሚፈትኑ ርኩሳን
አጋንንት አይቀርቡትም ተላላፊ በሽታ ወይም ተስቦ
ተቅማጥ ርኃብ ቸነፈር የውኃ መታጣት የልብስ መራቆት
መዥገር አይደርሱበትም ሌጌዎን የተባለ ክፉ ጋኔንም
ፈጽሞ አይቀርብም። ፋኑኤልና ሩፋኤል እስከ ዘለዓለሙ
ይጠብቁታል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ
የሰማይ መላእክት በተድላ በደስታ ወደ ሰማይ ያሳርጉታል።
እንዲሁም ጌታችን በርካታ ቃልኪዳኖች ላባታችን
ተሰቷቸዋል ገድላቸውን ገዝተን እናንብበው በቤታችን
እናስቀምጠው ።

አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
በሚያዚያ 9 ቀን አርፉ ::

የአባታች የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
ረድኤት እና በረከት አይለየን 🙏🏽



ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /

📞 +251923075264

@deacongetabalewamare
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ቅድስት_ሃና

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Created by ; @qagnewcreatives

@deacongetabalewamare
ከመ ለቢወነ ብከ ናእርፍ በማኅደረ ሕይወት ፤
ፈጥረህ የምትገዛ የባሕርይ አምላክ ሆይ ! አንተን አውቀን ከገቡ መውጣት ካገኙ ማጣት በሌለባት መንግሥተ ሰማያት እንኖር ዘንድ

እንዘ ንገብር ፈቃደከ : ሀበነ ንሑር በትአእዛዝከ ፤
ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪትን ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ጠብቀን እንኖር ዘንድ እውቀቱን ስጠን

( ጸሎተ ኪዳን )

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
ቅዱሣት ሥዕላት ሠዐሊ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አንተ ከኔ ጋር ነህ... አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ......... አማኑኤል
ድል አርገህልኛል.... አማኑኤል
የጭንቄን ተራራ...... አማኑኤል
በጉባኤ መኃል....... አማኑኤል
አፌ አንተን አወጀ.... አማኑኤል
የከበረ ደምህ....... አማኑኤል
ነፍሴን ስለዋጀ...... አማኑኤል

ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
📞 +251923075264
🍂🌹 ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 🌹🍂
#ጥር_4 ሞትን ሳያይ  እንደተሰወረ፤ የፍልሰቱ መታሰቢያ

+  በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ እሳቱ ላላቃጠለህ
+  መለኮት ለሳመህ  ድንግል ላቀፈችህ  +
+  ድንግል ላቀፈችህ  ላንተ #ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባሃል  +

+   ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ   ዮሐንስ ታኦሎጎስ
+  ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ        ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
+   ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ           ዮሐንስ ድንግል 

አባቱ 🍂 ዘብዴዎስ ሲባል
እናቱ 🍂 ማርያም ባውፍልያ ትባላለች።

. #ቅዱስ_ዮሐንስ የጌታችን ደቀመዝሙር ከመሆኑ አስቀድሞ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር ገና በወጣትነቱም የመሲሁን የክርስቶስን መምጣት ከመምህሩ ከመጥምቀ መለኮት ስለተረዳ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፤
ዕድገቱም በገሊላ ነበር።

ሐዋርያነቱንም በደስታ እና በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስ ሳይለይ በመከራውም ሰዓት አስከ መስቀሉ ድረስ አብሮት ነበር አልተለየውምም። ፍቁረ እግዚእ መባሉም ከጌታችን ባለመለየቱ ጌታችንም ይወደው ስለነበር ነው።

በክርስቶስ መስቀል አጠገብ ከእመቤታችን ጋር በሀዘን እና በልቅሶ ቢገኝ ጌታችን እነኋት እናት ብሎ በእርሱ አንጻር ለእኛ እናታችን ትሆነን ዘንድ ሰጥቶናል፤ እንዲሁም ለእናቱ እነሆ ልጅሽ ብሎ በእርሱ አንጻር ለእርሷ ልጇቻ እንሆን ዘንድ ሰጥቶናል

#ቅዱስ_ዮሐንስም የጸጋ እናቱን ወደ ቤቱ ከወሰደ በኋላ እመቤታችን ከዮሐንስ ጋር 15 ዓመት ኖራለች። ጸጋን የተመላች እመቤታችን የተቀበለው ቅዱስ ዮሐንስ ምስጢር ተገልጾለት ምስጢረ መለኮትን እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ ብሎ “ በመጀመሪያ ቃል ነበር ...” ብሎ ድርሰቱን ጀምሯል።

ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ
     🍂  የዮሐንስ ወንጌል
    🍂   3 መልእክታት
     🍂 የዮሐንስ ራዕይ
እነዚህን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጽፏቸዋል።

ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ከሆነው ከደቀመዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር የሐዋርያነት ተጋድሎውን የፈጸመው፤ ያስተማራው በቀደመችው ኤፌሶን በአሁኗ ቱርክ ነው።

#የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያሰበ ፣ እያዘነ እያለቀሰ 70 ዘመን ቁጽረ ገጽ ሆኖ ኖሯል።
በቅድሥት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንሥር ነዉ፡፡ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡

. #ንሥር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ፤
ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡

ንሥር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡

ንሥር አይኑ ንጹህ ነዉ ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡

🍂 በዚህም #ዮሐንስ_ዘንሥር ተብሏል፡፡

ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡
ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ

#ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? “ ( ዮሐ 21፡20 )
ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡
በማቴ 16፡18 ላይ “ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ “
ያለዉ ቃል ለ#ቅዱስ_ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡

🙏🏾  #የቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ
በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏🏾
ወርኃዊ መታሰቢያ በዓሉም በ4 ነው

ከብዙ ጸጋህ ለእኛ ለባሮችህ
ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን
እንማጸንሃለን 🙏🏽

👉 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
+251913684351

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
+  በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ +
🍂 እሳቱ ላላቃጠለህ +
+  መለኮት ለሳመህ  +🍂 
+  ድንግል ላቀፈችህ  ላንተ
🍂#ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባሃል  +

             
+   ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ   
+  ዮሐንስ ታኦሎጎስ
          
            🙏🏾

+  ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ       
+  ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
         
           🙏🏾

+   ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ          
+    ዮሐንስ ድንግል 

            🙏🏾

ከብዙ ጸጋህ . . . ለእኛ ለባሮችህ
ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን
እንማጸንሃለን 🙏

👉 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
       0923075264
@deacongetabalewamare
ከ ሐ ዋ ር ያ ት ፡ ጋ ር ፡ ሸ ሽ ቶ : ያ ላ መ ለ ጠ : ቅ ዱ ስ : ዮ ሐ ን ስ

#ጥር_አራት ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የዕርገቱ መታሰቢያ ቀን ነው ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ሄኖክና እንደነ ኤልያስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገ ፍቁረ እግዚእ የተባለ ቸር አባት። #ቅዱስ_ዮሐንስ_እኮ

ሰማያዊ ሰው ፥ ንሥረ ክርስቶስ
ምድራዊ መልአክ ፤ ከጌታ ደረት የተጠጋ
የቃና ዘገሊላ ታዳሚ ፤ የፍጥሞ ደሴት ግዞተኛ
ድንግልን በቤቱ ያስጠጋ ፤ የኤፌሶን ሰው አጥማጅ
የክርስቶስ ፍቅር ምርኮኛ ፤ የጥብርያዶስ ዓሣ አጥማጅ
ከመስቀሉ የማይነቃነቅ ታጋሽ ፥ ዖፈ መድኅን ፤ ነባቤ መለኮት
በቀራንዮ የጌታውን መዋረድ ያየ ፤ ምጽአትን አልፎ የሚያይ ደኃራዊ
ሰማይ የሚያደርስ የብርሃን ዐምድ ፤ በቀራንዮ መስቀሉ ሥር የታመመ
በብዕሩ ሙሴን የቀደመ ቀዳማዊ ፤ በደብረ ታቦር የጌታውን ክብር ያየ
በጌታ ቀን በመንፈስ የዋለ ተስፈኛ ፤ ወደ መቃብሩ ግን የሚሮጥ ችኩል
ጌታ ይወደው የነበረ ሐዋርያ ፥ ፍቅርን በመስቀል አይቶ ተፋቀሩ ሲል የኖረ
መላእክት ከእርሱ ሊማሩ ሚችሉት ምሥጢር የተገለጠለትነባቤ መለኮት
በሕማሙቀን ፊቱየጠቆረ ኀዘንተኛ፤በራእዩ ከእግሩሥር ወድቆ የተደመመ

ለ ነ ባ ቤ : መ ለ ኮ ት : ለ ቅ ዱ ስ : ዮ ሐ ን ስ
የ ሚ በ ቃ : ቃ ል : ይ ኖ ር : ይ ሆ ን

ፍቁረ : እግዚእ : የተባለ : ቅዱስ : ዮሐንስ : ወንጌላዊ : በረከት
ረድኤቱ : ከሁላችንም : ጋር : አድሮ : ለዘላለም : ይኑር : አሜን

✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ጥር 3 2017 ዓ.ም

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
       0923075264
@deacongetabalewamare
+ + ያን ጊዜ #ኢየሱስ_በዮሐንስ ሊጠመቅ + + ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።

#ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል
አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።

#ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤
እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።
ያን ጊዜ ፈቀደለት።

ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤
እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ
እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤

እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦
#በእርሱ_ደስ_የሚለኝ_የምወደው_ልጄ_ይህ_ነው_አለ

( ማቴ 3 ፥ 13 -17 )

🙏🏽 እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ 🙏🏽

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
@seali_kesis_amare_kibret

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
www.tgoop.com/deacongetabalewamare
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከተለዩ የተለየች የተባልች የተባለች #የኪዳን_ጽላት_ያለብሽ
የተሠወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ ፤ ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ። ( የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም )

✍️ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት 🎨
@seali_kesis_amare_kibret 🖌️

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት #ሠዐሊ

+251913684351
+251923075264

www.tgoop.com/deacongetabalewamare
ደ ብ ረ ፡ ይ ድ ራ ስ : ተ ራ ራ : ወ ስ ደ ው :
አ ፅ ሙ ን : በ ተ ኑ ት

#ጥር_18 ቀን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በብዙ ተጋድሎ ውስጥ ሆኖ « እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው » በማለት የተመዘዘ ሰይፍ የነደደ እሳትን የከሀዲውን የዲድያኖስ ቁጣ ሳይፈራ መከራን ታግሷል የጌታውን የአምላኩን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የመሰከረበት ዕለት ሲሆን ።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በማይመረምረው ጥበበ እግዚአብሔር በመታመኑ ብዙ መከራ ደረሰበት በጉድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አብስለው አቃጥለው አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ በዚህ ጥር 18 ቀን ደብረ ይድራስ ወደ ተባለ ረጅም ተራራ ወስደው አፅሙን በተኑት ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት አንድ አካል ሆኖ ወደ ቀድሞ መልኩ ዳግም ተመልሶ አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በመሄድ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ።

ለቁጥር የበዙ አሕዛብ አይተው አደነቁ ከንጉሥ ሠራዊትም ከአሕዛብም ብዙዎችን በጌታችንም አመኑ በማመናቸውም ምክንያት በከሀዲው በንጉሥ ዲድያኖስ ሰማዕትነትን ተቀበሉ ።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በታላቅ ድምቀት ይህንን ቀን ታሳቢ በማድረግ በዓልን ሰርታ ታከብረዋለች ።

✎﹏ዳዊት ተስፋዬ Daweit Tesfay ✍️
ጥር 18 2017 ዓ.ም

የታላቁ ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ
ረድኤት ረድኤት በረከቱ አይለየን
በአማላጅነቱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏🏽

🍂 በ England uk ለሚድልስቦሮ ደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከሠራናቸው ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የሰማእቱ የ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥዕል

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
www.tgoop.com/deacongetabalewamare
🍂 በ England uk ለሚድልስቦሮ ደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከሠራናቸው ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የሰማእቱ የ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥዕል

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264

www.tgoop.com/deacongetabalewamare
🌹+ + አስተርእዮ + +🌹
#ሞት_ለሚሞት_ይገባል
#የማርያም_ሞት_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል "

"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"

እንኳን ለ 2016 ዓ.ም #አስተርእዮ ማርያም በዓል አደረሳችሁ!!!

#እመቤታችን_ለምን_ሞተች?

🍂 #ጥር_21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ይታሰባል፡፡

ሞት በአዳም በደል ምክንያት የመጣ ዕዳ ነው፤ባህርያዊ ሳይሆን ባህርያዊ መስሎ ከባህርያችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር ፍዳ ነበር፡፡ ሞት ጌታችን ሳይገድለው/ሳይሽረው በፊት ወደ ሲኦል መውረጃ መንገድ ነበር፤
ለአጋንንት እግር እርግጫ፤ ለመንጸፈ ደይን ተመቻቻተን የምንሰጥበት ሂደት፤ሥጋ በመቃብር የሚፈርስበት፤ነፍስ በሲኦል የምትሰቃይበት ክስተት ነበር፡፡

🍂ክርስቶስ ሲመጣ ግን ይህ ሞት የሚለው ንባብ ሳይቀየር ትርጉሙና ምሥጢሩ ተቀየረ፤መጠጫው ጽዋው ሳይቀየር መጠጡን እንደመቀየር ነው፤መሞት በሐዲስ ኪዳን መሻገር ነው፤ወደ ዘለዓለም ሕይወት መጠራት፤መቃብርም ለትንሣኤ ዘጉባኤ መቆያ ስፍራ ነው፡፡

🍂 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን ሞተች? ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት ከሆነ እመቤታችንም የሞተችው ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ፤

አነዚህ ሰዎች በሐዲስ ኪዳን ሞት ምን እንደሆነ ያለመረዳታቸውና እንዲሁም የእመቤታችን ሞት ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን ባለማወቃቸው ምክንያት የሚናገሩት ነው፡፡

🍂 ሞት ጥንተ አብሶ ያለበት ብቻ ነው የሚሞተው ከተባለ ጌታችን ራሱ መሞቱ ጥንተ አብሶ ስላለበት ነው ያሰኛል፤ ይህ ደግሞ እርሱ ንጹሕ ሆኖ ሳለ ስለእኛ ሞተ የምንለውን የድኅነት ፅንሰ ሀሳብ ከንቱ ያደርግብናል፤ስለዚህ ሞት ከክርስቶስ በኋላ የመብቀል ሂደታችን መሆኑን እንመርምር፡፡

🍂 ይህን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይነግረናል:—
"አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም"፤ይላል 1ኛ ቆሮ 15፡36፡፡ ሰለዚህ ሞት በሐዲስ ኪዳን ሕያው ለመሆን የምናልፍበት ሂደት (process) ነው፡፡

ራሱ ጌታችንም ሲያስተምረን:—

"እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም"፤ዮሐ 5፡24፡፡

ዳግመኛም ፦ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አያይም" ብሏል፤ዮሐ 8፡51፡፡

ይህም ማለት ነፍስ ከሥጋ አትለይም ማለት አይደለም፤እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ነፍስ በገነት እንደምትኖር፤ ከዚያም በትንሣኤ ዘጉባኤ ጊዜ ነፍሳችን ከሥጋችን ጋር ተዋሕዳ ተነሥተን ከመላእክት ጋር እያመሰገንን የምንኖረውን ዘላለማዊ ሕይወት ለመግለጽ እንጂ፡፡

🍂 እመቤታችን ቃሉን በመስማትና በማመን በመጠበቅ የመጀመሪያዋና ተወዳዳሪም የሌላት ናት፤ ማንም ሊሰማው የማይችለውን "ቃል ሥጋ ኮነ" ን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማች መስማት ብቻ ሳይሆን ያመነች ናት፤ቅድስት ኤልሳቤጥ "ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃል ዘነገሩኪ እምኀበ እግዚአብሔር ፤
(ከእግዚአብሔር የተነገረሽ ቃል እንደሚፈጸም ያመንሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ) ብላ እንዳመሰገነቻት (ሉቃ 1፡45) "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" ብላ ስታምን ነበር ሞትን ያለፈችው፤ትንሣኤ ልቡናን ቀድማ የተነሣችው፤ ይህ ምሥጢር የተከናወነባት ናት፤እያንዳንዱን የጌታን ቃል በልብዋ ትጠብቀውና ታስበው እንደነበር ተጽፏል፤ሉቃ 2፡51፡፡

🍂 እንዲህ ከሆነ ሕይወት የሆነውን ጌታ ፀንሳ፤ወልዳ የድንግልና ጡት ያጠባች ሆና እንዴት ትሞታለች?
ሕይወትን የዳሰሱ እጆች፤ሕይወትን የተመለከቱ ዓይኖች፤ሕይወትን ያቀፉ ጉልበቶች እንዴት ለሞት ይሰጣሉ? ብለን ስንጠይቅ የሚከተሉት ምላሾች ይኖሩናል፡፡

➊ ከተገፋችበት ፤ከተንከራተተችበትና የኀዘንና የመከራ ሰይፍን ካስታናገደችበት ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ወደመንግሥተ ሰማያት መጠራቷን፤የማያልፈውን ዋጋ እንደተቀበለች ለማሳየት እንጂ የሞት ሞት የሚባለውን መፍረስና መበስበስን፤ወደ ሲኦል መውረድን የሚያሳይ እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ይህንንም ቅዱስ ያሬድ "ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘ ይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ዳዊት አቡሃ በመሰንቆሁ እንዘ የኀሊ፤የሰው እጅ ያልሰራት ድንኳን ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረላት እመቤታችን አባቷ ዳዊት በመሰንቆው እያመሰገናት ከሚያረጀው ዓለም ወደማያረጀው/ወደማያልፈው ሄደች"
በማለት እነደነገረን ነው፡፡

➋ ከሰማይ የወረደች (ኃይል አርያማዊት) ናት የሚሉ አሉና ሰው እንደሆነች እና ከምድር እንደተገኘች፤ሙሉ የሰውነት ማንነት ያላት መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤ እመቤታችንን ሞት ባያገኛት ካልዕ ፍጥረት (ልዩ ፍጥረት) ስለሆነች ነው ብለው ብዙዎች በተከራከሩ ነበር፤ይህም ደግሞ ክርስቶስ የነሣውን ሥጋና ነፍስ (ምሥጢረ ተዋሕዶን) ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተው ነበርና በዚህ ምክንያት በሕገ ሰብእ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ስለተገኘች በሕገ ሰብእ ሞት ተጠርታለች፤ ይህ ሞቷ እሷን ሌላ ፍጥረት የጌታን ተዋሕዶ ምትሐት ከማለት የሚታደግ መድኃኒትም ጭምር ነው፡፡

➌ ፍትሑ ርቱዕ (ፍርዱ ቅን የሆነ) እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ ያጠይቃል፤ እመቤታችን እንደማንኛውም ሰው ሞትን ባታይና ባትቀምስ ፍርዱ ትክክል አይደለም፤ አንዱን በሞት ይወስዳል ሌላውን ይተዋል፤ወዲህም ልጅዋ አምላክ ነውና ሞትን ያልቀመሰችው በልጅዋ ምክንያት እንጂ እርሷ የተለየ ቅድስና ስላላት አይደለም በተባለ ነበርና ሞትን እንድትቀምስ ፈቅዷል፤ሞትን መቅመሷ በክብር ላይ ክብር ቢጨምርላት እንጂ ቅንጣት ታህል ክብር አይቀንስባትምና፡፡

ይህንንም ደራሲው፦

"ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤
#ክርስቶስ_ሥጋውን_ለነሳበት_አካል_በሞት_አላዳላም" በማለት ተናግሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድም ፦

"እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኩሉ
አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ"

(በፍርድ እንደማያዳላ ስለዚህ ነገር ዕወቁ፤የእርሱ እናት፤የሁሉ እናት እመቤታችን ሞትን ትቀምስ ዘንድ ወልድ በማይሻር ቃሉ አዘዘ) በማለት አስረግጦ ተናግሯል። (የዕለቱ ዚቅ)፡፡

#በነገረ_ማርያም ላይ እንደተጻፈው እመቤታችን የዕረፍት ጊዜዋ መድረሱን ጌታችን ሲነግራት እንዴት እኔ የአንተ እናት ሆኜ ሞት ያገኘኛል? በማለት ጠይቃለች፤ቅዱስ ያሬድ እንደገለጸው "እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ ከመ ኩሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤እንደማንኛውም ሰው ሞት በጎበኛት ጊዜ የአምላክ እናት እንደምን አለቀሰች?" (የዕለቱ ዚቅ)፡፡
ጌታችንም አንቺ ስትሞቺ ባንቺ ሞት ምክንያት ከሲኦል የሚወጡ ነፍሳት አሉ በማለት ነገራት፤

🍂#እመቤታችንም ርኅርኅት ናትና በኔ ሞት ምክንያት ነጻ የሚወጡ ነፍሳት ካሉ አንድ ጊዜ አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት ብላ መልሳለታለች፤ይህም ማለት ሁሉም ነፍሳት በእመቤታችን ሞት ምክንያት ከገነት ይወጣሉ ማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ባወቀ የእናቱ ሞት ቤዛ እንዲሆናቸው የመረጣቸው ነፍሳት መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

• በብሉይ ኪዳን ጥንተ አብሶ ያለባቸው ሰዎች ሲሞቱ መልአከ ሞት ይታያቸው ነበር ለእመቤታችን ግን ልጅዋ ራሱ ክርስቶስ ነው የተገለጠላት፤

• በብሉይ ኪዳን የሞቱ ሰዎች ወደ ሲኦል ነበር የሚወርዱት እመቤታችን ግን ሥጋዋ በገነት ነፍሷ በልጅዋ እጅ ነበር፤

• ከአዳም ልጆች ወገን የመጨረሻውን ትንሣኤ የተነሣ የለም፤እመቤታችን ግን እንደ ልጅዋ ተነሥታለች ዐርጋለች፤መዝ 131፤8፡፡

🌹 #ሰለዚህ_የእመቤታችን_ሞት_ይደንቃል
ሁላችን ከሞታችን በፊት የሰራነው ብዙ ኃጢአት አለ፤ እመቤታችን ግን ንጽሕት ናት
ሞቷም በሲኦል ስላሉ ውስን ነፍሳት በልጅዋ ፈቃድ ቤዛ ሆኖ የተሰጠ፤የተከፈለ ነው፡፡

#ሞት_ለሟች_ይገባል
👏 #የድንግል_ሞቷ_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል !!! 👏

/👉ምንጭ #ከመጋቤ_ሐዲስ_ነቅዐ_ጥበብ_ከፍያለው/

🙏🏾 የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🏾
ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን ያሳድርብን!!!

የልጅዋ የወዳጅዋ ቸርነት አይለየን

#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እና እኔ #ሠዓሊ_ዲን_ጌታባለው_አማረ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን
በዚህም ገጽ የቅዱሳንን መንፈሳዊ ሕይወት ከተጋድሏቸው ጋር ፤ የቅዱሳን መላዕክትን ተራዳኢነት እንዲሁም ገድላት ድርሳናትን ከቅዱሳት ስዕላት ጋር ተስማምተው ያገኙበታል ።

@deacongetabalewamare
🌹+ + አስተርእዮ + +🌹
#ሞት_ለሚሞት_ይገባል
#የማርያም_ሞት_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል "

"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"

እንኳን ለ 2017ዓ.ም
#አስተርእዮ ማርያም በዓል አደረሳችሁ!!!
እምሰማያት ወረደ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፤ ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለ፳ኤል፤ ወረደ ስኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ፤ ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ፤ መድኅን እማርያም።

🙏🏾 የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🏾
ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን ያሳድርብን!!!

የልጅዋ የወዳጅዋ ቸርነት አይለየን

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት
#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
2025/02/05 04:49:29
Back to Top
HTML Embed Code: