Telegram Web
🌹🍂እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 🍂
ግንቦት 21 በ #ደብረ_ምጥማቅ እንደተገለጸለች

#ደብረ_ምጥማቅ ፦ ከሠላሳ ሶስት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው #ግንቦት_21 ቀን የሚከበረው ይህ የእመቤታችን በዓል ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ የወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ሲሆን በዚህ ቀን በግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ተገለጽላቸው ነበር ።

🍂 #እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር ይኸውም አልቀረም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል ።

በዚህ ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበር ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሣት ታይታለች

እስከ አምስት ቀንም ምእመናኑን አረማውያኑን አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች ከዚህም በኋላ ምእመናንም አረማውያንም በየዓመቱ እነዚህን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25 ለአምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል ።

. #ለኛም_ለልጆቿ_በሕይወታችን_ሁሉ
. #እየተገለጠች_በረድኤት_በበረከት_ትባርከን !!

©✎﹏ዳዊት ተስፋዬ Daweit Tesfay

🍂 #ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሳሉት

‎ዲ/ን ጌታባለው አማረ
‎የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሥዕለ አቡነ #ተክለሃይማኖት
🎨 ዲያቆን ጌታባለው አማረ
🖌️ የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ 🎨
📞+251923075264
🍂+ + #አቡነ_ሃብተ_ማርያም + +
ግንቦት 26 በዓለ ልደታቸው

አባታቸው 🌷 ፍሬ ቡሩክ
እናታቸው 🌷 ቅድስት ዮስቴና ይባላሉ

🍂 የጻድቁ አባታችን #አቡነ_ሃብተ_ማርያም አባታቸው በስተምስራቅ በምትገኝ ራውዓይ በምትባል ቦታ ይኖሩ የነበሩ ባለጸጋ ነበሩ በዚህም ዮስቴና የተባለችውን በሕግ ጋብቻ አግብተው በንጽሕና በቅድስና ሕይወት እግዚብሔርን በማስደሰት ይኖሩ ነበር።

በወንጌል ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋም ምን ይረባዋል የሚለውን ሀሳብ በልቧ ስለነገሰ ። ወደ ምድረበዳ አመራች አመራች በዚያም ዋሻ አግኝታ ስትገባ አንድ ባሕታዊ አገኘች ። አርሳቸውም ልታሰናክይኝ መጣሽን ከዚህ ሂጂ አሏት እርሷም አመጣጧን እና ለምናኔ ሕይወት እራሷን አዘጋጅታ እደመጣች ነገረቻቸው ።

🍂 እሳቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸው ፦

🌷 " ዜናው ወደ ዓለም ወደ ዓለም ሁሉ የሚወጣ ፤
በሕይወተ ሥጋም እያለ የብዙዎች ሰዎችን ነፍስ ከሲኦል የሚያወጣ ፤ በንጽሐ ልቡና ወደ አርያም ወጥቶ የሥላሴን የአንድነት አና የሦስትነት ምስጢርን የሚያይ ልጅን ትወልጃለሽ" 🌷 አላት።

ቅድስት ዮስቴናም የባሕታዊውን ቃል አክብራ
ወደ ቤቷ ተመለሰች።
🌷 ቅዱስ አባታችንም
በነሀሴ 26 ቀን ተጸነሱ

ከጥቂት ጊዜያትም በኋላ በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ ባሕታዊ ፤ መልኩ ያማረ ደምግባቱ የተወደደ ወንድ ልጅን #በግንቦት_26_ቀን_ወለደች
በዓርባኛውም ቀን ለጅነት የገኝ ዘንድ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ወሰደችው ክርስትና ስሙም እንዲህ ተባለ ፦
🔥#ሃብተ_ማርያም 🔥

🌺 የጻድቁ አባታችን አቡነ #ሃብተ_ማርያም
ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርልን

ቃልኪዳናቸው ከስጋ በሽታ ( ከቸነፈር ፣ ከወረርሽኝ )
ከነፍስ ቁስል ( ከኃጢአት ) ይሰውረን 🙏🏾



ሠዓሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare
🌺 የጻድቁ አባታችን አቡነ #ሃብተ_ማርያም
ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርልን

ሠዓሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare
#በዓለ_ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ 🔥
ሁሉም #በአንድ_ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ 🔥

༺◉❖─🔥─═❖◉༻

ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።

🔥 #እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች 💥 ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
#በሁሉም_መንፈስ _ቅዱስ ሞላባቸው፥
መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው
በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።

( ሐዋ. 2 ; 1 - 4 )

༺◉❖═─◉●◉ 🔥 ◉●◉──═❖◉༻

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

+251923075264

www.tgoop.com/deacongetabalewamare
🌸🍂 ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል 🍂🌸
#ሰኔ_12

🍂 የከበረች #አፎምያ ያረፈችበት ዕለት ነው
እግዚአብሔርን የሚፈራ የአንድ ሰው ሚስት ነበረች ።
ባሏ ብዙ ምጽዋትን ያደርግ ነበር በየወሩም ሦሶቱን በዓላት ያደርግ ነበር ፤ እነዚህም ፦

* በ29 /የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት መታሰቢያ /
* በ21 /የቅድስት ድንግል ማርያምን /
* በ12 / የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን /

🍂 የሚሞትበት ቀን በደረሰም ጊዜ እርሱ ያደርገው የነበረውን ምጽዋት እንዳታስታጉል እነዚህንም 3 በዓላት እንድታከብር አዘዛት

🌸 #ቅድስት_አፎምያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ ይሰጣት ዘንድ ባሏን ለመነችው። እርሱም አደረገላት

🍂 እርሱም ካረፈ በኋላ ያደርገው የነበረውን እያደረገች በቅድስና ሕይወት ጸንታ ትኖር ጀመር። ጸላዔ ሠናይ የሆነ ሰይጣን ስለቀናባት ይፈትናት ዘንድ መነኩሲት ተመስሎ ፤ ባልሽ በስጋ ተለይቶሻል ከእንግዲህ ምጽዋትን አታድርጊ፣ ሌላ ባል አግብተሽ በደስታ ኑሪ እያለ ክፉ ምክርን ይመክራት ጀመር ።

🍂 እርሷም ሌላ ላላገባ ለእግወዚአብሔር ምያለው ፤ ርግቦችም እንኳን ከአንድ በቀር ሌላ አያውቁም ፤ አለችው ምክሩንም እነዳልተቀላት ባወቀ ጊዜ መልኩን ለውጦ ጮኸባት በሌላም ቀን እመጣለው ብሏት ጥሏት ሄደ።

#በሰኔ_12 ቀንም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ስታከበር ሰይጣን አንደለመደው ይፈትናት ዘንድ መልአክ ተመስሎ ወደርሷ መጣ ። የቀደመ ክፉ ምክሩን ከመጻህፍት እየጠቀሰ ያስታት ዘንድ ይነግራት ጀመር። የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክስ የያዝከው በትረ መስቀልህ ወዴት አለችው።

🍂 #ሥዕለ_ቅዱስ_ሚካኤልን አምጥታ ብታሳየው ፤ ወደ ከበረ ሚካኤል ብትለምን ፈጥኖ ደርሶ አዳናት። ዲያብሎስንም ከእርሷ አሳደደው።

🌸 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ቅድስት አፎምያን አንቺ በዚህች ቀን ከዚህ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም በምት ትለያለሽና ሄደሽ ስራሽን አከናውኚ ። እነሆ እግዚአብሔር ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻልና አላት ሰላምታም ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዓረገ ።

የበዓሉንም ሥርዓት በሚገባ ፈጸመች ።
ኤጲስ ቆጶሱን ካህናቱን ወደ ጠራች እነርሱም መጡ ።
ገንዘቧን ሁሉ ለዳያን መጸወተች

ከዚህም በኋላ ቆማ ጸለየች
የከበረ መልአክ የሚካኤልን ሥዕል ከፊቷ አደረገች
በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ
#በሰኔ_12_ቀንም_አረፈች

🌸 #አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን


👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
🌸 #አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን


👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
📞 + 251923075264
ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል _የባሕራንን የሞቱን ጦማር ወደ #ሕይወት እንደቀየረለት ፤ #ሰኔ_12

༺◉❖═─◉●◉🌹◉●◉──═❖◉༻

#ከገናናው_መልአክ_ከቅዱስ_ሚካኤል🙏🏾

#አምላከ_ቅዱሳን_ረድኤት_በረከትን_ይስጠን 🙏🏾

༺◉❖═─◉●🌹◉●◉─═❖◉༻

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሣሉት
📞 +251923075264

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
www.tgoop.com/deacongetabalewamare
#ሕንጸተ_ቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም።
🍂የቤተ ክርስቲያን መታነጽ በእመቤታችን ስም #ሰኔ_21

🍂 #ጌታችን በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ወደዱ፡፡

በዚህ ጊዜ ርእሰ ሐዋርያት እያለ እኛ መሥራት አይገባንም ብለው በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ እርሱም ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር መጥቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፡፡

🍂 በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶ ቅዱሳን ሐዋርያትን #በፊልጵስዩስ አገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራዉን የአብያተ ክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቤአችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡

#በዚያም_ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፤ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡

🍂 ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰም እሳት ሲያገኘው እንዲለመልም፣ ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳበላቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመዉታል፡፡

#ሕንጻ_ቤተ_ክርስቲያኑ የተሠራዉም ጌታችን
በዐረገ በ፲፱ኛው፤
እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲኾን፣ በ፳፩ኛው ቀን (በማግሥቱ) ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡
ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ “ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ “ ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

( መጽሐፈ ስንክስራ የሰኔ 20 ፣ መጽሐፈ ግስ ወሰዋሰው)

ንጽሕት በድንግልና ፣
ሥርጉት በቅድስና
እመቤታችን ወላዲተ አምላክ
ከመከራ ስጋ
ከመከራ ነፍስ
ትሰውረን
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare
ወርቅ የሆንከው ጥበበኛው አባቴ ታሪክ ለመስራት አሁን ጥበበኛ እጆህን አንሳ : በቡሩሾችህም ቀለማትን 🖌️አሰባጥረህ ታሪክ ለመሥራት ተዘጋጅ . . . ! 🎨

🍂 በቃል የሚነገረውን ወንጌል በትውፊትም የተቀመመውን ሥርአት እና ቀኖናቸውን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን በታሪካዊው እና ድንቅ በሆነው በኳታር ዶሀ ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንድትሥል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥበብ ማስተዋሉንም የስጥህ።

እኔም ልጅህ በዚህ ታሪካዊ ሥራ ከጎንህ ሆኜ አግዝህ ዘንድ ፍቃዱ የሆነ እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🏽

ወንድሜ Biruk Thomas
ከ 2 ቀን በኋላ እንቀበልሀለን

እግዚአብሔር እረድቶን አግዞን
የምንሄድበትን አላማ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀን እንደምንመለስም ሙሉ እምነት አለኝ

👉🏽 ጉዟችን የተቃና ይሆን ዘንድ በመንገዳችንም ሁሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ

በጸሎታችሁ አስቡን !🙏🏽


ሰኔ 22 / 2017 ዓ/ም
June 29 / 2025


ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264
" 🔥 አቤት ደስታዬ እናንተም ደስ ይበላችሁ 🔥 እኚህን ቅዱሳት እጆች ያሏቸውን ሠዎች ማየትም ማግኘትም ምንኛ መታደል ነው ::

ታላቁን የኳታር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴን ቤተ ክርስቲያንን ቅዱሳት ሥዕላትን በተቀላቀሉ ውብ ቀለሞች በመስቀላቸው ብዕርነት በዕንቁ እና በወርቅ ሊያሽቆጠቁጡት እጅግ የተወደዱ ሊቅ የቤተ ክርስቲያኒቷን መዓዛ ያጣጣሟት የአባታቸውን የክህነት ዘር ያስቀጠሉ በሥዕላቸው ትንተና ከሁኔታ ከእይታ ከትርጟሜ ጋር አጣምረው ቅዱሳት ሥዕላትን አይምሮ ላይ ሁሉ ተስሎ እንዲቀር የሚያደርጉት ይህም ጸጋ በዘመናችን የተቸራቸው ዘራቸው በሙሉ ቤተ ክርስቲያኒቷን የሚያገለግሉ ካሕናት የሆኑላት Kesis Amare Kibret ከተወደደው የእርሳቸውን ፈለግ ተከትሎ እየቀደሰም እየሳለም የቤተ ክርስቲያናችንን ዘር ካስቀጠለ ልጃቸው ከሠዓሊ Dn Getabalew Amare ጋር ኳታር ገብተዋል ::
#እግዚአብሔር ፍጻሜውን ያሳምርልን እንኳን ደህና መጣችሁልን !! "

( ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " )

ለተደረገለን መልካም አቀባበል እጅግ በጣም እናመሰግናለን #እግዚአብሔር ፍጻሜውን ያሳምርልን እንኳን ደህና ቆያችሁን "
2025/06/30 09:27:53
Back to Top
HTML Embed Code: