Telegram Web
🌹 #ዮም_ፍሥሐ_ኮነ
#በእንተ_ልደታ_ለማርያም 🌹

የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ

🌺 በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ🌺

የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት 👏🏾
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት 👏🏾

+ + + + +

#ምስጋናን_የተመላሽ_ድንግል_ሆይ
#በማንንና_በምንስ_ምሳሌ_እንመስልሻለን

አማኑኤል የማይተረጎም የሥጋን ልብስነት
ከአንቺ የለበሳት መሥሪያ ነሽ።
ዝሐውን ከአዳም ጥንተ ሥጋ አደረገ ማጉም የአንቺ ሥጋ ነው። መወርወሪያውም ቃል እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መሕኑም ከልዕልና የወረደ
የልዑል እግዚአብሔር አምሳል ነው።
ሠሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው።

ወዮ ይህ ነገር እጹብ ድንቅ ነው።
የቀደሙ አባቶች ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩብሽ ድልድይ ሆይ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርሺ መሰላል ሆይ የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ ።

🙏ከገነት #በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ።🙏
/ ቅዳሴ ማርያም ቁ.29 - 31/

🙏🏾 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
የልደት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችኝ
ጣዕሟን በአንደበታችን ያኑርልን 🙏🏾
🙏🏾 🙏🏾 🙏🏾

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሳት ሥዕላት ሰዐሊ /
+251923075264

www.tgoop.com/deacongetabalewamare

#አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ
በአነዋወር አንድ
በገጽ ሦስት ሦስት ናቸው ።
~ ~ ~
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
በአካል ሦስት
በመለኮት አንድ ናቸው ።
~ ~ ~
አብ በአካሉ ፍጹም ነው
ወልድም በአካሉ ፍጹም ነው
መንፈስ ቅዱስም በአካሉ ፍጹም ነው
እሊህ ሦስቱ አካላት በመለኮት አንድ ናቸው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያልና የሚያስፈራዓይኑ እንደ እሳት የሚነድ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የራስ ጸጉሩ አንደበረድ የነጻ
እንደ ሰርዲኖስ እና ኢያሰጲድ ዕንቊ የከበረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የመቅደሱ አጥር በእሳት የታጠረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
በጠላት ፊት የማይበገር እሱ ጽኑዕ አዳራሽ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ጠፈርን ያለምሰሶ መሬትን ያለ መሠረት ፈጥሮ ያለ ድጋፍ በቃል ብቻ ያፀና እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ሁሉን በየወገኑ የሚገዛ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
መንግሥቱ የማያልፍ ግዛቱም ለዘለዓለም የሚኖር እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የሦስትነቱ ሥርዓት የማይለወጥና ለሦስትነቱ ምስጋና የሚገባው እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
መባርቅት የሚላኩለት ነጎድጓድ የሚያመሰግኑት እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ የሚሆን እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።

🍀 🍀 🍀 🍀 🍀
ዓለምን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ እሱ
እግዚአብሔር ነው።
ቁጣውን በቸርነቱ ባሕር የሚያሰጥማት እሱ
እግዚአብሔር ነው ።
የመቅሠፍቱን እሳት በይቅርታው ውሃ የሚያጠፋ እሱ
እግዚአብሔር ነው ።
የማይቀየም የዋህ ንስሐን የሚወድ እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው ።
ኃጢአትን በቸርነቱ ጥላ የማሸፍን እሱ
እግዚአብሔር ነው።
አበሳን በቸርነቱ ጒድደጓድ የሚደፍን እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው ።
በደልን በትዕግስቱ መጋረጃ የሚጋርድ እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው።

✝️ 🙏 🙏 🙏 ✝️
ለእሱ ለብቻው ምስጋና ይገባል ።
#ለመንግሥቱም እዘዝ ይገባል ።
#ለሦስትነቱ ክብር ይገባል ።
#ለከኃሊነቱ ኃይል ይገባል ።
#ለመለኮቱ ሥልጣን ይገባል ።

ለዘለዓለሙ አሜን
🙏
°°°°°°°°°°°°°°°°°°

#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እንደሣሉት

#ሠዓሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
ቅዱሳት ስዕላትን ሠዓሊ

@deacongetabalewamare
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በግዕዝ : በዕዝል እና በአራራይ ዜማ ያስጌጣት : የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ማኅሌታይ #ቅዱስ_ያሬድ በግንቦት 11 ቀን የተሠወረበት በዓል ነው ። እንኳን አደረሳችኹ

#ያሬድ 🌹 ማለት ፦ እንዚራ ፣ በገና ፣ መሰንቆ ማለት ነው እነዚህ የዜማ መሳሪያዎች ሲሰሙ ኃሴትን እንዲፈጥሩ ✥ የቅዱስ ያሬድም ዜማ ነፍስን የሚያስደስት አጥንትንም የሚያለመልም ነው።

አንድም ፦ ያሬድ፦ ( ירד የራድ) የዕብራውያን ስም ሲሆን ትርጉሙም ወረደ - ተሰጠ (ከአምላክ) ማለት ነው፤

እናቱ ታውክልያ ( ክርስቲና )
አባቱ ይስሐቅ ( አብድዩ ) ይባላሉ።

🍂 ✢ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በሚያዚያ 5 ቀን 505 ዓ/ም ተወለደ ። አባቱም የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር ፤
ቅዱስ ያሬድ ገና በልጅነቱ /በ7 ዓመቱ/ አባቱ በሞት ስለተለየው እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ልታስገባው ስለፈለገች አጎቱ አባ ጌድዮን ወደ ሚያስተምርበት ቤተ ቀጢን ጉባኤ ቤት አስገብታዋለች።

🍂#ያሬድ ግን ከሌሎች ተማሪዎች አንጻር በትምህርቱ ደካማ ነበር፤ በዚህም ተስፋ ቆርጦ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ሲመለስ በጉዞ ደክሞት ከአንዲት ዛፍ ስር አርፎ በነበረበት ሰዓት አንዲት ትል ተስፋ ባለመቁረጥ በመውደቅ እና በመነሳት በሰባተኛውም ወደዛፉ እንደወጣጭ ተመልክቶ፤ ያየውን በሕይወቱ ተርጉሞ ተስፋ መቁረጥን ትቶ ወደ መምህሩ ተመልሶ፦ ትምህርቱን ቀጥሏል።

🍂✢ ኋላም ትምርቱን በሚገባ እየተከታተለ ፤ አስቀድሞ አልገባ ያለውም ትምህርት ተገልጾለት ብሉይንን ከሐዲስ ኪዳን ተምሮ አጠናቆ በአጎቱ ወንበር ተተክቷል።

✢ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊ የሆነው ዜማ ተገልጾለት በሦስት የዜማ ስልት ፤

🌹 ግዕዝ
🌹 ዕዝል
🌹 አራራይ

በስምንት የዜማ ምልክቶች ድርሰቱን ደረሷል።
✢ ድርሰቶቹም ፦ 5 ሲሆኑ እነርሱም
🌹 ድጓ
🌹 ጾመ ድጓ
🌹 ዝማሬ
🌹 መዋሥዕት
🌹 ምዕራፍ

✢ ደብረ ሐዊ ከተባለው ተራራ ላይ በምናኔ ሕይወት ብዙ ዓመታትን ካሰለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በግንቦት 11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰውሯል።



አሠርገዋ ለኢትዮጵያ ፤ በስብሐት ወበሃሌ ሉያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ አስተካልሐ በቅዳሴ ፤ በዘሱራፌል አርአያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ ለበግዕ በትንሣኤሁ ፤ ደመ ጥብሑ አርወያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ በመኃልይሁ አቅነያ



#የማኅሌታይ_ቅዱስ_ያሬድ 🙏🏽
ረድኤት በረከት በሁላችን ይሁን 🙏🏽

👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
Kesis Amare Kibret
📞 +251913684351

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
አሠርገዋ ለኢትዮጵያ ፤ በስብሐት ወበሃሌ ሉያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ አስተካልሐ በቅዳሴ ፤ በዘሱራፌል አርአያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ ለበግዕ በትንሣኤሁ ፤ ደመ ጥብሑ አርወያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ በመኃልይሁ አቅነያ



#የማኅሌታይ_ቅዱስ_ያሬድ 🙏🏽
ረድኤት በረከት በሁላችን ይሁን 🙏🏽

👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
Kesis Amare Kibret
📞 +251913684351
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂 ጸጋሽን ያብዛልሽ #እህቴ : ከዚህም በበለጠ ይምትስዪበትን ትእግስትን ማስተዋልን ይጨምርልሽ 🖌️

#ሠዐሊት_ሕይወት_አማረ 🎨
የዓለም ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት በጥብቅናው ድምፀ ግፉዓን፣ በጥቡዕነቱ መገሥጽ፣ በክህነቱ የቤተ ክርስቲያን መዓዛ የሆነ ፣ የአፈ በረከት : የአፈ መአዛ : የአፈ ጳዝዮን : የአፈ መአር : #የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የዕረፍቱ መታሰቢያ በግንቦት 12 ቀን ሆነ።

🍂 ዐሥራ ሁለተኛው የቊስጥንጥንያ መንበር የነበረ፣
ከአራቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያን ዐቃቢያነ እምነት ከሆኑት ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ከቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያና ከቅዱስ ባስልዮስ ጋር በግብር የተካከለ፣ በገዳማዊ ሕይወቱ ብሕትው፣ በንጽሕናው ተአማኒ፣ በአእምሮ ምጡቅ፣ በአንደበቱ ርቱዕ፣ በስብከቱ መገሥጽ፣ በፍርዱ ፈታሒ በጽድቅ፣ በመግቦቱ አበ ምንዱባን (የድኆች አባት) #ቅዱስ_አፈወርቅ

#የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
የቃሉ ትምህረት በልቦናችን ይጻፍልን
የሕይወቱም መአዛ በልቦናችን ላይ ይብራልን 🙏🏽

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ @deacongetabalewamare
ግንቦት 12 ቀን እናታችን #ቅድስት_ክርስቶስ_ሰምራ ከወዳጇ ከፈጣሪዋ ቃል ኪዳንን ተቀበለች ። ከሲኦልም : 10 ሺህ : ነፍሳትን : ይዛ : ወጣች

🍂 በሸዋ ቡልጋ ክፍለ ሀገር ጌዬ በተባለ አካባቢ የተወለደችው #ቅድስት_ክርስቶስ ሠምራ አባቷ ደረሳኒ እናቷ ዕሌኒ በእግዚአብሔር ፊት የታመኑ ሰዎች ስለ ነበሩ ልጃቸውን የቤተክርስቲያን ሥርዓት የብሉይና እና የሐዲስ ኪዳንን መጻሕፍት በማስተማር አሳደጓት ፡፡

🍂 ዕድሜዋ ለአቅመ ሔዋን ሲደርስ ወላጆቿ የኢየሱስ ሞዓ ልጅ የሆነውን ሠምረ ጊዮርጊስን አጋቧት ዐሥር ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች እርሷም ልጆቿን በሥርዓትና በሕገ እግዚአብሔር አሳደገቻቸው ።

በዚያ ዘመን የነገሰው ንጉሥ ዓፄ ገብረ መስቀል ደግ ሰው ነበር በአንድ ወቅት ንጉሡ ስለ #ቅድስት_ክርስቶስ ሠምራ ቁንጅናና ደግነት በሰማበት ወቅት በግዛቱ ከተደነቁት 174 ሴቶች መካከል አንዷ ስለነበረች ስለእርሷ ዝና አወቀ ፡፡

🍂 ንጉሡም ያገለግሏት ዘንድ 272 ያህል ብላቴናዎችን ላከላት ከንጉሡ የተላኩላትንም አገልጋዮች አስተባብራ ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዛት በስሙ ቤተክርስቲያን አሠራች የመልአኩን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤተ መቅደስ በማስገባት በዚያ ስታገለግልና ስታስገለግል ኖረች ፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ከአገልጋዮቿ አንዷ ላይ ርኩስ መንፈስ አደረ አልታዘዝም ማለትም ጀመረች ይህን ጊዜ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደጋግማ መከረቻት ያቺ ብላቴና ግን ልትመከር አልቻለችም በዚህም ሳቢያ ክፉኛ ብታዝንባት ብላቴናዋ ሞተች ፡፡

🍂 እጅጉን ያዘነችው እናታችን « ይህማ የነፍስ ግድያ ይሆንብኛል » ብላ አምርራ አለቀሰች ወደ እግዚአብሔር በጸለየች ጊዜ ፈጣሪ አገልጋይቱን ከሞት አስነሳላት ፡፡

ውስጧም በሐሴት ተሞላ ፤ እንዲህም አለች « በዓለማዊ ሕይወት ውስጥ ስኖር ይህን ተአምር ካደረገልኝ በምናኔ ሕይወት ብኖር ደግሞ ምን ያህል ድንቅ ሥራ ያደርግልኛል » ብላ ባለቤቷንና ልጆቿን እንዲሁም ወላጆቿን ትታ መነኮሰች ፡፡

#እናታችን_ክርስቶስ_ሠምራ ደግና ርኅሩኅ ነበረችና ጌታን እንዲህ ብላ ለመነችው « አቤቱ ፈጣሪዬ እኔን ባሪያህን ከክፉ ነገር ሁሉ ሠውረህኛልና ዲያብሎስን ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ » ብትለው ጌታችንም « ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዕፁብ ድንቅ ልመና ለመንሽኝ ! ሌሎች በኋላሽም የነበሩ በፊትሽም የሚመጡ ያልለመኑትን ልመና ለመንሽኝ » አላት ቅዱስ ሚካኤልንም ወደ ዲያብሎስ እንዲወስዳት አዘዘው ፡፡

#ሲኦል ሲደርሱ ምሕረትን የሚሻ ከሆነ እንድትጠይቀው ቅዱስ ሚካኤል ባዘዛት ጊዜ ፤ « ሳጥናኤል » ብላ ጠራቸው ዲያብሎስም መልሶ ሳጥናኤል ብሎ የጠራኝ ማን ነው ? አለ ፡፡ እርሷም « እኔ ነኝ » አለችው ፡፡

ወደ እኔ ለምን መጣሽ ሲላት ‹ ከፈጣሪህ ጋር አስታርቅህ ብየ › አለችው እርሱም አንቺን ከቤትሽ ከንብረትሽ ሳለሽ አስትሻለሁ ብየ ብመጣ ያጣሁሽ ሰው እኔን ልታስታርቂኝ መጣሽ ? ግን ይህን ያደረገ ያ የቀድሞው ጠላቴ ሚካኤል ነው ፤ ሲጻረረኝ የሚኖር ከክብሬም ያወረደኝ እሱ ነው እንጂ አንቺ ምን ጉልበት አለሽ ብሎ እጇን ይዞ ወደ ሲኦል ወረወራት ፡፡

🍂 በዚያች ቅጽበት ቅዱስ ሚካኤል ሲኦልን በሰይፉ መታው ፤ ተከፈተም ፣ በውስጡም ብዙ ነፍሳት እርስ በርስ ሲነባበሩ አየች ፤ ነፍሷም ታበራ ስለነበር 10 ሺህ ያህል ነፍሳት መጥተው በላይዋ ሰፈሩባት ፣ ከሲኦልም ይዛቸው ወጣች እነዚያን ነፍሳት የማረላትንም ፈጣሪዋን አመሰገነች ፡፡

ከዚህ በኋላ ሥጋዋ ከነፍሷ ተዋሕዶ ወደ መሬት ተመለሰች ፤ በቁመቷ ልክ ጉድጓድ አስቆፍራ ፤ በዙሪያዋ ጦሮችን አስተከለች ይህም ወደፊትና ወደኋላ በምትልበት ጊዜ እንዲወጋት ነበር ለ12 ዓመትም እየሰገደች ኖረች ፡፡

ጌታችንም እንዲህ አላት « አንቺን የሚወዱ ፤ ስምሽን የሚጠሩ ፤ ዝክርሽን የዘከሩና በዓልሽን ያከበሩ እስከ አሥራ ሁለት ትውልድ እምርልሻለሁ » አላት በመጨረሻም ነሐሴ 24 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታ መላእክት አሳረጓት ።

🍂 #የቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ የከበረ ዐፅም ጌዬ የተባለ ገዳም ውስጥ ተቀምጧል ይህም ገዳም እርሷን መዘክርና መማጸን ለሚሹ ምእመናን የተሠራ ነው ፡፡

#የእናታችን_የቅድስት_ክርስቶስ_ሰምራ አማላጅነቷ ረድኤቷ በረከቷ ጠብቆቷ ለኛ በስሟ አምነን ለምንማጸን የመንፈስ ልጆቿ ይሁን ይደረግልን ለዘዓለሙ አሜን ፡፡ 🙏🏽
© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ @daweittesfay

✥••┈┈••● ✞ ●••┈┈••✥

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት ከ25 ዓመት በፊት የሣሉት የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥዕል ።
ሥዕሉም በወላይታ ሀገረ ስብከት በታላቁ ገዳም ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ይገኛል ።

✥••┈┈••● ✞ ●••┈┈••✥

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣን ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
✥••┈┈••● ✞ ●••┈┈••✥

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት ከ25 ዓመት በፊት የሣሉት የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥዕል ።
ሥዕሉም በወላይታ ሀገረ ስብከት በታላቁ ገዳም ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ይገኛል ።

✥••┈┈••● ✞ ●••┈┈••✥
#እያዩት_ከፍ_ከፍ_አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው” ( ሐዋ. 1÷9 )

🍂 #ዕርገት ማለት ወደላይ ከፍ ከፍ ማለት ሲሆን የመሬትን የስበት ኃይል የሚያሸንፍ ከፍታ ነው፡፡ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ያረገው የመሬት የስበት ኃይልሳይገድበው ነው፡፡ የክርስቶስ ዕርገት ቀድሞ በትንቢት የተነገረ፤ በሚያምኑት ዘንድ በናፍቆት ሲጠበቅ የቆየ እና በራሱ በጌታችን የተሰበከ ነው፡፡

‎ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ፴፫ ዓመታት ከሦስት ወራት በምድር ኖሯል፡፡ በ፴ ዓመቱ ተጠመቀ ለ፫ ዓመታት አስተማረ፣ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ ቤዛ ሆነልን፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታንተለይቶ ተነሣ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ተገለጠላቸው፡፡

‎ዛሬም ጌታችን ኢየሱስ ከዕርገቱ በፊት ከተነሣ በኋላ ስላስተማራቸው ትምህርቶች፣ ደቀመዛሙርቱን ስላዘዛቸው ትዕዛዝ እናያለን፡፡

‎ጌታችን ከተነሣ በኋላ ባሉት ፵ ቀናት በተለያዩ ጊዜያት ለደቀመዛሙርቱ ተገልጾ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ያስተምራቸው ነበር፡፡ ስለክርስቶስ የተነገረውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢት ከዚያ በፊት አላስተዋሉም ነበር፡፡ ጌታችንም ስለ እርሱ የተጻፉትን ተረጎመላቸው፣ አዕምሮቸውንም ከፈተላቸው መጻሕፍትንም አስተዋሉ፤ እምነታቸውን አጸናላቸው፡፡ ስለ ትንሣኤው የነበራቸውን ጥርጣሬም ከልቦናቸው አጸዳላቸው፡፡

‎የሚከተሉትን ትዕዛዛት እና ኃላፊነቶችም ሰጣቸው፡-
‎* ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡ ማር ፲፮ ፥ ፲፭

‎* ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፡፡ የሐዋ ፩ ፥ ፭

‎* እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ… አስተምሯቸው፡፡ ማቴ. ፳፰ ፥ ፲፱ – ፳

‎* እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፡፡ የሐዋ.ሥ ፩ ፥ ፰

‎በወንጌል ለመስበክ እና በስሙ ለማጥመቅ ወደ ዓለም ሲወጡ፣ እንደሚገረፉ ወደ ነገሥታት የፍርድ አደባባይም እንደሚያወጧቸው ነገሯቸዋል፡፡ እስከመጨረሻም የጸና ግን ይድናል በማለትእስከ ዓለም ፍጻሜ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆንና መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ኃይልን እንደ ሚያገኙምቃል ገብቶላቸዋል፡፡

‎ከሙታን በተነሣ በ፵ ኛው ቀን ደቀመዛሙርቱን ወደ ደብረዘይት ወሰዳቸውና ባረካቸው፡፡ ተሰብስበው ትምህርቱን እየሰሙም ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለ፡፡ ወደ ሰማይም ዐረገ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረው፡፡

‎ደቀመዛሙርቱ ክርስቶስ ወደ ዐረገበት ቀና ብለው እየተመለከቱ ሳለ ሁለት መላዕክት ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው “ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይሄ ከናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሏቸው፡፡ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ በተነሣ በአርባኛው ቀን በድል ዐረገ፡፡ ወደ ሰማይ እያረገ ሲሄድ እንዳዩት ደግሞ በዓለም ላይ ሊፈርድ ይመጣል፡፡ ማረጉን አምነን ዳግም መምጣቱን እንናፍቅ፡፡�

‎” ደቀመዛሙርቱም ጌታ ካረገበት ከደብረ ዘይት እግዚአብሔርን እያከበሩ ተመለሱ፡፡ እንደታዘዙት መንፈስ ቅዱስን እስኪቀበሉም በኢየሩሳሌም ቆዩ ፡፡

‎እኛም በኢየሩሳሌም በተመሰለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎትና በአገልግሎት በመትጋት ልንቆይ ይገባል ።


🍂 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት

‎ዲ/ን ጌታባለው አማረ
‎የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
🌹🍂እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 🍂
ግንቦት 21 በ #ደብረ_ምጥማቅ እንደተገለጸለች

#ደብረ_ምጥማቅ ፦ ከሠላሳ ሶስት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው #ግንቦት_21 ቀን የሚከበረው ይህ የእመቤታችን በዓል ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ የወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ሲሆን በዚህ ቀን በግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ተገለጽላቸው ነበር ።

🍂 #እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር ይኸውም አልቀረም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል ።

በዚህ ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበር ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሣት ታይታለች

እስከ አምስት ቀንም ምእመናኑን አረማውያኑን አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች ከዚህም በኋላ ምእመናንም አረማውያንም በየዓመቱ እነዚህን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25 ለአምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል ።

. #ለኛም_ለልጆቿ_በሕይወታችን_ሁሉ
. #እየተገለጠች_በረድኤት_በበረከት_ትባርከን !!

©✎﹏ዳዊት ተስፋዬ Daweit Tesfay

🍂 #ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሳሉት

‎ዲ/ን ጌታባለው አማረ
‎የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሥዕለ አቡነ #ተክለሃይማኖት
🎨 ዲያቆን ጌታባለው አማረ
🖌️ የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ 🎨
📞+251923075264
🍂+ + #አቡነ_ሃብተ_ማርያም + +
ግንቦት 26 በዓለ ልደታቸው

አባታቸው 🌷 ፍሬ ቡሩክ
እናታቸው 🌷 ቅድስት ዮስቴና ይባላሉ

🍂 የጻድቁ አባታችን #አቡነ_ሃብተ_ማርያም አባታቸው በስተምስራቅ በምትገኝ ራውዓይ በምትባል ቦታ ይኖሩ የነበሩ ባለጸጋ ነበሩ በዚህም ዮስቴና የተባለችውን በሕግ ጋብቻ አግብተው በንጽሕና በቅድስና ሕይወት እግዚብሔርን በማስደሰት ይኖሩ ነበር።

በወንጌል ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋም ምን ይረባዋል የሚለውን ሀሳብ በልቧ ስለነገሰ ። ወደ ምድረበዳ አመራች አመራች በዚያም ዋሻ አግኝታ ስትገባ አንድ ባሕታዊ አገኘች ። አርሳቸውም ልታሰናክይኝ መጣሽን ከዚህ ሂጂ አሏት እርሷም አመጣጧን እና ለምናኔ ሕይወት እራሷን አዘጋጅታ እደመጣች ነገረቻቸው ።

🍂 እሳቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸው ፦

🌷 " ዜናው ወደ ዓለም ወደ ዓለም ሁሉ የሚወጣ ፤
በሕይወተ ሥጋም እያለ የብዙዎች ሰዎችን ነፍስ ከሲኦል የሚያወጣ ፤ በንጽሐ ልቡና ወደ አርያም ወጥቶ የሥላሴን የአንድነት አና የሦስትነት ምስጢርን የሚያይ ልጅን ትወልጃለሽ" 🌷 አላት።

ቅድስት ዮስቴናም የባሕታዊውን ቃል አክብራ
ወደ ቤቷ ተመለሰች።
🌷 ቅዱስ አባታችንም
በነሀሴ 26 ቀን ተጸነሱ

ከጥቂት ጊዜያትም በኋላ በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ ባሕታዊ ፤ መልኩ ያማረ ደምግባቱ የተወደደ ወንድ ልጅን #በግንቦት_26_ቀን_ወለደች
በዓርባኛውም ቀን ለጅነት የገኝ ዘንድ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ወሰደችው ክርስትና ስሙም እንዲህ ተባለ ፦
🔥#ሃብተ_ማርያም 🔥

🌺 የጻድቁ አባታችን አቡነ #ሃብተ_ማርያም
ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርልን

ቃልኪዳናቸው ከስጋ በሽታ ( ከቸነፈር ፣ ከወረርሽኝ )
ከነፍስ ቁስል ( ከኃጢአት ) ይሰውረን 🙏🏾



ሠዓሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare
🌺 የጻድቁ አባታችን አቡነ #ሃብተ_ማርያም
ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርልን

ሠዓሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare
#በዓለ_ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ 🔥
ሁሉም #በአንድ_ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ 🔥

༺◉❖─🔥─═❖◉༻

ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።

🔥 #እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች 💥 ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
#በሁሉም_መንፈስ _ቅዱስ ሞላባቸው፥
መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው
በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።

( ሐዋ. 2 ; 1 - 4 )

༺◉❖═─◉●◉ 🔥 ◉●◉──═❖◉༻

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

+251923075264

www.tgoop.com/deacongetabalewamare
🌸🍂 ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል 🍂🌸
#ሰኔ_12

🍂 የከበረች #አፎምያ ያረፈችበት ዕለት ነው
እግዚአብሔርን የሚፈራ የአንድ ሰው ሚስት ነበረች ።
ባሏ ብዙ ምጽዋትን ያደርግ ነበር በየወሩም ሦሶቱን በዓላት ያደርግ ነበር ፤ እነዚህም ፦

* በ29 /የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት መታሰቢያ /
* በ21 /የቅድስት ድንግል ማርያምን /
* በ12 / የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን /

🍂 የሚሞትበት ቀን በደረሰም ጊዜ እርሱ ያደርገው የነበረውን ምጽዋት እንዳታስታጉል እነዚህንም 3 በዓላት እንድታከብር አዘዛት

🌸 #ቅድስት_አፎምያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ ይሰጣት ዘንድ ባሏን ለመነችው። እርሱም አደረገላት

🍂 እርሱም ካረፈ በኋላ ያደርገው የነበረውን እያደረገች በቅድስና ሕይወት ጸንታ ትኖር ጀመር። ጸላዔ ሠናይ የሆነ ሰይጣን ስለቀናባት ይፈትናት ዘንድ መነኩሲት ተመስሎ ፤ ባልሽ በስጋ ተለይቶሻል ከእንግዲህ ምጽዋትን አታድርጊ፣ ሌላ ባል አግብተሽ በደስታ ኑሪ እያለ ክፉ ምክርን ይመክራት ጀመር ።

🍂 እርሷም ሌላ ላላገባ ለእግወዚአብሔር ምያለው ፤ ርግቦችም እንኳን ከአንድ በቀር ሌላ አያውቁም ፤ አለችው ምክሩንም እነዳልተቀላት ባወቀ ጊዜ መልኩን ለውጦ ጮኸባት በሌላም ቀን እመጣለው ብሏት ጥሏት ሄደ።

#በሰኔ_12 ቀንም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ስታከበር ሰይጣን አንደለመደው ይፈትናት ዘንድ መልአክ ተመስሎ ወደርሷ መጣ ። የቀደመ ክፉ ምክሩን ከመጻህፍት እየጠቀሰ ያስታት ዘንድ ይነግራት ጀመር። የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክስ የያዝከው በትረ መስቀልህ ወዴት አለችው።

🍂 #ሥዕለ_ቅዱስ_ሚካኤልን አምጥታ ብታሳየው ፤ ወደ ከበረ ሚካኤል ብትለምን ፈጥኖ ደርሶ አዳናት። ዲያብሎስንም ከእርሷ አሳደደው።

🌸 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ቅድስት አፎምያን አንቺ በዚህች ቀን ከዚህ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም በምት ትለያለሽና ሄደሽ ስራሽን አከናውኚ ። እነሆ እግዚአብሔር ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻልና አላት ሰላምታም ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዓረገ ።

የበዓሉንም ሥርዓት በሚገባ ፈጸመች ።
ኤጲስ ቆጶሱን ካህናቱን ወደ ጠራች እነርሱም መጡ ።
ገንዘቧን ሁሉ ለዳያን መጸወተች

ከዚህም በኋላ ቆማ ጸለየች
የከበረ መልአክ የሚካኤልን ሥዕል ከፊቷ አደረገች
በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ
#በሰኔ_12_ቀንም_አረፈች

🌸 #አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን


👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
🌸 #አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን


👉🏽 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
📞 + 251923075264
ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል _የባሕራንን የሞቱን ጦማር ወደ #ሕይወት እንደቀየረለት ፤ #ሰኔ_12

༺◉❖═─◉●◉🌹◉●◉──═❖◉༻

#ከገናናው_መልአክ_ከቅዱስ_ሚካኤል🙏🏾

#አምላከ_ቅዱሳን_ረድኤት_በረከትን_ይስጠን 🙏🏾

༺◉❖═─◉●🌹◉●◉─═❖◉༻

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሣሉት
📞 +251923075264

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
www.tgoop.com/deacongetabalewamare
2025/06/25 18:55:45
Back to Top
HTML Embed Code: