Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቀረበ።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ በዝርዝር በማጣራት የመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደያቀርብ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ባለፉት ዐሥራ አምስት ቀናት ሲያከናውናቸው የሰነበተውን የማጣራት ሥራዎች በማስመልከት ያዘጋጀውን ሪፖርት ዛሬ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል።

አጣሪ ኮሚቴው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአካል ተገኝቶ ማጣራት እንዳይችል የተከለከለ መሆኑን በመጥቀስ መረጃውን ለማሰባሰብ ይቻል ዘንድ ተበዳዮች በስልክ፣በቴሌግራምና በዋትስ አፕ እንዲሁም በአካል በመቅረብ በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ፣በድምጽና በቪዲዮ በተቀረጸ ማስረጃ ጭምር መረጃዎችን ማሰባሰቡን፣መተንተኑን፣ማደራጀቱንና ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጿል።

በሪፖርቱም ከመልካም አስተዳደርና ከብልሹ አሠራር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በማስረጃ ተደግፈው የቀረቡ ሲሆን በማጣራት ሥራው የተረጋገጡ ጉድለቶችንና ጥፋቶችን መሰረት በማድረግም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ችግሮቹን ለመፍታትና የካህናትና የአገልጋዮችን ቅሬታ ዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብለው የቀረቡ  በሰባት ነጥቦች የተተነተኑ  የመፍትሔ ሐሳቦችና በዘጠኝ ነጥቦች የተተነተኑ ችግሮቹንና የመፍትሔ ሐሳቦችን አቅርቧል።

የጥናት ሰነዱ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል።

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ድምፀ_ተዋህዶ
✨✨✨✨✨
@dmtse_tewaedo
@dmtse_tewaedo
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ 3ኛ አመት የAccounting ተማሪ
የሆነችው እህታችን ሀይማኖት ደግፌ ባደረባት ህመም ምክንያት ትምህርቷን መከታተል አልቻለችም ህመሟም የጡንቻካንሰር አይነት ሲሆን በህክምና አጠራሩ Rhabdomiosarcoma ሲሆን ለዚህም በሰርጅሪ ህክምና ተድርጎላት አሁን የ chemotherapy ህክምና እየወሰደች ትገኛለች ቀጥሎም የ Radiotherapy ህክምና ያስፈልግታል ለዚህም ደግሞ የሚያስፈልገው ገንዘብ ሲሰላ ከ 100,000 ብር በላይ ድረስ ያስፈልጋታል ለዚህም እሷም ሆነ ቤታሰቦቹዋ የማሳከም አቅም ስለሌላቸው እናንተ
ወገኖቻችን ወገናዊ እጃችሁን እንድትዘረጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
እባካችሁ እህታችንን በአቅማችን በመርዳት ወደ ቀድሞ ጤንነቷ ተመልሳ ትምህርቷን እንድትከታተል እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።


Haymanot Degife Bosen 1000191370922

በስልክም ማነጋገር ለምትፈልጉ 0986252118


"እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፡ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።" ሐዋ 20:35
መምህራችን መምህር ኤርሚያስ ታሟል።
አንድ ሰላም ለኪ ድገሙለት እግዚአብሔር በጤና ይመልሰው።

ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ፤ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ፤ ማርያም እምነ ናስተበቊዐኪ ፤ እምአርዌ ነዓዊ ተማሕፀነ ብኪ ፤ በእንተ ሐና እምኪ ፤ ወኢያቄም አቡኪ ፤ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ ።

ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ : -
ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ፤ ወትትሐሠይ መንፈስየ ፤ በአምላኪየ ወመድኃኒየ ፤ እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ፤ ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ ፤ እስመ ገብረ ሊተ : ኃይለ ዐቢያተ ፤ ወቅዱስ ስሙ ፤ ወሣህሉኒ : ለትውልደ ትውልድ ፤ ለእለ ይፈርህዎ ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ ፤ ወዘረዎሙ ለእለ የዐብዩ ኅሊና ልቦሙ ፤ ወነሠቶሙ ለኃያላን እመናብርቲሆሙ ፤ አዕበዮሙ ለትሑታን ፤ ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን ፤  ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ለብዑላን ፤ ወተወክፎ ለእስራኤል ቊልዔሁ ፤ ወተዘከረ ሣህሎ ፤ ዘይቤሎሙ ፤ ለአበዊነ : ለአብርሃም ፤ ወለዘርዑ እስከ ለዓለም ፤ አሜን ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ። ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንህነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት። አላ አድኅነነ ወባልሓነ እምኲሉ እኩይ እስመ ዚኣከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰለም ለኪ ቡርክት አንቲ እም አንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ  እግዚአብሔር ምስሌኪ ሰአሊ ወጸልዪ  ምሕረተ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ምህረቱን ይላክሎት መምህር
🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 pinned «#ሥርዓተቤተክርስቲያን!!! #ጥያቄ፡- በቤተ-ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለጋብቻ የሚፈቀደው አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ነው፡፡ እና አንድ ልጅና አንዲት ልጅ ከልብ ተዋድደው ሊጋቡ ነው፡፡ ከመዋደዳቸው የተነሳ ሳይተያዩ ካደሩ ምግብ አይቀምሱም፡፡ ሥራ መሥራት አይችሉም፡፡ ብቻ ስሜት የሚባለው ነገር በጣም ገኖባቸዋል፡፡ በቤተ-ክርስቲያችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል? ነው ወይስ የራሱ እስከሆነች…»
የበጎነት መልስ ከእርሱ ነው።
-
ከጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ጀምሮ  ባጋጠመኝ ድንገተኛ ህመም ምክንያት በሃሌ ሉያ ፣በቤጂንግ ፣በውዳሴ እና በዘበብ ሆስፒታሎች እኔ ለማትረፍ በተደረገው ህክምና ላሳችሁት በጎነት ከእኔ ከታናሹ የሚከፍላችሁ ምንም የለኝ በጎነታችሁን የማይረሳ እርሱ እግዚአብሔር ያክብሪልኝ እያልኩኝ ብፁዓን አባቶቼ እና ወዳጆቼ ሁላችሁም ያለማቋረጥ ስልክ ስትደውሉ የማነሳበት ሁኔታ ላይ ስላልነበርኩኝ ነው ይቅርታ እየጠየኩኝ ነገር ግን ጸሎታችሁ ደርሶልኝ ሃይል አገኝቻለሁ የልጄ አምላክ ረድቶኝ ቀና ብያለሁ።
-ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
መምህር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ ከ ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
Forwarded from đŸŸ˘áŠ“á‰łáŠ’áˆ ፖሮሞሽን🟢
ወዳጄ ሆይ! ድሃ ስለሆንኩኝ ምጽዋትን መስጠት አይቻለኝም አትበል፡፡ ይህ ሰበብና ምክንያት ነው፡፡
ከዚህ የተነሣ (መመጽወት አልችልም ብለህ) የምታዝን ከኾነስ ድህነት ምጽዋትን ከመስጠት እንደማይከለክል እርግጡን እነግርሃለሁ፤ አንተም ስማ፡፡ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም እፍኝ ዱቄት ብቻ ከነበራት ሴት በላይ ድሃ ልትሆን አትችልም /1ኛ ነገ.17፥12/፡፡ ዳግመኛም ሁለት ሳንቲም ብቻ ከነበራት ከመበለቲቱ በላይ ልታጣ አትችልም /ሉቃ.21፥2/፡፡

ይህቺ መበለት ሁለት ሳንቲሞቿን አውጥታ ስትሰጥ የሰጠችው ያላትን ሁሉ ነው (ሌሎቹ የሰጡት ከትርፋቸው ስለሆነ ወደ ቤታቸው ቢመለሱ የሚበሉትና የሚጠጡት አላቸው፡፡ እርሷ ግን የነበራት ሁለት ሳንቲም ብቻ ነውና ስትመለስ እንደ እነርሱ ምንም የላትም)፡፡
በመሆኑም እነዚህ የሰጠቻቸው ሁለት ሳንቲሞች ባለጸጎቹ ከትርፋቸው ከሰጡት እጅግ የበዛ ገንዘብ ይልቅ በብዙ ዕጥፍ የሚበዛ ነው፡፡ መብዛቱ ግን ልቡናዋ ሊሰጠው ከወደደው መጠንና ባሳየችው ቀናዒነት አንጻር እንጂ በጣለችው የገንዘብ መጠን አይደለም፡፡

ስለዚህ አንተም እንደ ዓቅምህ የምትሰጠው ምጽዋት ከአፍአ ሲያዩት ጥቂት ቢመስልም በዚህ ትጠቀማለህ እንጂ አትጎዳም፤ ትንሽ ሰጥተህ ከትርፋቸው ብዙ ከሰጡት ይልቅ ታላቅ የሆነ ዋጋን ታገኛለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ      
✨#ድምፀተዋህዶ âœ¨
                                           
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  đŸ”ş 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
Forwarded from đŸŸ˘áŠ“á‰łáŠ’áˆ ፖሮሞሽን🟢
በትግራይ ክልል የሚገኙ የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ !


ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከትን ሲመመሩ የነበሩት የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ" የተባለው ሕገወጡ "ቤተ ክህነት" ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታውቋል።


በትግራይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እና ገዳማትን በሕገወጥ መልኩ ተቆጣጥሮ የሚገኘው ይኸው ቡድን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከባድ "የቀኖና" እርምጃ እወስዳለሁ ሲል መዛቱንም ከተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ታውቋል።


የትግራይን ሕዝብ ለፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ይህ ቡድን አሁንም በጥፋት ሥራዎቹ የቀጠለ ሲሆን በ"ሕገ ቤተ ክርስቲያን" ስም አንድ ሰነድ ማጽደቁ ነው የተገለጸው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እስከ አሁን የተባለ ነገር ባይኖርም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር።

ዘገባውን ለማሰናዳት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ተጠቅመናል።

             ✨
✨#ድምፀተዋህዶ âœ¨
                 âœ¨                       
Forwarded from đŸŸ˘áŠ“á‰łáŠ’áˆ ፖሮሞሽን🟢
ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል 

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት  አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን  ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)

      
✨#ድምፀተዋህዶ âœ¨
                                           
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  đŸ”ş 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
Forwarded from đŸŸ˘áŠ“á‰łáŠ’áˆ ፖሮሞሽን🟢
ተጠንቀቁ እንጂ አትፍሩ!

አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሃገር ጉዞ ሲደርግ አንድ እጅግ አጥፊ የሆነ አውሎ ነፋስ ወደ እሱ አገር አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ኃይል አውሎ ነፋሱን አስቁሞ፣ “ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ፡፡ ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንዳማታጠፋ ቃል ካልገባህ አታልፍም አለው” አውሎ ነፋሱም፣ “በእርግጥ ነው ወደዚያ አቅጠጫ ነው የምሄደው፤ ነገር ግን የአንተን ሃገር ሕዝብ በፍጹም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለሁ” አለው፡፡

ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካታዎቹ እንደሞቱ ሰማ፡፡ በጣም በመቆጣት አውሎ ነፋሱን ተከታትሎ ደረሰበትና፣ “ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድን ነው ብዙ ሰው የገደልከው?” አለው፡፡ አውሎ ነፋሱም እዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩኝ እንጂ የሃገርህን ህዝብ አንዱንም አልነካሁም፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ነፋስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው”፡፡

አንዳንዴ በሃገራችን ከሚከሰተው ችግር ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከት፣ የሚወርሰን ፍርሃት፣ የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽና የፍርሃትና የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉ የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአአምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፋን፡፡

አንባቢዎቼ በወቅቱ በደረሰብን አስጊ ሁኔታ ስለራሳችንና ስለቤተሰቦቻችን የማሰባችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምክንያት የለሽ ፍርሃት ከመተራመስና ራስን ለከፋ ነገር ከማጋለጥ እንጠበቅ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ንስሐ ገብተን ፣ ቅዱስ ቁርባንን ተቀብለን እንዘጋጅ

ፈጣሪ እናንተንና የእናንተ የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅላችሁ፡፡

✨❤️❤️✨
#ድምፀተዋህዶ
✨❤️❤✨

                                           
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  đŸ”ş 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን

ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት::
የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::
እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኪዎስን ጠራው::
ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ልይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኪዎስ ቤት መዳን ሆነለት::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር::
ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር::በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው::
ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ:: እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::
ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው:: ይሄ ይጎድልብኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር:: እጥረትህ መከበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::
እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያት ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኪዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም:: ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::
እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ነበር::
ግንቦት 23 2014 ዓ ም
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

#ድምፀ_ተዋህዶ

           YouTube channel
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  đŸ”ş 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️ ናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
Forwarded from đŸŸ˘áŠ“á‰łáŠ’áˆ ፖሮሞሽን🟢
#ጥቅምት21 በዚህች ቀን 'ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ' ብሎ ለእመቤታችንን ትንቢት የተናገረላት የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው 

ÂŤ ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ 
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሃሊብ ፀዓዳ»    [ ማኅሌተ ጽጌ ]

ትርጉም

«በመከር ጊዜ አበባ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡»

«የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ. እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ የኤልዳ ነቢዩ ኢዩኤል /ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ብሎ/ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፤ ተፈጸመ፡፡»
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት፡፡ ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን «አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል እውነት ሆኖአል፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ፡፡ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ» በማለት ተናግሮአል፡፡/ዮሐ.4፡37/፡፡ ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ /ለፍሬ/ መድረሱን መናገሩ ነው፡፡ ስለሆነም «ማዕረረ ትንቢት፤ የትንቢት መካተቻ» ማርያም አላት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና «ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች» እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ በአበባ ትመሰላለች፡፡

ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት፡፡ በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ «ወዘመነ ጽጌ እንግዳ፤ እንግዳ የሆነ አበባ» አላት፡፡

ከዚህ በኋላ
«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ነቢየ ኤልዳ፣
ያንጸፍጽፍ እም አድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ፣
ፀቃውዓ መዐር ጥዑም ወሀሊብ ፀዓዳ. . .» በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኀብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጎበኛቸውና ረሀቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ «ብዙ መብል ትበላላችሁ.ትጠግቡማላችሁ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ.ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ.በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጎርፋሉ » /ኢዩ.3.18፤ 2.26/፡፡

«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፤ያንጸፍጽፍ እምአድባሪሁ ወእምእግሪሁ ለይሁዳ ፀቃውዐ መዓር ወሀሊብ ፀዓዳ»፡፡ ይህም ማለት ነቢዩ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ያለው በአንቺ ተፈጸመ ማለት ነው፡፡ ይህም እመቤታችን ክርስቶስን በወለደች ዕለት መሪሩ ጣፍጦ፣ ይቡሱ ለምልሞ ተገኝቷል፡፡ ይህ ለጊዜው ሲሆን ፍጻሜው ደግሞ ከእርሷ በነሣው ሥጋና ደም ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፣ ከልጅነት ተራቁቶ፣ በረሀበ ነፍስና በጽምዓ ነፍስ ተይዞ የነበረውን የሰው ልጅ ከጎኑ ውኃን ለጥምቀት፤ ሥጋውንና ደሙን ምግበ ነፍስ አድርጎ የአምስት ሺህ አምስት መቶውን ዘመነ ረሀብ እንዳስወገደልን ያስረዳል፡፡

ድንግል ሆይ፤  ክብር የክብር ክብር ካለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

      
✨
#ድምፀተዋህዶ âœ¨
                                           
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  đŸ”ş 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
በሶሪያ ኦርቶዶክስ  ያዕቆባዊት ቤተክርስቲያን የሕንድ ሜትሮፖሊታን የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

  ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ እ.ኤ.አ ሐምሌ 22 ቀን 1929 ዓ.ም ቡቸንክሩዝ በተባለ የሕንድ ግዛት የተወለዱ ሲሆን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሼር የምትተዳደረውን የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሊቀ ጵጵስና መርተዋል።

ብፁዕነታቸው በዕድሜና በሕመም ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዕረፍት በማድረግ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አመሻሽ ላይ በሕንድ ኮቺ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጢዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ፣ ለሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለመላው የቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ቀሳውስትና ምእመናን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። 

የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን !!!

© ተሚማ

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://www.tgoop.com/dmtse_tewaedo
ከአባቶች አንደበት
       
      ➕
፩ "ፀሎት የሚያፈቅር ሰው ብታይ
     ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ ፤ ወደ እግዚያአብሔር የሚፀልይ ከሆነ መንፈሳዊነቱን ሞቷል ህይወትም የለውም "
           ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፪ "ፀሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሎአል "
              ማር ይሳቅ

፫ "ፀሎት አእምሮን ወደ እግዚያአብሔር ማቅረብ ነው "
              ማር ይሳቅ

፬ "ፀሎት ፀጋን ይጠብቃል ፤ ቁጣንም ያሸንፋል ትቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል "
                ከአባቶች

✝️፭ "የመንፈስ ፍሬዎች ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም "
          ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፮ "ፀሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግባት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው"
                ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/13 10:16:48
Back to Top
HTML Embed Code: