Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
9819 - Telegram Web
Telegram Web
እንዳያመልጣችሁ ሊያመልጣችሁ አይገባም

     ከብዙ ወራት በፊት እነዚህን ሁለት ወንድሞች በአካል ሳገኛቸው በብዙ ልፋት እና ትጋት ውስጥ ሆነው ነበር ልባቸው ለአንድ አላማ ተሰልፎ የክርስቶስን አምላክነት ፈጣሪነት በመፅሐፍ ለማሳተም ሲደክሙ ተመለከትኳቸው ገና መፅሐፉ ወደ ማተማሪ ቤት ሳይገባ ያነሷቸውን ሀሳቦች ሲያወጉኝ ልቤ ተስፋን ሰነቀ ከዚህ በፊት በእስልምና  የእቅበተ እምነት ተከራካሪዎች ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄ በሚደንቅ ሁኔታ ምላሾችን ሲነግሩኝ ስለ እነርሱ አምላኬን አመሰገንኩ ። ወንድም ብሬ እና አቡ ወጣትነታቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ዘመን ባፈራው የቴክኖሎጂ አገልግሎት በብዙ የሚያገለግሉ ብርቱዎች ናቸው ። የብዙ ጊዜ ልፋታቸው የማይደገሙ ምላሾችን የያዘው ድንቅ መጽሐፋቸው በቲክቶክ መንደር በአቡ ቤት ይመረቃል ።


 ከዘማሪ ዲ/ን ሰለሞን አቡበከር ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ
#ድምፅ ተዋህዶ
#ሰውን_ወዳጁና_ርህርሁ_እግዚአብሔር

ሰው ጨካኝ ሲሆን #እግዚአብሔር ግን ሁሉን የሚወድ ቸርና ርህርህ ነው፡፡ ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ከሦስቱ ቅጣቶች መካከል አንዱን እንዲመርጥና አማራጩ ሲቀርብለት የተናገረው ቃል ድንቅ ነው፡፡ " ምህርቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፡፡" 2ኛ ሳሙ 24 ፥ 14፡፡ ጻድቁ እዮብም በሦስቱ ባልደረበቹ እጅ በወደቀ ጊዜና እነርሱም እርሱን መውቀሳቸውን ባላቋረጡ ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው ፡- "ነፍሴን የምትነዘንዙ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ይኸውም ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፡፡" ኢዮ 19 ፥ 2 - 3፡፡ #እግዚአብሔር ግን ከሰው በእጅጉ በተለየ መልኩ መሐሪና ርህርህ መሆኑን በሚከተሉት ውስጥ እንመለከታለን፡፡

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

#ድምፀ_ተዋህዶ
↗️ለወዳጆ ሼር ያድርጉ
https://www.tgoop.com/dmtse_tewaedo
🥰 ❤️‍🔥❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📚አዲስ መፅሐፍ ምረቃ

✝️ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል የተሰኘውን መጽሐፍት ሊያስመርቁ ነው

🫡ጥቅምት 2️⃣/2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣ዓ.ም በቦሌ መድኃኔዓለም አዳራሽ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ

መጽሓፉ 📚
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ:
1•የእመቤታችንን  ሕይወት  የያዘ ሙሉ የነገረ ማርያም  አስትምህሮ
2•በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ
3•ዕርገቷን የሚመለከቱ
4•እመቤታችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች
5•በእመቤታችን ፍቅር እንዴት መጽናትና ማደግ ይቻላል

የሚሉትን ዓበይት ጉዳዮች የሚተነትን ነው

628 ገጾች
12 ምእራፎች አሉት
✝️✝️✝️
#ድምፀ_ተዋህዶ
https://www.tgoop.com/dmtse_tewaedo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✝️ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ✝️ ይመክራል፦"
ደስታና ሰላምን የሚነጥቁ ሦስት የሰይጣን ወጥመዶች አሉ፦
➡️ስላለፈው መጸጸት፣
➡️ስለሚመጣው መጨነቅ እና
➡️ ስለ ዛሬው አለማመስገን ናቸው"

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ድምፀ_ተዋህዶ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት የተገነባው  ዘመናዊ ስቱዲዮ   በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው "ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር "ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት'  ቡራኬ ተመረቀ።
በመዝግጅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ከመላው ዓለም ለ43ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የተሰባሰቡ ልዑካን ተገኝተዋል ።
ስቱዲዮው አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለት ሲሆን በተጨማሪም በስቱዲዮው የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎች እና የግንኙነት ካሜራ ተሟልቶለታል። የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል ያለው ሲሆን ግንባታው ባለፉት ከ2 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ዘመናዊ መሣሪያዎች ከውጪ ሀገራት ተገዝተው ተገጥመውለታል።
በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መስራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ድርጅቱ በሚያሠራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተውጽኦ እንደሚያመጣ ተገልጿል።

#ድምፀ_ተዋህዶ
ንስጥሮስ ሆይ …እወድሃለው…እጠላሃለው

ክርስቶሳዊ ፍቅር ማለት ሰውን ከሰውነቱ እስከ ኃጢያአቱ መውደድ ነው ። እንደ ጌታ ካሰብክ ሰውን ኃጥእ ፃድቅ ሳትል በሰውነቱ ብቻ ትወደዋለህ ። ይይህን ይነት መወደድ ቢከብድም ክርስቶሳዊ ፣ ቅዱሳዊ መውደድ ነው ። ጌታችን አጢያአተኞችን ሳይሆን አጢያትን ነው የሚጠላው ። ዘማዊ ቤሆን/ብትሆን/ ዝሙትን/ዋን/ ጥላ እንጂ ዘማዊ ነው /ናት/ ብለህ ሰውዬውን /እሷን / አትጥላ ።

ሌባ ቢሆን ሌብብነትን ጥላ እንጂ ሌባ ነው ብለህ ሰውዬውን አትጥላ። ሰካራም ቢሆን መጠጥን ጥላ እንጂ ጠጪውን አትጥላ ። ውሸታም ቢሆን ውሸትን ጥላ እንጂ ዋሸ ብለህ ሰውዬውን አትጥላ ። ንፉግ ፣ ተሳዳቢ፣ ነገረኛ ፣ ምቀኛ ፣ ጠንቋይ አስጠንቋይ ፣ ዘረኛ ፣ መተተኛ ፣ እምነተ ቢስ ፣ አጭበርባሪ ፣ ከዳተኛ ፣ወዘተ ቢሆን  መጥፎ ተግባሩን ጥላ እንጂ ሰውዬውን አትጥላ ። ቅዱስ  ቂርሎስ የክርስቶስን መለኮትነት ፣ የእመቤታችንን የአምላክ እናትነት የካደው ንስጥሮስን ፣ ንስጥሮስ ሆይ አንተን እወድሃለሁ ኑፉቄህን ግን እጠላለሁ" በማለት ሰውን ተግባሩን እንጂ ሰውነቱን መጥላት እንደ ሌለብን ተናግሯል ።

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://www.tgoop.com/dmtse_tewaedo
🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 pinned «ንስጥሮስ ሆይ …እወድሃለው…እጠላሃለው ክርስቶሳዊ ፍቅር ማለት ሰውን ከሰውነቱ እስከ ኃጢያአቱ መውደድ ነው ። እንደ ጌታ ካሰብክ ሰውን ኃጥእ ፃድቅ ሳትል በሰውነቱ ብቻ ትወደዋለህ ። ይይህን ይነት መወደድ ቢከብድም ክርስቶሳዊ ፣ ቅዱሳዊ መውደድ ነው ። ጌታችን አጢያአተኞችን ሳይሆን አጢያትን ነው የሚጠላው ። ዘማዊ ቤሆን/ብትሆን/ ዝሙትን/ዋን/ ጥላ እንጂ ዘማዊ ነው /ናት/ ብለህ ሰውዬውን /እሷን / አትጥላ…»
ድክመቶቼን ማወቄ ምንድነው የሚጠቅመኝ? ካልን አንድ ሰው ድክመቶቹን ካወቀ እግዚያአብሔርን ያውቃል።"ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና"፪ኛ ቆሮ ፲፪፡፲። ኃጢአቴ ምን ያህል አስነዋሪ እንደሆነ ሳረጋግጥ የእግዚያአብሔር ፀጋ እሻለሁ። ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲ ብሏል "ጌታ ሆይ እኔ ኃጢያአተኛ ነኝ እና ከእኔ ተለይ" ሉቃ ፭፡፰። ቅዱስ ጴጥሮስ ምናይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ተሰምቶታል ። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው "አትፍራ ከህንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"ሉቃ ፭፡፲ ቅዱስ ጴጥሮስ ለታላቅ ተልእኮ እና አገልግሎት የበቃው መቼ ነበር ? ይህ የሆነው ራሱን ባወቀ ቅፅበትና "እኔ ኃጢያአተኛ ነኝ " ብሎ በተናገረ ጊዜ ነበር ። የሰው ልጅ በእንህ ዓይነት ስሜ ውስጥ በሆነ ጊዜ እግዚያአብሔር እንዲህ ይላል።
"አትፍራ ከእንግዲ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ" ። ስለዚህ እራሳችንን ማወቅ ማለት እግዚያአብሔርን ማወቅ ማለት ነው ።

የሕይወት መዓዛ ከሚለው መፃሐፍ የተወሰደ '

#ድምፀ_ተዋህዶ
⚡️⚡️⚡️
@dmtse_tewaedo
@dmtse_tewaedo
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/14 08:25:33
Back to Top
HTML Embed Code: