Telegram Web
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ነገ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም
(Nov 24/2024 G.C) ይገባል፡፡
“አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል" / ኤፌ 5÷14/

ወዳጆቼ ብዙዎቻችን ስልክ ስናወራ ሳንቲሜ ቆጠረ እንጂ ዕድሜዬ ቆጠረ አንልም ከዕድሜው ይልቅ ለሳንቲም ዋጋ እንሰጣለን። በስልክ ከወዳጆቻችን ጋር የምናወራውን ያክል እንኳ ከፈጣሪያችን ጋር ማውራት ሸክም ሆኖብናል።

በመንፈሳዊ ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት በፕሮግራም ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው መኋዝ ያለብን።  ነገ እጀምራለው ነገ ይህን አደርጋለው እያልን ቆጠሮ ብንሰጥ ትርፉ መሰላቸት ነው ማድረግ ያለብንን ዛሬ አሁኑን እንጀምረው። የእግዚአብሔር ፈቃዱም አሁኑኑ እንድንድን ነው።

ነቢያት ስላልመጣው ዘመን ያውቁ ነበር ፤ እኛ ግን የምንኖርበት ዘመን ምንነት እንኳ ተሰውሮብናል። ሐዋርያት ሄደው ዓለምን ዞረው ይሰብኩ ነበር ፣ እኛ ግን በተመቻቸ ቦታ መጥታችሁ ተሰበኩ እንላለን። ሰማዕታት ለክርስቶስ ፍቅር ሞቱ ፣ እኛ ግን ለጥቅማችን ፣ ለምኞታችን ፣ ለኃጢያታችን እንሞታለን። ጻድቃን የዚህን ዓለምን ጣዕም ንቀው መነኑ ፣ እኛ ግን ዓለም መራራ ሆናብንም እንኳ ደግመን ደጋግመን እንፈልጋታለን።

ቅዱሳን አባቶቻችን ከሕግ አልፈው በትሩፋት ኖሩ ፣ እኛ ልጆቻቸው ግን የታዘዝነውን እንኳ መፈጸም ተስኖናል። ደናግል መነኮሳት የክርስቶስ ሙሽሮች ሆኑ ፣ እኛ ግን በአንድ ሃይማኖታችን ጸንተን ክርስቶስን መከተል (ማምለክ) አቅቶናል። ሊቃውንት አባቶቻችን አህያ እንኳ የማትሸከመውን መጽሐፍ በቃላቸው አጠኑ ፣ እኛ ግን አንድ ጥቅስ ለማጥናት ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን።

ጌታ ሆይ እባክህን እኛን እንቅልፋሞቹን ከእንቅፋችን አንቃን !


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  https://www.tgoop.com/dnhayilemikael
እንኳን ለአባ ሳሙኤል ዓመታዊ እረፍት በዓል ለዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ ።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክቡር የሚሆን የወንጌል ቃል እንሰማ ዘንድ እንሳለመው ዘንድ በእርሱም ደስ ይለን ዘንድ በዚህ የበቃን ያድርገን  ሁሉን የያዘ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ለአንተ ምስጋና ይገባል ዳግመኛም ክቡር የሚሆንን የወንጌልን ቃል በልቦናችን ትጽፍ ዘንድ እንለምንሃለን እንማልድሃለንም
❖ ወዳጄ እስኪ ልጠይቅህ፤ አንተም አንቺም መልሱልኝ!

ጌታችን ዛሬ ቢመጣ የምትመልሰው የምትመልሺው መልስ ምንድን ነው

✍️"ንስሐ ያልገባሁት፣ ሥጋ ወደሙን ያልተቀበልሁት፣ ምግባር ትሩፋት ያልያዝሁት ዕድሜዬ ገና ነው ብዬ አስቤ ነው፤ ሥራ በጣም በዝቶብኝ ስለ ነበረ ጊዜ አጥቼ ነው፤ ዛሬ ነገ እያልኩ እየረሳሁት እንጂ እንደዚያ ማድረግ አቅቶኝ አልነበረም"

ምክንያትህ እነዚህ ናቸው
እኅቴ! ሰበቦችሽ እነዚህ ናቸው

❖ በዚያ ሰዓት ግን እነዚህ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፤ እናት ልጇን በማታድንበት ሰዓት እነዚህ ምክንያቶች ምንም አይረቡም፡፡

ታዲያ ለምን ትዘገያለህ
እኮ ለምን ትዘገያለሽ
ያኔ ዋይ ዋይ ከምትዪ... ያኔ የማይጠቅም ጸጸት ከምትጸጸት ለምን ዛሬ አትጠቀምበትም
ለምን ራስህን አታድንም

📌 ምንጭ
✍️ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ራስን ዝቅ ስለማድረግ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

እጅግ የምወዳችኁ ልጆቼ! ምንም ያኽል የምግባር ማማ ላይ ብንወጣም ከኹሉም ይልቅ ጐስቋሎች እንደኾንን ልናስብ ይገባናል፡፡ ትዕቢትን ከልቡናችን ነቅለን ካልጣልን በቀር ምንም መንበረ ጸባዖትን ብንደርስም ጠልፎ እንጦርጦስ ይወረውረናል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለኁ፡፡

ዳግመኛም ትሕትናን በልቡናችን ውሳጤ የምናኖር ከኾነ ምንም ያኽል በኃጢአት ሸለቆ ብንወድቅም መንበረ ጸባዖትን ታደርሰናለች ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለኁ፡፡ ከፈሪሳውያን ይልቅ ቀራጮች በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ያገኙት ልበ ትሑታን ስለነበሩ ነው፡፡ ትዕቢት፣ ልቡናንም ከፍ ከፍ ማድረግ ከዲያብሎስ ይልቅ የከፋን እንኾን ታደርገናለች፡፡ ፈያታዊ ዘየማን ከሐዋርያት አስቀድሞ ገነት የገባው ልበ ትሑት፣ ኃጢአቱን ዐውቋት ይናዘዛት ስለነበር ነው፡፡ ኃጢአታቸውን ዘወትር የሚያስቡ ደግሞም የሚናዘዝዋት ሰዎች ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡

ምንም ያኽል በጐ ምግባር እንደሠሩ የሚያውቁ፥ ነገር ግን ምንም በጐ ምግባር እንዳልሠሩ ኾነው ልቡናቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉ ሰዎች ሹመት ሽልማታቸው እንዴት የበዛ ይኾን? ኃጢአተኛ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው በትዕቢት ከተያዘ ጻድቅ ሰው ይልቅ ንዑድ ክቡር ነው፡፡ እንግዲኽ ኃጢአተኛ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው ይኽን ያኽል ንዑድ ክቡር ከኾነ፥ ጻድቅ ኾኖ ሳለ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሰው ደግሞ ከዚኽ ይልቅ እንዴት ይከብር ይኾን? የምግባሩ መዓዛ፣ የትሩፋቱ በጐ ጠረን እስከየትኛው ሰማይ ይወጣ ይኾን? አዎ! የዚኽ ሰው የምግባሩ ዕጣን መንበረ ጸባዖት ይደርሳል፡፡ በእውነት ያለ ጥርጥር በማዕከለ ሠራዊተ መላእክት ይገባል፡፡

ከዚኹ በተቃራኒ በበጐ ምግባር ያጌጠ ሰው ትዕቢተኛ በመኾኑ ብቻ ይኽን ያኽል ጉዳት የሚያመጣበት ከኾነ፥ በኃጢአት ዐዘቅት ተዘፍቀው ሳሉ ትዕቢትን የሚጨምሩ ሰዎች እንደምን ይዋረዱ ይኾን?

የምወዳችኁ ልጆቼ! ይኽን ኹሉ የምላችኁ በጐ ማድረግን ቸል እንል ዘንድ አይደለም፤ ከኹሉም አስቀድመን ልቡናን ከፍ ከፍ ማድረግ አስወግደን ልበ ትሑታን እንኾን ዘንድ ስለምሻ ነው እንጂ፡፡ ትሕትና የጥበብ ኹሉ መሠረት ናት፡፡ ምንም ያኽል በጐ ምግባር ቢኖረን፣ ምጽዋትም ቢኾን፣ ጸሎትም ቢኾን፣ ጾምም ቢኾን፣ ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ምግባር ቢኖረን የእነዚኽ ምግባራት መሠረት የሚኾን ትሕትናን ካልያዝን ቤታችን በአሸዋ እንደተሠራ ቤት ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ እነዚኽ በጐ ምግባራቶቻችን ያለ ትሕትና ብቻቸውን መቆም አይችሉም፡፡ ምንም ያኽል ትዕግሥተኞች ብንኾን፣ ደናግላን ብንኾን፣ ፍቅረ ንዋይ የጠፋልን ብንኾን፣ ሌላም እናንተ የምትጠቅሱት በጐ ነገር ቢኖረን ትሕትና ግን ከሌለን እነዚኽ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ንጹሐን መሥዋዕቶች አይደሉም፡፡

ስለዚኽ እጅግ የምወዳችኁ ልጆቼ! በቃላችንም፣ በግብራችንም፣ በሐሳባችንም ትሕትናን ገንዘብ እናድርግና ከላይ የጠቀስናቸውን በጐ ምግባራት በርሷ መሠረትነት እናንፃቸው (እንገንባቸው) ብዬ እማልዳችኋለኁ፡፡
"ስለ ሰርግ ቀን" የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ወጣቶች ትዳራቸው፥ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኾንላቸው ከፈለጉ ከኹሉም አስቀድመው ሊያደርጉት የሚገባቸው ልክ እንደ ቃና ዘገሊላው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጋቸው ዕለት እንዲገኝ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰርጋቸውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ማከናወን ማለት ነው፡፡

ሊቁም ይህን አስመልከቶ ሲናገር እንደዚህ ይላል፡- “ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በመገኘትና ጸጋውን በመስጠት ሰርግን ቀድሷል፡፡ ሌሎች ይረባል ይጠቅማል ብለው ካመጡት ስጦታ ይልቅ ከፍ ያለ ስጦታ ይዞ በመምጣት ይኸውም ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ ሰርግን አክብሯል፡፡ … ስለዚህ የዲያብሎስ ትርኢትን በማምጣት ጌታችን ያከበረውን ሰርግ አናቃልል፡፡ ወደ ትዳር የሚገቡ ሰዎችም በቃና ዘገሊላ በተደረገው መልኩ ያግቡ፡፡ በመካከላቸው ክርስቶስ እንዲገኝ ያድርጉ፡፡ ‘ይህንንስ እንዴት ሊያደርጉ ይችላሉ? ጌታችን ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በአካል እንደ ተገኘ ዛሬም መገኘት ይችላልን?’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ አዎ! ካህናትን ይጥሩ፡፡ ጌታችን ‘እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል’ በማለት ተናግሯልና (ማቴ 10፥40)፡፡

እንደዚህ በማድረግ ዲያብሎስን ያርቁት፦
  ➛ ጸያፍ ዘፈኖችን፣
  ➛ ርኵሳን ሙዚቃዎችን፣
  ➛ ሥርዐት የለሽ ውዝዋዜዎችን፣
  ➛ አሳፋሪ ንግግሮችን፣
  ➛ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣
  ➛ ወሰን የለሽ ሁካታዎችንና ሳቆችን፣
እንደዚሁም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነውርን የተሞሉ ድርጊቶችን ያርቁ፡፡ ከእነዚህ ይልቅ የክርስቶስ አገልጋዮችን ይጥሩ፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋቸው ይገኛል፤ ይታደማልም፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ የተወሰደ)
ማን ያስተምር? አንበቡት ታተርፉበታላችሁ።

መምህራን በ3 ይከፈላሉ

ኀጥአን መምህራን ፣ከሀድያን መምህራንና ደጋግ መምህራን ይባላሉ። የመጀመሪያዎቹ ኀጥአን መምህራን በሥጋ የደከሙ በኀጢአት የዛሉ ከጸሎት የሰነፉ ከአርዓያነት የራቁ ናቸው። እምነትና እውቀት ግን ያልተወሰደባቸው ማለት ነው። ፈጽሞ አይጸልዩም አይጾምም ማለታችን ግን አይደለም። በአዋጅ ሕግ ይገዛሉ በዶግማ በቀኖና ጸንተው ቢኖሩም በሕይወት ምሳሌ መሆን በአርዓያነት መጠቀስ ግን አይችሉም።

እነዚህ መምህራን ኀጠአን ቢሆኑም።ሰው ኀጢአት እንዲሰራ በአደባባይ አይሰብኩም በእግዚአብሔር ፊት ቢወድቁም ፈጽሞ ሕዝብ አያሰናክሉም።

በዓርዓያነት የሚጠቀስ ግብር ባይኖራቸውም ኀጢአትን አያደፋፍሩም።በድካማቸው ይሰቀቃሉ።

ያስተማሩትን ባለመኖራቸው ይጨነቃሉ።

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከነዚህ መምህራን ቃሉን እንድንማር ከሕይወታቸው ደግሞ እንዳንማር አዞናል።

ስለምን ቢሉ

ለሰው የሚተርፍ ሕይወት የላቸውምና።

ቃሉን ግን እንዳያስተምሩ አልከለከላቸውም። ጸጋቸው ጨረሶ አልተገፈፈም። በጊዜው ለራሳቸው የማይጠቀሙ ቢሆኑም ሕዝቡን ለማዳን የቃሉ ማስተላለፊያ ያደርጋቸዋል። ከበሽተኛ ዶክተር መታክም እንደማይከለከል የዶክተሩም በሽታም መድኀኒቱ እንደማይበክለው ሁሉ ድክመታቸው ቅዱስ ቃሉን አያረክሰውም።

ባይመለሱ ጸጋቸውን ገፎ ከአገልግሎት ያርቃቸዋል።

እግዚአብሔር እስከተጠቀመባቸው ድረስ ግን እኛም እንጠቀምባቸዋለን። እግዚአብሔር ሲከለክላቸው ደግሞ እንከለከላለን።

እነርሱ የግል ኀጢአተኛ ስለሆኑ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ አይረክስም።እግዚአብሔር የዓለምን ድኅነት በቀያፋ በበለዐም አድሮ የእስራኤል ተስፋ ሲናገር እንደሰማነው ሁሉ።

አገልጋዩ የበቃ ባይሆን ራሱ ይከስማበል እንጅ የሌላውን መዳን አይከለክልም።

2ኛዎቹ ከሐዲያን መምህራን ይባላሉ።

እነዚህ በራሳቸው ማስተዋል የተደገፉ በራሳቸው መጠበብ የእግዚአብሔርን ቃል ያለአግባብ ተርጉመው የሚያስተምሩ ነውራቸውን እንደወንጌል የሚሰብኩ ቃሉን በአደባባይ የሚክዱ ናቸው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሐዋርያትን ሰብስቦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ ሲላቸው ከትምህርታቸው ራቁ ማለቱ ነው። ዛሬ ዛሬ ከንፉቃን መምህራን ሕይወትን ከክሀድያን መምህር እውቀትን ለመሸመት መጣጣር መርዝ በማር በጥበጦ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው እንደማለት ይቆጠራል።

በታጠበ ትሪ በተቀመመ ወጥ በተዋበ እንጀራ ቢቀርብም መርዝ መድኀኒት አይሆንምና።ከጥርጥር ሐሳባቸው ከሚበርዝ ተልኳቸው መጠበቅ የክርስቲያን ሁሉ ግዴታ ነው።

3ኛዎቹ እንደወርቅ የተፈተኑት ደግሞ ደጋግ መምህራን ይባላሉ።እነዚህ ደጋግ መምህራን እውቀታቸው እውቀትን ሕይወታየው ሕይወትን እየወለደ በእልፍ የሚባዙ የቃሉ ምሥክር ገድላት ናቸው። ከሚያስተምሩት የሚኖሩት ይበልጣልና ብዙውን በሕይወታየው ጥቂቱን በቃላቸው ያስተምራሉ። እነዚህን መምህራን ፈልጎ ያገኘ ነፍሱ ትረካለች ሕይወቱ ትቀደሳለችና ከሚኖሩበት ገዳም ከሚያስተምሩበት ጉባዔ ድረስ ተጉዞ በረከታቸውን መቀበል ምርቃታቸውን ማግኘት ያስፈልጋል።
ቅዱስ እግዚአብሔር ደጋግ መምህራን አያርቅብን።በያሉበት በረከታየው ይድረሰን።

https://www.tgoop.com/dnhayilemikael
ጾም፦
🍂ጾሞ የመልአካዊነት ግብራችን መገለጫ ናት።
🍂ጾም የነፍስ ምግብ የሥጋ ደግሞ መስልብ ናት።
🍂 ጾሞ የመንግሥተ ሰማያት ኑሮን በምድር ላይ መጀመሪያ ናት።
ጾም የተዐቅቦ መለማመጂያ፣የቅድስና መሰላል ናት።
🍂 ጾም የፍትዎት ማጥፊያ የተስፋ ወንጌል ግን ማለምለሚያ ናት።
🍂ጾም የጸሎት እናት የአርምሞ እኅት የዕንባም ነቅዕ ናት
🍂ጾም የኃይለ ነፍስ የተፈጥሮ ነፍስ መገለጫ ናት
🍂ጾም የደፈረሰ ህሊና ማጥሪያ ናት።
🍂ጾም የቃለ መጽሐፍ መፈጸሚያ ናት
"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም።"ማቴ.፬፥፬ እንዲል።
https://www.tgoop.com/dnhayilemikael
🙏🙏🙏🙏ለሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ጸሎት መጸለይ ለምን እንደሚከብድህ ታውቃለህ?

ወንድሞች በአንድ ወቅት አባ አጋቶንን ጠየቁት፤ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት (ድካም) ይጠይቃል?”። እርሱም መለሰ “ይቅርታ አድርጉልኝ፣ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከመጸለይ የበለጠ ከባድ ሥራ ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ለመጸለይ በፈለገ ጊዜ ሁሉ፣ ጠላቶቹ አጋንንት እንዳይጸልይ ሊከለክሉት ይሻሉ፤ ከመንገዱ ሊያደናቅፉት የሚችሉት ከጸሎት እንዲርቅ ሲያደርጉት ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። ሰው ማንኛውንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠራ፣ በሥራውም ቢጸና እረፍትን ያገኛል። ጸሎት ግን እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ [እረፍት የሌለበት] ውጊያ ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ውጊያ ከሰው ሳይሆን ከአጋንንት ነው እና ሁላችሁንም የሱን ጦር ሚያርቁልንን ጾም ጸሎት በማድረግ ሚከላከሉልንን መላእክት ማቅረብ አለብን ።
2025/02/23 22:28:00
Back to Top
HTML Embed Code: