Telegram Web
ተደጋግሞ ሲነገር ውሸት እንደሆነ ያሳብቅ ካልሆነ ህዝቡ በቀን ተቀን ህይወቱ ምን ያህል ፍዳውን እየበላ እንደሆነ ያውቃል።

@EliasMeseret
በጅማ ከተማ በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን እና  ህዝቡ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ “እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው’ ያለው” በማለት ጠ/ሚሩ ያሰፈሩትን ሀሳብ አየሁ።

የጅማ ህዝብ ደግሞ ባለፈት ሶስት ወራት በግሌም፣ በመሠረት ሚድያ በኩልም ሲያሰማ የነበረውን ጩኸት ከታች በምስሉ ላይ ተመልከቱ ⤵️

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ የሰራቸው ዜናዎች:

1. https://www.tgoop.com/meseretmedia/282

2. https://www.tgoop.com/meseretmedia/516

@EliasMeseret
#FactCheck የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በርካታ ታዳጊዎች ከመንገድ እየታፈሱ ወደ እርሻ ጣቢዎች በግድ እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፁ ይታወቃል

"እርሻዎቹ የት ይሆኑ?" ብላችሁ ለጠየቃችሁ እና ማጣራት ለምትፈልጉ፣ ዋና መዳረሻው በሚድሮክ ሆራይዘን ፕላንቴሽን ስር የሚተዳደረው የበበቃ ቡና እርሻ ልማት ነው። "ሚድሮክ ፈቅዶ ነው ወይ ተገዶ ነው?" ለሚለው ምላሽ ቢሰጥበት ጥሩ ነው።

ሚድሮክ በዚህ ዙርያ አስተያየት እንዲሰጥ ደጋግሜ ብጠይቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል፣ ህዝብ ግን ልጆቹ የት እየተወሰዱ እንደሆነ የማወቅ መብት አለው።

በነገራችን ላይ ታፍሰው እየተወሰዱ ያሉት የጎዳና ላይ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ እንደ ሊስትሮ፣ ፍራፍሬ መሸጥ፣ የጉልበት ስራ በመስራት፣ መኪና በማጠብ ወዘተ የሚተዳደሩ እና ቤተሰብ ያላቸው ልጆች ጭምር ናቸው።

@EliasMeseret
ከሁለት ኢትዮጵያዊ አንዱ፣ ወይም 60 ሚልዮን ገደማው ኤሌክትሪክ አያገኝም

መንግስት 13 ሀገራትን በኤሌክትሪክ ለማስተሳሰር እየሰራ ነው።

@EliasMeseret
የተፈጠረ ብዥታ የለም፣ ህዝቡ ሊደረግ የታሰበው ገብቶት ነው

እንደ አንድ የመንግስት የመረጃ ምንጭ፣ በሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ይህን ህግ በመጠቀም እስከ 60 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ (ለመዝረፍ) ታቅዷል።

@EliasMeseret
500 ሺህ የፌስቡክ ወዳጅ 🙏🏽

@EliasMeseret
የጉልበት ስራ ሰርቼ ይቺን ቀን ሳይርበኝ ባሳልፍ ብሎ በየመንገዱ የሚንከራተት የሀገሬ ወጣት እየታፈሰ የሚደርስበት የግፍ ፅዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው

@EliasMeseret
ክፉ ግዜ!

ነፍስ ይማር!

@EliasMeseret
መቼም በአጥር ሾልካ ገብታ ወይም በፓራሹት ወርዳ አይሆንም፣

ይህ እንደ አንድ ተራ ክስተት ብቻ ሊወሰድ አይገባም፣ አመራሩ ሳያውቅ እንዲህ አይነት ድርጊት በሀላል የሚፈፀም ከሆነ የኤርፖርቱ ግቢ ደህንነት ምን ያህል አስተማማኝ ነው የሚል ጥያቄንም ያጭራል።

@EliasMeseret
እስከዛሬ የሚፅፉት እና የሚናገሩት ስለኢትዮጵያ መስሎኝ የሰጠሁት አስተያየት ቆጨኝ

ለካ ስለሌላ ሀገር ነው 🤔

@EliasMeseret
#FakeNewsAlert አልጀዚራ እንደዚህ ብሎ አልዘገበም፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የአቶ ሙላቱ ተሾመን አስተያየት ግን ዛሬ አቅርቧል

ሊንክ: https://www.aljazeera.com/opinions/2025/2/17/to-avoid-another-conflict-in-the-horn-of-africa-now-is-the-time-to-act

- 'እርቅ' የተባለው ነገር ሲመጣ ኤርትራ ሀገሯ እንዳልገባ ከዛ ሁሉ ሚድያ ለይታ አገደችኝ፣

- የእኛው መንግስት ደግሞ ኤርትራን ጋብዞ የትግራይን ህዝብ ሲያስፈጅ እና ዜና ስሰራ 'ውሸት ነው፣ የኤርትራ ሀይል አልሀገባም፣ ሀገር ለማተራመስ የባንዳ ስራ ነው' ብሎ ፈረጀኝ

Now this!

@EliasMeseret
2025/02/19 03:44:28
Back to Top
HTML Embed Code: