Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+++ የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት ++
       
አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ እንጅ የምፈጽም ባለመሆኔም ምክንያት በድቡሽት ላይ እንደተሠራ ቤት ሆኛለሁ።

ጥልቀት በሌለው አኗኗር ላይ የተገነባው መንፈሳዊነቴ ጎርፍ በጎረፈ፣ ነፋስ ባለፈ ጊዜ የሚናወጥ ደካማ ሆኖብኛል።
ዓለምን ለማሳለፍ ዳግመኛ መምጣትህን ባሰብሁ ጊዜ እደነግጣለሁ።

ጻድቃን “አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና” እያሉ የምትመጣበትን ቀን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሴት በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ እኔ ግን አሁንም ለንስሐ ዕድሜ እንድትጨምርልኝ እለምናለሁ።

በተራራው ስብከት ጊዜ ተገኝቼ ስታስተምር ባልሰማህም፤ በደብረ ታቦር በተገለጥህ ጊዜ ክብርህን ካዩት መካከል ባልሆንም፤ በደብረ ዘይት እጅህን ጭነህ ከሾምኻቸው ውስጥ ባልመደብም አንተ ግን ለእኔ ምሕረት ማድረግን አትሰለችም። ወደ አንተ ባልመጣ እንኳን በተኛሁበት መጥተህ “ልትድን ትወዳለህ?” ማለትህ አይቀርም።

ከሰማይ የወረድህልኝ ሆይ! ኢያሱ ለእስራኤል ርስታቸውን እስኪያወርሳቸው ፀሐይን እንዳቆምህለት በምድር ላይ ያለን ኃጥአን ልጆችህ ሰማያዊት ርስትህን ሳንወርሳት ፀሐይ አትጥለቅብን፤ ዕድሜአችን አይለቅብን።  አሜን!

( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

https://www.tgoop.com/eotcy
ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት)

ኒቆዲሞስ የዐብይ ሰባተኛ ሰንበት !!

ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)

በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ­ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሃ ፫፤፪

ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?

፩/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል ብትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

‹ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሃ ፱፤፬

፪/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን

‹ፍጹምፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ዮሃ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።

፫/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል

‹ በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫

አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።


፬/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና

‹ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።


፭/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድረስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።

መዝሙር

ሖረ ኅቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሉ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅንሕነ ነአምነ ብከ . . . . . . . .

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ 7:1-14 „ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ።በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም። እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ። አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤ ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤ ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል። ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት። እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር። ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ።“1ኛዩሐ 4:18 –ፍፃሜ „–ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን። “
https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ"

(ሽራፊ ሃሳብ 1 ከኒቆዲሞስ ምንባብ)

ኒቆዲሞስ በውድቅት ሌሊት ወደ ጌታችን መጣ። ሌሊት እንግዲህ በቂ ብርሃን የሌለበት ፣ እንቅፋት የሚበዛበት ፣ ጭልም የሚልበት ፣ ግራ ቀኝ ቢያዩ ሰው የሚታጣበት ፣ ማጅራት ከሚመቱ ወንበዴዎች በቀር በመንገድ ሌላ ሰው የማያጋጥምበት ፣ ብርድና ቆፈን ሰውነትን የሚያስጨንቅበት ሰዓት ነው። ይህ የአይሁድ መምህር በሌሊት የመጣበት ምክንያቱ ብዙ ሲሆን ለእምነት ማነስ ማሳያ የሚሆን ሰው ነው።

ዛሬ ደግሞ ለአፍታ ኒቆዲሞስን "በሌሊት ወደ ኢየሱስ በመምጣቱ" በጥቂቱ እናመስግነው።  ብዙ እግሮች ወደ ኃጢአት በሚሮጡባት ሌሊት ወደ ክርስቶስ የሮጠውን ይህንን ሰው እስቲ እናድንቀው!  ይህንን የሌሊት ግርማ ሳይበግረው ወደ ኢየሱስ የተጓዘ የጨለማ ተጓዥ ፣ ይህንን ሰዓታት ቋሚ ፣ ይህንን ማሕሌት ቋሚ በጥቂቱ ብናመሰግነው ምን አለ? ከጌታ ፊት ቆሞ ቅኔ የተመራውን ፣ ስለ ልደት እየተናገረ ስለ ጥምቀት የሚያመሰጥረውን የፈጣሪን ቅኔ ተቀብሎ ሊያዜም ከጀመረ በኋላ መቀበል ሲያቅተው ጌታችን  "አንተ የአይሁድ መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን?" ብሎ የገሠፀውን ኒቆዲሞስን እስቲ ዛሬ በበጎነቱ አርኣያ እናድርገው።

በሕይወታችን ውስጥ የተስፋ ብርሃን ጭልም ባለብን ጊዜ ፣ እንቅፋት በበዛብን ወቅት ፣ ግራ ቀኝ አይተን ሰው ባጣንበትና ብቸኝነት በዋጠን ሰዓት ፣ ክፉ ከማድረግ በማይመለሱ ጨካኞች በተከበብን ሰዓት እኛስ ወዴት እንሔዳለን?

ሕይወቱ "ሌሊት" የሆነበት ሰው ሁሉ  ወደ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ቢሔድ እንደሚሻለው ከኒቆዲሞስ የተሻለ ምሳሌ የለም። ሕይወቱ የጨለመ ባይሆን እንኳን ልቡ የጨለመበት ፣ በኃጢአት ጠል የጠቆረ ፣ በበደል ብርድ ቆፈን እጅ እግሩ የታሰረ ከእኛ መካከል ስንት አለ?

እመነኝ ፣ ተስፋ ቆርጠህ ቁጭ ብለህ እስከሚነጋልህ ብትጠብቅ አይነጋም። ይልቅ ተነሥና "በሌሊት ወደ ክርስቶስ ሒድ" እርሱ ተስፋ ለቆረጠው ማንነትህ ዳግመኛ መወለድ እንዳለም ይነግርልሃል። ኒቆዲሞስ ጌታችንን ሊያየው ሔዶ  ራሱ ታይቶ እንደመጣ አንተም ወደ እርሱ የቀረብህ እንደሆነ ራስህን ታያለህ።

በ"ሌሊት" ውስጥ ለሚኖር ሰው ነግቶ ፀሐይ ትወጣልኛለች ብሎ ከሚጠባበቅ ይልቅ በሌሊት እንደ ኒቆዲሞስ ተነሥቶ ወደ ጽድቅ ፀሐይ ወደ ክርስቶስ ቢሔድ ይሻለዋል።  ወደ እርሱ ለሚሔድ ሰው ሌሊቱ ይነጋል ፣ ክርስቶስ ያለበት ሌሊት ከቀን ይልቅ ብሩሕ ነው ፣ እውነተኛው ብርሃን ያለበት ጨለማም ጨለማ አይደለም። ስለ እርሱ "ጨለማም በአንተ ዘንድ አይጨልምም" ተብሎ ተጽፎአልና።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በዛሬው መርሐ_ግብሬ እስኪ ይህን ልበላችሁ
የተለመደ ትብብራቹን ለሁሉም አድርሱልን

ከእርሱ ማንንም አታስበልጡ ልላችሁ እወዳለሁ ይነበብ👇👇👇

🔘  ከእግዚአብሔር በላይ ማንንም አታስቀድሙ
ከእግዚአብሔር በላይ የምቶዱት ሰው የለም?
የሆነ ነገር የለም? የምንወዳቸውን ሰዎች ላለማስቀየም ብለን እግዚአብሔርን አላስቀየምንም (ኀጢአት አልሰራንም?)፣ ለእግዚአብሔር ልንሰጠው የሚገባውን ጊዜ ለሰዎች  ብለን አላቃጠልንም?
ለምን ይሆን ሰዎችን ከማስቀየም እግዚአብሔርን ማስቀየም የቀለለን?
🛑 ከክርስቶስ በላይ የምንወደው የሆነ ነገር ካለ በቃ ጣኦት አምላኪ ነን።
ለዛ ነገር ያለን ፍቅርም ፍቅር አይደለም የውሸት ስሜት ነው።ለአንድ ነገር ወይም ሰው ያለን ፍቅር ከክርስቶስ የበለጠ ከሆነ ውሸት ነው ተራ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ በወላጆችና በልጆች መካከል ሊኖር የሚገባውን ገደብ ሲያስረዳ ምን አለ "ልጆች ሆይ ወላጆቻችሁን #በጌታ ታዘዙ" ለምን በጌታ አለ ብንል የምንታዘዘው ትዕዛዝ በጌታ ቃል የተመዘነ መሆን እንዳለበት ሲነግረን ነው። እርግጥ ነው ቤተሰብን መታዘዝ እግዚአብሔር ማገልገል ነው።ግን እግዚአብሔር የሚያስደስተውና የማያስደስተው አለ ሁሉንም በእግዚአብሔር ቃል መዝኖ መፈፀም ነው የሚገባው። ለምሳሌ ደሞ እጮኝነት ላይ ከትዳር በፊት አንዱ ወገን ሩካቤ ስጋ እንዲፈፅሙ ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወገን ደሞ አይ ዝሙት ነው እግዚአብሔር ያዝንብላል ሲል አትወደኝም ማለት ነው? አትወጅኝም ማለት ነው?  ብትወደኝ ብትወጂኝ ኖሩ አሽ ትይ/ ትል ነበር የሚል ምላሽ ሲሠጡ ይህን ሰው ከማጣ እግዚአብሔርን ልጣ የሚል ሀሳብ ያለው ድርጊት እንፈፅማል ለምን እንደው ባላውቅም ክርሰቶስን ካሶጣን ፍቅራችን የሚሠምር ይመሥለናል።ግን እህቴ ቆይ የእግዚአብሔር ህግ ለማክበር ፈቃደኛ እንዳልሆነ  እየተረዳሽ አግብተሽው ልትኖሪ ያሠብሽው ምን ነካሽ?
ቅዱስ ጳውሎስ ባሎችን ሲመክር ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ውደዱ ያለውን የሚፈፅም ይመስልሻል? አንተስ ብትሆን ክርስቶስን ለመታዘዝ ዝግጁ ያልሆነችን ሴት ለማግባት ስታስብ ለባሎቻችሁ ተገዙ የሚለውን በትዳር ስትኖሩ ትፈፅመዎለች ብለህ ታስባለህ?
ምን አልባት እንዲህ አይነት ጥያቄ ቢቀርብላችሁ ያው ምን አልባት ሰይጣን እየፈተነው ስለሚሆን ልንፀልይለት በትህትና ልናስረዳ ይገባል ከዛ አቋማቸውን አልቀይር ካሉ ምን ይባላል  አመሠግናለሁ ቻዉ ከማለት ውጭ። ከክርስቶስ ማንም ሊለየን ስለማይገባ።
ግን አንድ እንድታውቁ የምፈለገው ነገር ከትዳር በፊት ሩካቤ ስጋ እንፈፅም አለማለቱ ብቻ ኦርቶዶክሳዊ መርህን ያሟላል/ታሟላለች ማለት ነው ማለት አደለም እርግጥ ነው አንዱ የኦርቶዶክሳዊነት መገለጫ ነው ግን ብቻ አድርገን ከወሰድንው ትልቅ መሠረታዊ ስህተት ውስጥ እንገባለን።

ማስጠንቀቂያ  @eotcy

ከሆነ ጊዜ በኃላ ለወንድ ወይም ለሴት ብሎ ሃይማኖት መቀየር እየተበራከተ መጥቷል። #ክርስቲያኖች እስኪ አስቡት እንዴት አምላካችንን በወንድ ወይም በሴት እንቀይራለን?
ከአምላኩ በላይ ወዶሽ ወይም ወዳህ አምላኩን/ኳን/ የከዳ አንቺን/አንተን/ እንደማይከዳሽ/ህ/ ምን ዋስትና አለሽ/ህ/?  ሁላችንም ከምንም በላይ  እስከ ሞት ድረስ ያፈቀረንን ክርስቶስን እናስቀድም
ለሁላችሁም ክርስቶስን ያስቀደመ ህይወት ተመኘሁላችሁ 🙏🙏🙏

የወደቃችሁ ከጥፋታችሁ ተምራችሁ ወድቃችሁ ያልቀራችሁ ጀግኖች (አናትሽ ሄዎን በውሸት ቃል ተታላ ብትወድቅም ንስሀ ገብታ ዛሬ ቅድስት ሄዎን ተብላ ትጠራለች እግዚአብሔር ምሯት በገነት ነች አንችም ተነሽ ወንድሜ አንተም ተነስ አባታችን አዳም ከውድቀቱ ተነስቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷል) ያልወደቃችሁ በርትታችሁ እስከመጨረሻው ፀንታችሁ ትኖሩ ዘንድ።
ምንም ይሁን ምን ስናደርግ እግዚአብሔር ምን ይላል የሚለውን መርምረን ይሁን።


https://www.tgoop.com/eotcy 
ሱሪ የሚለብሱ፣ሜካፕ የሚቀቡ ወ.ዘ.ተ እንዲህ አይነት ሴቶች  የማይረቡ ርካሾች ናቸው

ያው ታውቃላችሁ የጌታ ፍጡር ሁሉ ክቡር ነው የሰው ልጅ ደግሞ እጅጉን መልካም ነው። ይህን ርዕስ ለምን ማንሳት ፈለኩ መሰላችሁ አንዳንዶቻችን ትንሽ ወደ ቤተክርስቲያን ቀረብ ስንል ያለፈው ማንነታችንን እንረሳና እኛ ድሮ እንሰራው የነበረውን ኀጢአት  ወይም ያልሰራነው ሊሆን ይችላል ሲሰሩት ስንመለከት መፍረድ እንጀምራለን ልናዝንላቸው ሲገባ እናዝንባቸዋለን ሱሪ የሚለብሱ፣ ሜካፕ የሚቀቡ ሴቶችን በቃ በጥላቻ እናያቸዎለን ግን ታውቃላቹ ሱሪ የሚለብሱ ከኛ የተሻለ ስብዕና ያላቸው አሉ ( ሁሉም ሳይሆኑ አንዳንዶች ማለቴ ነው) እኔ ሴቶች ሱሪ ቢለብሱ ምንም ችግር የለም ጌታን ያስደስታል ማለቴ አይደለም ማስተላለፍ የምፈልገው ንቀታችን እንተወው  እና እንዴት እንዲያቆሙ እናግዛቸው ነው። ሱሪ መልበስ ከአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሴት አይጠበቅም ነውር ነው 😡 አንበል። ልክ ነው ግን አባባላችንን እናስተካክል። "እህቴ መልካም  ነሽ ስብዕናሽ ደስ ይላል ከኔ የተሻልሽ ነሽ ደግሞ ይሄን ነገር ብታስተካክይ እጅግ ደስ ይላል አምላክሽ ባንቺ ይሰበካል ወንድሞችሽን ከማሰናከል ትተርፊያለ 😍 በእውነት ይሄን ለመተው እንድትችይ ጌታ ይርዳሽ፣ ክርስቲያን እንደመሆናችን ከሌሎች ሰዎች እንለያለን በአለባበሳችን፣ በአነጋገራችን ፣በአመጋገባችን፣ በአረማመዳችን በሁሉ ነገራችን  አርአያ ልንሆን ይገባል። እህቴ መተው ይከብድሽ ይሆናል ኃጢአት ለኛ ጣፋጭ ነው  ግን ኃጢአትን እንድንጠላ ጌታ ይረዳናል። ብቻ ፋላጎት ኖሮን ጌታን ፈቃዴን ሰጥቼሀለሁ አስችለኝ እንበለው እሱ ፈቃድ ከሰጠነው ሀይልን አቅምን ይሰጠናል" በቃ እንዲህ ተስፋ የሞላው ድንቅ ቃል እንንገራት መጀመሪያ ግን የምቶዱላቸውን ፀባይ አስቀድማችሁ ንገሯት ያው በጎው ሲቀድም መልካም ነው። እንደው ግን በሴቶች ተጠቅሜ ተናገርኩ እንጅ ምን አልባት ፀጉሩን ከሚገባ በላይ የሚያሳድግ ወንድ በቃ አረማመዱ ሁሉ ነገሩ ዱርዬ የሚመስል ለሆነ ልጅም ሊሆን ይችላል ስትመክሩ አካሄዳችሁን ጌታ በሚወደው መንገድ ይሁን ተጠቀሙት ከናንተ የተሻለ ስብዕና ሊኖረው ይችላል ልጁ ማንም በምንም ክፉ ኀጢአት ውስጥ ቢሆን እንዘንለት እንጂ አንዘንበት🙏🙏🙏

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
አንብቡት አጭር አስተማሪ_ታሪክ ነው

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር አስማሪው ጋር መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው
ያወራሉ፡፡ አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው
አድርጎ ነው ሚያየው፡፡

ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ጽዶችና ሳሮችን
የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፤ተማሪው የጽዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ
አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም ያወለቀውን ጫማ
ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን
እንመልከተው” ይለዋል፡፡አስተማሪውም“ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን
እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም፡፡

ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን
ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ
ከተህበት ና፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡ ተማሪው አስተማሪው እንዳለው ቀስ
ብሎ የሰውዬው ጫማ ላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋር ደበቅ ብለው
የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ፡፡ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን
ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል፡፡

ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት
ማንም ሰውየለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው
በሗላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል፤ሰውዬው
አላመነም!!በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ “ጌታዬ
የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል፤ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው
አይደል!!

የልጆቼ ዳቦ ማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል!! ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ፡፡
ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከትልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች፡፡

አስተማሪውም
“ቅድም ካሰብከው ታሪክ ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም”
አለው፤ተማሪው እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ
ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም፤ በህይወቴ የማረሳውን ትምህርት ነው ያስተማሩኝ፤
እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው፡፡

ለሰዎች የደስታ ምንጭ ከመሆን በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ
       
አስተማሪ ትምህርቶች ለማግኘት ቴሌግራምተቀላቀሉ
 "...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
☞︎︎︎ አንተ ሰው  ይሔንን ጹሑፍ አንብብ

ከዓለም አታላይ እንቅልፍ ይነቃል 👇👇

ሰው የሆነ ሁሉ ያንብበው
ሰው ሆይ እሞታለሁ ብለህ ታስባለህ
ለመኖር ብለህ ትዋሻለህ
ለመብላት ብለህ ትሰርቃለህ
ለእርካታ ብለህ ትዘሙታለህ
ሀብታም ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለህም
እኖራለሁ ብለህ ግንብ ትገነባለህ ቤት ትሰራለህ
አውቃለሁ ብለህ ትማራለህ
እወልዳለሁ ብለህ ታገባለህ አልመች ሲልህ ትፈታለህ
በእግሬ አልሄድም ብለህ መኪና ትገዛለህ
ሚስት ከቤት እያለችህ ከውጪ ትመኛለህ
አንድ ወልደህ ከሆነ ሁለተኛ ታስባለህ
ዲፕሎማ ካለህ ለዲግሪ ትማራለህ
ድግሪ ካለህ ለማስትሬት ትማራለህ
ማስትሬት ካለህ ለፒአች ዲ ትማራለህ
አንድ ቤት ካለህ ሁለተኛ ቤት ታስባለህ
አንድ መኪና ካለህ ሌላ መኪና ያምርሃል
ክፍለ ሃገር ካለህ አዲስ ለመኖር ታስባለህ
አድስ አበባ ከሆንክ አውሮፓ አሜሪካ ትመኛለህ
አሜሪካ ከሆንክ ሌላ ፕላኒት ለማየት ትጓጓለህ
ትንሽ ስልጣን ካለህ ትልቅ ስልጣት ትመኛለህ
የቀበሌ ሊቀመንበር ከሆን የወረዳ አስተዳደር ለመሆን ታስባለህ
የወረዳ አስተዳደር ከሆንክ የዞን ሀላፊ መሆን ያምርሀል
የዞን ሀላፊ ከሆንክ የክልል ርእሰ መስተዳድር ለመሆን ትሮጣለህ
የክልል እርሰ መስተዳድር ከሆንክ ሚንስቴር ለመሆን ታስባለህ
ሚንስቴር ከሆንክ ጠቅላይ ፕሬዝዳንት መሆን ያምርሀል
ዲያቆን ከሆንክ ቄስ መሆን ያምርሃል
መነኩሴ ከሆንክ ጳጳስ መሆን ትፈልጋለህ

☞︎︎︎ ወዳጄ ሆይ የምትሞትበትን ቀን ታስባለህ

☞︎︎︎ መቼ ነው የምሞተው ብለህ ታወቃለህ

አንተ እኮ 🫵የዛሬ ነህ የነገን አታውቅም
ግን ስለ ነገ ብዙ ታስባለህ

ወዳጄ ሆይ ከፈጣሪህ ፊት የሚያስቆምክ ስራ ሰርተሃል

በየት በኩል ነው የምቆመው ብለህ ታውቃለህ
በግራ ነው ወይስ በቀኝ የምትቆመው ስራህ በየት ነው የሚያቆምህ
ሞት ሳይቀድምህ ዛሬውኑ ወስን
እየተዘናጋና ለሥጋ ብቻ ስትኖር ለነፍስህ ሳትኖር እንዳትሞት
ለመጽደቅም ለመኮነንም የስራህ ውጤት ነው
መልካም ከሰራህ የጽድቅ ልጅ ነህ
ክፉ ከሰራህ የኃጢአት ልጅ ነህ
በምድር ያለው ነገር ሁሉ ከሞት አያድንም
ዝናህ ሀብትህ እውቀትህ ስልጣንህ ሁሉ ምድራዊ ነው

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2


꧁  🀄🀄

https://www.tgoop.com/eotcy
ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው
በሆሳዕና ለምን ቀለበት እናስራለን
በሆሳዕና ጌታችን ለምን በአህያ_ላይ ተቀመጠ
በሆሳዕና ለምን ዘንባባ አነጠፉ


እና ሌሎች በደንብ ይነበብ ሼር!

☞︎︎︎ ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው

ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ
የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡


☞︎︎︎ ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)

☞︎︎︎ በአህያ መቀመጡ፦

ትህትናን ለማስተማር
የሰላም ዘመን ነው ሲል
ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡

አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ።
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

☞︎︎︎ ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
☞︎︎︎ ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

☞︎︎︎ ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡
Join🙏🙏🙏

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ፡-

መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው

#ሼር
https://www.tgoop.com/eotcy
🔴ማክሰኞ የትምህርት እና የጥያቄ ቀን

ይህ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ በተናገረው ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡

ሰኞ ቀን ጌታችን በረገማትን በለስ  መድረቅ ሐዋርያት ሲደነቁ እምነት ያለው ሰው ሁሉን ማድረግ እንደሚችል ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡
‹‹ ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት ጴጥሮስም ትዝ ብሎት መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ››ማር 11፥20-26 እያለ ያስተማረበት ዕለት ስለሆነ የትምህርት ቀን ይባላል

ሌላው ይህ ዕለት ጌታችን  ሰኞ ዕለት  ካደረጋቸው ነገሮች ተነስተው አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት ዕለት ነው
‹‹ ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው። . . . ›› /ማቴ 21 ፥23- 27/
https://www.tgoop.com/eotcy
ይህ ጥያቄ ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀረቡት ጥያቄ ነበር ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበረውን ገብያ ስለበተነው የነጋዴዎቹን  መደባቸውን ስለገለበጠ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነውና በማን ሥልጣን አደረከው ብለው ጠየቁት ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን›› ቢላቸው ጸረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው
ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ አሳብ ስለሚያውቅ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ነው›› ቢሉት ‹‹ለምን አላመናችሁበትም?›› እንዳይላቸው፤ ‹‹ከሰው ነው›› ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት፣ እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ስለፈሩ ‹‹ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው ከዚህ ታሪክ የተነሳ ይሄ ቀን የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
ረቡዕ የምክር እና የዕንባ ቀን

  ይህ ቀን የምክር ዕለት፣ የዕንባ ቀን ተብሎ ይጠራል በዚህ ዕለት አይሁድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሲመክሩ ቆይተው  ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ባቀረበው ሐሳብ ስለተስማሙ ይሙት የሚል ፍርድ የጸናበት ቀን ነው ከዚህ የተነሳ ዕለተ ምክር ተብሎይጠራል፡፡   
   @eotcy
ሊቀካህናቱ እና ፈሪሳውያን ሕዝቡን ሰበሰቧቸውና ‹‹ እነሆ ይህ ሰው ብዙ ተዓምራት ያደርግ ጀመር ምን ብናደርግ ይሻላል እንዲሁ ዝምብለን ብንተወው ሕዝቡ ሁሉ ያምንበታል›› ተባባሉ፡፡ ሹመቱ በዚያ ወራት የሆነ የካህናት አለቃ ስሙ ቀያፋ የሚሉት ‹‹እናንተ ምንም ምክር አታውቁም አንድ ሰው ብንገድል አይሻልምን? ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ምክንያት ከሚጠፋ›› ዮሐ 11፥49-50 የሚል ሐሳብ አቀረበ፡፡
እንዲህ ማለቱ ክርስቶስ ለሕዝቡ ቤዛ እንደመጣ አውቆ ሳይሆን እግዚአብሔር በተዓምራት አናገረው ልክ በሆሳዕና ዕለት ድንጋይ በተዓምራት እንዳናገረ መንፈስ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እዚህ ዓለም የመጣው ለሕዝቡ ቤዛ እንደሆነ ስለሕዝቡ ሁሉ እንደሚሞት በተዓምራት አናገረው ከዚህ ቀን ጀምሮ ካህናት ጌታቻንን ሊገድሉት መከሩ፡፡
@eotcy
    ይህ ዕለት ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ እንዲሆን የተጠራው ይሁዳ  ጌታን አሳለፎ ለመስጠት ከሊቃነ ካህናት ጋር የተማከረበት  ጌታን አሳልፎ ለመሥጠት  በሠላሳ ብር የተሰማማበት ዕለት  ነው ፡፡
‹‹ በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ። ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? አላቸው እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።›› ተብሎ እንደተጻፈ ማቴ 26፡-14-16
@eotcy
በተጨማሪም ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በስምዖን ዘለምጽ ቤት ተቀምጦ ሳለ ማርያም እንተ ዕፍረት (ባለ ሽቶዋ ማርያም ) የሦስት መቶ ዲናር  መልካም መዓዛ ያለው ሽቱ  ገዝታ በራሱ ላይ ያፈሰሰችበት ዕለት ነውና የመልካም መዓዛ ቀን  ይባላል ፡፡ ኃጢአቷን ይቅር  ይላት ዘንድ በእግሩ ሥር ተደፍታ በዕንባዋ ስላጠበችው የዕንባ ቀንም ተብሎይጠራል ፡፡
ስለዚህ ይህን ቀን ስናስብ የማርያም እንተ እፍረትን ንስሐ ተቀብሎ ምህረትን የሰጠ  ጌታ ኃጢታችንን ይቅር ይለን ዘንድ በንስሐ እና በዕንባ ወደ እርሱ እየተመለስን መሆን አለበት ፡፡
Https://www.tgoop.com/eotcy
𖣘 በሕማማት የሚጸለዩ ጸሎቶች ምን ምን ናቸው
𖣘 በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም
𖣘 የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድእና የመሳሰሉ ጥያቄ መልሶች

ጸሎት

በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፣ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፣ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።  ( በዚህ ሀሳብ ላይ በሌላ ጹፍ እንመለሳለን)

በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም:-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

𑁍 "ኪርያላይሶን"

ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡

𑁍 "ናይናን"

የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡

𑁍 "እብኖዲ" 

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው

𑁍 "ታኦስ"

የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡

𑁍 "ማስያስ"

የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው

𑁍 "ትስቡጣ"

ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።

𑁍  "አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡

𑁍  "አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ  ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው

𑁍 "አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡

፨ የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገዱት
አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና
ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ
ይቅርታ ያገኝ ዘንድ 41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ፡-
12 ጊዜ ---- እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- በእንተ እግዝዕትነ ማርያም
𑁍 መሐረነ  ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- ኪራላይሶን (አቤቱ ማረን)
5 ጊዜ ---- ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ (አምስቱ የጌታ ችንካሮች)
ሐሙስ የምሥጢር እና የነጻነት ቀን

ይህ ዕለት ብዙ ምሥጢር እና ታሪክ የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ በብዙ ስሞች ይጠራል ጥቂቶቹን ከምክንያታቸው  ጋር እንዲህ አቅርበናቸዋል

☞︎︎︎ ጸሎተ ሐሙስ:- የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡

☞︎︎︎ ሕጽበተ ሐሙስ:- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡ ይህን

☞︎︎︎ የምሥጢር ቀን :- ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ ‹የምሥጢር ቀን› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኅብስቱንና ጽዋውን አንሥቶ ‹‹ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ፤ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፤›› በማለት እርሱ ከእኛ፤ እኛም ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምሥጢር  ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

☞︎︎︎ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ:- መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመኾኑ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ይባላል (ሉቃ. ፳፪፥፳)፡፡ ‹ኪዳን› ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ዅሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለ ኾነ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ተባለ፡፡

☞︎︎︎ የነጻነት ሐሙስ:- ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለ ኾነ ‹የነጻነት ሐሙስ› ይባላል፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፡፡ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤›› በማለት ከባርነት የወጣንበትን፤ ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመኾኑ ሊቃውንቱ ‹የነጻነት ሐሙስ› አሉት (ዮሐ. ፲፭፥፲፭)፡፡
ስለዚህ ይህን ዕለት ከኃጢአት እና ከዲያቢሎስ  ባርነት  በእግዚአብሔር ቸርነት ነጻ መውጣታችንን የምናስብበት ስለሆነ የተከፈለልንን ዋጋ አስበን ዛሬ ከታሠርንበት የኃጢአት ሠንሰለት በንስሐ ነጻ ሆነን ልናስበው ይገባል፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
ምሴተ ሐሙስ እና ጉልባን ምን አገናኛቸወ

ጉልባን ከባቄላ ክክ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም የጥራጥሬ እህሎች ጥሬውን ተከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በዕለተ ሐሙስ የዕለቱ ሥርዓተ ጸሎት እና ስግደት አልቆ ቅዳሴው ተከናውኖ ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው የሚመገቡት ነው  ይሄውም ስለ ሦስት ነገር ይደረጋል

፩ የኦሪትን ምሳሌ ለመፈጸም
@eotcy
እስራኤላውያ ከግብጽ ባርነት በዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛ ሞተ በኩር መውጣታቸውን እናሳታውሳለን በመጨረሻው ሞተ በኩር ግን ፈርኦን እነርሱን  ማስቀረት አልቻለም ነበር  እሥራኤላውያንም ተቻኩለው ሲወጡ በቤተ ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ፡፡ ይህንን በዓል ( ፋሲካን ) ሲያከብሩ በግ አርደው ያልቦካ ቂጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው ከባርነት በወጡ ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ፡፡ዘዳ 13፡-1 
እኛም አስቀድሞ በሙሴ ላይ ህገ ኦሪትን የሠራ ህዝቡንም መርቶ ከነዓን ያስገባ እርሱ እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በሥጋዌ መገለጡን በማመንና ጌታ ራሱ አዲሱን ኪዳን  ከመሥራቱ አስቀድሞ  ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ  እኛም ሐዲስ ኪዳን የተመሰረተባትን ዕለት ስናስብ  ቀድሞ የነበረውንና ለሐዲስ ኪዳን ጥላ (ምሳሌ) የሆነውን ሥርዓት ለመታሰብያ እናደርጋለን፡፡
ሌላው እስራኤላውያን ጉልባን በልተው ግብጽን ተሰናብተው እንደወጡና ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደገቡ እኛም ከሰሙነ ሕማማት በኋላ የመከራውን ዘመን ተሰናብተን አማናዊውን ሥጋና ደም ተቀብለን ርስት መንግስተ ሰማያትን ለመውረሳችን ምሳሌ ነው ፡፡

፪ የሐዘን ሳምንት መሆኑን ለመግለጽ
@eotcy
እንደ ሀገራቸችን ባህል ንፍሮን  ዕንባ አድርቅ ይሉታል ብዙ ጊዜ ለለቀስተኞች ይዘጋጃል ምክንያቱም ሞት ተናግሮ አይመጣምና በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ ለለቅሶ ቤት ይሰራል ስለዚህ ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ሞትና በድንግል ማርያም ኃዘን ምክንያት ኃዘንተኞች ስለሆንን  ይህንን ለማመልከት ጉልባን እናዘጋጃለን

፫ የጌታን መከራ እና ሕማም ለማሰብ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ብሎ ከተቀበላቸው ሕማማተ መስቀል መካከል አንዱ ሆምጣጤን መጠጣቱ ነው በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሰናል፡፡
******

ውድ የዚህ ቻናል ተከታታዮች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልተበረዙ ስርዓቶች ሁሉም ሰው ያውቅ ዘንድ ካነቡ በኃላ ለሌላው ማስተላለፍ አይርሱ
@eotcy
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች pinned «ሐሙስ የምሥጢር እና የነጻነት ቀን ይህ ዕለት ብዙ ምሥጢር እና ታሪክ የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ በብዙ ስሞች ይጠራል ጥቂቶቹን ከምክንያታቸው  ጋር እንዲህ አቅርበናቸዋል ☞︎︎︎ ጸሎተ ሐሙስ:- የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡ ☞︎︎︎…»
መልካሙ አርብ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት አርብ መልካሙ አርብ ተብሎ ይጠራል ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን በዚህ ስያሜ ተጠርቷል የስቅለት አርብም እየተባለ ይጠራል ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም ጌታ በመስቀል ላይ መሰቀሉ ይታሰብበታልና በመሆኑም በዚህ ዕለት የስቅለቱ መታሰቢያ አጎበር ተዘርግቶ ከርቤ /የሞቱ ምሳሌ/ እየታጠነ ስቅለቱን የሚመለከት ምንባባት በውርድ ንባብ ሲነበብና ሲሰገድ ይውላል፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
አይሁድ ክርስቶስን ሐሙስ ማታ በይሁዳ መሪነት ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።
https://www.tgoop.com/eotcy
በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ።አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"
                   ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

https://www.tgoop.com/eotcy
👉13ቱ ሕማማተ መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት

👉አምስቱ ችንካሮች

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው 
አምስቱ ችንካሮች

1 ,ሳዳር በሚባል ችንካር ቀኝ እጁ ቸነከሩት
2, አላዶር በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3, ዳናት በሚባል ችንካር ሁሉቱን እግሩ ቸነከሩት
4, አዴራ በሚባል ችንካር መሓል ልቡን ቸነከሩት
5, ሮዳስ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

     👉 አምስቱ የእመቤታችን ሀዘናቶች

1 ,ኛ ከአምስቱ አንደኛ አይሁድ እንዲገሉት በቤተ መቅደስ ስምኦን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው ።
ሉቃስም ምዕራፍ 2፥ 34- 5

2, ኛ ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተ መቅደስ ባጣሁህ ጊዜ ነው ።
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፣41 -48

3, ኛ በሥስተኛው እጅህን እግርህን አስረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፍት ባሰብሁ ግዜ ነው።
ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ፣1

4,  በዕለተ አርብ እራቁትህን ቸንክረው በሁለቱ ወንበዴ መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብሁ ጊዜ ነው። አለች
ዮሐን ምዕራፍ 19 ፥17 -22

5, ኛ ወደ አዲስ መቃብር ውስጥ እንዳደርህ ባሰብሁ ጊዜ ነው።

ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19፥ 38 42

ከብርሃነ ትንሳኤው ያድርሰን የእግዚአብሔር ቸርነት የእመ ብርሃን ምልጃ አይለየን አሜን
➪ ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦

☞︎︎︎ ቀዳም ሥዑር፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

☞︎︎︎ ለምለም ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

☞︎︎︎ ቅዱስ ቅዳሜ፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)                     
                        
╭══•:|★✧✧★|: ══╮
                      @eotcy
                      @eotcy
                      @eotcy
╰══•:|★✧✧★|:  ══╯
2025/02/23 10:35:30
Back to Top
HTML Embed Code: