Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የእናት ምልጃ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ

በማቴ 15÷21-28 ላይ አምልኮተ እግዚአብሔር ከማያውቁ አህዛብ መካከል የሆነች ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ከነናዊት ሴት ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርባ ጌታ ሆይ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች። ይቺ ሴት ለልጅዋ አማላጅ ሆና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመምጣቷ እንደዳነችላት ተገልጧል። እስኪ አስተውሉ በጌታ አንደበት ውሻ የተባለች አህዛባዊት የሆነችው ይህቺ ኃጢአተኛ ሴት ለልጇ አማላጅ ሁና ድኅነት ካሰጠች ሰማያዊ ንጉስ እግዚአብሔር ፍፁም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የወደደላት ቅድስት ድንግል ማርያም እንዴት አታማልድም ተብሎ ይነገራል እንደት የእናት አማላጅ አትሆንም ተብሎ ይነገራል

እሷኮ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ጌታ ካንች ጋር ነው አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ.. ሉቃ 1÷28 ተብላ የተመሠገነች የከበረች እግዚአብሔር እናት ናት።

በእርግጥ እውነት ነው አዎ እመቤቴ አታማልድም እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ያለችው ትውልድ ለሆኑት እንጂ ላልሆኑትማ እንዴት ልታማልድ ትችላለች የምትመሰገነውስ ትውልድ ነኝ ብሎ ለሚያምነው እንጂ ለማያምነውማ እንዴት ሁኖ ይቻለዋል።

የእናት ምልጃ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ መባሉ እውነት አይደለምን

የእመቤታችን የእናትነት ፍቅሯን በልባችን ጣሟን በአንደበታችን ያኑርብን
#ሼር

@eotcy
@eotcy
@eotcy
ይህን ያውቁ ኖሯል

አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን

፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ
፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ)
፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ)
፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ

እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች።

፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል
፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፭..ነቢዩ እዝራ
፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል)
፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል)

በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን!

የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን💒
Https://www.tgoop.com/eotcy
ግንቦት 12 -  ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።

ቅዱሳን የማይታየው እግዚአብሔርን በሕይወታቸው አጉልተው የሚያሳዩን ናቸው።

የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የዓለም ሁሉ መምህር የኾነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያረፈው በ407 ዓ.ም በስደት እያለ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሕዝቡ ዘንድ ይወደድና ይከበር የነበረ አባት ስለ ነበር ገና በስድሳ ዓመቱ ማረፉ እጅግ መራራ ኀዘን ነበር። ይህም ዘወትር በልቦናቸው ሰሌዳ በኀሊናቸው ጓዳ ይኖር  ነበር።

በ434 ዓ.ም የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ የኾነውና
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደቀመዝሙር የነበረው ቅዱስ ጵሮቅለስ  አንድ ቀን በሃጊያ ሶፊያ እያስተማረ ሳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እያመሰገነ ሰበከ  "ዮሐንስ ሆይ መላ ዘመንህን በሀዘን በመከራ አሳለፈክ ዕረፍትህ ግን የተወደደችና የተከበረች ኾነች! ቅዱሱ ሰውነትህ ያረፈበት መካን ንዑድ ክብርት ናት። ፍቅርህ የቦታን ወሰን አለፈ መታወስህ ይህን አጥርና ድንበር አፈረሰ…

ቅዱስ ፖትሪያርክ ጵሮቅለስ ይህን እየተናገረ እያለ ቃሉን ያደምጡ የነበሩ ሁሉ ማልቀስ ጀመሩ  ትምህርቱንም ሊያስጨርሱት አልተቻላቸውም። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስን እጅግ ይወዱት ነበርና!

"እኔም ስለ እርሱ እላለሁ በእውነት አፈወርቅ አፈ እንቁ……በእውነት አፈ ጳዝዮን ነው በድርሰቶቹ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት አፈ ባሕርይ። በእውነት አፈ መዐር በቃሉ ጣፋጭነት ምዕመናንን የሚያለምለም በእውነት አፈ ሦከር በእውነት በትምህርቱ መዓዛ  የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቶ አፈ ርኄ ነው። በእውነት በውግዘቱ ሥልጣን ከሐዲዎችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ አፈ መጥብሃ ነው። በእውነት የማይናወጥ አምድ፣ የማይፈርስ መሠረት፣ በእውነት ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ነው። በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ ነው።"
[መፅሐፈ ምስጢር - አባ ጊዮርጊስ
https://www.tgoop.com/eotcy
*ምክረ አጋንንት*

በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ

📌ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
📌ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
📌ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
📌ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
📌ላስቀድስ ትላለህ ፤ ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
📌ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል።
📌ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
📌አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
📌በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ።
በመጨረሻም የተወሰነልህ ግዜ ያልቃል ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።😢
📌ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
📌 ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል
📌ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
📌 ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
📌ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ።
ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
📌ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።😭😭😭
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።

ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
❗️ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
❗️በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር።
📌 ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
📌የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሔር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+
...
በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" ::

እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት።

ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ።

https://www.tgoop.com/eotcy
🙊🙊ስድብ በቀጠሮ🙊🙊
▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️

🗣ሴትየዋ በሰፈሩ ውስጥ የታወቀች ተሳዳቢና ተንኳሽ ናት። ወቅቱ የአቢይ ጾም መግቢያ አካባቢ ነው "አሁንስ በጾም በጸሎት ተወስኜ መኖር አለብኝ" ብላ ለራሷ ቃል ትገባና የንስሐ አባቷን ታማክራለች።

🕯 የንስሐ አባቷም በውሳኔዋ ተደስተው መልካም ማድረጓን ገልጸው እንዲህ ሲል ይመክሯታል። "ልጄ አደራሽን ይህ የሱባዔ ወቅት ሁላችን በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትና ስለ ኃጥያታችን የምናለቅስበት ነው እኛ ክርስትያኖች በይኽ ጊዜ እንኳንስ እርስ በእርስ ልንጣላ ይቅርና ጠላታችንን የምንወድበት፣ ስንበድል ይቅርታን የምንልበት የንስሐ ጊዜ ነው።ስለይኽ እንኳን አንቺ ቀድመሽ ልትናገሪ ቢናገሩሽም እንኳን በትእግስት ማለፍ ይኖርብሻል። አደራ ልጄ በርቺ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን። ብለው ባርከው ያሰናብቷቷል።

💎ጾሙ ተጀመረና በሦስተኛው ቀን ሴትየዋ የከሰዓቱን ቅዳሴ አስቀድሳ ወደ ቤቷ ስትገባ "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደተባለው የመንደሩ ሴት በነገር ጠመዳት። እስኪ ተመልከቷት አሁን ላያት ሰው እውነተኛ ክርስቲያን አትመስልም?? ወገኛ......እያሉ ዘለፏት እሷ ግን የንስሐ አባቷ የመከሯትን አስታውሳ እንዳትሳደብም ጾም በመሆኑ እንዲህ አለች "እሺ አሁን ስደቡኝ ግድ የለም ይኽ ጾም ይፈታና እያንዳንድሽን ልክ አስገባሻለሁ። .......

😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ሁሌም ቢሆን ተናግሮ አናጋሪውን ያዝልኝ ማለት ደግ ነው ቢሆንም ግን የብዙዎች ክርስትና እንደ ፋብሪካ ሠራተኛ በሺፍት(በፈረቃ) ነው። በጾም ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ይገሰግሳሉ ለፋሲካ ግን የመጠጥና ጭፈራ ቤቱን ያጨናንቁታል።

👉👉የሁዳዴ ክርስቲያን የፋሲካ ዘፋኝ መሆን አይገባንም ።
     "በጊዜውም አለጊዜውም ጽና "
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ኪዳነ_ምሕረት

ስላንቺ ላወራ ስል እንባዬ ይቀድመኛል😥
ፍቅርሽን ውለታሽን ምገልጽበት ቃላት ያጥረኛል ከደጅሽ መጥቼ አለቀስኩ አቀረቀርኩም ግን አንቺ የልጅሽ ሀዘን አቶጂምና ቀና አረክሽ ችግሬን ላይመለስ ከእኔ አራቅሽው ታድያ በየትኛው አንደበትና ቃል አንቺን ላመሥግንሽ🙏
አንቺን ለምኜ የአጣሁት የለም

እናቴ

እኔማ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ ኅጥያት መስራት አላቆምኩም፤ አንቺንም ማፍቀሬን አላቆምኩም
ይገርመኛል የአንቺ ትሕትና እደዚ ኅጥያተኛ ሆኜ ከኔ አትለይኚም እንዴት አይነት ፍቅር ❤️ ቢሆን ነው እንዴትስ ያለ መውደድ ነው፤ እንዴትስ ብዬ ላውራው ምንስ ቃል ተጠቅሜ ስላንቺ ፍቅር ልናገር እመቤቴ፤ ያንቺስ ደግነት በዛብኝ ከአይምሮ በላይ ሆነብኝ እናቴ አንቺን ሳመሰግን ነፍሴ ከሥጋዬ ልትለይ ትደርሳለች ገና ለማመስገን ስምሽን ስጠራው እንባዬ ይመጣል😢 የፍቅርሽ ኃይሉ በጣም ከባድ ነው። ሊመጠን፤ ሊለካ፤ ሊመዘን...ጭራሽ አይቻልም እና አንቺ ለኔ ያለሽ ፍቅር ልዩ ነው ኪዳነ_ምህረት እናቴ

👉 እናቴ በስንፍናዬ ላላመሰግንሽ እችላለሁ በስምሽ ላልጸልይ እችላለሁ መቼም ግን ስምሽን ሳልጠራ አልውልም

እ_ወ_ድ_ሻ_ለ_ሁ

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
ኃጢአቷን የምትጽፈዉ ሴት

አንዲት ሴት ነበረች ኃጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኃጢአት የሰከረ ለኃጢአትም ተገዥ የሆነች ይች ሴት የተለያየ ኃጢያት የምትሰራ ናት ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ተሰርቃለች፣ ትገድላለች፣ በአል ትሽራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልቧ ኃጢአት ነበር። ነገር ግን የምትሰራዉን ኃጢአቷን ሁሉ እየጻፈች ታስቀምጥ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን የጻፈችዉን ኃጢአቷን ብታየዉ ስንክሳር አክሎ ተመለከተችዉ ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚለዉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነዉ። የዚች ሴትም ኃጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችዉ ደነገጠችና ኃጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ አለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችዉ አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ።

አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታሳየዉ ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኃጢአት ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኃጢአት ነበረች ሊፈሩዋት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች አባቴ ይችሳ አለችዉ አባ ባስልዮስም ይችን ኃጢአትሽንስ ማስተሰረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነዉ ሂደሽ ለእርሱ ንገሪዉ አላት።
አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኃጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገልጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነዉ። ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነዉ።
እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶሪያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱስ ኤፍርም ደረሰች።

አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ግን ኃጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጂ ስትመላለስ ኃጢአቷ እንዲቀልላትም ነዉ። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪዉ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸዉ እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞዉ በህይወት አታገኝዉም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘዉት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈዉ ኃጢአትሽን ከአስክሬኑ ላይ ጣይዉ አላት እሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቃያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።

የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኃጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችዉ አስክሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኃጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች በዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች።

እንደዚች ሴት ኃጢአቱን የሚያስታዉስ ማነዉ?
ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነዉ?
ስለ ኃጢአቱ በረሃ የተከራተተ ማን ይሆን?

የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም መጨረሻ ያሳምርልን ኃጢአቷን የደመሠሠ የሁላችንም ኃጢአት ይደምስስልን!

ለንስሐ የሚሆን ፍሬ አድርጉ

የዉዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
እስኪ ልጠይቃችሁ

አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የሆነ ቦታ [ ለምሳሌ ተራራው ሥር ] ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ ? ወደዚያ ቦታ [ ወደ ታራራው ለመውጣት ] ለመሔድ አስፋላጊ ነው የምትሉትን [ ቅድመ ዝግጅት ] ሁሉ አታደርጉምን ? [ እንዳያመልጣችሁ በጊዜ ሔዳችሁ ]  ቀኑን ሙሉም ቢሆን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁትምን ? 

እግዚአብሔር እሰጣቹዃለሁ ያለው አንድ ሺህ ቅንጣት ወርቅ አይደለም ወይም ምድርን ሁሉ አይደለም።  ከእነዚህ ሁሉ የምትበልጠዋን መንግስተ ሠማያትን ነው እንጂ ...

ታድያ ከዚያ የሚበልጥ ስጦታ ምን አለ ? 🤷🏾‍♂
[ ምንም የለም ]  ይሕን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ [ ወደ ተራራው የማይወጡ ] ሰዎች እንደምን ያሉ ምስኪኖች ናቸው
| ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቶስን ያከበሩ ፣ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፣ እውነትን የመሠከሩ ፣ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፣ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ ፣ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፣ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፣ ከዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።

ቅድስት ሆይ አንች እኮ:- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፣ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፣ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት ፣ የሁሉ ፈጣሪ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ። በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም  የለችም አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናት ስትሆኝ ድንግል ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።
ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናቴ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለሁ አዎ አሁንም እላለሁ መልካም ያደረገ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ። ምሳ.31:29

የቃልኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን

https://www.tgoop.com/eotcy
ግንቦት 21 #ደብረ_ምጥማቅ
@eotcy
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነዉ

👉ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ
@eotcy
👉 እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ

👉ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል
@eotcy
👉ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል ሁለተኛም ደግሞ ፃድቃን በአንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ

👉ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር
@eotcy
👉 እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳይኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል
@eotcy
👉እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ

👉ለአባቶቻችን የተለመነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛም ትለመነን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን "አሜን"


👉 ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
#ለቻናሉ_ቤተሰቦቼ 😘

አንድ የቆሎ ተማሪ ይለምን ዘንድ ወደ ከተማዋ ወጣ በእንተ ስሟ ለማርያም እያለ ለመነ የሰጠው የለም ስለ እግዚአብሔር አለ የተመለከተው የለም ሁለም እግዚአብሔር ይስጥህ ከማለት በቀር አንድስ እንኳን የሚላስ የሚቀመስ አጣ በዚህ ተበሳጭቶ ወደ ቤተ ሲሄድ መንገድ ላይ የሚያስተምሩትን አባት አገኛቸው ምነው ልጄ ማዘንህ ቢሉት

ተወኝ የኔታ ከጠዋት ጀምሬ ስንከራተት ዋልኩ ግን እግዚአብሔር ይስጥህ ከማለት ውጪ ምንም አላገኘሁም ኧረ ሰው ከፍቷል አባ አለ ተማሪው

ልጄ ተሞኘህ እግዜር ይስጥህ ከማለት የበለጠ ቸርነት አለን
እግዚአብሔር የሚሰጠውስ ከሰው ጋር እኩል ይሆናልን አሉት ይሄን እያሰበ ወደቤቱ ሄደ ከሁሉ እርሱ እንዳተረፈ ገባው እናም እንዲህ አለ

እግዜር ይስጥህ በሉኝ ✟
የሀገር ሀብታችሁን እየነገራችው ከምታስደስቱኝ
የጣፈጠ ምግብ እያቀረባችሁ ከምትመግቡኝ
በለመለመ መስክ እያስቀመጣችሁ ከምታሳርፉኝ
ስለ ወላዲቷ እግዜር ይስጥህ በሉኝ
ቢበርደኝ የተዋበውን ልብስ አትስጡኝ
ቢጠማኝ ይጠማኝ ዘንድ ውሀ አትስጡኝ
ለእግሬ ጫማ አልፈልግም
ለፊቴ ዘይት አልመኝም
እተኛበት ንፁሕ ፍራሽ እበላ ዘንድ ትንሽ ቁራሽ
አልጠይቅም
ለመኖሬ ማህተም ከሞት ማምለጫ አይሆኑኝም
ይልቁን ከሻታችሁ የልቤን ደስታ
ከገባችሁ የኔ እውነት ምኑም ነገር አይመችም እግዚአብሔር የሌለበት

ቤተሰቦቼ ስለዚህ እኔም ልበላችሁ የምትወዱኝ እህት ወንድሞቸ እግዚአብሔር ይስጥህ በሉኝ በሱ ፈንታ እኔን በማርያም በእናቴ።

በቸር ቆዩልኝ 

ባይሆን ቻናሉን ለወዳጆ በመጋበዝ ካሱኝ🙏

https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌 አስራት በኩራት ምንድነው
📌 ጥቅሙስ

መስጠት ማለት በኩራት፣ አስራት፣ መባና ልዩ ስጦታን ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲሆን ማቅረብ  ይኸውም ያለንን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር እንደተቀበልን ማሳያና ለእግዚአብሔር ያለንን አክብሮት ፍቅርና አምልኮ የመግለጫ መንገድ ነው።

የስጦታ ዓይነቶችና ትርጉማቸው፦

👉 አስራት
ዘፍ 14፡20፣ ዕብ 7፡4-5
- አስራት በብሉይ ኪዳን ከአስር አንድ እጅ ማለት ነው - ዘፍ 28፡22።
አስራት በአዲስ ኪዳን ግን ከአስር አንድ እጅ ባለፈ በዘራኸው ልክ ነው - 2ቆሮ 9፡6-7
- አስራት የእግዚአብሔር ንብረት ነው - ሚል 3፡8-10
- አስራት የሚሰጡ (የሚያስገቡ) ሰዎች በታማኝነት የእግዚአብሔርን ንብረት መልሰው ለእርሱ የሚሰጡ ናቸው - ዘዳ 14፡22-23
- አስራትን በማስገባት (በመስጠት) ውሰጥ በረከት አለ - ሚል 3፡8-10

👉 በኩራት
በኩር (የመጀመሪያ) ከሚለው ቃል የወጣ ነው። በኩራት የእግዚአብሔር ነው - ዘፀ 23፡19፣ ዘሌ 23፡10-11
- በኩራት መስጠት ማለት እግዚአብሔርን በነገሮቻችን ሁሉ ማስቀደም ማለት ነው - ዘኁ 3፡13፣ ዘዳ 15፡19
- የበኩራት ስጦታ ትዕዛዝ ነው - ዘፀ 13፡2፣ ዘዳ 26፡2
- የመጀመሪያውን ስንሰጥ ያለን ነገር ይባረክልናል - 1ሳሙ 2፡20-21

👉 መባ -
እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ገቢ አስራት አውጥተን ከሚቀረው ድረሻችን ላይ ለወንጌል ስራ፣ ለድሆች መርጃ፣ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የምሰጠው ስጦታ ነው። ይህ አይነቱ ስጦታ በልብ ደስታ በራሳችን ውሳኔ በአቅማችን መጠንና ከዚያም በላይ የምንሰጠው ይሆናል - ዘፀ 25፡1-5፣ 2ቆሮ 8፡1-2፣ ዘፀ 34፡20

👉 የፍቅር ስጦታ
ለእግዚአብሔር ቤት ስራና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ፍቅርን ለመግለጽ የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ ጊዚያቶች ሊደረግ ይችላል - ሐዋ 11፡27-30፣ ፊሊ 4፡16-18

#የምንሰጥበት_ምክንያት እና #አላማ

#እግዚአብሔር_እንድንሰጥ_አዟል - ዘፀ 25፡1-5፣ ዘሌ 25፡31፣ ዘኁ 18፡21ቤት

ስጦታችን የእግዚአብሔርን መንግስት የማስፋፋት ስራና የእግዚአብሔር  አገልግሎት ላይ የሚውል ነው - 1ቆሮ 9፡4-14፣ 2ቆሮ 8፡4፣ ፊሊ 4፡15-18

በመስጠት እግዚአብሔርን እናከብራለን፣ እናመልካለን - ምሳ 3፡9-10

በመስጠት የእግዚአብሔርን በረከት እንለማመዳለን - ሚል 3፡10-12፣ ሉቃ 6፡10ታማኝ

በመስጠት ለእግዚአብሔር  እንሆናለን (አንሰርቀውም) - ሚል 3፡8-10

👉 እንዴት መስጠት እንዳለብን

❗️የምንሰጠው አስቀድመን ራሳችንን ለእግዚአብሔር በመስጠት ነው -

❗️የምንሰጠው በሃዘን (በግድ) ሳይሆን በደስታ ነው -

❗️የምንሰጠው እንደገቢያችን ብቻ ሳይሆን ከጉድለታችንም ጭምር መሆን አለበት -

❗️የምንሰጠው ለሰዎች ለመታየት መሆን የለበትም -

❗️የምንሰጠው በስጦታችን ለመመካት መሆን የለበትም -

ስለ ስጦታ ያስተማረንና አስቀድሞ ያሳየን ራሱ እግዚአብሔር ነው። ከስጦታዎች በላይ የሆነውን ስጦታ ለሰው ልጆች ሰጥቷል (ዮሐ 3፡16-30፣ ሮሜ 8፡32)። ይህ በምድራዊ ቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ ላመኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ አድርጓል። ቤተ ክርስቲያን ይህንን የምስራች ለአለም ሁሉ ለማድረስ እንድንችልና የእግዚአብሔርን ቤት ስራ እንድትሰራ አማኞች የታዘዙትን የፈቀዱትን ስጦታ ለወንጌል መስጠት አለባቸው።

https://www.tgoop.com/eotcy
+ረፈደ አትበል+

ሰይጣን እኛን ከሚያዘናጋበት መንገድ አንዱ ወደ ጽድቅ የምትሄድበት ጊዜ አሁን ረፍዷል "አሁን እኮ ትዳር መስርተሃል"ብዙ ሀላፊነት አለብህ "ደግሞም ብዙ ጓደኞች አፍርተሃል"እነሱን ትተህ ወዴት ትሄዳለህ?መፅሐፋም እሚለው በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ነው ሆኖም ግን አንተ ወጣትነትህን በአጋጉል ቦታ አሳልፈኸዋል "አሁን በቃ መንፈሳዊነት ካንተ protocol ጋር አይሄድም ፣በዚያ ላይ ያልሰራኸው ሀጢያት የለም ፣እንዴት ፈጣሪስ ይቅር ይልሀል ? እያለ ከተተበተብንበት የሀጢአት እስራት እንዳንወጣ የተቻለውን ያደርግል። እኛም ደግሞ ከዚህ ለመውጣት የተቻለንን አናደርግም! 😓


ወንድሜ ስማኝማ ልንገርህ አብርሃም የሀጢአት ምሳሌ ከሆነችው ከካራን በ 75 አመቱ ነው ነበር የወጣው፣ ከአገርህ ከዘመዶችህ ከአባትህ ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ሲለው ምክንያት አልደረደረም ፣እሺ ብሎ ነው የወጣው ። ወንድሜ በሃጢአት ያረጀህ ከመሰለህ ፣እንደ አብርሃም 75 ዓመት አልሞላህምና ተቻኩለህ ቶሎ ውጣ ፤ እንደ ሀገር መኖርያ ካደረከው በደል ቶሎ ውጣ !አባትና እናትህን ማክበር አስትተው አባት እና እናት ከሆኑብህ ኃጢያቶች ቶሎ ውጣ!!

ብቻ አንተ ውጣ እንጂ ፣ አንተን ታላቅ ሕዝብ ማድረግ ፣ ከነዓን ማስገባት ለእግዚአብሔር አይሳነውም ። የእርሱ ወዳጅ ስትሆን አብዝቶ ይባርክሃል በል ቶሎ በል ወንድሜ ዛሬውኑ ከካራን ውጣ እግዚአብሔርንም ይዘህ ጉዞ ወደ ከነዓን ጀምር !!!
         
   ውጣ ውጣ እባክህ ወንድሜ ረፈደ አትበል !ውጣ!!!
          ውጪ ውጪ እህቴ ረፈደ ሳትይ ውጪ !!!
እባካችሁን ወንድም እህቶቼ እንውጣ 🙏
መልዕክቱን ለጓደኞቻችሁም አስተላልፉ ዳግም።
    (ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ )
       ፣ተግባር ላይ ለማዋል እንጠንክር ችላ አንበል። 🥰
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

https://www.tgoop.com/eotcy
እውነት እስኪ ይችን እውነታ አንብቡልኝ

ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታየ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንደት ይሆናል
የሰላምታሽ ድምፅ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና" ሉቃ.፩÷፳-፵፫🙏
#ልብ_በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንደት የተመረጠች ናት
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ቃል አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሏታል ምን አይነት መመረጥ ነው
ሰላምታዋን በሰማ ጊዜ በማሕጸን ያለ ጽንስ እንኳ በደስታ የዘለለ ምን አይነት ቅድስና ነው
@eotcy
ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ኤልሳቤጥ ካመሰገነች ድንግል ማርያምን ፕሮቴስታንት አላመሰግንም የሚል ምን ተሞልቶ ነው
በመልአኩ አንደበት ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የተባለችን እናት እኛም እንደመልአኩ እናመሰግናታለን።
እኛስ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እመቤታችንን
እንዳመሰገነቻች ኤልሳቤት እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እናመሰግናታለን መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እንድትመሰገን
ሲያደርግ አይተናል። የጌታዬ እናት እንላታለን በመንፈስ ቅዱስ ሆና የጌታዬ እናት አንች ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንደት ይሆንልኛል፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፣ የማህጸንሸ ፍሬ የተባረከ ነው.....እያልን እናመሰግናታለን
ይህን ያደረገ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልፅ አይተናልና።
@eotcy
ሰማያዊ መልአክና ምድራዊት ሴት ተባብረው በአንድ ቃል በአንድ መንፈስ ቅዱስ ያመሰገኗትን አላመሰግንም የሚሉ በምን መንፈስ ሆነው ነውመንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን አስመሰገነ እንጅ ሲከለክል አላየንም። አላመሰግንም የሚሉ ከምን እንዳገኙት እንኳ አይነግሩንም።
ሰይጣንና ክፉ የገንዘብ ፍቅር ክብሯን ሸፍኖባቸዋልና።
እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተረዳነው እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳጼጥ እናመሰግናታለን።
ሁላችችንም እንደ ቅዱስ ዮሐንስ በእምነት ወደቤታችን ወስደናታል

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
"ባልሽን የገደልሽው መርዟ አንች ነሽ"

ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።

ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦ "እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።

እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ"። አለቻት።

ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"

እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦

1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ

2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ

3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው

4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር ታዘዥው

5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ

6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይው ድረስ ብቻ ነው።

እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።

ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።

እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽ ስጭው" አለች።

ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"

እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት

ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለ ፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።

እናትየዋ፦  ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላው ሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውን ትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠት ያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽ የምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።
ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ ፍቅር ስጭው!

እንዲህ በጥበብ ትዳርን የሚያክል ተቋም የሚታደጉ እናቶችን፣ አባቶችን እግዚአብሔር ያብዛልን።አሜን!

ብታጋሩት መልካም ታደርጋላችሁ።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy
@eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/06/28 10:52:07
Back to Top
HTML Embed Code: