Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ተስፋ_የለኝም_አትበሉ

በአንድ ወቅት በዝሙት ስራዋ በከተማው የምትታወቅ ሴት የምታገኘውን ገንዘብ ትመጸውት ነበር። ቅዱስ አባ #ጳውሚን ይህን ተግባሯን ሰምቶ ሰዎችን ማጠያየቅ ጀመረ። እንዴት ነች ይህን መጥፎ  ስራዎን ትታለችን? ለውጥ አላት? ቢላቸው ነገሩን አጋነው ከራሷ አልፋ ሰዎችንም ቀጥራ ቀሚ መተዳደርያዋ እንዳደረገችው ነገሩት። ይህቺ ሴት ወደ እዚህ ቅዱስ አባት መምጣት እንደምትፈልግና እንዲጸልይላት እንደምትፈልግ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ተፀይፈዋት እንዳላመጧትም ደረሰበት።

ይህ አባት ካለችበት ቦታ ሄደ። ከዚህ በፊት #የእግዚአብሔርን ቃል ሲጸልይ ሰምታ ስለነበር እንዳየችው #እግሩ_ስር_ወድቃ_ማልቀስ_ጀመረች#እግዚአብሔር ይቅር እንዲለኝ ጸልይልኝ፣ ከአሁን ጀምሮ እከተልሃለሁ እያለች አምራ አለቀሰች። እሱን ተከትላ ወደ ሴቶች ገዳም ገባች። በምንኩስና መላ ዘመኗን #እግዚአብሔርን አገለገለች።
        🟢🟡🔴
#ተስፋ_የለኝም: #እግዚአብሔር አይምረኝም አትበል (ይ)
ማንም ይሁን ማንነትህ አንተን የሚወድህ #እግዚአብሔር_ይቅር_ይልሃል ተስፋ አትቁረጥ።
ዱርዬ ነው: ጸጉሩን ይፈትላል: ሱሪውን ዝቅ ያደርጋል: ሜካፕ ታበዛለች: ሱሪ ትለብሳለች በሚል መደምደሚያ ከምንፈርድባቸው በፍቅር እናቅርባቸው እመኑኝ ከእኛ የተሻሉ ታዋቂ ክርስቲያኖች ይሆናሉ።

የምንሰጠው ምጽዋት ከእኛ ንፉግነት ሰርተህ አትበላም?
እጅ እግር እያለህ ብለን እየተሳደብን የሰጠነው ሳይሆን በፍቅር የሰጠነው ምጽዋት በሰማይ ዋጋ አለው
#ቆርኔሌዎስ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ። ሐዋ 10፣2

መልካም  ቀን ይሁንላቹ
           🟢🟡🔴
            @eotcy
            @eotcy
            @eotcy
+ረፈደ አትበል+

ሰይጣን እኛን ከሚያዘናጋበት መንገድ አንዱ ወደ ጽድቅ የምትሄድበት ጊዜ አሁን ረፍዷል "አሁን እኮ ትዳር መስርተሃል"ብዙ ሀላፊነት አለብህ "ደግሞም ብዙ ጓደኞች አፍርተሃል"እነሱን ትተህ ወዴት ትሄዳለህ?መፅሐፋም እሚለው በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ነው ሆኖም ግን አንተ ወጣትነትህን በአጋጉል ቦታ አሳልፈኸዋል "አሁን በቃ መንፈሳዊነት ካንተ protocol ጋር አይሄድም ፣በዚያ ላይ ያልሰራኸው ሀጢያት የለም ፣እንዴት ፈጣሪስ ይቅር ይልሀል ? እያለ ከተተበተብንበት የሀጢአት እስራት እንዳንወጣ የተቻለውን ያደርግል። እኛም ደግሞ ከዚህ ለመውጣት የተቻለንን አናደርግም! 😓


ወንድሜ ስማኝማ ልንገርህ አብርሃም የሀጢአት ምሳሌ ከሆነችው ከካራን በ 75 አመቱ ነው ነበር የወጣው፣ ከአገርህ ከዘመዶችህ ከአባትህ ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ሲለው ምክንያት አልደረደረም ፣እሺ ብሎ ነው የወጣው ። ወንድሜ በሃጢአት ያረጀህ ከመሰለህ ፣እንደ አብርሃም 75 ዓመት አልሞላህምና ተቻኩለህ ቶሎ ውጣ ፤ እንደ ሀገር መኖርያ ካደረከው በደል ቶሎ ውጣ !አባትና እናትህን ማክበር አስትተው አባት እና እናት ከሆኑብህ ኃጢያቶች ቶሎ ውጣ!!

ብቻ አንተ ውጣ እንጂ ፣ አንተን ታላቅ ሕዝብ ማድረግ ፣ ከነዓን ማስገባት ለእግዚአብሔር አይሳነውም ። የእርሱ ወዳጅ ስትሆን አብዝቶ ይባርክሃል በል ቶሎ በል ወንድሜ ዛሬውኑ ከካራን ውጣ እግዚአብሔርንም ይዘህ ጉዞ ወደ ከነዓን ጀምር !!!
         
   ውጣ ውጣ እባክህ ወንድሜ ረፈደ አትበል !ውጣ!!!
          ውጪ ውጪ እህቴ ረፈደ ሳትይ ውጪ !!!
እባካችሁን ወንድም እህቶቼ እንውጣ 🙏
መልዕክቱን ለጓደኞቻችሁም አስተላልፉ ዳግም።
    (ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ )
       ፣ተግባር ላይ ለማዋል እንጠንክር ችላ አንበል። 🥰

https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንተ ሰው  ይሔንን ጹሑፍ አንብብ

ከዓለም አታላይ እንቅልፍ ይነቃል 👇👇

ሰው የሆነ ሁሉ ያንብበው
ሰው ሆይ እሞታለሁ ብለህ ታስባለህ
ለመኖር ብለህ ትዋሻለህ
ለመብላት ብለህ ትሰርቃለህ
ለእርካታ ብለህ ትዘሙታለህ
ሀብታም ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለህም
እኖራለሁ ብለህ ግንብ ትገነባለህ ቤት ትሰራለህ
አውቃለሁ ብለህ ትማራለህ
እወልዳለሁ ብለህ ታገባለህ አልመች ሲልህ ትፈታለህ
በእግሬ አልሄድም ብለህ መኪና ትገዛለህ
ሚስት ከቤት እያለችህ ከውጪ ትመኛለህ
አንድ ወልደህ ከሆነ ሁለተኛ ታስባለህ
ዲፕሎማ ካለህ ለዲግሪ ትማራለህ
ድግሪ ካለህ ለማስትሬት ትማራለህ
ማስትሬት ካለህ ለፒአች ዲ ትማራለህ
አንድ ቤት ካለህ ሁለተኛ ቤት ታስባለህ
አንድ መኪና ካለህ ሌላ መኪና ያምርሃል
ክፍለ ሃገር ካለህ አዲስ ለመኖር ታስባለህ
አድስ አበባ ከሆንክ አውሮፓ አሜሪካ ትመኛለህ
አሜሪካ ከሆንክ ሌላ ፕላኒት ለማየት ትጓጓለህ
ትንሽ ስልጣን ካለህ ትልቅ ስልጣት ትመኛለህ
የቀበሌ ሊቀመንበር ከሆን የወረዳ አስተዳደር ለመሆን ታስባለህ
የወረዳ አስተዳደር ከሆንክ የዞን ሀላፊ መሆን ያምርሀል
የዞን ሀላፊ ከሆንክ የክልል ርእሰ መስተዳድር ለመሆን ትሮጣለህ
የክልል እርሰ መስተዳድር ከሆንክ ሚንስቴር ለመሆን ታስባለህ
ሚንስቴር ከሆንክ ጠቅላይ ፕሬዝዳንት መሆን ያምርሀል
ዲያቆን ከሆንክ ቄስ መሆን ያምርሃል
መነኩሴ ከሆንክ ጳጳስ መሆን ትፈልጋለህ

ወዳጄ ሆይ የምትሞትበትን ቀን ታስባለህ

መቼ ነው የምሞተው ብለህ ታወቃለህ

አንተ እኮ 🫵የዛሬ ነህ የነገን አታውቅም
ግን ስለ ነገ ብዙ ታስባለህ

ወዳጄ ሆይ ከፈጣሪህ ፊት የሚያስቆክ ስራ ሰርተሃል

በየት በኩል ነው የምቆመው ብለህ ታውቃለህ
በግራ ነው ወይስ በቀኝ የምትቆመው ስራህ በየት ነው የሚያቆምህ
ሞት ሳይቀድምህ ዛሬውኑ ወስን
እየተዘናጋና ለሥጋ ብቻ ስትኖር ለነፍስህ ሳትኖር እንዳትሞት
ለመጽደቅም ለመኮነንም የስራህ ውጤት ነው
መልካም ከሰራህ የጽድቅ ልጅ ነህ
ክፉ ከሰራህ የኃጢአት ልጅ ነህ
በምድር ያለው ነገር ሁሉ ከሞት አያድንም
ዝናህ ሀብትህ እውቀትህ ስልጣንህ ሁሉ ምድራዊ ነው

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

@eotcy
@eotcy
ክርስቲያናዊ አለባበስ

         አንብቡት ይጠቅማቹሃን👇

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ስለ አለባበሳችን እንወያያለን ዛሬም እህቶቻችን ላይ እናተኩራለን አበዛኸው ምነው እኛን ብቻ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው፡፡

ስለ አለባበስ መነጋገር ያስፈለገን እውነተኛ ክርስቲያን በአነጋገሩ፣ በአረማመዱ፣ በአመጋገቡ፣ በአለባበሱ፣ ብቻ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆን ስላለበት ነው ይኸውም ሁሉን በአግባብና በሥርዓት ስለማድረግ ነው እህቶቻችን ላይ ማተኮር ያስፈለገው ደግሞ በአብዛኛው በዚህ ረገድ ትችት የሚበዛው እነሱ ላይ ስለሆነ ነው፡፡

እነሆ ውድድሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረና እየከፋ ነው ለመልካም ነገር መወዳደር ባልከፋ ነገር ግን በከተማችን በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የምናየው የእህቶቻችን አለባበስ አንዷ ከሌላዋ ልቃና በልጣ ለመታየት የሚደረግ ግብግብ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ በእርግጥ እህቶቻችን በዚህ እንደማይስማሙ እናውቃለን አብዛኞቹም ስለተመቸኝና የምወደው አይነት አለባበስ ስለሆነ ነው እንዲህ የምለብሰው ይሉናል ይሁን እንጂ እውነታው ሌላ ይመስላል ምክንያቱም:-

* ብርድልብስ ለብሰን እንኳን በማንቋቋመው የብርድ ወቅት ሰውነትን በቅጡ የማይሸፍን ብጣሽ ጨርቅ ጣል አድርጎ መውጣት እንዴት ያለ ምቾት ነው?

*እጅግ አስጨናቂ ሙቀት ባለበት ሰዓት ሰውነት ላይ ተጣብቆ ሌላ ጭንቀት የሚፈጥር አለባበስ እንደምን ብሎ ያስደስታል?

ዓላማችን ምንም ይሁን እሱ ላይ የመከራከር ፍላጎት የለንም ነገር ግን አለባበሳችንን እንደ ክርስቲያን እንፈትሸው ዘንድ ይገባልና ይህ ተፃፈ

መሰልጠን ወይስ መሰይጠን?

አብዛኞቹ ሴቶች ይህን ተግባር ስልጣኔ እንጂ ስህተት ነው ብለው አያምኑም፡፡ ለነዚህ ሴቶች ከኃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከባህላችን ጭምር ያፈነገጠውን የምዕራባውያን አለባበስ መልበስ ዘመናዊነት ነው፡፡ ላንቺስ? መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል?

    ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ መሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ እርግጥ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊ ህይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢያት አጋልጦ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት አይቻልም እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ የሚለውን ጭምር ነውና በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢያት ነው፡-

“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡” ማቴ. 18፡6

አንዳንድ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል

“እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው፡፡” ትን.ሶፎ. 1፡18

እንግዲህ የሴቶቹን እንቀበል ወይስ የእግዚአብሔርን ምርጫው ያንቺው ነው እህቴ መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል፡- “ከስው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል፡፡” የሐዋ. 5፡29

በሴቶችና በወንዶች መካከል የአለባበስ ልዩነት ሊኖር ይገባል

“ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ታዲያ ቀሚስን የወንድ ሱሪን የሴት ማን አደረገው? ይህ የሰነፍና ለስህተታቸው ምክንያትን የሚሹ ሴቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል አውቀን ልንፈፅመው እንጂ በቃሉ ላይ የምንፍቅና ጥያቄ እናነሳ ዘንድ ተገቢ አይደለም ግን ደግሞ ተፈጥሯችንን ብቻ በማየት ህሊናችን እራሱ ቢናገር ሱሪ የሴት ነውን? ቀሚስስ የወንድ ነው እንዴ “ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን? 1ኛ ቆሮ. 11፡14

ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም፡፡” 1ኛ. ቆሮ. 11፡16

ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም ክርስትና በምርጫ ነውና፡፡

በፊትህ እሳትና ውሃን አኑሬአለው ወደ ወደድከው እጅህ ክተት፡፡” ሲራ. 15፡15

እዚህ ላይ ግን ቀሚስ ሲባል ከውስጥ ሱሪ የማይሻለውን ብጣሽ ጨርቅ እንዲሁም ቁመቱ ረዥም ሆኖ ከሰውነት ጋር የሚጣበቀውን አይነት አለባበስ ማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል፡፡

https://www.tgoop.com/eotcy

እህቶቻችን ሆይ ማስተዋልን ትላበሱ ዘንድ እንለምናችኋለን መሰልጠንና መሰይጠንም ትለዩ ዘንድ ይሁን ሰውነትሽ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነውና ሁሉን በአግባብና በሥርዓት አድርጊለት፡፡

ደግሞም ክርስትና ራስ ወዳድነትን አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላው ሰው ልናስብ ያስፈልገናል እኛስ ሰውን ወደ ዝሙት ሊያመራው ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨነቅን ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ወንድማችንን ስለማሰናከል ምን አለ

መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም፡፡” 1ኛ.ቆሮ 8፡13

https://www.tgoop.com/eotcy
እንግዲህ ክርስትና እዚህ ድረስ ነው ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ወንድሞችና እህቶቻችን የምናስብባት ለእነሱም መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን ሁሉን በአግባብና በሥርዓት የምናደርግባት፤ እምነታችንን በምግባር የምንገልጽባት ናት፡፡

በእውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን፡፡ ትን.ኤር. 13፡27

እህቴ ሆይ አንቺም ኤርሚያስ እንዳለው ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቂ የምዕራባውያን በዓል ከሆነው አለባበስም ሆነ የምንዝር ጌጥ ራስሽን አርቀሽ በሚያኮራው ኢትየጵያዊ ባህላችን ትዋቢ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡

ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡ አሜን!!!!

ሁላችን ምግባር ያለው እምነት እንዲኖረን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!!!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቀደመችው እውነተኛይቱ መንገድ!!!

      የቅዱሳን አምላክ ማስተዋል ይስጠን 🤲

ወ ስ ብ ሐ ት   ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ   ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ   ክ ብ ር   አ ሜ ን  🤲
የምንለወጠው ምን ስናደርግ ነው

በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደ በረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰ'ሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም !

“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ ፈጽመው ሊወገዱ እንደ ማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

@eotcy
በዝምታው ፥ በቅድስና ሕይወቱና በብቸኝነት የሚታወቁት ጻዲቅ ዝምተኛው መነኩሴ "አባ ዮስጦስ" በገዳመ እንጦስ ከተናገሯቸው በጥቂቱ፦

<ስለ ዝምታ>

☞ ከማድረግ መናገር ይቀላል ነገር ግን ልብ ወደ ሰማይ የሚወጣው በመናገር አይደለም ፤ ወደ ጌታችን መቅረብ የምትችለው በቃላት አይደለም፡፡

☞ አንዳንድ ጊዜ ዝምተኛ ነኝ ነገር ግን ዝምታዬ ከእንባዬ ይልቅ ኃይል እንዳለው ይሰማኛል፡፡

☞ ዝምተኛ ብሆንም ልቤ ግን በቃላት የተሞላ ስለሆነ እግዚአብሔር ሳልናገር ይሰማቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ልብ ግን የርኅራኄ ፏፏቴ ነው፡፡

☞ ቅድስና ቆሽሾ ከመታየት ጋር የማገናኘው ነገር የለም ፤ ከልብ ንጽሕና ጋር እንጂ፡፡

☞ ማናችንም በራሳችን መልካም አይደለንምና ፤ የእግዚአብሔር ምሕረት ያስፈልገናል፡፡

☞ እኔ መነኩሴ ስለሆንኩ ከእናንተ የምሻል ይመስላችኃል? አልሻልም ፥ጠባቡ በር ግን በመስቀል የተሞላ ነው ፤ለእያንዳንዱ ሰው አንድ መከራ አለው፡፡

☞ እግዚአብሔር ግን ሁላችንንም ይፈልገናል ፤ እርሱ ማናችንንም ከእርሱ ተነጥለን እንድንጣል አይፈልግምና፡፡

☞ እኔ ግን ማድረግ የምችለው ብቸኛ ነገር ዝምታ መማሬ ነው ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ፡፡

  <"አሁን ስንት ሰዓት ነው?????????>"

አባ ዮስጦስ ዝምተኛው መነኩሴ
የአባታችን በረከት አትለየን፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
💀 የሰይጣን ለቅሶ 💀
አንድ ለመመንኮስ የፈለገ ወጣኒ ወደ አበመኔቱ ይሄድና እንዲያመነኩሰው ይጠይቀዋል አበመኔቱም እንዳመነኩስህ ከፈለክ ሂድና በእስክንድርያ አደባባዮች እኔ ዘማዊ ነኝ እያልክ ለመንገደኛው ሁሉ ንገር ይለዋል ይህም ወጣት እንደታዘዘው ሲያደርግ ውሎ በነጋታው ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲገባ በዚያ የተሰበሰቡት ሁሉ "አንተ ዘማዊ እያሉ አፌዙበት
አበመኔቱም "አዎ አንተ ሀጢያተኛ ነህ" ብሎ አስወጣው ወጣቱም ምንም ሳይናገር ወጣ ይህ ወጣት ከወጣ በኋላ ግን አበመኔቱ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እንዲህ አላቸው
👉"በትክክል ለምንኩስና የታጨች ነፍስ ይህቺ ናት እናንተ ስትስቁበት አጋንንት ግን ሲያለቅሱ አያቸው ነበር፣ እኛ ሀጢአቱን ስንዘረዝር መላእክት ግን ስሙን በብርሃን መዝገብ ሲፅፉት ተመለከትኩ አላቸው፣
ያንንም ወጣት ጠርቶ አመነኮሰው
👉ብዙ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን ፣ ከመንፈሳዊ አገልግሎት፣ ከበጎ ስራ ከሚያርቁት ነገሮች ዋነኞቹ ትችት እና ሀሜት ነው ብንል ማጋነን አይሆንም በተለይ ደግሞ ለመንፈሳዊ ተግባር አዲስ የሆኑትን እስከመጨረሻው ላያስመልስ የሚችል ተግባር ነው
👉ወዳጄ የቱንም ያህል ብትሰደብ ፤ የቱንም ያህል ብትናቅ፤ የቱንም ያህል ሰዎች ተሰብስበው ስላንተ ቢያወሩ ፤ በተሰደብከው ልክ ክብርህም ይጨምራልና ከደጁ እንዳትርቅ
👉አንቺን ብሎ ጸሎተኛ ፤ አንቺን ብሎ ጾመኛ፤ አንቺን ብሎ ዘማሪ ፤አንቺን ብሎ ቤተክርስቲያን ተሳላሚ ፤ አንቺን ብሎ ቆራቢ ፤ .......ብዙ ብዙ ነገር እያሉ ሊያሸማቅቁሽ ቢሞክሩ ከመንገድሽ እንዳትወጪ ሰዎች በሳቁብሽ ልክ ፈታኝሽ ዲያቢሎስ ያለቅሳልና
👉 እናንተም ፈራጆች ሆይ ሰው ላይ ስትፈርዱ ሰይጣን በናንተ ይስቃል፣ የሰውን ሀጢአት ስትመዘግቡ ሰይጣን በደስታ የናንተን ሀጢአት ይፅፈዋል
ስለዚህ ለወዳጆችህ እየፀለይክ ሰይጣንን አስለቅሰው
በቅዱስ መስቀሉ ጠላታችን ዲያብሎስን ከእግራችን በታች ይጣልልን
አሜን 🙏
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+• ጊዜው ገና ነው •+

አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከዕለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ። 

አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱም አይሠራም። ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላው ደግሞ ተነሳና፥ “እኔን ላከኝ። ፈጣሪም አለ፥ ገነትም አለ፥ ሲኦልም አለ፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ።” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል።

ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ፥ ለማዘግየት ይፋጠናል። በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።” (1 ተሰ 2:18) ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል፥ ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል።

እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም። ስለ ጸሎት ብታስብ፥ "አሁን ደክሞሃል። ጊዜው አይደለም። ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል። ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ። የምትጾምበት ጊዜ አይደለም፤ ሌላ ጊዜ ትጾማለህ።" ይልሃል። ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ፤ ጊዜው አይደለም፥ ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል። ንስሃ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ፥ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም። ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ፥ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል።
🟢🟡🔴
በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ፥ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) እንደሚል እናስታውስ። ለመዳናችን ቀጠሮ አንስጥ።

----------

https://www.tgoop.com/eotcy
+++ የዘመኑ ፈተና... +++

የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?

  ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ?

በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!

እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡

ያም ጸጉር ተስተካካይ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚህ ደግሞ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››

‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2

ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!

https://www.tgoop.com/eotcy
#አምናለሁ_እና_አላምንም +

ልጁ የታመመበት አባት ነው። ጌታን " #ቢቻልህስ_ልጄን_ፈውስልኝ " አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።

ይህን ጊዜ ሰውዬው  " #ወዲያውም_የብላቴናው_አባት_ጮኾ#አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24

የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው "

ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም

ያምናል እንዳንል " #አለማመኔን " ይላል ፤ አያምንም እንዳንል " #አምናለሁ " ይላል። የቸገረ ነገር ነው ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም  ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው " የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::

እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው #የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::

አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ  "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::

ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ #አላውቀውም:: #የምተርከው_ክርስቶስ_እንጂ_የሚተረክ_ክርስትና_የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::

#መች_በዚህ_ያበቃል::

እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢኃት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::🙏

እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው::🙏
ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው🙏 እላለሁ::

እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ?
ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም:: 😭

ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው::🙏
እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው::🙏
አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው::🙏
እማራለሁ አለመማሬን እርዳው::🙏
ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ #ሼር

@eotcy
@eotcy
@eotcy
2025/01/10 02:25:45
Back to Top
HTML Embed Code: