Telegram Web
ጉድለትህን ተጠቀምበት

ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶሰን ለማግኘት ተቸገረ። ሕዝቡ ብዙ ነው የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት። የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው።

እሱ ዛፍ ላይ ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም። ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኪዎስን ጠራው።

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው።
"ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው። ጌታ ወደ ቤቱ ገባ ለዘኪዎስ ቤት መዳን ሆነለት።

ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር። ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሊጣላ ሊቆይ ይችል ነበር።

ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር።
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉስ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው። የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር።
እግዚአብሔር የማዳኑን ቀን የቆጠረለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር። በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው።

ስለ ቁመቱ የማወራ እንዳይመስልህ።
ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ። እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም።

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም እሱን ማለቴ ነው። ይሄ ይጎለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር እጥረትህ መክበሪያህ ነው። ጉድለትህም መዳኛህ ነው።
ችግሮችህ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምታባቸው መስታዎቶችህ ናቸው

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን። በጉድለትህ እንደ ዘኪዎስ ከፍ በልበት። ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም።
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ።
በቤትህ መዳን ይሆንልሀል፡፡ ከዚያም ስላጠረህ ስለተጎዳህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ።

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው። ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2


@eotcy
@eotcy
@eotcy
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች በረሃ ውስጥ እየተጓዙ እያሉ ድንገት አለመግባባት ተፈጠረና አንደኛው አንደኛውን በጥፊ ይመታዋል። የተመታው ጥፊው ቢያመውም ምንም ሳይናገር ዝም አለና
አሸዋው ላይ ዛሬ የምወደው ጓደኛየ በጥፊ መታኝ ብሎ ፃፈ ከዛም እየተጓዙ እያሉ ትልቅ ባህር ያለበት ወንዝ ያገኙና መታጠብ ፈልገው ይገባሉ እየዋኙ እያሉ ያ በጥፊ የተመታው ልጅ ይሰምጣል በዚህ ስዓት ጓደኛው እንደምንም ብሎ ሂወቱን ያተርፈዋል ከሞት የተረፈው ልጅ ቋጥኝ ድንጋይ ፈልጎ ድንጋዩ ላይ እየፈለፈለ ዛሬ የምወደው ጓደኛዬ ሕይወቴን አተረፈኝ ብሎ ፃፈ ጓደኛውም ገርሞት ቅድም በጥፊ ስመታህ አሸዋ ላይ ፃፍክ አሁን ከሞት ሳተርፍህ ደግሞ ድንጋይ ላይ ለምን እንደዚህ አደረክ አለው። ጓደኛውም እንዲህ አለው የምንወዳቸው ሰዎች ሲበድሉን በደላችንን የይቅርታ እና የምህረት ንፋስ እንዲያጠፋው አሸዋ ላይ መፃፍ አለብን ጡሩ ነገር ሲያደርጉልን ግን ውለታቸውን እንዳንረሳ ሁሌም እንድናስታውሰው ድንጋይ ላይ መፃፍ አለብን አለው።

ባለህም በሌለህም ነገር ሁሉ አመስግን አንተ አለህና።
ሰላሙን ያምጣልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን
https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሳቹሁ  
 
           ዕርገት

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡

ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡    

እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡


@eotcy
✧━━━━━━━━━━━━━━━✧
     ❍ㅤ            ⎙ㅤ           ⌲                        ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ          ˢᵃᵛᵉ           ˢʰᵃʳᵉ
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
እንኳን አደረሳቹሁ                ዕርገት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ…
እንኳን አደረሳችሁ

ለመባረክም እጁን በሐዋርያቱ ላይ ያኖር ዘንድ ቆመ። ሰውነቱን ከመለኮት ክብር ያሳትፋት ዘንድ ወደላይ ከፍ ከፍ በማለት ራቃቸው። ስለሰው ልጆች ፍቅር በምድር ላይ ያገኛት ያለፈው መከራ ተፈጸመ አሁን ግን ያለመለየት በተዋህዶ በመለኮት ክብር ዐረገ። በአብም ቀኝ ተቀመጠ።

የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለመሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን ታጅቦ ዐረገ መለኮቱ ይተጋለታልና። ወደ አየራትም ነጥቆታልና። ኪሩቤል ሊያሳርጉት አልመጡም። እርሱ ራሱ በመለኮት ኃይል አብን ተካክሎ በቀኝ ተቀመጠባቸው። የማረጉም ምስጋና ለእኛ መሰላል ኾነን።

ከገሊላ ሴት እንደተወለደ በአሰብን ጊዜ ወደ አባቱ እንደአረገ እናስታውሳለን። በድንግል ማርያም ጭኖች እንደታቀፈ ስናስታውሰው በአባቱ እቅፍ እንዳለ እናስባለን። በደብረ ዘይት ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደተቀመጠ ባሰብነው ጊዜ በመላዕክቱ እልልታ እንደ ዐረገ በአባቱም ቀኝ እንደተቀመጠ እናስታውሰዋለን። ከምድር ወደሰማይ የሚያደርሰን የሃይማኖታችን መሰላል እርሱ ነው።

        🌺አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 🌺
     https://www.tgoop.com/eotcy
አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት
አንድ ቀን በምስጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው
መሬት ጠብ..ጠብ አለ። ምእመኖቹ ጨነቃቸው ምን ሆነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው "ጌታዬ ሆይ እባክህ ለቅዱስ ስጋህና ለክቡር ደምህ አብቃኝ" ነበር የሚሉት።

ምእመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም "አንተን ለማገልገል ለስጋና ለደምህ አብቃኝ" እያልኩ ነው። አሏቸው። ምእመኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርሰዎ እኛን እያቆረቡ እንዴት እንድህ ይላሉ አሏቸው። እርሳቸውም "የመስቀሉ ፍቅር ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለግልበት ስጋና ደሙንም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበትን ቀን ነው የምለምነው" ብለው መለሱ።

ወዳጆቼ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ። ለስው የምንሰራ ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። "አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው" እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው አይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን።

አንዳንዶቻችን፦ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መፆም፣ መስገድ፣ መፀለይ፣ መቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ፣ነጠላ መልበስ ግዴታ አልያም ህግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን። መቼ ነው ግን ፍቅሩ ገብቶን ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደረስብናል ብለን ሃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዙ ነን።

አምላክን ፈርተን ሲኦል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን ሁሉ እንተዋለን። ግን ስለ ፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ሃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን? ወገኖቼ እየሰበክን እየዘመርን እያስቀደስንና እየቀደስን ያልዳን አለንና እርሱ ፍቅሩን ይሳልብን።
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ

የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።

የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ  የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።

እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦

ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤  እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።

ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
       እኛ ግን፦
"አማንኬ ይደልወኬ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሊ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።
      ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

Https://www.tgoop.com/eotcy
ከቅዳሴው ማብቂያ ተዐምርሽ ሲነበብ ስሰማ የተፃፈው ያንስብኛል🙏🙏
ብዙዎች ጣዕምሽን ያልቀመሱ ቀምሰው ያላመኑ የካዱ ንጽሕት ሆነሽ ተገኝተሽ  አዳምን ከእስራት እንዳስፈታሽ የረሱ የሄዋንን  ታሪክ እንደቀየርሽ የዘነጉ ጌታ ጌታ እያሉ  እናቱን አንቺን የሚንቁ የሚያናንቁ ለክብርሽ  መንበርከካችን  የሚያስገርማቸው  ለምስጋናሽ ከሚገባሽ በታች  ጎንበስ ማለታችን የሚገርማቸው  ፍቅርሽን ያላጣጣሙት እናትነትሽን የካዱ ንዋይ አታሏቸው አንቺን መውደዳች ተዐምርሽን ሰምተን ለሚመስላቸው እንዴት ብዬ ላሳያቸው ለኔ ያደረግሽው_ለኔ_የሰራሽው በመጽሐፍ የሰፈረው  የተነገረልሽ  ለኔ  ካደረግሽው  እጅጉን  እንደሚያንስ  🙏🙏🙏🙏
ፍቅርሽን ቀምሶ ከመካድ  እናትነትሽን ከመካድ በምልጃሽ ጠብቂን 🙏 ለአዳም እህቱ የኖህ መርከቡ የያዕቆብ መሰላል የጌታዬ የመድኀኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስ  እናቱ  ላንቺ  ክብርና  ምስጋና  ይሁን🙏🙏🙏
ማርያም ሆይ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ምህረትና ይቅርታን አሰጪን🙏🙏
💚💛❤️

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
ሳነብ ካገኘውት ስለወደድኩት ላካፍላችሁ
@eotcy
ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ አበቃህ ወይኔ ባሌ!" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።
@eotcy
ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።
@eotcy
ከዚያም በድል አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ።
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"
" እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።
@eotcy
የሰው ልጅ ጎዶሎ ነው የተሟላ አይደለም፣ ፍፁምነት ለእግዚአብሔር ነው።
ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት ... በሀሳብም በአካልም እንዲሞላሉ ተደርገው ነው ጌታ የፈጠራቸው። አንዱ የጎደለው ሌላው አለው። አንዱ የማይችለዉን ሌላው ይችለዋል ፣ ለአንዱ የማይታየው ለሌላው ይታየዋል።
@eotcy
ለመናናቅ፣ ለመገፋፋትና ለመለካካት ሳይሆን ዓለምን አብረን እንድንኖር፣ ፈተናዎቿንም አብረን እያሸነፍን ወደ  ገነት እንድንጓዝ ነው ፈጣሪ ወደዚህች ምድር ያመጣን።
@eotcy
☞︎︎︎ አንዱ የሌላኛዉን ሀሳብ ጆሮ ሰጥቶ ያዳምጥ፣ አይናናቅ፣ አያጣጥል

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!›› ለምን እንላለ

እነሆ ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ምእመናን በሚቀምሱት የዕለት ምግብ አማካኝነት በነፍስም በሥጋም እንዲድኑ አስገራሚ የምሕረት ቃልኪዳን እንደተቀበሉ የሚናገር የገድል ተአምራታቸው ይህ ነው፡- ብዙዎች ስማቸውን ጠርተው በሚቀምሱት ምግብ አማካኝነት ከተለያዩ በሽታዎች የተፈወሱ አሉ፡፡ ይህ ቃልኪዳናቸው ለኹላችን ይደረግን ዘንድ ከመመገባችን አስቀድሞ የእግዚአብሔርን ስም እንጥራ (አቡነ ዘበሰማያትን ማለቱ ነው፡፡) ከተመገብን በኋላም የዕለት ምግባችንን ስለሰጠን እግዚአብሔርን እናመስግን፡፡ ዘወትር ከተመገብን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹ስለ ወዳጅህ ስለ አቡነ አቢብ›› እያልን ሦስት ጊዜ እንቅመስ፡፡ አስቀድሞ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ አቢብ ተገልጦላቸው ‹‹…ወዳጄ አቢብ ሆይ! የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበልኩትን ሕማማተ መስቀል እያሰብህ ይህንን ሁሉ ገድል ፈጽመሃልና ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ ንዑድ ክቡር ቅዱስ አባታችን አቡነ አቢብም ‹‹ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መቼም ሰው ሁሉ ሳይመገብ አይውልም አያድርምና በተመገበ ጊዜ ስሜን ጠርቶ የተማጸነውን ማርልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አባታችን አቡነ አቢብ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅር ካደነቀ በኋላ ‹‹…ከማዕድ በኋላ ስብሃት ተብሎ የተረፈውን ‹በእንተ አቢብ› ብሎ ሦስት ጊዜ የተመሰገበውን ሰው ሁሉ እምርልሃለሁ›› በማለት ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡

ያልተጠመቀ አረማዊ አሕዛብም እንኳን ቢሆን "ስለ አቡነ አቢብ" ብሎ ከተማጸነ ጌታችንን ያንን ሰው ወደቀናች የእምነት መንገድ ሳይመራውና በንስኃ ሳይጠራው በሞት እንደማይወስደው ለአባታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ለማዳን ትንሽ ምክንያትን የሚፈልግ ያለ ምክንያትም የማያድን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ እስከዘላለም ድረስ ይክበር ይመስገን!

ሰው ተመግቦ እንኳን መዳን እንዲችል ይህን ድንቅ ቃልኪዳን ለአባታችን ሰጥቷቸዋልና በየቀኑ በዚህ ቃልኪዳን እንጠቀምበት፡፡ ተመግበን ከጨረስንና ስብሃት ካልን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹በእንተ አቡነ አቢብ›› ብለን እንቅመስ፡፡
በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 25 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ጻድቁና ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ከቃልኪዳናቸው ረድኤት በረከት ይክፈሉን!
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
(ምንጭ፡- ደብረ ሰላም ቃጭልቃ አቡነ አቢብ ገዳም ያሳተመው ገድለ አቡነ አቢብ፣ ገጽ 105)


https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ማለት ምን ማለት ነው?

ይህ አባባል በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከወንጌል ስብከት፣ ከመዝሙር ከምክር ተግሳጽ በኋላ ምእመናን በአንድነት ላቀረበው አካል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያት ያውርስልን አገልግሎት ዘመንዎትን ያርዝምልን በእድሜ እና በጸጋ ይጠብቅልን ፣ ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን .... ወዘተ እያልን መንፈሳዊ ምርቃን እንመርቃለን! ምን ማለት ነው ቃለ ህይወት ያሰማልን? ቃለ ሕይወትስ ምንድን ነው??
በወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው፣ ለሥም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ (ዮሐ.14:15) እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ በሃይማኖት ኑሩ ጎልምሱም.....(1ኛቆሮ 16:13) በሃይማኖት ጤናማ
(ቲቶ 1:13-14) ሆናችሁ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት እንደሆንኩ በእኔ አምናችሁ ለነፍሳችሁ እረፍት አግኙ
(ማቴ.11:29)..... ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ... እስክመጣ ድረስ ትእዛዜን ጠብቁ ያለውን ይዘው በሃይማኖት ኖረው መልካም ተጋድሎን አድርገው  በጌታ ለኖሩ በእሱና በቃሉ ላላፈሩ (ሉቃ.9:26) ንስሀ ገብተው ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው ለዘለዓለም ሕይወት ራሳቸውን ላዘጋጁ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ እንዳለ
(ዮሐ.15:10) በፍቅሩ ለኖሩ በመጨረሻም ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሥራችሁ ለመክፈል (ራዕ.23:32) እስክመጣ ድረስ በፍቅር ኑሩ ያለውን ለፈፀሙ ...በአጠቃላይ በጌታ ለኖሩ ፍሬዎች የሰው ልጅ በክብር በሚመጣበት ጊዜ (ማቴ.25:31) በጎቹን ፍየሎቹን በሚለይበት ጊዜ (ማቴ.25:34) ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
ብሎ ጌታ የሚፈርደው ፍርድ የሕይወት ቃል ይባላል።
ሥለዚህ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ማለት ይህን የተወደደ ለዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጥ ቃል ያሰማልን፤
በቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ይደምርልን እንደማለት ነው፤
ግሩም ምርቃት! አሜን እኛንም የጥምቀት ልጆቹን በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር ይደምረን።
https://www.tgoop.com/eotcy
ምክረ አበው

የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።(መጽሐፈ ምክር)

"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል። (አረጋዊ መንፈሳዊ)

ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)

‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/

‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/

‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/

‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/

‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/

‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/

‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››  /ቅዱስ እንጦስ/
"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል። (አረጋዊ መንፈሳዊ)

ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)

‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/

‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/

‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/

‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/

‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/

‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››  /ቅዱስ እንጦስ/
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ፤ (#በዓለ_ሃምሳ )

በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ #ሰኔ 16 #ቅዳሜ_ለእሑድ_አጥቢያ_በኹሉም_ገዳማትና_አድባራት_ይከበራል፤ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል፤ በአዲስ አበባ #በብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ፣(ዊንጌት) #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስ_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ) ና በምሁር አክሊል ፤ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡
#በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ.ክ ንም ይከበራል ፡ ተጨማሪ ከታች......

፠ ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል /መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫/፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስን ምዕመናንንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡

#በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ  በዓሃምሳ በብሉይ
እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤
፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡
፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡
፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡

፠ ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡

#አማናዊ_ትርጓሜ_በሐዲስ ( አማናዊ ትርጓሜ በሐዲስ)
፠ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡ በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡
፠ የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡  ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡

፠ ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፤ ‹‹ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን›› በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
@eotcy
#ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ
፠ ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው:  /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡
@eotcy
#መንፈስ_ቅዱስ
፠ መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ፥ የሚቀደስ፥ የሚወደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ አካላዊ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፥ አይወልድም፥ አይወለድም፡፡
@eotcy
በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው  /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር፥ ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብ ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡
@eotcy
እውነተኛ ማንነታችን በስም ፣ በማዕረግ በዕውቀት ፣ በዕድሜ....ተሸፍኖ ሊኖር ይችላል፣ ዛሬ ብዙዎቻችን ጋር ያለው ከልብ ያልኾነ የማስመሰል ክርስትና ነው።

ቤተ ክርስቲያን ሄደን
ስለ ተሳለምን
ስለ ተማርን
ስላስተማርን
ስላስቀደስን
ስላነበብን
ስለ ዘመርን
ገዳማት ስለጎበኘን
ስላደነቅን

ክርስትናን እየኖርን ከመሰለን ተሳስተናል።

ይኽ የሥርዓተ አምልኮ ክፍል እንጂ ፣ በራሱ ብቻውን ክርስትናዊ ሕይወት መገለጫ አይደለም።

የተክል ፍሬ እንዲያፈራ
ውሃ፣
አፈር
የፀሐይ ብርሐን እንደሚያስፈልገው፣

ከላይ የተዘረዘሩትን (መሳለሙ ፣ ማገልገሉ)
መንፈሳዊ ፍሬ እንዲናፈራ የሚያደርገን ናቸው እንጂ በራሳቸው ግብ አይደሉም።

አብዛኞቻችን ግን በእነዚህ ብቻ ታጥረን (ረክተን) ቆመናል)

የክርስትና / የመንፈሳዊ ሕይወት መገለጫው
ፍቅር፣
ቅድስና፣
ንጽሕና፣
ትሕትና፣
ትዕግስት፣
ቅንነት፣
ይቅር ባይነት፣
በሌላ አለመፍረድ፣
.....የመሳሰሉት ናቸው።

በመመላለሳችን እነዚህ ኹሉ ከሌሉ (ቢያንስ ለመተግበር ካልቀረብን) የክርስትና ጭምብልን አጥብቀን እየተወንን እንጂ ክርስትናን እየኖርነው አይደለም።

ብርሃን ከጨለማ በቀላሉ እንደሚለይ ክርስትናንም በግብሩ (በምግባሩ) በሥራው ከአሕዛብ በቀላሉ ይለያል።

መለያው ደግሞ "ሕይወቱ" እንጂ የአገልግሎት ተሳትፎው አይደለም።

ይሄን ለይተን ክርስትናን የምንተገብርበት ጥበብ ያድለን
ብርሃን
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ክርስቲያናዊ አለባበስ

         አንብቡት ይጠቅማቹሃን👇

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ስለ አለባበሳችን እንወያያለን ዛሬም እህቶቻችን ላይ እናተኩራለን አበዛኸው ምነው እኛን ብቻ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው፡፡

ስለ አለባበስ መነጋገር ያስፈለገን እውነተኛ ክርስቲያን በአነጋገሩ፣ በአረማመዱ፣ በአመጋገቡ፣ በአለባበሱ፣ ብቻ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆን ስላለበት ነው ይኸውም ሁሉን በአግባብና በሥርዓት ስለማድረግ ነው እህቶቻችን ላይ ማተኮር ያስፈለገው ደግሞ በአብዛኛው በዚህ ረገድ ትችት የሚበዛው እነሱ ላይ ስለሆነ ነው፡፡

እነሆ ውድድሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረና እየከፋ ነው ለመልካም ነገር መወዳደር ባልከፋ ነገር ግን በከተማችን በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የምናየው የእህቶቻችን አለባበስ አንዷ ከሌላዋ ልቃና በልጣ ለመታየት የሚደረግ ግብግብ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ በእርግጥ እህቶቻችን በዚህ እንደማይስማሙ እናውቃለን አብዛኞቹም ስለተመቸኝና የምወደው አይነት አለባበስ ስለሆነ ነው እንዲህ የምለብሰው ይሉናል ይሁን እንጂ እውነታው ሌላ ይመስላል ምክንያቱም:-

* ብርድልብስ ለብሰን እንኳን በማንቋቋመው የብርድ ወቅት ሰውነትን በቅጡ የማይሸፍን ብጣሽ ጨርቅ ጣል አድርጎ መውጣት እንዴት ያለ ምቾት ነው?

*እጅግ አስጨናቂ ሙቀት ባለበት ሰዓት ሰውነት ላይ ተጣብቆ ሌላ ጭንቀት የሚፈጥር አለባበስ እንደምን ብሎ ያስደስታል?

ዓላማችን ምንም ይሁን እሱ ላይ የመከራከር ፍላጎት የለንም ነገር ግን አለባበሳችንን እንደ ክርስቲያን እንፈትሸው ዘንድ ይገባልና ይህ ተፃፈ

መሰልጠን ወይስ መሰይጠን?

አብዛኞቹ ሴቶች ይህን ተግባር ስልጣኔ እንጂ ስህተት ነው ብለው አያምኑም፡፡ ለነዚህ ሴቶች ከኃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከባህላችን ጭምር ያፈነገጠውን የምዕራባውያን አለባበስ መልበስ ዘመናዊነት ነው፡፡ ላንቺስ? መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል?

    ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ መሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ እርግጥ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊ ህይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢያት አጋልጦ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት አይቻልም እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ የሚለውን ጭምር ነውና በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢያት ነው፡-

“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡” ማቴ. 18፡6

አንዳንድ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል

“እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው፡፡” ትን.ሶፎ. 1፡18

እንግዲህ የሴቶቹን እንቀበል ወይስ የእግዚአብሔርን ምርጫው ያንቺው ነው እህቴ መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል፡- “ከስው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል፡፡” የሐዋ. 5፡29

በሴቶችና በወንዶች መካከል የአለባበስ ልዩነት ሊኖር ይገባል

“ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ታዲያ ቀሚስን የወንድ ሱሪን የሴት ማን አደረገው? ይህ የሰነፍና ለስህተታቸው ምክንያትን የሚሹ ሴቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል አውቀን ልንፈፅመው እንጂ በቃሉ ላይ የምንፍቅና ጥያቄ እናነሳ ዘንድ ተገቢ አይደለም ግን ደግሞ ተፈጥሯችንን ብቻ በማየት ህሊናችን እራሱ ቢናገር ሱሪ የሴት ነውን? ቀሚስስ የወንድ ነው እንዴ “ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን? 1ኛ ቆሮ. 11፡14

ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም፡፡” 1ኛ. ቆሮ. 11፡16

ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም ክርስትና በምርጫ ነውና፡፡

በፊትህ እሳትና ውሃን አኑሬአለው ወደ ወደድከው እጅህ ክተት፡፡” ሲራ. 15፡15

እዚህ ላይ ግን ቀሚስ ሲባል ከውስጥ ሱሪ የማይሻለውን ብጣሽ ጨርቅ እንዲሁም ቁመቱ ረዥም ሆኖ ከሰውነት ጋር የሚጣበቀውን አይነት አለባበስ ማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል፡፡

https://www.tgoop.com/eotcy

እህቶቻችን ሆይ ማስተዋልን ትላበሱ ዘንድ እንለምናችኋለን መሰልጠንና መሰይጠንም ትለዩ ዘንድ ይሁን ሰውነትሽ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነውና ሁሉን በአግባብና በሥርዓት አድርጊለት፡፡

ደግሞም ክርስትና ራስ ወዳድነትን አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላው ሰው ልናስብ ያስፈልገናል እኛስ ሰውን ወደ ዝሙት ሊያመራው ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨነቅን ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ወንድማችንን ስለማሰናከል ምን አለ

መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም፡፡” 1ኛ.ቆሮ 8፡13

https://www.tgoop.com/eotcy
እንግዲህ ክርስትና እዚህ ድረስ ነው ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ወንድሞችና እህቶቻችን የምናስብባት ለእነሱም መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን ሁሉን በአግባብና በሥርዓት የምናደርግባት፤ እምነታችንን በምግባር የምንገልጽባት ናት፡፡

በእውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን፡፡ ትን.ኤር. 13፡27

እህቴ ሆይ አንቺም ኤርሚያስ እንዳለው ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቂ የምዕራባውያን በዓል ከሆነው አለባበስም ሆነ የምንዝር ጌጥ ራስሽን አርቀሽ በሚያኮራው ኢትየጵያዊ ባህላችን ትዋቢ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡

ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡ አሜን!!!!

ሁላችን ምግባር ያለው እምነት እንዲኖረን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!!!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቀደመችው እውነተኛይቱ መንገድ!!!

      የቅዱሳን አምላክ ማስተዋል ይስጠን 🤲

ወ ስ ብ ሐ ት   ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ   ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ   ክ ብ ር   አ ሜ ን  🤲
አስተማሪ መልእክት ነው አንብቧት

ልቦናውን ሰብሰቦ መጸለይ ያቃተው ወጣት አንድን አባት እንዲህ ሲሉ ይጠይቃቸዋል፣

አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ሳነብ ልብናዬ
አይሰብልኝም። አፌ ቢያነብም ልቦናዬ አይተረጉምም
አፌ ቃል ይናገራል አዕምሮየ ግን የጎደለኝን ያጣሁትን ነገር ያሰላስላል።

እኔ ደግሞ ዝም ብዬ ሳስበው:- ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኔ በልቤ ላይ የዚህን አለም እያሰብኩ በአፌ ብቻ ባነበንበው እንደገደል ማሚቶ አፌ ላይ ብቻ እየነጠረ ይሄዳል እንጂ ጸሎት አይሆንልኝም።
ስለዚህ አባቴ የአፍ ብቻ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል? ብሎ ጠየቃቸው።

አረጋዊ አባትም:- እንዲህ ሲሉ አስረዱት
አየህ ልጄ ዐይነ ስውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው የበትሩን ድምፅ ሰምቶ ይመታኛል ብሎ ይሸሻል እንጂ ዐይነ ስውር ነው አላየኝም ብሎ ባለበት አይጠብቀውም። ስለዚህም አንተም አስተውለህ ብትጸልይ መልካም ቢሆንም ለጊዜው ግን ጭራሽ ከምታቆመው በአፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት የሚሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና መቼም ቢሆን ጸሎትህን አትተው።
........አጋንንትንም ማባረር አንድ ታላቅ ጥቅም ነውና። ብዙ ከመጸለይህም አንጻር አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ታደርስሃለች።
እናም ልጄ ልብህ ምንም ዝርው ቢሆንም አፍህም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነውና ይህንንም እንዳታቆመው።
አሁን አንዱን ይዘህ ወደ ፊት ደግሞ ሁለቱንም ለማግኘት መጣር ይኖርብሃል እንጂ አንተው በዳይ አንተው አኩራፊ ሆነህ ጭራሽ ከአምላክ ርቀህ የጠላት ሰይጣን መጫዎቻ እንዳትሆን ጸሎትህን አትተው አሉት። እኛም እኮ ብዙ መጸለይ ፈልገን በብዙ ሰበብ ሳንጸልይ እንቀራለን ፈጣሪ ግን የልባችንን ያውቃልና ሁሌም ሃሳባችንን ይሞናልናል እግዚአብሔር ሃሳባችንን ሕልማችንን እውን ያድርግልን

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
Https://www.tgoop.com/eotcy
+++ " #ለዚህ_መቼ_ጸለይን" +++

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰባዊ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲረዳ የተቋቋመ የካህናት (የቀሳውስት) ጉባኤ ነበረ። የቀድሞው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳም ይህን ስብስብ እንዲቀላቀሉ ለአባ ሚካኤል ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት የዚህ ጉባኤ አባል ሆኑ። ታዲያ አንድ ቀን አባ ሚካኤልን ጨምሮ የጉባኤው የበላይ ኃላፊ የሆኑት ጳጳስና ሌሎችም ካህናት የተጣሉ ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ተሰበሰቡ። ይሁን እንጂ የባልና የሚስትየው ጠብ እንዲህ በቀላሉ ሊበርድ የሚችል አልነበረምና ጳጳሱም ሆኑ ቀሳውስቱም ሁለቱን ለማስማማት ብዙ ቢጥሩም ግን አልተሳካላቸውም።

በስተመጨረሻም ጳጳሱ ወደ አባ ሚካኤል እየጠቆሙ "አባ ሚካኤል ለምን ዝም ብለው ተቀመጡ? እስኪ እርሶ ይሻላል ብለው የሚያስቡትን ይንገሩን" አሏቸው። አባ ሚካኤልም "ብፁዕነትዎ፣ #እንጸልይበት" አሉ። ጳጳሱም " #ይህን_ጉባኤ_ከመጀመራችን_በፊት_እኮ_ጸልየናል" ቢሏቸው አባ ሚካኤል " #አዎን_አባታችን_ለዚህ_ችግር_ግን_አልጸለይንም" አሉ። ከዚያ ሁሉም ለጸሎት ተነሡ። በጳጳሱ ፈቃድ በአቡነ ሚካኤል መሪነት ጸሎት አደረጉ። ጸሎቱ እንዳለቀም እነዚያ የተጣሉት ባልና ሚስት ክርክራቸውን ሁሉ ትተው በጉባኤው ፊት በፍቅር ተቃቀፉ። ሰላም አወረዱ። ይህን ጊዜ ከቀሳውስቱ አንዱ "አባታችን ከመጀመሪያ እንዲህ ቢሉን ምን ነበር #አሳረፉን_እኮ" ብለው ጉባኤውን ፈገግ አሰኙት።

እኛስ ያልጸለይንባቸው ስንት ችሮች አሉብን

ብዙ ቋጠሮ የሚፈታው ግን በብዙዎች የሚረሳው ትልቁ መፍትሔ፣ ጸሎት

(አባ ሚካኤል ኢብራሂም (1899-1975) የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉና እጅግ የሚያስቀና የጸሎት ሕይወት የነበራቸው አባት ናቸው። በእርሳቸው ጉዳይ ከሰሞኑን መመላለሳችን አይቀርም።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/06/28 10:49:46
Back to Top
HTML Embed Code: