አይዞሽ
አንቺ ከመኖሪያሽ ተነስተሽ ወደ አንድ ከተማ በመኪና ስትጓዢ ለዓይን ያማረሽን ለምላስ የጣመሽን ምግብ ቋጥረሽ ትጓዣለሽ። እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው የሲና ምድረ በዳን ሲያልፉ የቋጠሩት ምሳና እራት አልነበረም። በማያርሱበት በማይዘሩበት በማያጭዱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ጎራ ብለው የሚበሉበት ሬስቶራንት በሌለበት፣ የታሸገ ምግብ የሚገዙበት ሱፐርማርኬት ባልኖረበት ምድረ በዳ ላይ እግዚአብሔር መናና ድርጭት እየመገበ መራቸው። ከመሀላቸው አንዳች የተራበ አልነበረም። እግዚአብሔር መሪ የሆነበት ህይወትና ጉዞ በጉድለት ሳይሆን በበረከትና በጠል የተመላ ነው። ወዳጄ አምላክሽ እስራኤልን በምድረ በዳ የመገበ፣ እውር አሞራን የሚቀልብ፣ ድንጋይ የተጫነውን ትል የማይረሳ፣ ትንሿን ትንኝ ሳይዘነጋ የሚመግባት ጌታ ነው። አንቺንማ ሞቶልሽ እንዴት ይረሳሻል ርቦሽ እንዴት ይጨክንብሻል በፍፁም!
ምድረ በዳ በሆነ የህይወት ቀጠና ብታልፊ፣ ዘርተሽ የማታጭጂበት ሰርተሽ የማታተርፊበት፣ ቀድተሽ የማትጎነጪበት ሁኔታ ላይ ብትሆኚ እንኳ በሚያስፈልግሽ ሁሉ መለኮታዊ እጁን ይገልጥልሻል።
ምድረ በዳ ነው ብሎ ሰው ሲጨነቅ በምድረ በዳ አንቺን ለመርዳት የማይከለክለው ጌታ የበረከቱን ጠል ያዘንምልሻል። በሲና ምድር እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች ለጉብኝት አልፈዋል፣ ሀገር አቋርጠው ሄደዋል ያቋርጡ እንጂ መና አልበሉም ከአለት ውኃ አልጠጡም የጠጡት በእግዚአብሔር ያመኑት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ሰው በሚራብበት ዘመን ትጠግቢያለሽ፣ ሰው በሚጠማው ዘመን ትረኪያለሽ፣ በሚሞትበት ዘመን በህይወት ትኖሪያለሽ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያዘጋጃል! "እናት ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ታበላለች እግዚአብሔር ግን ከሞትም ቀስቅሶ ይመግብሻል።" በአንዳች አትጨነቂ እግዚአብሔር ያዘጋጃል።
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
መልዕክት፣አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ
በ @Yeabm
🕊//ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር //🇪🇹
@Etelawyan 🇪🇹
@Etelawyan3 🇪🇹

እህቴ 👸 ሆይ አርአያሽ (ሮል ሞዴልሽ) ማነች ⁉️
👉አስተዋይ ሴት እንድትሆኝ ሁሌ ፀልይ አንች የ ቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ልጅ ነሽ😘
💖ድንግል ሆይ ልደትሽ በረከታችን ነው!!!
💖ድንግል ሆይ የልደትሽ ቀን ሙላታችን ነው!!!
💖የእመቤታችን የልደቷ በረከት ይደርብን! \ ምልጃዋ ሀገራችንን ይጠብቅልን ሕሙማንን ይፈውስልን!!!
🌹የተወለድንበትን ቀን ከምንረግምበት ፈተና ሁሉ እግዚአብሔር ይሠውረን! 🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥• 💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥• ❤️

Forwarded from የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏 (𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊)
#ይቅር__በለኝ🙏
#ከኃጢያታችን የበለጠ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝነው ይቅር አይለንም ብለን ማሰባችን ነው። በደል የሌለበት አምላክ ከእኛ ከትቢያዎቹ ጋር ራሱን አቻ አድርጎ "ኑና እንዋቀስ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዛቶ ትጠራለች" ብሎ የምሕርት ጥሪ እያቀረበ ይቅር አይለኝም ሰንል ሲሰማን ያዝናል። (ኢሳ,፩፥፲፰)
አንተ በክፉ ሥራህ ራስህን ብትጠላውም እንኳን #እግዚአብሔር ግን አይጠላህም፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው #እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር አንተ #ለራስህ ካለህ ፍቅር ይበልጣል» እንደ ይሁዳ ብትክደው ፣ ወዳጅህን ብትሸጥ፣ ንጹሕ ደም በግፍ ብታፈስስ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ብትዘርፍ፣ እንደ ይሁዳ በአምላክነቱም ጨርሶ ባታምን እንኳን ፈጣሪ የሚጠብቀው የምትሞትበትን ሳይሆን #የምትጸጸትበትንና የምትመለስበትን ቀን ብቻ ነው። በወንጌሉ «እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት» እንደሚል #እግዚአብሔር ከእርሱ እጅግ በጣም ርቀህ እያለህ እንኳን እያየ ያዝንልሃል እንጅ አያዝንብህም። (ሉቃ. ፲፭፥፳)
#_ሰናይ__ቀን🙏

እግዚአብሔር ዝም ሲል 😢
አስተውላቹ ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ሲል ተናጋሪ ይበዛል ኢዮብ ትዝ ይላቿል ምንም በማያውቀው ጉዳይ ምክንያት ያለው ንብረት ሁሉ አንድ በአንድ ሲጠፋበት፣ የገዛ ሚስቱ እንኳን ስትክደው ፣ ሰውነቱም በገል ብረት ሲቆሳስል እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ዝም ሲለው ነበር ፤ ነገር ግን ኃላ ላይ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የነበረውን ሀሳብ ሲጨርስ በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ እንደ ገና እንዳሰበው ቅዱሱ መጽሐፍ 📖 ይነግረናል ።
ወዳጆቼ አስቸውሉ የእግዚአብሔር ድምጽ በጣም አስፈልጓቹ ድምጹን ግን ሳትሰሙት ስትቀሩ እግዚአብሔር በህይወታቹ ላይ እናንተ ሳታውቁ የሆነ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ አስቡ፤ አንዳንዴ ደግሞ በእግዚአብሔር ዝም ውስጥ እናንተ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ልታልፉ ትችላላቹ ነገር ግን ከብዙ ዝምታዎች በኋላ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስትሰሙ የቀድሞ ዝምታው ለምን እንደነበር ይገባቿል።
ዝምታው ውስጥ ክብር አለ 🔥

ምን አይነት ፍቅር ነው 🙆
መግደላዊት ማርያም ትባላለች ፈጣሪዋን በጣም ከመውደዷ የተነሳ " በቃ ጌታሽ እኮ ሞቷል " ተብላ እንኳን ሽቶ ልቀባው ነው በሚል ሰበብ የሞተ ስጋውን ለማየት ለሊቱ እስኪነጋላት አጠብቅም ፤ ባይገርማቹ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ በህይወት እያለ " አንተ ጌታችን ነህ " ብለውት ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ እንደ ሰው ሲሞት ሀሳብ ቀይረው ሁሉም ወደ ኋላ ተመለሱ ይቺ ድንቅ ሴት ግን በህይወት እያለ በራሷ ላይ ብቸኛ ጌታ ያረገችውን ኢየሱስን ሞቶም እንኳን ልትቀይረው አልፈለገችም፤ ምን አይነት ፍቅር ነው 😭 ምን አይነት መረዳት ቢኖራት ነው ኢየሱስ ሞቶም እንኳን ለእርሱ ያላት ፍቅር አልቀዘቅዝ ያለው እናንተዬ ለካስ ፈጣሪ እንዲም ይወደዳል....ትዝ ካላቹ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የገለጠው ለዚች ድንቅ ሴት ነበር 🔥
የተወደዳቹ እህቶቼ ትናንት ላይ ይህቺን ልባም ሴት 😍 የነካት ይሄ ታላቅ ፍቅር ዛሬ ላይ ሁላችንንም ይንካን የእርሷን የልብ ማስተዋል ለእኛም ያድለን 🔥🔥

ስለ አጉል ፍቅር...ሳምሶንን ጠየቁት ☺️
ስለ አጉል ፍቅር መዘዝ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከሳምሶን በላይ ሊያስተምረን የሚችል ሰው ማግኘት ይከብዳል.... ሳምሶን የእግዚአብሔርን ክብር የተሸከመ ትልቅ የእግዚአብሔር ሰው እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን በአንዲት ደሊላ በምትባል ሴት ልቡ ተይዞ ያንን ትልቅ ክብር ከላዩ ላይ አሶስዷል ፤ በዚህም ዘመንም ልክ እንደ ሳምሶን ብዙ ልጆች በ Relationship ጉዳይ ላይ ማንን ወደ ህይወታቸው ማስገባት እንዳለባቸው አያውቁም ለዚህም ይመስለኛል 🤔 በዚህ ጉዳይ ላይ ቶሎ የሚጎዱት...የተወደዳቹ ልባም እህቶቼ እና ወዳጆቼ 🥰 እናንተ የያዛቹትን ለማስለቀቅ የእናንተን ቀልብ የሚስቡ ወንድና ሴት ልጆችን ማምጣት ለሰይጣን በጣም ቀላል እንደሆነ አትርሱ፤ ትናንት ላይ ሳምሶን አጥፍቶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ትልቅ ትምህርት ትቶልን አልፎአል እናንተ ግን ዛሬ ላይ የሳምሶንን ህይወት መድገም የለባቹም...
ማሰብ ባለባቹ ጉዳይ ላይ ቆም ብላቹ አስቡ ካለዚያ በዚህ ዘመን ደሊላዎች የከበረውን ነገራቹን ታጣላቹ ።
🙏ሰናይ ምሽት💚💛❤️🕊️🕊️🕊️
🙌ምሽታችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ምሽት ወዳጆቼ🙌

ወዳጆቼ 🥰 ማፍቀርም ሆነ መፈቀር የማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ባህሪ ነው
🌹ፍቅር መስዋትነት ነው ላፈቀሩት ሰው ደስታ ፣ሰላም ፣ምቾት፣እረፍት ሲሉ የራስን ደስታ አቶ ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ የሚከፈለውን ዋጋ ነው።
🌹የእውነት ያፈቀረ ሰው ለኔለኔ ከሚል ስሜት የፀዳ ፥ ለኔ ከማለት ይልቅ ለወደደው ሰው ራሱን ሳይሰስት መስጠት ነው ለኔ።
👉ፍቅር የማንነት... የዘር... ወይንም የገንዘብ ጥያቄ አይደለም.......የህሊና የነብስ እና ራስን አሳልፎ የመስጠት 😍ጥያቄ እንጂ.....💖
ፍቅር እኔ....እኔ...ለኔ....ለኔ ከሚል የራስ ወዳድነት ቀንበር የፀዳ ነው፡፡
❣እውነተኛ ፍ...ቅ...ር በእድሜ የማይለካ...በችግሮች የማይገታ በማግኘት ያልተጀመረ በማጣትም የማይቀየር የሰብአዊነት ጥምረት ነው::❤
👉 ከባዱ ነገር ፍቅር መጀመር ሳይሆን በፍቅር መቆየት ነው::
👉ስለ ፍቅር ቢያወሩ የሚያምርባቸው ፍቅርን በፊልም የተማሩት ሳይሆን በፍቅር የኖሩት ናቸው ፡፡😘
👉ፍቅር ማለት😘 እወድሻለው እወድሀለው ከመባባል በላይ በተግባር የሚፈተን....በመተማመን የሚፀና...በመደማመጥ 😍የሚሆን...በመከባበር❤ የሚሰምር ...የህይወት ማጣፈጫ ቅመም የሆነ የፈጣሪ የፀጋ ስጦታ ነው፡፡ ማፍቀር መፈቀርም መታደል ነው፡፡ሁለቱንም ማግኘት ደግሞ መመረጥም መባረክም ነው፡፡😍
ፈጣሪ "ፍቅርን" ያብዛልን!!!😜አምላካችን የሚያከብረን የሚያምነን አጠፋህ ብቻ ሳይሆን አጥፍቻለሁንም የሚያውቅ ፈጣሪው ይቅር ሲል ይቅር እንደሚለው አውቆ ይቅርታን በልቡ ያተመ እዉነተኛ አፍቃሪ ይስጠን ❤️😘
┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄
#ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️

አረ ወገን እያስተዋልን 🤔
ሰው እንዴት እግዚአብሄር ይስጥልኝ ሲባል ....አይ ምንም ችግር የለም እንዴት ይባላል 🙊
👉ይህ ቋንቋ ለርዕስ አይመች ለምንም አይመች ።
👉 አሁን ይሄ ምን ይባላል በወላዲቷ ?
ባህል፣ እምነት ምንም አይገልፀውም እንደው ከንቱ ልማድ ካልሆነ በቀር
ሰዎች እግዚአብሄር ይስጥህ(ሽ) ሲሉን ሁልጊዜ መልሳችን ችግር የለውም የሚል ነው እስቲ ማን ይሙት 🙈 አሁን እኛ ችግር የለብንም ?
👉ያውም ተቆጥሮ ተሰፍሮ የማያልቅ ነዋ .....በችግር ያደግን ፣በችግር የተመረቅን፣ በችግር ወላፈን ተጠብሰን የኖርን የምንኖር አይደለንም ? እንዲህ ማለት በኛ አይምርም 🙅♂ ኑሮ ናላችንን አዙሮት ፣በበሽታ ጠውልገን፣ ሌቱ ጠሮብን፣ ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖብን እግዜር ይስጥህ ስንባል ችግር የለም እንላለን ⁉️
አሜን🙏 ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ማንን ገደለ 🤔 እንደው የአምላክ እናት የአስራት ሀገር የብዙ ቅዱሳን መካናት መገኛ በቅዱሱ መፅሐፋችን ኢትዩጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተሰኘች ደግሞ ኢትዩጵያ ሲባል ምድሪቷና ዛፎቹ ጋራ ሸንተረሩ ሳይሆን ህዝቦቿን መሆኑን አትዘንጉ እንኳን እኛ ብዙ የተባለልን ቀርተን
👉 ፈረንጆች እንኳ የእግዚአብሄር ስም ላልተጠራበት ምስጋና ቴንኪው ሲባሉ ዩ አር ዌልካም ነው የሚሉት እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን የተሰኘንስ እግዚአብሄር ይስጥልን ስንባል ችግር የለም ማለታችን ያሳፍራል ከዕርሱ ከቸር አምላካችን በላይ ማን አለ ማን ይስጠን 🤔
🌹 ወዳጆቼ በዛ በሰፊው እጁ እየሰፈረ የሚያኖረን መልካም አባት እርሱ ነው ።
ከኛ አንደበት ይሄ ቃል ሲገኝ ያስነውራል ።
ቅድስናችን በአንደበታችን ጭምር ነውና የምንናገረው ቃል ሁሉ የተቀመመና ማስተዋል ያለበት እንጂ ከንቱ ንግግር መናገር የለብንም ለማለት ነው ወዳጆቼ ።
ከዚህ በኃላ መልሳችን አሜን 🙏 ብቻ ነው ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወዳጆቼ 🙏

ወዳጆቼ ይነጋል 🥰
👉ለአንዳንዶቻችን መሽቶብናል፣
👉 ለአንዳንዶቻችን ጀንበር አዘቅዝቃብናለች፣
👉ለአንዳንዶቻችን በር ተዘግቶብናል፣
👉 ለአንዳንዶቻችን ተስፋ መቁረጥ ጓዙን ጠቅልሎ እኛ ጋር ከትሞብናል፤
👉 ለአንዳንዶቻችን በፀሐይ ጨልሞብን መሸሸጊያ አጥተናል ።
👉 ምናልባት የስራ ማመልከቻችሁ ተቀባይነት አጥቶ ይሆናል፣
👉ምናልባት ፕሮሰሳችሁ አላለቀላችሁ ኢምባሲ ተቀባይነት አታችሁ ይሆናል፣
👉 ምናልባት የጠየቃችሁት ይቅርታ ተቀባይነት እጥቶ ይሆናል ግን ወዳጆቼ አንዳች ልባችሁ አይሸበር አምላካችሁ አባታችሁ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሄር ተቀብሏችኃል 🥰
ደግሞ እግዚአብሄር የተቀበለውን ማንም አይጥለውም ሰዎች ቢቀበሏችሁ ባሉበት ቦታ ነው እግዚአብሄር ግን ሲቀበላችሁ በሰማይና በምድር ነው በኢትዮጵያ ተቀባይነት ብታገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ የሚፅፍላችሁ እስከ ድንበሩ ነው ።
እግዚአብሄር ግን ድንበር የለውም በሰማይና በምድር ነው። በእውነት እግዚአብሄር ተንከባክቦ አንከብክቦ በትከሻው አሰማርቶ ነው የያዘን።
የዓለም ውበቷ ይሄ ነው 😢
የእግዚአብሔር ቃል ግን "ማታም ሆነ ፤ ጠዋትም ሆነ" (ዘፍ 1፥13) ሰው ከጠላህ ጠላህ፣ ከጨከነ ጨከነ፣ ጥርሱን ከነከሰብህ ነከሰ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ይራራልሃል። ጨለማውን በዛው አያስቀረውም ያነጋዋል ጠዋትን ያመጣልሃል። የሚጨልመው ላንተ ሊመስልህ ይችላል ለደከማቸው ማረፊያ ነው ላንተ ደግሞ የንጋት መምጫ ዋዜማ ነው። እግዚአብሔር ለአንተ ጨለማ ቀን የለውም የሚነጋ ፣የሚያብብ ፣ የሚደምቅ፣ የሚያምር፣ የሚስብ ቀን ይወጣልሀል።
ሁሌም አስታውስ ወደ ጎን 360 ዲግሪ ብትዟዟር ካንተ በቀር የምታየው የሚረዳህ ላይኖር ይችላል፤ ቀና ስትል ግን የሰማይ ደጅ ላንተ ክፍት ነው። አባትህና የርሱ የሆነው ሁሉ ያንተ ነው።
አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል። እግዚአብሄርን አላልፍም ብሎ የሚገዳደር የትኛውም ሀይል የለም። አሳላፊው ስላለ ያልፋል። አልነጋም ብሎ ስታክ አርጎ የሚቀር የጨለማ ለሊትና የልብ ክረምት የለም።
በጨለመብህ ጊዜም ቢሆን ጭለማ ውስጥ ጌታ ሊያሳይህ የፈለገውን ነገር ለማየት ሞክር።
ፀሐይዋ ወደመኝታዋ ስትሄድ ጥላዋን ትልክልናለች ጨለማው ሲደምቅ የሚያምሩ ከዋክብትን እናያለን። በጨለሙብን ነገሮች ውስጥም እንባችን የጋረዳቸው ከዋክብቶች ይኖራሉ እነሱን እያየህ ለሊቱ መንጋት ይሆንልሀል።
አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል
ዛሬ ባንተ ላይ የሆነው ካንተ በፊት ብዙ ሚልየን ሰዎች ላይ ደርሷል። አንተ መጀመሪያ አይደለህም መጨረሻ ግን ልትሆን ትችላለህ። ምንም ይሁን ምን ቢመሽም ይነጋል።

እህቴ ሆይ አጠገብሽ ያለው የልብሽ ንጉስ 👑
<ለፍቅር መግለጫ> ይሆንሽ ዘንድ ሀብት ባይደረድርር እጁን ባይዘረጋም ማጀቢያ ማሞቂያ ንዋይ ባይኖረውም <>ግን ይወድሻል ይሄን አትጠራጠሪ በመቃው አንገትሽ ለይ ሀብል ባያስርልሽም
በወርቅ ላይ ወርቅ ባይደረድርልሽም
<ግን አትጠራጠሪ በንፁህ ልቡ ያለመታከት ያፈቅርሻል> ;_እንዴት ⁉️ ካልሽኝ ደግሞ አንዲህ እልሻለሁ🗣
👉እጅም ይቀጥናል
👉ሀብትም አላቂ ጠፊ ነው
👉ማጀቢያ ማሞቂያው ንዋይም አላፊ ነው
👉ሀብሉም ተበጣሽ ተቆርጦ ቀሪ ነው 🤷♂
<ግን እዚህጋር ማስተዋል ያለብሽ >
የሰጠሽ ልብ ከሁሉም ይበልጣል አያልቅም አያልፍም ብረትም አይደል ተቆርጦ አይወድቅም
ፍቅር ከለገሱት ፍቅር ይመልሳል
ለታመነው ታምኖ ዘላለም ይኖራል ። ..😊.............................😊.............................😊.............................😊.............................😊......................... 😊.............
የአብስራ ነኝ
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያዋለን አምላካችን ምሽታችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያሳድረን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤

►ዓይን ያለ ፍቅር ካየ ምን አገባኝ ይላል።
:
►ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡
:
►ምላስ ያለ ፍቅር ከወጣ ይሰብራል።
:
►እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል።
:
►እግር ያለ ፍቅር ከሄደ ድልድይ
♡የተሰጠን የእድሜ ገደብ እንኳንስ ለፀብ ለፍቅርም አይበቃምና አምላክ ከወረት ፍጹም የጸዳ ንጹሕ ፍቅር ለሁላችንም አብዝቶ ያድለን!(አሜን)
🎤የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm 📩
ይሄን ፖስት ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አርጉ ቻናሉንና ግሩፑንም አስተዋውቁ

👩❤👨#ፍቅር_ማለት_ሌሎች_እኛን መውደዳቸው ሳይሆን እኛ ሌሎችን መውደዳችን ነው❗
♥ፍቅር መልካሙን ሁሉ የሚያጣፍጥ ቅመም ነው፡፡😍
🎗ይህች 🌍ዓለም ስታልፍ ኢትዮጵያም ታልፋለች ለዘላለም የሚኖረው ፍቅር ብቻ ነው💯
💔ፍቅር የጦር መሣሪያ የላትም፣ የጦር መሣሪያ የያዘውን ግን ትማርካለች❤🔥
💞ፍቅር ከሐኪሙ ኪኒን ይልቅ በሽተኛን ትፈወሳለች፡፡ ከዳኛው ቃል ይልቅ እስረኛን ትፈታለች፡፡😍
💔ከወጌሻው ይልቅ የተሰበረውን ትጠግናለች፡፡ ፍቅር ቀጣይ የሚሆነው በይቅርታ
ነው💘
❣መንገድ የሚረዝመው በድልድይ ነው፡፡ ፍቅርም የሚረዝመው በይቅርታ
ነው፡፡🙏 💓
😘የፍቅር ፍጻሜው ንብረት መስጠት አይደለም❤🔥ፍቅር እራሱን መስጠት ነው¶
ራሱንም ይቀበላል°°°>>
💗አቦ ፍቅር😍
ይስጠን ለሁላችንም🙏
😍ከወደዱት ለወዳጆዎ ሼር ያድርጉን💞
✍️የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm
••••••፨፨♥፨፨•••••••

ሰው ሁሉ ቢረሳህ... ፈጣሪ ሁሌም እንደማይረሳህ እስታውስ፤
ሰው ሁሉ ቢጥልህ... ፈጣሪ እንደማይጥልህ አትርሳ፤
ሰው ሁሉ ቢጠላህ... ፈጣሪ እንደሚወድህ ልብ በል፤
የፈጣሪ ፍቅር ህያው ነው። ማንንም በዚህ ምድር አይጥልም።
~ ዮሴፍን በግብፅ ያከበረ
~ ሙሴንም በፀጋ ያጠረ
~ መካኒቱን ሀና ልጅ ያስታቀፈ
~ ዳዊትን ከበረሀ ያነሳ አምላክ
በሰፊው መዳፉ ይዞ ካለንበት ችግር፣ ብቸኝነት፣ ሀዘን እና መከራ ያወጣናል ፤ እምነታችን በሰው ሳይሆን በፈጣሪያችን ላይ ይሁን❗️
እስቲ #Share💯Share
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያዋለን አምላካችን ምሽታችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያሳድረን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
ሰው ሁሉ ቢጥልህ... ፈጣሪ እንደማይጥልህ አትርሳ፤
ሰው ሁሉ ቢጠላህ... ፈጣሪ እንደሚወድህ ልብ በል፤
የፈጣሪ ፍቅር ህያው ነው። ማንንም በዚህ ምድር አይጥልም።
~ ዮሴፍን በግብፅ ያከበረ
~ ሙሴንም በፀጋ ያጠረ
~ መካኒቱን ሀና ልጅ ያስታቀፈ
~ ዳዊትን ከበረሀ ያነሳ አምላክ
በሰፊው መዳፉ ይዞ ካለንበት ችግር፣ ብቸኝነት፣ ሀዘን እና መከራ ያወጣናል ፤ እምነታችን በሰው ሳይሆን በፈጣሪያችን ላይ ይሁን❗️
እስቲ #Share💯Share
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያዋለን አምላካችን ምሽታችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያሳድረን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
ከጓደኞቻቹ ጋር ላቀያይማቹ ነው 🤫
ወደ እናንተ ልመለስ እና እናንተጋስ ያሉት ጓደኞች እንዴት ናቸው ይራመዳሉ ወይስ ሽባዎች ናቸው ? እናንተንስ የመቀየር አቅም አላቸው ወይስ እነርሱ ራሱ ሰው ያስፈልጋቸዋል ?
እስኪ መልሱልኝ እውር እውርን መምራት ይችላል🤚 ? አይችልም አይደል 🤗 ስለዚህ የሆነ ጉዳይ ላይ ማየት የሚከብዳቹ ከሆነ በዛ ጉዳይ ላይ በደንብ ማየት የሚችሉ ሰዎችን ጓደኞቻቹ አድርጉ ካለዚያ እናንተን ሊቀይሩ በማይችሉ ሰዎች ምክንያት ብቻ ብዙ ነገሮችን ታጣላቹ።
እስቲ #Share💯Share
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያሳደረን አምላካችን ቀናችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያውለን ሰናይ ቀን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
ትዝ ይላቿል ያ 38 አመት ሙሉ ወደ መጠመቂያው ውሃ የሚወስደው ሰው አጥቶ በመጨረሻ ኢየሱስ የፈወሰው ሰው ? (ዮሐንስ ወንጌል 5 ላይ)....
እሺ ያስ ሰዎች የቤት ጣራ ቀደው ኢየሱስ ጋር ያደረሱት ሽባው ሰው ? ( ማርቆስ 2 ላይ ).. በነገራችን ላይ እዚህ ጋር ሁለቱም ሰዎች ሽባዎች ናቸው ፣ ሁለቱም መራመድ አይችሉም ፣ ሁለቱም የሰው ድጋፍ ይፈልጋሉ ነገር ግን በመካከላቸው አንድ ልዩነት ነበረ 😊 የምን ልዩነት ካላቹኝ "የጓደኛ ልዩነት " ይሄን ክፍል በደንብ አንብባቹት ከሆነ ያ 38 አመት ሙሉ ሽባ የነበረው ሰው ጓደኞቹም እንደርሱ ሽባዎች ነበሩ ለዛም ነው ለ 38 አመታት ሙሉ ማንም የሚረዳው ጠፍቶ በሌሎች ሰዎች ሲቀደም የነበረው ነገር ግን እዚኛው ሽባ ሰው ጋር ስንመጣ ጓደኞች መራመድ የሚችሉ ፍፁም ጤነኞች ነበሩ 👌 እንደውም በጣም የሚገርመው እነኚ ጓደኞቹ ሽባውን ጓደኛቸውን ፈጣሪ ፊት ለማቅረብ ብለው ጣራ እስከመቅደድ ድረስ ደርሰው ነበር 🙆 ...ወደ እናንተ ልመለስ እና እናንተጋስ ያሉት ጓደኞች እንዴት ናቸው ይራመዳሉ ወይስ ሽባዎች ናቸው ? እናንተንስ የመቀየር አቅም አላቸው ወይስ እነርሱ ራሱ ሰው ያስፈልጋቸዋል ?
እስኪ መልሱልኝ እውር እውርን መምራት ይችላል🤚 ? አይችልም አይደል 🤗 ስለዚህ የሆነ ጉዳይ ላይ ማየት የሚከብዳቹ ከሆነ በዛ ጉዳይ ላይ በደንብ ማየት የሚችሉ ሰዎችን ጓደኞቻቹ አድርጉ ካለዚያ እናንተን ሊቀይሩ በማይችሉ ሰዎች ምክንያት ብቻ ብዙ ነገሮችን ታጣላቹ።
እስቲ #Share💯Share
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያሳደረን አምላካችን ቀናችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያውለን ሰናይ ቀን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
📖"በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ"📖
📖 (መዝ. 65÷11)
ወዳጆቼ ❤️ እንኳን ከዘመነ ዩሐንስ ወደ ዘመነ ማቲዎስ ከ 2🌻16 ወደ 2🌻17 ዓ.ም በሰላም በጤና አሸጋገረን አደረሰን አደረሰሽ! አዲሱ ዓመት የእግዚአብሔር ቃል የሚከበርበት፣ እርስ በእርሳችን አንድነት የምንፈጥርበት፣ በፍቅር የእግዚአብሔር ደቀመዛሙርት የምንሆንበት፣ በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን የምንቆይበት ፣ ለጠፉ ወገኖቻችን የምንፀልይበት ፣ ንስሀ የምንገባበት እና ለስጋ ወደሙ የምንቀርብበት ያድርግልን አዲሱ አመት
✍️ሀገራችን ሰላም አግኝታ ለእድገት ምንፋጠንበት
✍️ይበልጥ ወደ ፈጣሪያችን የምንቀርብበት
✍️በሀገር ፍቅር የምንደምቅበት
✍️ወደ 21ኛው ክፍለ ዘመን ተሸጋግረን በዘር በሀይማኖት ከመፋጀት ወጥተን ለሀገራችን በአንድነት የምንቆምበት
✍️በየግላችንም በስኬት ምንደምቅበት
✍️ሰው ለሰው በሽታ ከመሆን መድሀኒት የሚሆንበት
✍️ተማሪውም በትምህርቱ ውጤታማ
✍️ሰራተኛውም በስራው ስኬታማ የሚሆንበት አመት ያድርግልን አሜን 🙏
አንቺም ውዷ ሴት የልብሽ መሻት ያሰብሽው ሁሉ ከኀጢአት በስተቀር የሚፈፀምበት ይሁንልሽ!
🌻ባለፈው ዘመን ስንርቀው ቀርቦ፣ ስንበድለው ትቶ፣ ስንጠፋም ፈልጎ ለንስሃ እና መልካም እንድንሰራበት የሰጠንን እያንዳንዱን ቀን ስንበድልበትና ኃጢአት ሰርተን ስንረክስበት ታግሶን አሁንም ደግሞ ሌላ አዲስ ቀንን አዲስ ዘመንን የሰጠን አምላካችን ስለማይነገር ስጦታው ሁሉ ስሙ የከበረ የተመሰገነ ይሁንልን በእውነት ።
🌻የእናትነት ፍቅሯ እና ምልጃዋ ያልተለየን ስለቸርነቷ እናታችን የምንላት ቅድስት ድንግል ማርያም ስሟ ይክበር ይመስገንልን ።
🌻ይህቺን አመት ተዋት/ተወው እያሉ ተቆርጦ ከመጣል፣ ደርቆ ከመቃጠል፣ ከቅስፈት፣ ከሞት፣ ከአደጋ፣ ከክፉ ገሃኔን፣ ከእንግልት... በምልጃ በፀሎታቸው ያልተለዩን የተራዱን የጠበቁን ቅዱሳን መላእክት፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት፣ ሐዋርያትና መነኮሳት ቅዱሳን ሁሉ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው።
መልካም የአገልግሎት⛪️፣ የፍቅርና🥰 የሠላም🕊 ዘመን ይሁንልን።
🌻ቀንን በ ቀናት
🌻ሳምንትን በ ሳምንታት
🌻 ወርን በ ወራት
🌻ዘመንን በዘመናት
🌻የሚለውጥ እርሱ ግን የማይለወጥ ፈጣሪ መልካም ዘመንን ይጨምርልን🌻🌻🌼
🌼መልካም አዲስ አመት🌼
✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm

እህቴ 🙍♀፦
🔰አስተሳሰብሽ ካለባበስሽ የበለጠ ሲያምር፤ መልካምነትሽ ከምትቀቢው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ፤ ስነ ምግባርሽ ከመልክሽ ይበልጥ ሲገን፤ ፍቅርሽ ወደሰዎች ይበልጥ ካለፈ፤ እግዚአብሔርን መፍራትሽ ከሁሉ ነገርሽ ከበለጠ በእውነት አንቺ በጣም ውብ ነሽ።
ወንድሜ 🙎♂፦
♻️ይቅርታህ ከደረትህ ይልቅ ከሰፋ፤ ትዕግስትህ ከጡንቻህ ይልቅ ከወፈረ፤ የጸሎት ሕይወትህ ከኪሎህ ከገዘፈ፤ መንፈሳዊ ሕይወትህ ከፋሽንህ ከበለጠ በእውነት አንተ ውብ ነህ።
⚜ እግዚአብሔር የሰላሙን ካባ፣ የሞገሱን መጎናጸፊያ፤የፍቅሩን ሸማ፤ የክብሩን ጸዳል ያልብሰን ወዳጆቼ ሰናይ ቀን በቸር ያውለን ።
አዘጋጅ ✍ ፦ የአብሥራ ተስፈዬ
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
Join and share
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
🔰አስተሳሰብሽ ካለባበስሽ የበለጠ ሲያምር፤ መልካምነትሽ ከምትቀቢው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ፤ ስነ ምግባርሽ ከመልክሽ ይበልጥ ሲገን፤ ፍቅርሽ ወደሰዎች ይበልጥ ካለፈ፤ እግዚአብሔርን መፍራትሽ ከሁሉ ነገርሽ ከበለጠ በእውነት አንቺ በጣም ውብ ነሽ።
ወንድሜ 🙎♂፦
♻️ይቅርታህ ከደረትህ ይልቅ ከሰፋ፤ ትዕግስትህ ከጡንቻህ ይልቅ ከወፈረ፤ የጸሎት ሕይወትህ ከኪሎህ ከገዘፈ፤ መንፈሳዊ ሕይወትህ ከፋሽንህ ከበለጠ በእውነት አንተ ውብ ነህ።
⚜ እግዚአብሔር የሰላሙን ካባ፣ የሞገሱን መጎናጸፊያ፤የፍቅሩን ሸማ፤ የክብሩን ጸዳል ያልብሰን ወዳጆቼ ሰናይ ቀን በቸር ያውለን ።
አዘጋጅ ✍ ፦ የአብሥራ ተስፈዬ
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
Join and share
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
♠️ወዳጆቼ እማያልፍ የለም ሁሉም ያልፋል እንኳን መከራ 😭 እና ችግር 😢 እኛ ከእነዚህ ሁኔታዎች በላይ የሆነው የሰው ልጆች 👨👩👧👦 እንኳን ዘለዓለማዊ አይደለንም ተራችንን ጠብቀን ስንጠራ ሀዘን 😭 ለደስታ 😁 ቦታ እንደሚለቀው እኛም ሞተን ⚰ ለሚወለደው 🤱 ቦታ እንለቃለን እናልፋለን ይሄ እየመረረንም ቢሆን መዋጥ ያለብን የህይወት ህግ ነው 🤷♂
ስለዚህ ወዳጄ ይሄን አስተውል 🤔
👉የዛሬው መራብህ ያልፋል፤
👉የዛሬው መቸገርህ ያልፋል፤
👉የዛሬ ለቅሶህ ያልፋል፤
👉የዛሬው ተስፋ የመቁረጥ ስሜትህ ያልፋል፤
👉የዛሬ መድከምህ ዝለህ መሰልቸትህ ያልፋል፤
👉ጤናህ ተናግቶ መሰቃየትህ ያልፋል፤ 👉በወዳጅህ ባመንከው መከዳትህ ያልፋል፤
👉ጓደኛ ማጣት ያልፋል፤
👉ግራ ያጋባህ የሀገርህ ሁኔታ ያልፋል፤
👉ታስረህም ቢሆን ይሄም ያልፋል።
በደንብ ይደመጥ ታተርፉበታላችሁ 🌹
🎙የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
ስለዚህ ወዳጄ ይሄን አስተውል 🤔
👉የዛሬው መራብህ ያልፋል፤
👉የዛሬው መቸገርህ ያልፋል፤
👉የዛሬ ለቅሶህ ያልፋል፤
👉የዛሬው ተስፋ የመቁረጥ ስሜትህ ያልፋል፤
👉የዛሬ መድከምህ ዝለህ መሰልቸትህ ያልፋል፤
👉ጤናህ ተናግቶ መሰቃየትህ ያልፋል፤ 👉በወዳጅህ ባመንከው መከዳትህ ያልፋል፤
👉ጓደኛ ማጣት ያልፋል፤
👉ግራ ያጋባህ የሀገርህ ሁኔታ ያልፋል፤
👉ታስረህም ቢሆን ይሄም ያልፋል።
በደንብ ይደመጥ ታተርፉበታላችሁ 🌹
🎙የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
👱ወንድ ልጅ ሁለት ጊዜ ይወለዳል።
አንድ ጊዜ ህይወት ከምትሰጠው ሴት ሲወለድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር ከምትሰጠው ሴት ይወለዳል።
👵የመጀመሪያዋ ህይወቱን ትሰጠዋለች፤
ሁለተኛዋ ህይወቷን ትሰጠዋለች👰
🙌ምሽታችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን ሰናይ ምሽት ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
አንድ ጊዜ ህይወት ከምትሰጠው ሴት ሲወለድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር ከምትሰጠው ሴት ይወለዳል።
👵የመጀመሪያዋ ህይወቱን ትሰጠዋለች፤
ሁለተኛዋ ህይወቷን ትሰጠዋለች👰
🙌ምሽታችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን ሰናይ ምሽት ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
#የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር ከምግብ፣ ከውሃ ከመጠለያ፣ ከሁሉም መሰረታዊ ፍላጎቶች በፊት በህይወት እንዲቆይ ፍቅር ያስፈልገዋል።
🌹ፍቅር ከሌለው ባይሞትም ገዳይ ነው፤ ባንቀብረውም ሙት ነው።
🌹በህይወት ቢመላለስም ሬሳ ነው።
🌹ፍቅር ህይወትን በትክክለኛ የመንገድ አቅጣጫ የሚተልም የስብእና ገበሬ ነው።
✝የክርስቶስን ፍቅር ከመተረክ ባለፈ በህይወታችን እንግለጠው።
✝የሚጠጡት ውሃ በሰጣቸው በምትኩ በሰፍነግ ሆምጣጤ እንደሰጡት
🌹በሰጣችኋቸው እምነት ፈንታ ክህደትን የለገሷችሁ፤
🌹በሰጣችኋቸው ፍቅር ምላሽ ጥላቻን ያሳጨዷችሁን፤
🌹ስትስሟቸው የነከሷችሁን፤
🌹ክርስቶስን በበርባን እንደለወጡት በሌላ ሰው የለወጧችሁን ሁሉ እንደ ክርስቶስ ግሩም በሆነ ፍቅር ልባችሁን ከፍታችሁ በይቅርታ ተቀበሏቸው።
❤️ አልቀበልም ብላችሁ የገፋችሁትን ይቅርታ ዛሬ ተቀበሉ።
❤️አልሰጥም ያላችሁትን ይቅርታ ዛሬ ለግሱ።
❤️ፀፀትና በደል ባጎበጠው ህሊና መኖር ይብቃችሁ በይቅርታ ቀና በሉ ።
✝ፍቅርም እንደዚህ ነውና እንደዚህ አድርጉ ይላል ቃሉም ።
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌