Telegram Web
ኩባንያችን በ2017 በጀት ዓመት ነባር የቴሌኮም እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን አሟጦ በመጠቀም፣ አዳዲስ መጠነ ሰፊ ተጨማሪ ማስፋፊያዎችን በማከናወን እንዲሁም የደንበኛ ቁጥርን የሚጨምሩ እና ተሞክሮን የሚያሻሽሉ ተግባራትን በማከናወን አጠቃላይ የደንበኞቹን ብዛት በ6% በመጨመር 83 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት የሞባይል ደንበኞችን በ5.5% በመጨመር 79.7 ሚሊዮን ማድረስ፣ የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በ16% በመጨመር 47.4 ሚሊዮን ማድረስ እንዲሁም የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኞችን በ25% በመጨመር 934 ሺህ ለማድረስ አቅዷል፡፡

ኩባንያችን የቴሌኮም ሽፋንን በመጨመር የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 73% ለማድረስ ከማቀድ ባሻገር የእጅ ስልኮችን በቅናሽ በማቅረብ ለማህበረሰባችን ከኮኔክቲቪቲ ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች በማዳረስ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይተጋል፡፡

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/47EZVt1 ይጎብኙ፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
የሀገራችንን የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነትን በማሳደግ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ያለውን የቴሌብር አገልግሎት ተደራሽነት በማሳደግ በ2017 በጀት አመት የቴሌብር ደንበኞችን ቁጥር 55 ሚሊዮን ለማድረስ አቅደናል፡፡

የቴሌብር ወኪሎችን ቁጥር በ28% በማሳደግ 275 ሺህ ለማድረስ እንዲሁም በቴሌብር ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎችን ቁጥር በ102% በማሳደግ 367 ሺህ ለማድረስ እና የቴሌብር ደንበኞችን ቁጥር በ15.7% በመጨመር 55 ሚሊዮን ለማድረስ እቅድ ይዘናል፡፡

የቴሌብር ዲጂታል አገልግሎቶችን፣ የሀገር ውስጥ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርን፣ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ክፍያዎችን፣ አለም አቀፍ የኦንላይን ክፍያዎችን፣ ተጨማሪ አጋሮችን በማሳተፍ የሃዋላ አገልግሎቶችን በስፋት ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡

የቴሌብር አገልግሎትን በይበልጥ በማስፋት ተጠቃሚዎች በቀላሉ በእጅ ስልካቸው ክፍያ መፈጸም፣ ገንዘብ መላክና መቀበል እንዲችሉ እንዲሁም ተቋማትን የክፍያ ስርአታቸውን እንዲያዘምኑ በማስቻል የዲጂታል አገልግሎቶችን አካታችነት እና ተደራሽነት በማረጋገጥ ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የበኩላችንን ቁልፍ ሚና ማበርከት እንቀጥላለን፡፡

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/47EZVt1 ይጎብኙ፡፡

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalEthiopia #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #HOPR #HoF
ኩባንያችን በዛሬው ዕለት ከሼንዜን ግሪንቴክ አርኤፍ ኮሚዩኒኬሽን ሊሚትድ ጋር የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማልማት የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ያካተተ ስትራቴጂያዊ የአጋርነት ስምምነት አደረገ!

ስምምነቱ፣ በዋና ስራ አስፈጻሚያችን ፍሬህይወት ታምሩና በሼንዜን ግሪን ቴክ አር ኤፍ ኮሚዩኒኬሽን ሊሚትድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ አቶ ሊዮ ካይ መካከል የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተፈጸመ ሲሆን ሊዮ ካይ አፍሪካን ሲጎበኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ኩባንያችን የ2017 በጀት አመት እቅዱን ይፋ ባደረገበት በትላንትናው ዕለት ዋና ስራ አስፈጻሚያችን በዘርፉ የተሰማሩ ከአገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ አጋሮች አብረው እንደሚሰሩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ግሪንቴክ በቻይና አስር ግዙፍ ከሆኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የኮሙኒኬሽን እና ዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ አንጋፋ የሆነ ኩባንያ ነው፡፡


#Ethiotelecom #GrenTechRF #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
2024/09/28 05:27:17
Back to Top
HTML Embed Code: