📣 የመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም የድርጅታችንን ዜና መጽሔት ካልደረስዎት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ ዜና መጽሔቶችን( Past Issues) በሚለው ዘርፍ በመንካት ማግኘት ይችላሉ።
https://mailchi.mp/b66aa363c7c2/1bnk5keu58-9326547?e=4198e66800#LinkNine
ማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ይከተሉ
ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA
ቴሌግራም፡ https://www.tgoop.com/ethiopiawinnetaa
ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/
ዩትዩብ : https://youtube.com/@voiceofethiopiawinnet3661

👍2
የሐበሾች ልዩ ክብር በእስልምና
ሐበሾች በእስልምና ውስጥ ስላላቸው ልዩ ክብር እኛ ባለቤቶቹ ለታሪክ ትኩረት ሰጥተን ስላልመረመርንና ስላልዳሰስነው በሰነድነት ተፅፎ ሊቀርብ አልቻለም። በአሁኑ ዘመን ዕድሜ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ለጥናት ማዕከላት የእስልምና ሃይማኖት እየተስፋፋ በመምጣቱ ይህ ታሪክ ከተደበቀበት በመውጣት ላይ ይገኛል።
ስለዚህ ሐበሻ እንደ ሀገር፣ አስሃማ እንደ ንጉሥ፣ ሐበሾች እንደ ዜጋ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) በኩል በጊዜው የተሰጣቸው ክብር ምን እንደሚመስል ከነቢዩ ሀዲሶች፣ ከሙስሊም ምሁራንና ደራሲያን የተዘገቡትን የእኛነታችን/የኢትዮጵያዊነታችን ኩራት የሆነውን ይህን ታሪካችንን በመጠኑም ቢሆን ቀንጨብ አድርጌ ላካፍላችሁ ወደድኹ።
አላህ (ሱወ) ከሚጠቁማቸው እንጂ ከራሳቸው የማይናገሩት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ሐበሻን:-
1ኛ. «የእውነት ምድር» ብለዋታል። ይህ አባባል ምንም እንኳ መካ የተከበረው የአላህ ቤት የሚገኝበት ቢሆንም በወቅቱ ፍትሕና እውነት ስለጠፋ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) እና ተከታዮቻቸው ለስቃይና ችግር ተጋልጠው ነበር። የሚፈለገው ፍትሕና እውነት ግን በሐበሻ መሬት በጊዜው ተግባራዊ መሆን ችሎ ነበር። ስለዚህ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ሲታገሉለት የነበረው ፍትሕና እውነት ከመካ ከ16 ዓመት በፊት በሐበሻ ምድር ተረጋግጦ ነበር። ለዚህ ነው ሐበሻ የፍትሕና የእውነት ምድር በመሆን መካን የቀደመችው።
2ኛ. «የማይበድል ሀቀኛ ንጉሥ ያለባት ሀገር» ተብላለች። ይህም በዘመኑ በአካባቢው የተለያዩ ነገሥታት ቢኖሩም ሀቀኛና ፍትሐዊ ንጉሥ የነበረው ግን ነጃሺ ብቻ ነበር።
3ኛ. «እሱ ዘንድ ማንም በደል አይደርስበትም» የተባለውም ሀገሪቷ የእውነት ምድር በመሆኗ፣ ንጉሡም ፍትሐዊ በመሆኑ፣ እሱ ዘንድ ማንም ሰው ቀለም፣ ቋንቋ፤ ብሔር ሳይገድበው ሰብዓዊ መብቱና ክብሩ ይጠበቅለትና ይረጋገጥለት ነበር። ለዚህም ነው ስደተኞች ምንም እንኳን ከሐበሻ ጋር ቋንቋ፤ ብሔር፣ ባህል፣ ወግ፣ ቀለም ባያዛምዳቸውም በነበራቸው የ16 ዓመት ቆይታ በእነሱ ላይ የተፈፀመባቸው ግፍም ሆነ በደል ፈፅሞ አልነበረም። እምነታቸውን በነፃነት ተግባራዊ እያደረጉ ከመንግሥትም ሆነ ከሕዝቡ አስፈላጊ ድጋፍ፣ ድጎማና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መቆየት ችለዋል። የስደት ቆይታቸውን ጨርሰው እስከሚመለሱ ድረስ ከነሱ ውስጥ አንድም ቅሬታ ያቀረበ ስደተኛ አልነበረም። እንዲያውም ለሐበሻ ምድር፣ ለንጉሡና ለሕዝቧ ከፍተኛ ፍቅር እና ክብር ነበራቸው።
4ኛ. በዘመኑ:-
በመንግሥት ደረጃ እስልምናን በማስተናገድ ሐበሻ የመጀመሪያዋ የመንግሥት ሀገር ነች፤
እስልምናን በመቀበል ከመካ ቀጥላ ሁለተኛ ስትሆን በግለሰብ ደረጃም በወንዶች ሁለተኛ ነች። ይኸውም ቢላል ቢን ረባህ (ቢላል አል ሐበሺ) (ረዓ) እስልምናን በመቀበል ከአቡበከር (ረዓ) ቀጥሎ ሁለተኛው አማኝ በመሆኑ ነው።
ኢብነል አቲር የሚባሉት ዘጋቢ እንደጠቀሱት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ኡካዝ በሚባል የገበያ ማዕከል ለተሰበሰበው ሕዝብ ኢስላማዊ ጥሪ ያስተላልፉ ነበር። አንድ አምር ቢን አበሳህ የሚባል ታዋቂ ግለሰብ ነቢዩን (ሰዐወ) እንዲህ ሲል ጠየቃቸው። «ይህን ጥሪህን ማን ተቀበለህ?» አላቸው «አቡበከርና ቢላል» ብለው መለሱለት። ቢላል (ረዓ) እስልምናን ቢቀበልም ከአሠሪዎቹ ችግር እንዳይፈጠርበት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) በሰጡት ምክር መሠረት እስልምናውን በግልፅ አላወጀም ነበር፤
በሌላም በኩል ከሴቶች ሐበሻዋ ኡሙ አይመን (ረዐ) ከመጀመሪያዋ የነብዩ መሐመድ (ሰዓወ) ባለቤት ኸድጃ (ረዐ) ቀጥላ ነው እስልምናን የተቀበለችው፤
በሀገር ደረጃ ከመካ ቀጥላ ሐበሻ/የኢትዮጵያ ምድር ሁለተኛ ነች፤
ይቀጥላል...

👍1
በሀገር ደረጃ ከመካ ቀጥላ ሐበሻ/ኢትዮጵያ ሁለተኛ ነች፤
በርካታ የጥናትና የምርምር ባለሙያዎች በብዙ መድረኮች ላይ ሐበሻን እስላማዊ መሪ ሳይኖራት በተለይም በሙስሊሞችና በእስልምናው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ በነበራቸው የአፄዎቹ እንዴት እስልምና ጠንክሮ ሊቆም ቻለ? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። ለዚህም ወገኖቻቸው ግፍ ጥያቄ በዋነኛነት የሚወሳው እስልምና ገና በታወጀበት አፍላ ወቅት በነቢዩና (ሰዐወ) በተከታዮቻቸው ላይ የገዛ ወገኖቻቸው ግፍ ሲፈፅሙባቸው የሐበሻ ሕዝብና መሪዋ ለነብዩ (ሰዐወ) መልዕክተኞችና ለተከታዮቻቸው መጠለያ በመስጠትና በመንከባከብ ትብብር አድርገዋል፡፡
ለዚህም በነቢዩ (ሰዐወ) ዱዓና ጸሎት የተደረገላቸው ስለሆነ፣ ደግሞም እንደነ ዑስማን (ረዓ) የመሳሰሉ ታላላቅና አንጋፋ የነቢዩ (ሰዐወ) ተከታዮች ወደ ሐበሻ ተሰድደው ባገኙት እፎይታና መረጋጋት እጃቸውን ወደ ሰማይ በማንሳት ዱዓ በማድረጋቸው ጥለው ያለፉት የጸሎት አሻራ ውጤት ነው በማለት ይደመድማሉ። እንዲሁም ታዋቂውና በተከበረው መዲና ትምህርት የሚሰጡት ዝነኛው ደራሲ ሸኽ ያህያ ቢን ሚርዛ አነምካኒ አል አፍጋኒ እንዳሉት «ነቢዩን (ሰዐወ) በሕልሜ ባየሁዋቸው ቁጥር በዙሪያቸው አካብበዋቸው የማገኘው ሐበሾችን ነው» በማለት ተናግረዋል።
ሐበሻ ከሌላው ሀገርና አኅጉር ሁሉ ለየት የሚያደርጋት የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ምርጥና አንጋፋ ተከታዮቻቸውን ተቀብላ ማስተናገዷ ነው። በተጨማሪም እስልምና ሃይማኖት ከመካ በመውጣት ወደ አፍሪካ አኅጉር ለመድረስ መጀመሪያ ጉዞ ያደረገውና ያረፈው በሐበሻ ምድር ነው። ለዚህም አፍሪካዊያን ሙስሊሞች በሙሉ በየስብሰባው በነጃሺና ቢላል ታሪክ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማቸው ሲናገሩ ይደመጣሉ። በሌላ በኩልም በሐበሻ የተወለዱትና ሞተው የተቀበሩት ሶሀቢዎች በቁጥር ብዛታቸው ሐበሻን የመጀመሪያ ያደርጓታል።
እንደ ሂጅራ አቆጣጠር በ2ኛ ዓመት በተካሄደው የበድር ጦርነት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) 314 የሚሆኑ ተዋጊዎቻቸውን ብቻ አሰልፈው በታዋቂ የጎሳ መሪዎች የሚመራውና ከአንድ ሺሕ ከሚበልጥ የቁረይሽ ተዋጊ ኃይል ጋር ባደረጉት ፍልሚያ አሸንፈዋል። ያን ዕለት በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሙስሊሞች የመጀመሪያው ድል በተጐናፀፉበትና መላዕክት ሳይቀሩ ከሰማይ ወርደው የተዋጉበት ነው በሚባልለት በዚህ የጅሀድ ዐውደ ውጊያ ለእምነቱ መጀመሪያ ሸሂድ ሆኖ የተሰዋው መሀጃ አል ሐበሺ (ረዓ) ነበር። ይህም በታሪክ ሲታወስ ይኖራል።
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ለህልፈት ከበቁ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ትልቅ አደጋ ተከስቶ ነበር። ይኸውም በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ህልፈት እስልምና እንዳከተመ የቆጠሩና የእስልምና መሠረተ ሐሳብን የጣሱም ነበሩ። ትልቁ አደጋ ግን ራሳቸውን ነቢያት ነን ብለው የሰየሙ መነሳታቸው ነበር። እነሱም የማማ በሚባል አካባቢ ሙሰይለማ አል ከዛብ፣ በየመን አል አስወድ አል አንሲ ሲሆኑ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች በእስልምናና በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ውስጥ ትልቅ መከፋፈል መፍጠር ችለዋል።
ቁርአን ነው በማለትም ግጥሞች ማዘጋጀት ጀምረው ነበር። እነዚህ ሁለት አጭበርባሪዎችን የደመሰሷቸውም ሁለት የዘር ሀረጋቸው ከሐበሻ የሆኑ ጀግኖች ነበሩ። እነሱም ዋህሺይ ቢን ሀርብ አል ሐበሺ (ረዓ) ሙሰይለማን ሲገድል የነጃሺ የእህት ልጅ ፌይሩዝ አደይለሚ የሚባለው የየመኑን አል አስወድ አልአንሲ ገድሏል። በዚህ የተነሳ የእስልምና ክብርና የሙስሊሙ ኅብረተሰብ አንድነት ተመልሶ እንዲጠናከር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህም በኢስላም ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቶት ይገኛል።
በዓረቡ ዓለም የጎሳ መሪዎችም ሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ሙስሊም ሀገሮችን ያስተዳድሩ የነበሩ መሪዎች የጦር ሜዳ ጀግና ወይም በሳል መሪ ለማፍራት ሲሉ የሐበሻ እመቤቶችን ያገቡ ነበር። ይህንንም እንደ ቋሚ መርህ አድርገው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። በውጤቱም ብዙ ጀግናዎች፣ ብልህ አሊሞች፣ ገጣሚዎች ልጆችን ከሐበሻ ሴቶች አፍርተዋል። በሞግዚትነትም ቢሆን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) አቅፋ ያሳደገች ሐበሻይቷ እመቤት ኡሙ አይመን (ረዓ) ስለነበረች ይህንን ሁኔታ በመከተል ብዙ የዓረብ ሀገር መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የሐበሻ እመቤቶችን በብዛት ይመርጣሉ።
በእስልምና ታሪክ ሐበሻ ሁለት ጊዜ ኢስላማዊ ስደት የተደረገባት ብቸኛ ሀገር ነች።
የጀነት ውሀ መሆኑ በሐዲስ የተገለፀው የአባይ ወንዝ የሚመነጨው ከሐበሻ ምድር ነው።
በነቢዩ (ሰዐወ) ሀዲስ እንደተዘገበው “አራት የሐበሻ ዜጎች የጀነት ክቡራን ናቸው። እነሱም ቢላል፣ መሀጃ፣ ነጃሺ እና ሉቅማን ናቸው” ብለዋል።
(በረ/ፕሮፌሰር ኸጂ አዳም ካሚል ፋሪስ፤ "ሐበሾች በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዙሪያ" 2008 ዓ.ም/ 1437 ሂጀራ ከገጽ 145-152 መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበት የተወሰደ)

Happening Now: Attending a conference on CSOs and Academia collaboration in advancing Democratization and Human rights in Ethiopia
📣እንኳን ለ 82ተኛው ዓመት የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ክብርና ሞገስ ለአርበኛ አባቶቻቸን !
👍3
#EHRC
" ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለህ/ተ/ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።
በዚህም ወቅት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ በአማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አሳሳቢ እንደሆኑ ቀጥለዋል ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ አንስቶ መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ በአሁን ወቅት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ #በሲቪል ሰዎች ላይ ፦
- የሞት፣
- የንብረት መውደም፣
- የመፈናቀል ጉዳት መድረሱን በዚህም የሰብዓዊ መብት ስጋቱም መቀጠሉን አንስተዋል።
" መንግሥት የፀጥታ እርምጃ በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል ፤ " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል " ነገር ግን ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት እንድምታ ስላለው ፣ የሰብዐዊ መብት ተፅእኖ ስለሚፈጥር ይሄን በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።
" እስካሁን ባለው መረጃ በመነሳት ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋ ስለሆነ ኢሰመኮ #ውይይት እና #ሰላማዊ መፍትሄ አስፈላጊነትን አበክሮ በማሳሰብ ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል። " ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ዳንኤል ባቀረቡት ሪፖርት የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ሲታሰሩ የሚያዙበት መንገድ፣ ለሰብዓዊ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ፤ " በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘፈቀደ እስር እና በእስር ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች / አንዳንድ ቦታዎች ድብደባን ጨምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እስራት እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበርም ቀጥሏል " ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚፈፀሙት የዘፈቀደ እስሮች #የቤተሰብ አባላትን ጭምር ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው ሲሉ ለፓርላማው በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያስፈልገው ይሆን? ከኾነስ የትኞቹ ድንጋጌዎች በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ጥናት አካሒዷል።
በዚህ የጥናት ውጤት ይፋ ማድረጊያ እና መወያያ መድረክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ዘሃራ ሁመድን ጨምሮ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ኀላፊዎች፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ የመነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በየነ ጴጥሮስ (ፕሮፌሰር) ሕገ መንግሥቱ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ የክርክር ምንጭ መኾኑን ጠቅሰዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡ በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል ብለዋል። ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል ነው ያሉት።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ.ር) ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበትን ሁኔታ አስቀምጠዋል። በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ እንደሚሻሻልም አስገንዝበዋል።
በምሳሌት ያነሱት 391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል ነው ያሉት። በመኾኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊኾን እንደማይችል የሌሎችን ሀገራትን ሕገ መንግሥት በመጥቀስ አንስተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመኾኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል ነው ያሉት። በምሳሌነትም የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ስለመሻሻሉ ጠቅሰዋል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች መሻሻላቸውን አንስተዋል።
ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ ያሉት ዶክተር ስዩም አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል እንደሚገኝበት ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰው ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው እንደኾነ አስገንዝበዋል።
ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ እንደኾነ ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከኾነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ እንደሚችሉ አስረድተዋል። በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም እንደኾነም አሳስበዋል።

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላት ያሉት የአማካሪ ኮሚቴ አቋቋመ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላትን ያቀፈ የአማካሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከኮሚቴው አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በኮሚቴው እንዲካተቱ የተጋበዙ ግለሰቦች በተለያየ መልኩ ለኮሚሽኑ ስራዎች ድጋፍ የሚያደርጉ እንዲሁም በተለያየ ልምድ እና ሙያ ውስጥ መኖራቸውን ተገልጿል።
አባላቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እንዲሁም በምክክር ሂደት ላይ ስራዎችን ያከናወኑ ግለሰቦች እና የተቋማት ተወካዮች መሆናቸውም ተጠቁሟል።
ኮሚሽኑ ይህንን ኮሚቴ ሲያቋቋም በተቋቋመበት አዋጅ 1265/2014 ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን ጠቅሶ ለኮሚቴው ስራዎችን የሚያከናውንበትን የውስጥ መመሪያ ማዘጋጀቱንም አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በኮሚሽኑ የተከናወኑ ዋና ተግባራትን እና በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎችን በተመለከተ ለኮሚቴው አባላት ገለፃ ማድረጋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

📣 የሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም የድርጅታችንን ዜና መጽሔት ካልደረስዎት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ ዜና መጽሔቶችን( Past Issues) በሚለው ዘርፍ በመንካት ማግኘት ይችላሉ።
https://us5.campaign-archive.com/?u=d6fd3179dfa47de562581a350&id=5693530c24
በማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ያግኙን