Telegram Web
#𝘿𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 𝙩ypes

ባለፈው እንደተናገርኩት በአጭሩ 𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 ማለት ሰዎች ሌሎችን እንዴት ያለ ፍላጎታቸው እንደሚቆጣጠሩዋቸው እና ተጽእኖ እንደሚያሳድሩባቸው የማወቅ ዘዴ ነው። እና ይህ #𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 ደግሞ በውስጡ ብዙ ቴክኒኮችን ይይዛል ነገር ግን ዋና ዋና የምንላቸውን እንመልከት

1,#𝙈𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 :ይህ መንገድ ውሸቶችን እና ማታለሎችን በመጠቀም የአንድን ሰው ሀሳብ፣ ወሳኔ እንዲሁም እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ሂደት ነው።

#ለምሳሌ: ገበያ ውስጥ አንድ ነጋዴ በሱቅ ውስጥ ብዙ እያለው እንኳን "ይህ እቃ የመጨረሻው ዕቃ ነው ብትገዙት ይሻላል ሌላ ሰው ከሚወስደው"  ሊላቹ ይችላል ይህ እናንተ አአምሮ ውስጥ  አስቸኳይ እንደሆነ እንድታስቡ እና ቶሎ ውሳኔ እንድትሰጡ ያደርጋቹዋል።

2,#𝙂𝙖𝙨𝙡𝙞𝙜𝙝𝙩𝙞𝙣𝙜: ይሄ ደግሞ አንድ ሰው ስተናገረው ወይም ስላደረገው ነገር እንዲጠራጠር ማድረግ ነው፤ ማለትም ትውስታውን ማሳጣት ወይም ማደናገር እና በራሱ ግራ እንዲጋባ ማድረግ ነው።

#ለምሳሌ: ለጓደኛቹ የሆነ መጽሐፍ ሰጥታቹት እንዲመልስላቹ ብትጠይቁት እና "በፍጹም ለእኔ አልሰጠኽኝም ምናልባት ተሳስተህ/በሀሳብህ ይሆናል" ብሎ ቢመልስላቹ ሳትፈልጉት ትውስታቹን መጠራጠር ትጀምራላቹ።

3,#𝙉𝙖𝙧𝙘𝙞𝙨𝙨𝙞𝙨𝙢 : ይህ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ሲኖራቸው እና የሌሎችን ስራ ራሳቸው እንደሰሩት በማድረግ የሚያቀርቡ /ለራሳቸው ዓላማ የሌሎችን ጉልበት፣ አአምሮ የሚጠቁሙ ናቸው።

#ምሳሌ፦ በስራ ላይ ሁላቹም በጋራ ተጠባቹ የሰራቹትን ስራ አንዱ ከመሀላቹ ተነስቶ ለአለቃቹ "ይህን ሀሳብ ያመጣሁት እኔ ነኝ" በማለት ሊነግረው ይችላል በዚህም የሚፈልገውን ዕድገት ሊያገኝ ይችላል።

4,#𝙀𝙢𝙤𝙩𝙞𝙤𝙣𝙖𝙡 𝙗𝙡𝙖𝙘𝙠𝙢𝙖𝙞𝙡 ፦ አንድን ሰው ለማስገደድ/ለመጫን/ ወይም የምትፈልጉትን እንዲያደርግ ፍርሃትን፣የጥፋተኝነት ስሜትን እንዲሁም ማስፈራሪያን መጠቀም ነው።

#ምሳሌ፦ሚስትህ/ 𝙨𝙤𝙢𝙤𝙣𝙚 "ብር የማትልክልኝ ከሆነ ለቤተሰቦች ግድ እንደማይሰጥህ ለሁሉም እናገራለው" ቢላቹ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቹ እያደረጓቹ ነው።

የቀሩትን ሌሎች ክፍሎች በቀጣይ እናይ እና እንዴት ቴክኒኮቹን ለራሳችን እንደምንጠቀመው አሳያቸዋለሁ ግን ልብ እንድትሉ የምፈልገው ነገር እነዚህ የሰጠኋቹ ምሳሌዎች ሀሳቡን ለመረዳት ቀላል ስለሆኑ እንጂ መንገዶቹ በጣም አደገኛ እና ሰዎችን እስከማሳበድ፣ ራስን አስከማጥፋት፣ እንዲሁም አንድሰው ላይ ጥገኛ ሆነው የህይወት ዘመናቸውን እንዲጨርሱ የሚያደርጉ ናቸው። ስለዚህ ስንጠቀምባቸው ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት።

@ethioplot

ቻናሉን ለጓደኞቻቹ #ሼር ማድረግ አትርሱ
#𝘿𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 𝙩𝙮𝙥𝙚𝙨

ከባለፈው የቀጠለ

5,#𝙋𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙞𝙘𝙖𝙡 𝙖𝙗𝙪𝙨𝙚: ይህ ደግሞ የአንድን ሰው አእምሮ ለመቆጣጠር ያንን ሰው በንግግር ማቃለል እና ማስፈራራትን ያካትታል።

#ለምሳሌ:-አንድ አስተማሪ ተማሪውን ለማስፈራራት "መቼም ቢሆን ውጤታማ አትሆንም ደደብ ነህ!" የሚለው ከሆነ ተማሪው ላይ ሳይኮሎጂካል የሆነ ጥቃት እያደረሰበት ነው።


6,#𝙈𝙞𝙣𝙙 𝙘𝙤𝙣𝙩𝙧𝙤𝙡 :-ይህ ደግሞ እኛ የምንፈልገውን ነገር ያ ሰው እንዲቀበለው እና በጭፍን እንዲከተለን ለማድረግ ደጋግመን የምንናገረው የምናስፈራራው ከሆነ ነው።

#ለምሳሌ:-አብዛኛውን ጊዜ መሪዎች
"የእኛ ግሩፕ/ፓርቲ ብቻ ነው እናንተን ከእንደዚህ.... ነገሮች የሚጠብቃቹ"  ሊል ይችላል ይህም የእናንተ አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ስለሚያሳድር ያንን ሰው በጭፍንየ ትከተሉታላቹ።

7,#𝘿𝙚𝙘𝙚𝙥𝙩𝙞𝙤𝙣፦ የምንፈልገውን ነገር እና መታመን ከሌሎች ለማግኘት በመዋሸት እና እውነቱን በመደበቅ ሰዎችን የማታለል ሂደት ነው።
#ምሳሌ፦አንድ የቢዝነዝ ሰው ከእናንተ ጋር ሲያወራ"በአንድ ወር ውስጥ እጥፍ የሚሆን ብር ታገኛላቹ" ይላቹዋል ይህን ሲል ግን ቢዝነሱ ውስጥ ያሉትን እንቅፋቶች በፍጹም አይነገራቹም

እነዚህን እንደ አንድ የ𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 ቴክኒኮች ማየት ቢቻልም እያንዳንዳቸው ግን በውስጣቸው ብዙ ታክቲኮችን ይይዛሉ። በቀጣይ ዋና ዋና የምንላቸውን እናያለን።

@ethioplot
#𝘾𝙤𝙫𝙚𝙧𝙩 𝙢𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣
𝘾𝙤𝙫𝙚𝙧𝙩 ማለት ድብቅ የተሸፈነ የሚል ትርጉም ሲኖረው። 𝙈𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 ደግሞ አንድን ነገር በጥበብ ማንቀሳቀስ፣መቆጣጠር፣ ወይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ የምንፈልገውን ነገር ለራስ ጥቅም ማዋል የሚል ትርጉም ይኖረዋል። 

በአጠቃላይ 𝙘𝙤𝙫𝙚𝙧𝙩 𝙢𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 ማለት የአንድን ሰው አእምሮ ሰውየው በማያውቀው መልኩ መቆጣጠር ሲሆን ይህም የሚደረገው በቀላሉ ከሰውየው ጋር በመነጋገር እና ንግግራችንም በ𝙨𝙪𝙗𝙘𝙤𝙣𝙨𝙘𝙞𝙤𝙪𝙨 ማይንዱ ሲሰማው ነው።ዋና ዓላማውም የአንድን ሰው አመለካከት በጥያቄ በመቀየር እኛ የፈለግነውን ነገር በፈለግነው መንገድ ለማስደረግ ነው። 

ይህ 𝙢𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 በአብዛኛው 𝙥𝙧𝙤𝙥𝙖𝙜𝙖𝙣𝙙𝙖 ,𝙣𝙚𝙪𝙧𝙤𝙣-𝙡𝙞𝙣𝙜𝙪𝙞𝙨𝙩𝙞𝙘 𝙥𝙧𝙤𝙜𝙧𝙖𝙢𝙢𝙞𝙣𝙜, 𝙖𝙣𝙙 𝙥𝙞𝙘𝙠 𝙪𝙥 𝙖𝙧𝙩𝙞𝙨𝙩 𝙩𝙚𝙘𝙝𝙣𝙞𝙦𝙪𝙚 ይጠቀማል።  ይህን መንገድ ለመጠቀም ቀላሉ መንገድ ከምንፈልገው ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር ነው። ያንን ሰው ብናውቀውም ባናውቀውም ችግር አይኖረውም ዋናው ነገር በቀላሉ ከሰውየው ጋር መግባባት መቻላችን ነው።  ከስር እንዴት እንደምንጠቀመው እንመለከተዋለን።

@ethioplot
ከላይ የቀጠለ
𝙘𝙤𝙫𝙚𝙧𝙩 𝙢𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 ለመጠቀም መጀመሪያ ከምንፈልገው ሰው ጋር ጥሩ ግንኙነት መመስረት አለብን ይህንንም ለማድረግ ለሰውየው ቀልድ በመንገር ማሳቅ እና ከእኛ ጋር ነጻነት እና ምቾት እንዲሰማው ማድረግ እንችላለን በመቀጠል ይህን ግንኙነት ከፈጠርን በኋላ የሰውየውን ፈጣሪ እና አሳቢ የሆነውን ማይንዱን መቀየር አለብን፤ ይህም ማለት ከ ኖርማል የአስተሳሰብ ሁኔታ  𝙞𝙢𝙖𝙜𝙞𝙣𝙖𝙧𝙮 ወደ ሆነው አስተሳሰብ እንወስደዋለን ይህንንም ለማድረግ በአብዛኛው የምንፈልገውን ሰው " እንዲ ቢሆንስ? እንዲ ቢፈጠረስ? ሳለው እስቲ... " በማለት ነገሮችን 𝙞𝙢𝙖𝙜𝙞𝙣𝙚 እንዲያደርግ ማድረግ ነው። ይህን ካደረግን ያ ሰው ከኖርማል አስተሳሰቡ ነገሮችን ወደ በአእምሮ መሳል ይጀምራል። ከዚህም በኋላ ለዛ ሰው የምንፈልገውን ነገር ማዘዝ ወይም መጠየቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን።

@ethioplot
#𝙁𝙖𝙡𝙨𝙚 𝙙𝙞𝙡𝙚𝙢𝙢𝙖

ዛሬ የ 𝙢𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 𝙩𝙚𝙘𝙝𝙣𝙞𝙦𝙪𝙚 የሆነውን 𝙛𝙖𝙡𝙨𝙚 𝙙𝙞𝙡𝙚𝙢𝙢𝙖 እንመልከት። 𝙛𝙖𝙡𝙨𝙚 𝙙𝙞𝙡𝙚𝙢𝙢𝙖 ማለት ነገሮች ሁለት አማራጭ ብቻ እንዳላቸው አድርጎ ማቅረብ ማለት ሲሆን የምናቀርበው ነገር ብዙ አማራጮች ቢኖሩትም ለሰው ግን ስናቀርብ ያለውን ሰፊ አማራጮች ገድበን ሁለቱ ላይ ብቻ
𝙛𝙤𝙘𝙪𝙨 እንዲያደርግ ማድረግ መቻል ነው።

ይህንን ቴክኒክ እንዴት 𝙧𝙚𝙖𝙡 𝙡𝙞𝙛𝙚 ላይ  ምንጠቀመው ከስር ፎቶዎቹ ላይ ማየት ይቻላል።👇👇
@ethioplot
False dilemma examples
#𝙈𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 #𝙩𝙚𝙘𝙝𝙣𝙞𝙦𝙪𝙚𝙨

ማንኛውንም ጥያቄ ስትጠይቁ ቀጥታ አትጠይቁ ከዚህ ይልቅ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት በንግግራቹ መሀል መጠየቅ ስለምትፈልጉት ነገር ሆን ብላቹ የተሳሳተ መረጃ አውሩ በዚህ ጊዜ ሰዎች እናንተን ለማረም ሲል የምትፈልጉትን መልስ አብራርተው ይነግሯቹዋል።
#ለምሳሌ 
የአንድ ሰው ደሞዙን ለማወቅ ብትፈልጉ ደሞዝህ ስንት ነው ብላቹ አትጠይቁ!  ከዚህ ይልቅ "አንተ የምትሰራበት ዘርፍ/መስሪያቤት ከ5000 በላይ እንደማይከፍል ሰማሁ! " በሉ በዚህ ጊዜ ሰውየው የተናገራቹትን ስህተት ለማረም ሲል

"እረ እኔ እንኳን 10,000 ነው የሚከፈለኝ" በማለት መልሱን ይነግራቹዋል።

ስለዚህ ከቀጥታ ጥያቄ ይልቅ 𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 መጠየቀም የምትፈልጉትን መልስ ቀቀላሉ እንድታገኙ ይረዳቹዋል።

@ethioplot
ማንኛውም ንግግር በቀላሉ ለማሸነፍ  እነዚህን
#dark psychology ቴክኒኮች ተጠቀሙ

@ethioplot
2025/03/13 02:12:56
Back to Top
HTML Embed Code: