#ኢዜማ_ምን_ያስፈልገዋል ?
👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
ኢዜማ በአማራጭ ኃይልነት ጠንካራ ቁመና ያለው ፓርቲ ሆኖ እንዲወጣ አሁን ላይ “ምን ያስፈልገዋል?” ካልን ተራማጅ አስተሳሰብ ያለው የአዲሱ ትውልድ አካል የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ ቆራጥ እና ትጉህ አመራር ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን።
አሁን የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ኃላፊነትን የሚረከብበት ጊዜ ነው። ይህ ደግሞ ላለፉት 50 ዓመት ደጋግመን በሞከርነው እና ተፈትኖ በወደቀ የፖለቲካ ባሕል ውስጥ ተዘፍቆ ሊሳካ የሚችል አይደለም። አሁናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአዲስ መንፈስ አዲስ ትግል ይፈልጋል። አዲሱ የፖለቲካ ትግል የአዲሱ ትውልድ ኃላፊነት እና መብትም ጭምር ነው። በተለመደው መንገድ ባረጀ አስተሳሰብ ሄደን የተለየ ቦታ መድረስ ካለመቻላችንም በላይ የምንመኘውን ውጤት አናመጣም።
ይህ የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ድምፅ ነው። ይህ ድምፅ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተዘጋጀ፣ ፖለቲካን ተስፋ አስቆራጭ በኾነ ዝግታ አልያም በስሜት እየቸኮለም የማይጋልብ “ኢዜማን በልኩ!” ብሎ የተነሳ ቁርጠኛ አመራር ነው። ላለፉት ስድስት ዓመታት ሀገራችን የነበረችበትን አስጊ የጸጥታ ሁኔታ እና የመበተን ስጋት በቅጡ በመረዳት ኢዜማ በእርጋታ እና በስክነት ሲሠራ እንደቆየ የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ በሀገራችን ያሉትን ተለዋዋጭ ክስተቶች በጥልቀት በመገንዘብ እና በተለይም ሀገራዊ ምክክሩን እና 7 ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ከግምት በማስገባት በተግባር ኢዜማ በልኩ፣ በራሱ መንገድ፣ የራሱን ጉዞ ለማድረግ ተነስቷል።
ይህ ጉዞ ከኹሉም የፖለቲካ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግን ሀቀኛ ትብብር የሚፈልግ እንደኾነ አያጠያይቅም። እኛ እንደምናስበው ኢዜማ በዚህ ሰዓት ጠንካራ መዋቅር መዘርጋት እና ተልዕኮውን መሸከም እና መፈጸም የሚችል ቆራጥ ድርጅታዊ አመራር ያስፈልገዋል። ይህ አመራር የጠራ አረዳድ ያለው፣ እርስ በእርስ የማይጓተት፣ ስለ ዓለምአቀፍ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ እንዲሁም ውስጣዊ ድርጅታዊ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ያለው መኾን አለበት። ኢዜማ የጋራ ግብና ዓላማ ሰንቆ የሚሠራ፣ ኹሌም ለመማር ዝግጁ የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ እውነተኛ የአዲሱ ትውልድ አመራር ለመኾን ቆርጦ የተነሳ አመራር ያስፈልገዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም እኛ አራታችን (ሊቀመንበር፣ ም ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና ፋይናንስ) ተግባብተን ለመመረጥ እየሠራን እንገኛለን።
👉 ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk

የምርጫ ቅስቀሳ
የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎቸ ፓርቲያችን በታሪኩ ለሚያካሔደው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በፋይናንስና ትሬዥረር ለመወዳደር ሳመለክት ፓርቲዬ ኢዜማ የሚያራምደውን ማህበራዊ ፍትህ ጠንቅቄ በመረዳት የዜግነት ፖለቲካን ለማራመድ በማሰብ እና የዜግነት ፖለቲካ ከዘውግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነፃ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በዜግነታቸው ብቻ በእኩልነት ሊስተናገዱበት የሚችል ፓርቲ በመሆኑ ነው፡፡
ፓርቲያችን ኢዜማ በእውቀት /knowledge/ በጥልቅ አሳቢነት /Critical Thinking/ በምክንያታዊነት በመርህ የሚመራ ፓርቲ በመሆኑ በህዝብ ድምፅ እንጂ በጠመንጃ ኃይል መንግስታዊ ስልጣን ለመያዝ ፈፅሞ የማይሳተፍ መሆኑን ጠንቅቄ በመረዳት፣ ስልጣንን በሰላማዊ ትግል መፃኢ የሀገራችንን እድል በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ የስልጣን ባለቤት ሆኖ መራጩ ህዝብ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት ሰላሙ ተጠብቆ የህግ የበላይነት ተከብሮ የሚኖርባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ነው፡፡
በተለይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በ1993 ዓ.ም በነበረው የህዝብ ንቅናቄ የኢዲፓ (የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ) አባልና ተመራጭ በመሆኔ በትግሉ ወቅት በነበረኝ የህዝብ ተቀባይነት ለ3 ወራት በሸዋሮቢት እስር ቤት የመከራ ጊዜያትን አሳልፌአለሁ፡፡ ትግሉ የሚጠይቀውን ሁሉ ከመክፈል በተጨማሪ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ወጋገን ባንክ በመቀጠር የአስራ ሰባት ዓመት የሥራ ለምድ አበርክቶ ያለኝ ሲሆን በተገለፀው የሥራ ጊዜያት ውስጥ ምንም አይነት የዲስፕሊን ግድፈት የሌለብኝ እና በቅንነትና በታማኝነት እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡
በምኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ በርካታ ማህበራዊና ሰብአዊ አገልግሎት በማበርከት ከፍተኛ የሆነ ተቀበይነትና ተደማጭነት አለኝ ከላይ ከገለፅኩት በተጨማሪ እራሴን ለመለወጥ ባደረኩት ጥረት በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን ሁለተኛ ዲግሪ ለመያዝ በቅቻለሁ፡፡ ወደፊትም ሶስተኛ ዲግሪዬን ለመማር በዝግጅት ላይ ነኝ ባለኝ እውቀት በመጠቀም የፓርቲዬን የወደፊት አቅጣጫ ለማሳካት ሀገሬንና ህዝቤን እንዳገለግል ድምፃችሁን እንድትሰጡኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
ታዬ ሽመልስ
የፋይናንስ /ትሬዠረር ተወዳዳሪ/
👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
ተቋማዊ ባሕል በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ አባላት የሚኖራቸው የጋራ አረዳድ፣ ከሌሎች ድርጅቶች አባላት የሚለያቸው እሴት እና ስለተቋማዊ ጉዳዮች የሚኖራቸው ተቀራራቢ አመለካከትን የሚያካትት ነው። ተቋማዊ ባሕል የአንድ ድርጅት አባላት ውሳኔ የመስጠት አቅማቸው፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር ያላቸውን ነፃነት፣ ድርጅታዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የመመልከት ብቃታቸውን፣ ሂደትና ውጤት እንዲተሳሰሩ የማድረግ ችሎታቸውን፣ በጋራ ተናብበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኛነት እንዲሁም ለድርጅቱና ለሥራቸው ያላቸውን ተአማኒነትን የሚመለከት ጉዳይ ነው።
ከዚህ አንፃር ኢዜማ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከተለመደው የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀትና አሠራር የተለዩ ባሕሎችን ተግባራዊ አድርጓል። ኢዜማ ከሌሎች ድርጅቶች የሚለይባቸውን ባሕሎች ለመትከል ተንቀሳቅሷል። ይኹን እንጂ፤ የተጀመሩ በጎ ባሕሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና አዳዲስ ድርጅታዊ ባሕሎችን ለመትከል የሚያስችል ጠንካራ አመራር አልተፈጠረም። በሊቀመንበር ደረጃ የሚመራው የኢዜማ የድርጅት ክንፍ በሚጠበቀው ልክ ለመምራት አለመቻሉ ጅምር ተቋማዊ ባሕሎች በአባላት ዘንድ እንዳይሰርፁ እንዲሁም አዳዲስ የአሠራር ሂደቶች ስላልተፈጠሩ አባላት እምቅ አቅማቸውን አውጥተው እንዳይጠቀሙ ኾኗል። በመኾኑም፤ ተቋማዊ ባሕል ለኢዜማ ውጤታማነት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ እና የአባላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም ያለውን ጠቃሚነት በመገንዘብ፤ አባላት ድምጽ ሰጥተው የሚመርጡን ከኾነ ከተቋማዊ ባሕል አንፃር የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እናደርጋለን።
ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk
#ኢዜማን_በልኩ !!
የዳበረ ተቋማዊ ባሕል