የተከበራችሁ የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች
የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች
እኔ ጌታቸው ጳውሎስ እና
ኤልሳቤጥ ሉቃስ
ከሰኔ 28-29/2017 ዓ.ም ድረስ በሚከናወነው የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ እንደሚፈቅደው አሰራር በዚህ ጉባዔ የኢዜማ ከፍተኛ የጉባዔ ተመራጭ አመራሮች መካከል በሊቀ መንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር ታጭተናል። የከፍተኛ አመራሮች አስመራጭ ኮሚቴ ባደረገው የውስጥ ምዘና ላይ ኢዜማን በመሪነት ለማገልገል ብቁ ዕጩዎች መሆናችን ታምኖ ዛሬ ከፊት ለፊታችሁ ቆመናል።
በዚህ የፓርቲያችን ከፍተኛ የመወሰን ስልጣን ባለው የጠቅላላ ጉባዔ ፊት ቀርበን ለኢዜማ ምን እንደምንሰራ ያለንን ሀሳብ እንድናጋራ ስለፈቀዳችሁና ትኩረታችሁን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን!
ፓርቲያችን ኢዜማ ከምስረታው ጀምሮ የመጣበትን መንገድ በመገምገም ለቀጣይ ዘመን ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ ሁሉም የሚመለከተው የፓርቲው አካል በጋራ በመወያየት ኢዜማን እንደገና ማጠናከር: ማደራጀትና ወደ ትግል ማስገባት ይኖርብናል። ለዚህም ደግሞ በቀጣይ ፓርቲውን የቀደመ ክብሩን እንደገና ለመመለስ በአጭሩ የሚከተሉትን ሥራዎችን ለማስጀመርና በብቃት ለመምራት ተዘጋጅተናል።
የጠቅላላ ጉባዔው ሀሳባችን ተቀብሎ ይሁንታ ብናገኝና ብንመረጥ የሚከተሉትን ተግባራት እናከናውናለን!
1. ኢዜማ ይዞት የተነሳው የትግል መነሻ ሀሳብ እና ዓላማ ሳይሸራረፍ ዕውን እንዲሆን እንሰራለን:
2. ድርጅታችን በመርህ ላይ የፀና እንዲሆን እና በሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እንዲጪምር የማድረግ ስራዎችን እንሰራለን:
3. የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎች ያለስስት የሚታገሉለት እና የሚኮሩበት ድርጅት እንዲሆን እናደርጋለን:
4. የምርጫ ክልሎዎች ራሳቸውን በገንዘብ፣በሰው እና ቴክኖዎሎጂ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ከማዕከል የቴክኒክ እና ሙያ ድጋፎችን እናደርጋለን:
5. የ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ብቁ: ተመራጭና ተገዳዳሪ ድርጅት እንዲሆን የማዘጋጀት ሰራዎችን ከወዲሁ እንጀምራለን:
6. አባሎቻችን ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማንቃት: ማብቃት እና የማደራጀት ስራዎችን እንሰራለን:
7. የዜጎችን እና የአባላትን መብት እና ደህንነት እንዲከበር ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በትብብር እንሰራለን:
8. በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሀገራችን የመወሰን አቅም ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመታከት እንሰራለን:
9. የብሔር ፓለቲካ ወደ ኋላ ያስቀረውን ስሁት አካሄድ በዜግነት ፖለቲካ እንዲቀየር ከሚተባበሩን ተቋማት እና ግለሰቦች ጋር እንሰራለን:
10. ኢዜማ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የመሪነት ሚናውን እንዲጫወትና ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት ማንበር ሰመናዊ ኮከባችን እንዲሆን መምሪያዎቻችንና መዋቅሮቻችን እናበቃለን:
11. የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የጥንካሬው መሠረት በውስጡ የያዛቸው አባላት እና ደጋፊዎች እንደመሆናቸው የኢዜማ አባልነት ዜጎች ወደው ፈቅደው የሚመርጡትና በአባልነት የሚታቀፉበት በማድረግ የምርጫ ወረዳዎች እንዲጠናከሩ የሚያስችሉ ስራዎችን እንሰራለን:
12. የማህበራዊ ፍትህን ማስፈን ራዕያቸው ካደረጉ ከአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ሀገራት የሚገኙ መሰል ራዕይ ካላቸው ተቋማት ጋር በጋራ እንሰራለን።
13, ሴቶች: ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የማህበረሰባችን አካል ተደርገው በፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ከተመልካችነትና ከአድማጭነት ዘልቀው የመሪነት ሚናቸውን እንዲጫወቱ እንሰራለን።
ክቡራንና ክቡራት
ከላይ የጠቀስናቸውን ዐበይት ተግባራትን ስንከውን ከኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ: የፓርቲው ብሔራዊ አመራሮች: የምርጫ ክልሎችና ከሌሎች የኢዜማ አካላት ጋር በመቀናጀት ታላቅ ዓላማና ራዕይ ያነገበውን ፓርቲያችንን እንደገና ወደ ቀደመው ክብሩ እና ለህዝባችን ይዞት የገባውን ቃል እንዲፈፅም እንሰራለን።
በዚህ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፓርቲያችን እንደገና የመታደስና የማጠናከር ተግባር ለመፈፀም የጠቅላላ ጉባዔውን አደራ ለመቀበልና ይሁንታ ለማገኘት በታላቅ ትህትና እንጠይቃችኋለን!
ኢዜማን እንደገና!
ጌታቸው ጳውሎስ ( ዕጩ ሊቀመንበር)
ኤልሳቤጥ ሉቃስ (ዕጩ ምክትል ሊቀመንበር)

👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
እኛ የኢዜማ አመራር ለመኾን የምንወዳደር ግለሰቦች በለውጥ ሕግ እናምናለን። ግለሰቦችም ኾኑ ድርጅቶች ራሳቸውን ባልተቋረጠ መልኩ በመገምገም ዘመኑን የዋጀ ለውጥ ማድረግ አለባቸው። የድርጅታዊ አመራር ሳይንስ እንደሚያስተምረው፤ የማይለወጥ ነገር ቢኖር ራሱ ለውጥ ብቻ ነው።
ለውጥን ለማስተናገድ ዝግጁ ያልኾነ ድርጅት በፍጥነት በሚለወጡ ዓለምአቀፋዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ተደናቅፎ መውደቁ አይቀርም። ኢዜማ እንደ ድርጅት የአመራር መተካካትን የሚያከናውንበት ሥርዐት አለው። በየሦስት ዓመቱ ግልጽ ውድድር በማድረግ አዳዲስ አመራሮችና አስተሳሰቦች እንዲስተናገዱ ያደርጋል። ከዚህ አንፃር ፓርቲያችን ለለውጥ ዝግ አይደለም ማለት ይቻላል። ከሌሎች ድርጅታዊ የለውጥ አስተዳደር ማዕቀፎች አንፃር ግን እጅግ ብዙ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ እናምናለን።
በተለይም የአሠራርና የመዋቅር ማሻሻያዎችን እንደአስፈላጊነቱ ለመተግበር የሚያስችል የለውጥ አስተዳደር ሥርዐት ባለመኖሩ፤ የድርጅታችንን ዕድገት እንዳይፋጠን አድርጎታል። ለአሠራር ምቹ ያልኾኑ ጉዳዮች ዕየታዩ ሳይሻሻሉ በመቆየታቸው የኢዜማ ድርጅታዊ ጥንካሬ እንዲላላ ኾኗል።
በመኾኑም የታቀደና ግብታዊ ያልኾነ ለውጥ ለማስናገድ አልተቻለም። ስለዚህም፤ ንሥር ራሱን እያደሠ ሕይወቱን እንደ አዲስ እንደሚኖረው፤ ኢዜማም ዘመኑን የዋጀ የለውጥ አስተዳደር እንዲኖረው አባላት ድምጽ ሰጥተው የሚመርጡን ከኾነ ከተቋማዊ የለውጥ አስተዳደር አንፃር የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እናደርጋለን።
ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk.
#ኢዜማን_በልኩ !!
ተቋማዊ የለውጥ አስተዳደር

ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን በፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እንዲሁም አመራርነት በስፋት ማሳተፍ ከኮታ ማሟያነት ባለፈ ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈን አንዱ መሣሪያ እንደኾነ "ኢዜማን በልኩ!" ብለን የተሰባሰብን ዕጩ አመራሮች በጽኑ እናምናለን። ዋነኛው የኢዜማ ልክ አካታችነት መኾኑንም እንገነዘባለን።
አካታችነት የሚካተቱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማስደሰት የሚደረግ ብቻ ሳይኾን፤ ለዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ችግሮች መፍትሔ የማፍለቂያ መንገድም ጭምር ነው። በታሪክ ሂደትና በፖሊሲዎች አለመፈጸም ምክንያት ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በተለይም በፖለቲካው ዘርፍ በሚገባው ልክ አለመሳተፋቸው ብዙ ክፍተቶችን ፈጥሯል።
ከምንም በላይ ሴቶች እና አካል ጉዳተኛ ዜጎች በግለሰብ ደረጃ ያላቸውን አቅም ለሀገር እንዳያበረክቱ ኾኗል። ማኅበራዊና ቤተሰባዊ ቁርኝቶች እንዲበላሹ ያደረገውም ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን የሚያካትት ባሕል ባለመኖሩ ምክንያት ነው። በመኾኑም፤ “ኢዜማን በልኩ!” በሚል መርሕ የተሰባሰብነውን አመራሮች ከመረጣችሁን ከሴቶችና አካል ጉዳተኞች አካታችነት አንፃር የሚከተሉትን ቁልፍ ተግባራት እናከናውናለን።

https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk
#ኢዜማን_በልኩ !!
የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች አካታችነት

ለአንድ ተቋም ስኬት አስፈላጊ ምሶሶ ከኾኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የፋይናንስ ሥርዐት ነው። ኢዜማ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ የሥራ ክፍል በማቋቋም ድርጅቱ ዓላማውን እንዲያሳካ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
በተለይም በምርጫ 2013 ወቅት ለቅስቀሳና ለምርጫ አፈጻጸም የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ለመሸፈን ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል። ነገር ግን ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ የምርጫ ወረዳዎች ራሳቸውን በገቢ ባለመቻላቸው አብዛኛዎቹ መዋቅሮቻችን ያለቢሮ በየቤቱና በየካፌው ስብሰባ ለማድረግ ተገድደዋል።
ዛሬም ለኮንፍረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ የሚሳተፉ አባላት ወጪያቸውን በምርጫ ወረዳቸው ደረጃ ሸፍነው መሳተፍ አልቻሉም፡፡
በእርግጥ ችግሩ ከሌሎች ድርጅታዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ቢኾንም፤ ድርጅታዊ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዐቱ ግን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራበት አይደለም። በዚህም ምክንያት የሃብት ማሰባሰብ፣ የገቢ ምንጮችን ማስፋት፣ ያሉትን የፋይናንስ ሃብቶች ማስተዳደር እንዲሁም ቀጣይ የፋይናንስ ዕቅዶችን በተመለከተ በድርጅታችን ውስጥ ሰፊ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። ዓመታዊ በጀቶችን ስትራቴጂያዊ ለኾኑ ጉዳዮች በብልሀት የመጠቀም ድክመትም የችግሩ መገለጫ ነው።
በመኾኑም፤ የድርጅታችንን ስትራቴጂያዊ ግቦች የሚያግዝ የፋይናንስ ሥርዐት ለማስፈን አባላት ድምጽ ሰጥተው የሚመርጡን ከኾነ ከውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር አንፃር የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እናደርጋለን።

ውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር