Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ #ኢዜማ ን በልኩ ከተሠጡ የድጋፍ ድምፆች በጥቂቱ ይመልከቱ።
ማጠቃለያ!
⚖️
ከሰኔ 2-26/2017 ዓ.ም በሚቆየው የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የከፍተኛ አመራሮች የምርጫ ቅስቀሳ ስናካሂድ ቆይተናል። በእነዚህ የቀስቀሳ ቀናት በተቻለን መጠን ኢዜማ እንደገና መታደስ አለበት በሚለው ሀሳባችን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኢዜማ መዋቅሮች ጥያቄ መሆኑን በመረዳት ፓርቲያችን ሊያደርጉ የሚገባቸውን የማሻሻያ ሀሳቦችን ጠቁመናል። የፓርቲያችንም ከፍተኛ ስልጣን ያለው የጠቅላላ ጉባዔው በዕለቱ በማሻሻያና ሪፎርም ሀሳቦች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ በመላው ኢትዮጵያ የምንገኝ ኢዜማዊያን በአንድ ድምፅ አሰምተናል። በዚህም ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ኢዜማ ራሱን ገምግሞ እንደገና ወደ ሰፊው ህዝብ እንዲቀርብ ጥያቄ ሰንዝረናል።
ሪፎርም እና ተሃድሶ አስፈላጊ በመሆናቸው ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች: መዋቅራዊ ማሻሻያዎችና ተቋማዊ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉን አምነን ሁሉም የኢዜማ አባላት ባቀረብነው ሀሳባችን ላይ እንዲወያይ አድርገናል። የጉባዔው ይሁንታ ካገኘ የኢዜማን ማሻሻያ የሚመሩ አካላትን ለመጠቆም እንወዳለን። ከታች ወደ ላይ የቀረበውን የኢዜማን ማሻሻያ ሀሳብ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ሊመራው ይችላል። ሪፎርሙ ላይ ከመግባባት ከተደረሰ የፓርቲው መሪ ወይም ጉባዔው የሚሰይመው የሪፎርም ቋሚ ኮሚቴ ወይም ገለልተኛ የፖለቲካ ሙያ ኤክስፐርቶች በጥንቃቄ ሊመሩት ይችላሉ።
ይህን ተከትሎ ኢዜማ እንደገና ማሻሻያ የማድረግ ፍላጎቱ በጠቅላላ ጉባዔው ተቀባይነት ካገኘ ኢዜማን ለመጪው ዘመን ጊዜውን የዋጀ ተራማጅ የፖለቲካ ፓርቲ የማድረግ ፍላጎታችን ይሰምራል።
በዚህ የማሻሻያ ሀሳብ አስፈላጊነት የምታምኑ የጉባዔ ተሳታፊዎች የኢዜማን እንደገና ማሻሻያ ሀሳብ አስፈላጊነት የሚያምኑ አመራሮችን በምስጥራዊ የካርድ ድምፅ አሰጣጥ እንድትመርጡ አሳስባለሁ!
ለዚህ የውስጠ ፓርቲ ምርጫ ስኬት ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላት ማለትም የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ: የአስመራጭ ኮሚቴ: ዕጩ ተወዳዳሪዎች: የጉባዔ ተሳታፊዎች: የኢዜማ አባላትና አመራሮች እና ሌሎች በዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ከልብ አመሰግናለሁ!
የማሻሻያ ሀሳቡን ይዘው ከቀረቡት ውስጥ
ጌታቸው ጳውሎስ-ለሊቀመንበርነት
ኤልሳቤጥ ሉቃስ- ለምክትል ሊቀመንበርነት
ዶ/ር ካሣሁን ደለነ-ለዋና ፀሐፊነት
እንድትመርጡ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ!
ሙሉ የቃል ኩዳን ሰነዳችን ለማግኘት
https://www.tgoop.com/ethzema/4751
https://drive.google.com/file/d/1wscQokq5GqXMs6ORl5XiXsPUWuFzDdRn/view?usp=drivesdk

Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ #ኢዜማ ን በልኩ ከተሠጡ የድጋፍ ድምፆች ይመልከቱ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 28-29/2017 ዓ.ም. የሚደረገውን የ #ኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ ከጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ስብሳቢ ዮሐንስ መኮንን የተላለፈ መልዕክት።