የመርኃግብር ማሥታወሻ!!
በቀጣይ ስለሚኖረው ሀገራዊ ምርጫ
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (የኢዜማ ም/መሪ)
በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ
አቶ ኢዮብ መሣፍንት (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ)
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ)
ቀን: January 25/2025 (ጥር 17/2017 ዓ.ም.)
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አከባቢዎቹ: 12:00 PM ET / 9:00 AM PT
በአውሮፓ: 18:00
Zoom Meeting ID: 816 5104 2191
Passcode: 314670
የበይነ መረብ ውይይት ከ #ኢዜማ አመራሮች ጋር
በቀጣይ ስለሚኖረው ሀገራዊ ምርጫ
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (የኢዜማ ም/መሪ)
በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ
አቶ ኢዮብ መሣፍንት (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ)
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ)
ቀን: January 25/2025 (ጥር 17/2017 ዓ.ም.)
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አከባቢዎቹ: 12:00 PM ET / 9:00 AM PT
በአውሮፓ: 18:00
Zoom Meeting ID: 816 5104 2191
Passcode: 314670
የመርኃግብር ማሥታወሻ!!
የበይነ መረብ ውይይት ከ #ኢዜማ አመራሮች ጋር
በቀጣይ ስለሚኖረው ሀገራዊ ምርጫ
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (የኢዜማ ም/መሪ)
በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ
አቶ ኢዮብ መሣፍንት (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ)
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ)
ቀን: January 25/2025 (ጥር 17/2017 ዓ.ም.)
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አከባቢዎቹ: 12:00 PM ET / 9:00 AM PT
በአውሮፓ: 18:00
Zoom Meeting ID: 816 5104 2191
Passcode: 314670
የበይነ መረብ ውይይት ከ #ኢዜማ አመራሮች ጋር
በቀጣይ ስለሚኖረው ሀገራዊ ምርጫ
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (የኢዜማ ም/መሪ)
በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ
አቶ ኢዮብ መሣፍንት (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ)
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ)
ቀን: January 25/2025 (ጥር 17/2017 ዓ.ም.)
ሰዓት: ከምሽቱ 2:00
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አከባቢዎቹ: 12:00 PM ET / 9:00 AM PT
በአውሮፓ: 18:00
Zoom Meeting ID: 816 5104 2191
Passcode: 314670
በአባሎቻችን ላይ የሚደርሰው እስር ወከባና ግፍ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል!!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ ከሆኑት አንዱ የተለያዩ ሐሣቦች የሚደመጡባቸው፣ የሚወከሉባቸው ጤናማ መድብለ ፓርቲ ሥርዓት መኖር እንደሆነ ይገነዘባል።
በሀገራችንም በገዢው ፓርቲ እና ተፎካካሪዎች መካከል እንደ ባሕል የተገነባው ከእኔ ሐሣብ ውጪ ሌላው በፍፁም ትክክል አይደለም የሚል እሳቤ ዘመናዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሥርዓትን ከጀመርን አንስቶ የተጫነን ቀንበር ሆኖ እናገኘዋለን።
በዚህም ምክንያት ተፎካክሮ የተሻለ ሐሣብን በሕዝብ ቅቡል እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ በመመልከት ቀደም ባለው ጊዜያት እርስ በእርስ መገዳደል ዘግየት ብሎ ደግሞ ገዢው ሌሎች ተፎካካሪዎችን በማሠር፣ በመግደል፣ እንዲሠደዱ በማድረግ እና ሌሎች ማዋከብያ መንገዶችን በመጠቀም አንድ አውራ ገዢ ፓርቲ እንደ ልቡ የሚሆንበት ሥርዓት እንደ ባሕል ተጣብቶን ይገኛል።
ኢዜማ ይሕን መሠል አለመተማመን ለማጥራት በመጀመሪያ የፖለቲካ ፓርቲ ምንድነው? ተግባራቱስ? የሚለው ላይ ግልጽ አቋም አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም እንደኛ ባሉ የሀገረመንግሥት ምሥረታቸው ላይ አለመግባባት ባለባቸው ሀገራት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ላይ የፉክክር ብቻ ሳይሆኑ መተባበር የሚያሻቸው ጉዳዮች እንዳሉ እንደተረዳ ተፎካካሪ ፓርቲ ያለፉትን ስድስት ዓመታት ሕግና ሥርዓት ባከበረ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሰው ጥላሸት የለበሰ የፓለቲካ ባሕልን በመተማመን ላይ በመመሥረት ለማጽዳት በሚያስችል መልኩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ይህንንም አጠናክሮ ይቀጥላል።
የአንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ተግባር የጠራ የፖለቲካ አስተሳሰብ መያዝ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ግልጽ የድርጅት አሠራርና ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር መፍጠር፣ ከፖለቲካዊ አስተሳሰቦች የሚመነጩ ሀገርን ወደፊት የሚያሻግሩ አማራጭ ሃሳቦች በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሀብት እና የደኽንነት ጉዳይ ላይ ይዞ ወደ ሕዝብ በመቅረብ እና የሕዝብንም ይሁንታ በማግኘት የመንግሥት ኃላፊነትን መረከብ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ለብቻው ግን የተባለውን ለማሣካት በቂ አይደለም ይልቁንም በፖለቲካው ሜዳ ላይ ያሉ እንደ መንግሥት፣ የዴሞክራሲ ግንባታ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃን፣ ሲቪክ ማኅበራት እና ሌሎች ባላቸው ኃላፊነት ልክ ሚናቸውን ሲወጡ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን ሚና በአግባቡ አለመወጣት ወይም ከተሰጣቸው ኃላፊነት በላይ አልፈው መንቀሳቀስም ይህንን ምሕዳር ለአንዱ ሜዳውን ያለገደብ መፈንጪያ ሲያደርግለት ለሌላው እንቅፋት የበዛበት እንዲሆን ያደርጋል።
የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠቡ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንቅፋት የሆኑ ተግባራት በተለያዩ ጊዜያት ሲፈፀሙ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ደግሞ በተለይ ከፊታችን ይደረጋል ተብሎ በሚታሰበው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በሚመስል መልኩ እና በተናበበ ሁኔታ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ሊያደርገው የሚችለውን በሰው ኃይል እና ፋይናንስ መደራጀት ለማዳከም በማሰብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ አባሎቻችንን በማሠር እና ማወከብ ላይ ተጠምደው የሚገኙ የገዢው ፓርቲ ኃላፊዎችና የመንግሥት አካላት እየተመለከትን እንገኛለን፤ ከላይ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ሊያደርግ ከሚችላቸው ብለን ከጠቀስናቸው ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር መፍጠር እንዲሁም በሕገመንግስቱም በግልጽ የተቀመጠውን የመደራጀት መብትን በሚጥስ መልኩ ከታች የተዘረዘሩ አባሎቻችን ላይ ማዋከብ እየተፈፀመ ይገኛል።
እስካሁን ባለን መረጃ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች አባሎቻችን ፍትሕ ተነፍገው በእስራት ላይ ይገኛሉ
1) በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ የኢዜማ አስተባባሪ እና የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ም/ሰብሳቢ ማሕሌት ዘውዱ ከጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ የምትገኝ ሲሆን ያለበቂ ምክንያት የዋስ መብት እንኳ ተከልክላ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡
2) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን ታዬ ፋዱኮ፣ ዘነበ ዛፉ፣ ብርሃኑ ጩሌ፣ ክፍሌ ኮቶ፣ ተስፋዬ ጩቴ የሚባሉ አባሎቻችን በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ክፍሌ ኮታ እና ተስፋዬ ጩቴ ለ2 ዓመት ያህል ውሣኔ ሳያገኙ ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ሲሆን ታዬ ፋዱኮ በኮንሶ ፖሊስ መምርያ ለ5 ወር ፍርድቤት ሳይቀርብ በእስር ላይ ይገኛል፤ ቀሪዎቹ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።
3) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ባኮ ጋዘር 1 ምርጫ ክልል የገዢው የብልጽግና ፓርቲ እና የመንግሥት አካላት በዞኑ ከብልጽግና ፓርቲ ውጪ የሚንቀሳቀስ ሊኖር አይችልም በሚል ፍፁም ኢ-ዴሞክራሲያዊ መንገድ በጅምላ አባሎቻችንን እያሠሩ ሲሆን በረከት አደፍርስ፣ ተስፋዬ ሽብሩ፣ ኤፍሬም ኪዳነ፣ ተገኔ አልማው፣ አሸናፊ አታየ፣ ኩድ ኩክ፣ ምስጋናው ምስክር፣ ቅጣቱ ታደሰ፣ ሳልዬ ምልከቻ፣ አምንሾ ግዛቱ፣ በረከት በየኔ፣ ወርቁ ወንድሙ፣ እያሱ ባደገ፣ እስቁል አወና፣ ተስፋዬ ጎበና፣ ማወዘ ብርሀኑ እና አማኑኤል ጌታቸው የሚባሉ 18 አባሎቻችን ፖሊስ ሁለት ጊዜ ፍርድቤት አቅርቦ ማስረጃ ባለማቅረቡ ለሶስተኛ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ በዚሁ ዞን 23 አባላት ተይዘው በዋስ መለቀቃቸውን ከአካባቢው የፓርቲ መዋቅር የተላከልን ማስረጃ ያረጋግጣል፡፡
4) በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ተፈራ ሙጬ የተባሉ አባላችን ከጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ
5) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ምርጫ ክልል ሰብሳቢ የሆኑት ልዑልሰገድ አብረሃ ከጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ፍ/ቤት አልቀረቡም
6) በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ምርጫ ክልል ከ2013 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ ምርጫ ጀምሮ በአባሎቻችን እና አመራሮች ላይ እስር እና ወከባ ሲፈፀም ቆይቷል፡፡ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እስር ላይ የቆዩ 77 አባላቶች ከእስር ቢፈቱም አሁንም እስር እና እንግልቱ ቀጥሎ መፍትሔ ባለመገኘቱ ምክንያት ከ50 በላይ አባሎቻችችን ፍትሕ እና ፍርድ ሳያገኙ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
እንደ ኢዜማ ላለ ፉክክርን በሀሳብ ላይ ለማድረግ በሆደ ሰፊነት የአቅሙን ሁሉ እያደረገ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ላይ መሰል ድርጊት መፈጸሙ አሳዝኖናል፡፡ የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ በቃላቸው የሚገልጹት ፓርቲያችንም በሀገራችን ሊሰፍን የሚገባውን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት በተግባር ማየትን ሩቅ ያደርገዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው በአባሎቻችን ላይ የሚደርሰው እስር ወከባና ግፍ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ላይ አደጋ መደቀን እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኛ አለመሆን አድረገን የምንወስደው ሲሆን ሀገራችንን ወደኋላ እየጎተቱ የተለመደ አዙሪት ውስጥ እንዳይከተን ያሰጋናል፡፡ በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት አባሎቻችን እየደረሰባቸው ካለው ግፍ ወከባና እስር ነፃ እንዲሆኑ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
ጥር 20/2017 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ )
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
የመርኃግብር ማሥታወሻ!
ዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ
ቀን: ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24/2017 ዓ.ም.
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት
ዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ
ቀን: ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24/2017 ዓ.ም.
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት
ዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ መርኃ ግብር ተከናወነ
የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት የተገኙ ሲሆን የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የኢዜማ አካዳሚ መፅሐፍ ቤትን ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ቤተ- መፅሐፍት ተብሎ እንደሚሰየም አሳውቀዋል፡፡
የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት የተገኙ ሲሆን የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የኢዜማ አካዳሚ መፅሐፍ ቤትን ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ቤተ- መፅሐፍት ተብሎ እንደሚሰየም አሳውቀዋል፡፡