Telegram Web
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ50ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን ‹‹ the impacts of digitalization and artificial intelligence (AI) on workers' safety and health›› በሚል መሪ ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓለም ታሪክ እንዲሁም በሀገራችን አንቱታ ካተረፉ የመብት ትግሎች መካከል አንዱ የሆነው ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን የሚከበርበት ነው፤ በመሆኑም ፓርቲያችን በተለያየ ዘርፍ ተሠማርታችሁ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ እና ለሀገር እድገትና ልማት ለምታበረክቱት አስተዋጽኦ ልናመሠግን እንዲሁም እንኳን ለዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን አደረሣችሁ ለማለት ይወዳል።

አንድ ሀገር ያለ ሥራ እና ሠራተኞች አንድ እርምጃ ፈቀቅ የሚል እድገት እንደማይኖራት ይታወቃል። በሀገራችን ያለው የሥራ ዕድልና ሠራተኛ ፍላጎት እና አቅርቦት ምጥጥኖሹ እጅጉን በተዛነፈበት ይህንንም ተከትሎ የመጡ የሠራተኛውን ዕውቀቱን እና ወዙን የሚመጥን ክፍያ አለመኖር፣ የቅጥር አድሎ፣ ምቹ የሥራ ቦታ አለመኖር፣ የኑሮ ውድነት እና በመሣሠሉት ውስጥ ሆነው በተለይም በግብርና፣ ምርት፣ ግንባታ፣ ሕክምና፣ ትምሕርት እና መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች ተሠማርተው ለሀገር እድገት የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን ደግሞ በተለየ ሁኔታ ማክበር ይገባል።

ኢዜማ እነኚህ የሠራተኛውን ሕይወት ከባድ ያደረጉ መሠረታዊ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ፓርቲያችን ይዞት የተነሣው የማኅበራዊ ፍትሕ ጽንሰ ሐሣብ እና ይህንን መሠረት አድርገው ተሰናስለው በሚዘጋጁ ሕጎች እና ፖሊሲዎች እንደሆነ በጽኑ ያምናል።

እነዚህ ሕጎች እና ዋና የፖሊሲ ሐሣቦች ፍትሐዊ ክፍያ፣ የሠራተኞችን መብት በተሻለ ሁኔታ መጠበቅ በተለይም የአካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ማስከበር፣ የሥራ ቦታዎች ምቹነትን ማረጋገጥ የሚችሉ አፈፃፀሞች እና የመሣሠሉትን መያዝ ዋነኛ ናቸው።

ፓርቲያችንም ፖሊሲውን በዚህ መሠረት ቃኝቶ የያዘ የሠራተኞችን መብት ለማሥከበር ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን ለማሣወቅ ይወዳል። በሀገራችን የሚገኙ ሁሉም የሥራ ቦታዎች ለሠራተኞቻቸው ምቹና ጤናማ አካባቢን መፍጠር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

እንደሀገር በተስማማንባቸው ድንጋጌዎች መሠረት የሠራተኛ ማህበራት ፌደሬሽኖች እና ኮንፌዴሬሽን ለሚነሱ የመብት፣ የዝቅተኛ የሥራ ክፍያ ጣሪያ፣ የሥራ ላይ ጉዳት ዋስትናና የካሣ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ማንኛውም ያለሠራተኛው ፍቃድ የሚደረግ ጫናና ማዋከብ እንዲቆም ፣ የታዳጊ ልጆች የጉልበት ብዝበዛን ማስቀረት፣ የሥራ ላይ አድሎና መገለል እንዲቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ለዚህ መሣካት ሚና ካላቸው የሠራተኛ ማኅበራት እንዲሁም የሙያ ማኅበራት ጋር በቅርበት ጣልቃ ገብነት ባስወገደ መልኩ አብሮ ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ሲሆን ፓርቲያችን ለማኅበራቱ ሁልጊዜም በሩ ክፍት እንደሆነ ለመግለጽ ይወዳል።

የኢዜማ የሙያና ሠራተኛ ማህበራት መምሪያ
ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የውይይት መድረክ

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢዎች

የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት እንቅስቃሴና ተግዳሮቶቹ በዳዊ ኢብራሒም (የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት የኢንዱስትሪ ግንኙነት አማካሪ)

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በንጋቱ ወልዴ (የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ)

ቀን: ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00

ቦታ: ስታዲየም በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ
የመርኃግብር ማሥታወሻ!

የውይይት መድረክ

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት


የመነሻ ሐሣብ አቅራቢዎች

የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት እንቅስቃሴና ተግዳሮቶቹ በዳዊ ኢብራሒም (የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት የኢንዱስትሪ ግንኙነት አማካሪ)

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በንጋቱ ወልዴ (የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ)

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00

ቦታ: ስታዲየም በሚገኘው የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ
#ኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በሚል በኢዜማ ሙያ ማኅበራት መምሪያ የተዘጋጀው መርኃግብር በትላንትናው ዕለት ተካሔደ።

በመርኃግብሩ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት አማካሪ የሆኑት ዳዊ ኢብራሒም በዓለም አቀፍ እና በኢትዮጵያ የሠራተኛው የመብት ጥያቄዎች እንቅስቃሴ መነሻውን፣ በእንቅስቃሴው የተከፈለውን መሥዋዕትነት፣ የተጎናፀፋቸውን ስኬቶች እና ከዚህ በኋላ ትኩረት ሊያደርገባቸው ስለሚገቡ እንቅስቃሴዎች ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

እንዲሁም የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በሚል የኢዜማ ፖሊሲ ላይ ማብራርያ የሠጡት የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ጸሐፊ ንጋቱ ወልዴ ሲሆኑ ፖሊሲው ሲዘጋጅ ከላይ ተነሱ የተባሉ የመብት ጥያቄዎችን በሒደት ለመመለስ በሚያስችል እንዲሁም እንደ ሀገር በተለያዩ ዘርፎች ሠራተኛው የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ከፍ እንዲያደርግ ባለመ መልኩ መሆኑን ገልጸው ፖሊሲው ፓርቲው ይዞት የተነሣው ማኅበራዊ ፍትሕ እሳቤ ላይ ያጤኔጠነ እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲሁም ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር የተሠናሠለ መሆኑን በቅጡ የተረጋገጠ እንደሆነም አንስተዋል።
እንኳን ለ 84ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች መታሠቢያ ቀን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢዜማ 6ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ን እና የኢዜማ አካዳሚ ምርቃትን አስመልክቶ የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ያቀረቡት ንግግር።
ኢዜማ ከመንግሥት ጋር አብሮ መስራቱ መርህ የለሽ ሊያስብለው አይችልም


አሰፉ ተረፈ (የኢዜማ ብሔራዊ ኦዲት ኮሚቴ አባል)

በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 12 ትኩረቷን ፖለቲካ እና መርህ ላይ አድርጋ የተሠናዳች ሲሆን የወሩን እንግዳ ጨምሮ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ታሥነብበናለች፤ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/1ciHhYDVU-IojlXWD1UkAp1rC7aTA5pjx/view?usp=drivesdk

#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢዜማ አካዳሚ ምርቃት መርኃ ግብር ላይ የአካዳሚው አስተባባሪ ሐሮሌ ዮሴፍ ያደረጉት ንግግር።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ፀሐፊ ደስታ ዲንቃ በ #ኢዜማ አካዳሚ ምርቃት ላይ ያደረጉት ንግግር።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ( #ነእፓ ) ሊ/መንበር እንዲሁም ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ም/ሰብሳቢ አብዱልቀድር አደም በ #ኢዜማ አካዳሚ ምርቃት ላይ ያደረጉት ንግግር።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ( #አብን ) የሥራ አስፈፃሚ አባል የሱፍ ኢብራሒም በ #ኢዜማ አካዳሚ ምርቃት ላይ ያደረጉት ንግግር።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ( #ኢዜማ ) መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በ #ኢዜማ አካዳሚ ምርቃት ላይ ያደረጉት ንግግር።
ኢዜማ መብትን በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ መጠየቅን ይደግፋል!
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ላለፉት ረጅም ዓመታት ከሙያቸው ጋር በተገናኘ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እንደነበረ ይታወቃል። ሆኖም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግስት አካል ቀና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በቸልተኝነት በማየት ተጨባጭ ያልሆነ ተስፋ ከመስጠት የዘለለ ይህ ነው የሚባል ተግባራዊ መፍትሔ ሲሰጥ አልተስተዋለም፡፡
በተለይም ላለፈው አንድ ወር የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያቸውን በፅሁፍ ጭምር እንዳሳወቁ እና መልስ እንዲሰጣቸው በአደባባይ እየጠየቁ የሚገኙ ቢሆንም መንግስት ለጉዳዩ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒው እንቅስቃሴ ሲያደርግ መታየቱ አግባብነት ያለው ተግባር አይደለም፡፡
የባለሙያዎቹን ጥያቄ የመጠየቅ ህገመንግስታዊ መብት አክብሮ መንግስት በግልፅ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱ፣ ችግራቸውን የመረዳት ፍላጎት እንዳለው ለማሳየት ሙከራ አለማድረጉ እና ማስፈራሪያ አዘል አቅላይ መንገድን መከተሉ ሲብስም የተደረጉ ሙከራዎች ካሉ በወቅቱ በተገቢው መንገድ አለማሳወቁ ሃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የሚመነጭ የመንግስት ስህተት ነው።
የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄዎች ተገቢ መልስ የሚሰጥ የመንግስት አካል በመጥፋቱ ባለፈው ሳምንት ጥያቄው ከፍ ብሎ ወደ ከፊል ስራ ማቆም አድማ አምርቷል። በዚህም ምክንያት የጤና አገልግሎት ፈላጊው የማሕበረሰቡ ክፍል ለእንግልት እና ለስቃይ እየተዳረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ ከቀጠለም ማሕበረሰቡ ለተጨማሪ እንግልት እንዳይዳረግ ያሳስበናል፡፡
ባለሙያዎቹ ፖለቲካዊ ዓላማ እንደሌላቸው እና የትኛውም የፖለቲካ አካል ጥያቄያቸውን ተንተርሶ ትርፍ ለማግኘት እንዳይንቀሳቀስ ደጋግመው ማሳሰባቸው፤ ከኢዜማ መርህ ጋር የሚስማማ በመሆኑ መልዕክቱን በማክበር ኢዜማ ምንም አይነት ሀሳብ ላለመሰጠት በጥንቃቄ ሲመለከት ቆይቷል፡፡ ነገር ግን አሁን ያለው እንቅስቃሴ ወደ መፍትሔ ከማምራት ይልቅ እየተወሳሰበ ሕዝቡን ከፍተኛ ዋጋ እንዳያስከፍል ብሎም ለተጨማሪ ሀገራዊ ትርምስ የሚጋብዝ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ መገኘቱ አሳስቦናል። ሒደቱ በዚሁ ከቀጠለ በተግባር ለባለሙያው ጥያቄ መልስ ከማስገኘት ይልቅ ጠቃሚ ወዳልሆነ ሀገራዊ አለመረጋጋት የማምራት አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡
ኢዜማ የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄ በአግባቡ የሚረዳው እና መብትን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅን የሚደግፈው ተግባር ነው፡፡ በእርግጥ መብትን ለማስከበር የሚኬድበት ስልት ግን ዜጎችን ለአደጋ የማያጋልጥ ሊሆን ይገባል የሚል ፅኑ እምነት አለን። ሁላችንም እንደምንረዳው የስራ ማቆም አድማ የማድረግ መብት ለጤናው ዘርፍ ሲሆን ቀጥተኛ ገፈት ቀማሹ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተለያዩ የህክምና ተቋማት የሚመጣው የሕብረተሰብ ክፍል መሆኑ እሙን ነው። ይህ ከመሆኑ አንፃር አጣዳፊ ህክምና የሚፈልጉ ዜጎች በስቃይ ውስጥ የመቆየት ብሎም የመኖር ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት በመሆኑ እንዲሁም ተያያዥ የሞራል ጥያቄ የሚያስነሳ ከመሆኑ አንፃር ትክክለኛ ስልት አይሆንም፡፡
ይህን ታሳቢ በማድረግም ወደ መፍትሔው ለመሄድ እና ከአላስፈላጊ ውጥረት ለመውጣት
1ኛ. መንግስት ስህተቱን አምኖ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እየተደረገ ካለው የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩ የጤና ባለሙያዎችን እንዲፈታ ብሎም በመገናኛ ብዙኃን ወጥቶ ለባለሙያዎቹ ጥያቄዎች ያለውን መረዳት በአግባቡ እንዲገልፅ እንዲሁም ለመፍትሔው ከባለሙያዎቹ ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ቃል እንዲገባ እንጠይቃለን፡፡
2ኛ. የጤና ባለሙያዎችም ከስራ ማቆም አድማው ተመልሰው የመፍትሔው አካል ለመሆን በጋራ እንዲሰሩ እንጠይቃለን።
3ኛ. የጤና ባለሙያ ማህበራትን ያቀፈ እና የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት ያካተተ ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ፣ በመካከለኛ ጊዜ እንዲሁም በረጅም ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በመለየት ግብረ ኃይሉ ለባለሙያው እና ለማህበረሰቡ የደረሰበትን ውጤት በመገናኛ ብዙኃን እንዲያሳውቅ ምክረ ሀሳባችንን እናቀርባለን፡፡
በመጨረሻም በባለሙያዎቹ ደጋግሞ እንደተባለው ከዚህ ሂደት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መሞከርን እኛም አብዝተን የምንፀየፈው መሆኑን አስምረን እያረጋገጥን! ይህን መጥፎ ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ሀገራዊ ትርምስ እና ሁከት በመፍጠር መንግስት ላይ ያለን የፖለቲካ ቅሬታ መወጣጫ ለማድረግ መሞከርም ሆነ ሌሎች አድማዎችን አቀጠጣጥሎ የመንግስት ስልጣን ለመነቀነቅ የሚሞከር የሞኝ ሙከራ ጊዜው ያለፈበት የከሰረ መንገድ አድርገን የምንረዳው መሆኑን ለመግለፅ እንፈልጋለን፡፡
በዚህ የመብት ትግል ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ስትሳተፉ እስር እንግልት እና አፈና ለደረሰባችሁ የጤና ባለሙያዎች ሁሉ የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን በህጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ መብትን መጠየቅ በምንም መልኩ ሊያሳስር እና ሊያሳፍን እንደማይገባ በዚህ መንገድ ጥያቄውን ለማፈን መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆም ድርጊቱን እኛም አጥብቀን የምናወግዝ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
ግንቦት 10/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ ) ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ጥያቄን አስመልክቶ ከአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ።

https://www.youtube.com/live/6VlxY6lNNC8?si=5hl1S_UohRtGxVMj
2025/07/12 08:39:18
Back to Top
HTML Embed Code: