ኢዜማን እንደገና!
ምን ማለታችን ነው?
ፓርቲያችን ኢዜማ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ካሉት የሰላማዊ ፖለቲካ አራማጅ ፓርቲዎች በይዘትም በተደራሽነትም ከግንባር ቀደም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ የመጀመሪያው ነው። ይህ ፓርቲ በብዙ እህቶችና ወንድሞች የጋራ መስዋዕትነት የተመሰረተ እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የፀና ነው። ሚሊየኖች ተስፋቸውን የጣሉበት የፖለቲካ ስብስብ የተጣለበትን እምነት ይበልጥ ለማጠናከርና ታዓማኝነቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደገና ተጠንቶ: ጊዜውን የዋጄ መሆን አለበት።
ይህን ሰፊ የህዝባዊ ተቀባይነት ወደ የሚታይ የለውጥ ፋና ወጊነት ለማድረስ ትናንት የተነሳበትንና ዛሬ ያለበትን በመገምገም እራሱን ለነገ ማብቃት ይገባዋል። መላው ኢዜማዊያን በነቂስ ወጥተው የኢትዮጵያ ተስፋ የሆነውን ፓርቲ የውስጥ ግምገማና ምዘና በማድረግ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትልና ተቋማዊነት ለማረጋገጥ ተተኪዎችን ማፍራት ይገባዋል። የነበረውንና በሰፊው ህዝብ አመነታ ያገኘበትን የፖለቲካ አቋም: የተነሳበትን ህዝባዊ ጥያቄ ምላሽ ከምን እንደደረሰ የሚያጠናና በቀጣይ ለሚደረጉ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች ራሱን ያዘጋጀ የነገው ትውልድ አደራ ተቀባይ መሆን የሚችል ተቋም ሊገነባ ይገባል። እስከዛሬ የመጣበትን የኋሊት እያየ የወደፊት መድረሻውን ከተለዋዋጭ የፖለቲካ ኹናቴ ጋር እያስተያየ በየጊዜው ራሱን ማደስ የሚችል ተራማጅ ሀይል መሆን አለበት።
i, የውስጥ ግምገማ
ዋና ዋና የፖለቲካ መርሆቻችን ላይ እስከዛሬ ድረስ እንዴት እንደተጓዝን: በየትኞቹ ጎልተን ወጥተን በህዝብ ይሁንታ እንዳገኘን: የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች በጋራ በመቀመጥ ከትናንት እስከዛሬ የተጓዝንበት የአብሮነት መንገድ በነፃነት መተንተን መገምገምና ጥንካሬዎቻችንና ድክመቶቻችን መለየት አለባቸው። ይህ የውስጥ ተሃድሶ የፖለቲካ ፓርቲ ሥራዎቻችን በማጥራት በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሊሰፍን የሚችለውን የፖለቲካ ሂዴትና ተለዋዋጭነት መቋቋም የሚችል እንዲሆን አቅሙን ማሳደግ ይጠበቅበታል።
የውስጥ ግምገማችን መሠረታዊያን:
ሀ/ የመመሪያዎችና ደንቦችን
የተሻሻለው የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ በተግባር ሲፈተሽ ምን ዓይነት የአሠራር ለውጥ አምጥቷል? የመተዳዳሪያ ደንቡ ተግባራዊነት ምዘና ተደርጎበት በውስጡ የጎደለውን ክፍተት በመሙላት አሰሪ እና ገዢ በሆኑ መንገዶች መቃኘት ይገባዋል። የመተዳደሪያ ህገ ደንብ: የአሠራር መመሪያዎች: የስነ ስርዓት ደንቦች እና ሌሎች የጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔዎች በማይጣረሱ መልኩ ወደ ተግባር ሊለወጡ የሚገባቸው ስለሆነ በግልፀኝነትና በነፃነት ውይይት በማድረግ አቃፊ አሳታፊና ተፈፃሚ እንዲሆኑ መስራት
ለ/ በመደራጀታችንና በህብረት ፖለቲካ በመስራታችን እንደአንድ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ በሀገራችን በተነሱ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ የነበረንን: ያለንና የሚኖረንን ሚና በዝርዝር ትንታኔ በመለየት በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያለንን የማሳካት: የማሻሻልና የማስፈፀም አቅማችን በመዘርዘር የተግባር ግምገማ ሊናደርግ ይገባል
ሐ/ የግብረ መልስ ትንታኔ
እንደአንድ መሪ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ከምስረታችን ዕለት ጀምሮ ከነባር የፖለቲካ ታጋዮች እስከ አዳዲስ የፖለቲካ ትውልድ ገፆች: ደጋፊም አባላትም አመራርም ከነበሩ አካላት የትግል ምልከታ ግብረ መልሶችን ከልብ በመቀበል እራስን ወደውስጥ መፈተሽ ይጠበቅብናል። ከፓርቲያችን ውጪ ያሉ በተመሳሳይ የአንድነትና የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄ ከሚሰሩ ተቋማትና ደጋፊዎች: ከገዢውና ከተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዋናነት ደግሞ ከሰፊው መራጩ ህዝብ የሚሰጡንን ግብረ መልሶችን በመቀበል ኢዜማን እንደገና መስራት ይጠበቅብናል።
2, የመዋቅር ኹናቴ
ኢዜማን ከሌሎች የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለየው የአደረጃጀት መሠረቱን ከምርጫ ክልል መጀመሩ ነው። ይህ ፓርቲው ህዝባዊ መሠረት እንዲኖሩት ካደረጉት የኢዜማ አምዶች መካከል አንዱ ነው። ፓርቲያችን በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሄድ ከተፈለገ የማያቋርጥ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትል ያስፈልገዋል። የማህበራዊ መሠረቱን ተደራሽነትና ስፋት እንደገና በማጥናት እንደየአስፈላጊነቱ የመዋቅር ማሻሻያም ሊያደርግ ይገባል። የኢዜማ ተቋማዊ መሰረት ከዋና ቢሮው በተጨማሪ ሌሎች ጽ/ቤቶችም ክረምት በጋ የሚሰሩ 24/7 ለአባሎቻችን ክፍት የሆኑ የፖለቲካ ስራ የሚሰራባቸው ተቋማዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት።
3, ተተኪ ማፍራት
ለቀጣዩ ትውልድ የምናቀበለው የማህበራዊ ፍትህ የማስፈን ጥያቄን በሚታይ በሚጨበጥና በሚቆጠር የተተኪ ትውልድ ላይ መስራት አለበት። የኢዜማ አዲሱ ትውልድ የዘመኑን ፖለቲካ የተረዳ የኋላ ታሪኩን የማይዘነጋ ስለነገ የሚሰራ አዲስ የፖለቲካ ትውልድ ለመፍጠር በቁርጠኝነት መስራት አለበት። ፓርቲው በቀጣይ አንግቦት የተነሳውን ጥያቄዎችን የሚያስቀጥሉለት ስንት አባላት አሉት? ስንት አመራሮችን አብቅቷል? ይህ በወረቀትና በምዕናብ የሚቀርብ ብቻ ሳይሆን የሚታይና የሚጨበጥ መሆን አለበት።
እኚህ ከላይ የቀረቡትን የአማራጭ ሀሳቦች ላይ በመምከር ሁላችን የምንወደውንና ዋጋ የከፈልለትን ፓርቲያችን እንደገና በማደራጀት: በማደስ: ወደ ልህቀት መምራት እንችላለን።
ኢዜማ አጠቃላይ ሂደቱንና ጉዞውን ከመነሻው ሀሳብ ጋር በማነፃፀር እንደገና ራሱን ለመጭው የፖለቲካ ጉዞ ማዘጋጀት ስላለበት ይህ የፓርቲያችን የአብላጫው አባላት ጥያቄ መሆኑን ለማስገንዘብ ከጎኔ በመሆን ድጋፍ እንድታደርጉልኝና በቀጣይም ብቁ ተገዳዳሪ የሀገራዊ ፓርቲ ስብስብ እንድንሆን እንደገና መስራት ይጠበቅብናል።
ዶ/ር ካሳሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ

ለሊቀመንበርነት ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ይመኑ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በትምህርት ዝግጅቴ በሕክምና የዶክትሬት ዲግሪ አለኝ፤ የማኅበረሰብ ጤና አጠባባቅ ስፔሻሊስትም ነኝ፡፡ በተጨማሪም በቪዥዋል/ፐርፎርሚንግ ጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪ አለኝ፡፡ ከኢዜማ ምሥረታ በፊት በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ የድጋፍ ማኅበር ኮሚቴ ኾኜ ካናዳ ውስጥ የፖለቲካ መድረኮችን በማዘጋጀት ተሳትፍያለሁ፡፡ በ 2011 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ኢዜማን ለመመሥረት በነበረው ሂደት በጤና እና ትምህርት ፖሊሲ ዝግጅት ቡድን ውስጥ እንዲሁም የምርጫ ክልል 24 አባል ኾኜ ለኢዜማ ምሥረታ ጉባኤ ምርጫ ክልሉን ወክዬ ተሳትፊያለሁ፡፡ በምርጫ 2013 ኢዜማን ወክዬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተወዳድሪያለሁ፡፡
ከኢዜማ ምሥረታ ጀምሮ በተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ እንዲሁም ሰኔ 2014 ዓ.ም በተካሄደው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመኾን አገልግያለሁ፡፡ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ አስፈጻሚ አባልነት፣ በዓለም አቀፍ የድጋፍ ማኅበር ተወካይነት፤ ቀጥሎም የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ኃላፊ በመኾን እስከአሁን ድረስ ፓርቲያችንን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በመልካም ሥነምግባሬ፣ በትምህርትና ሥራ ተሞክሮዬ እንዲሁም ለሀገሬ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር እታወቃለሁ፡፡ በኪነጥበቡ ዘርፍ የግጥም ወዳጅ ሲኾን፤ ሦስት የግጥም ስብስበችን አሳትሜ ለሕዝብ አቅርብያለሁ፡፡ ዘንድሮ በሚካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም ለሊቀመንበርነት ለመወዳደር ዕጩ በመሆን አልፊያለሁ፡፡
ለምክትል ሊቀመንበርነት ማዕረጉ ግርማ ኃይሉ
በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በመሠረታዊ የጋዜጠኝነት ሙያ በተለያዩ ተቋማት ከሦስት በላይ ሰርትፊኬቶች ያለኝ ሲሆን፤ በሕግ ሙያ በኢንሹራንስ ኩባንያ ውስጥ በነገረ ፈጅነት፣ በግል ድርጅት ውስጥ በሕግ አማካሪነት እንዲሁም ካለፉት 4 ዓመታት ጀምሮ በሕግ አማካሪና ጠበቃነት እየሠራሁ እገኛለሁ።
በፖለቲካው ዘርፍ ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪነቴ ጀምሮ ህወሓት መራሹን ኢሕአዴግ በመቃወም በ1988 ዓ.ም የተደረገው ደማቅ የዐድዋ 100ኛ የድል በዓል አከባበርን በዋናነት በአዲስ አበባ እንዲከበር በሚጠይቀው ሰላማዊ ሰልፍ ከመሳተፍ ጀምሮ በመአሕድ/መኢአድ የወጣቶች እንቅስቃሴ ውስጥ በወጣት አመራርነት፣ በቅስቀሳ ቡድንና በኪነት መሪነት በመላው ሀገራችን በቀስቃሽነትና አደራጅነት፣ ፓርቲው በሚያዘጋጀው ጋዜጣ የወጣቶች አምድ ፀሐፊነትና የአሥራት ጋዜጣ ም/አዘጋጅ በመኾን አገልግያለሁ፡፡
በተጨማሪም፤ በፓርቲው ላእላይ ምክር ቤት አባልነት፣ በ1997 ዓ.ም በነበረው የቅንጅት ፓርቲ እንቅስቃሴ ውስጥ በዋና መሥሪያ ቤት በምርጫ ዘመቻ የምዕራብ ኢትዮጵያ ዴስክ አስተባባሪነትና ከምርጫው በኋላ በነበረው የምርጫ ማጣራት ሥራ ቅንጅትን በመወከል በደቡብ ኦሞ ዞን በፓናሊስትነት ተሳትፍያለሁ፡፡
በወቅቱ ከተነሳው ግርግር ጋር ተያይዞ በደረሰባቸው እስርና ድብደባ ለከፍተኛ ሕመም በመዳረጋቸው ምክንያት አካላቸውን እስከማጣት በመድረስ ለዓይነስውርነት ተዳርግያለሁ፡፡
በ 2011 ዓ.ም ኢዜማ ሲመሠረት ባለኝ አቅም ጠብታ አስተዋፅዎ ላበርክት በማለት በኢዜማ ውስጥ በምርጫ ክልል 12/13 በአባልነት፣ በወረዳው የሕገ ደንብ ተርጓሚና ዲስፕሊን ኮሚቴ አባልነት፣ በ 2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ኢዜማን ከሌሎች በተለየ መልኩ አካታችና እውነተኛ የኹሉም ዜጎች ፓርቲ መኾኑን ያሳየበትንና እስከዛሬም ድረስ ብቸኛ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለዓይነስውራን በብሬል ያሳተመ ፓርቲ እንዲኾን ጉልህ አስተዋፅዎ አድርጊያለሁ፡፡
ኢዜማ በመስከረም 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ባሻሻለው መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ባስቀመጠው መሠረት የአካል ጉዳተኞች መምሪያ በሥራ አስፈፃሚ አባልነት እንዲካተት በተወሰነው መሠረት ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ የመምሪያው ኃላፊ በመኾን፣ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ አባልነት፣ በ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ በአባልነትና የጉባኤው ም/ሰብሳቢ በመሆን፣ በ2016 ዓ.ም በተደረገው ኮንፈረንስ የአዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ፤ እንዲሁም ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡
በሥራ ትጋቴ፣ በዓላማ ጽናቴ፣ ባካበትኩት የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ተሞክሮ የምታወቅ ሀገር ወዳድ ዜጋ ነኝ፡፡ ዘንድሮ በሚካሔደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም በምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር ዕጩ በመሆን አልፊያለሁ።
#ኢዜማን_በልኩ

አሰፉ ተረፈ ውቤ እባላለሁ የትምሕርት ዝግጅቴ በአካውንቲነግ የመጀመሪያ ዲግሪ እና በቢዝነስ ማኔጅመንት ማስተርስ አለኝ።
በሥራ ዓለም በግል ድርጅቶች ውስጥ በአካውንታንትነትና በፋይናንስ ማናጀርነት ከ12 ዓመታት በላይ አገልግያለሁ፤ በግሌ ንግድ በመጀመርም ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ።
በተለያዩ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ።
ከኢዜማ ከምሥረታ ጀምሮ የምርጫ ወረዳዎችን በማዋቀር፣ በአዲስ አበባ ምርጫ ወረዳ 15 በሥራ አስፈጻሚነት እስከ 2014 ድረስ አገልግያለሁ። በተጨማሪም የብሔራዊ ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ እና ብሔራዊ የሴቶች መምሪያ ቋሚ ኮሚቴዎች ውሰጥ ተሳትፎ በማድረግ ለፓርቲው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ምርጫ ወረዳ 15ን በመወከል የኢዜማ ጉባኤ ተሳታፊ በመኾንም ለፓርቲው ይጠቅማል ያልኩትን ሀሳብ አካፍያለሁ፤ ውሳኔዎች ላይም አሻራዬን አሳርፊያለው።
በ 2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ወረዳ 15 የክፍለ ከተማ ምርጫ ታዛቢ፣ በ 2014 በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የብሔራዊ ክዋኔ እና ፋይናስ ኦዲት ዕጩ ኾኜ በመወዳደር በአንደኛ ደረጃ በጠቅላላ ጉባኤ ለመመረጥ በቅቼያለሁ።
እኔ አሰፉ ተረፈ ድርጅታችን ኢዜማን በዕውቀቴ፣ በጊዜዬ እና ጉልበቴ ኹሉ በማገልገል አብሬያቸው የሠራኃቸው ሁሉ ይመስክሩልኛል።
በማኅበራዊ ሕይወቴ ተግባቢና ሀገር ወዳድ ንቁ ዜጋ ነኝ። በአሁኑ ወቅትም የኢዜማ ብሔራዊ ክዋኔ እና ፋይናንስ ኦዲት ሰብሳቢ ኾኜ በማገልገል ላይ ነኝ።
በዘንድሮው የኢዜማ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለፋይናንስ ኃላፊነት (ትሬዠረር) ለመወዳደር ዕጩ በመኾን አልፊያለሁ።

የቅስቀሳ መልዕክት
የተቋም አመራርና አስተዳደር በተጠና፣ስልታዊ ቅደም ተከተሎችን መሠረት ባደረገና ውጤት ተኮር በኾነ መንገድ መከናወን እንዳለበት እሙን ነው። ለአንድ ሀገር ጥንካሬና ድክመት ዋነኛው ምሰሶ የተቋማት ግንባታ እንደኾነም ሳይታለም የተፈታ ነው። ጠንካራ ተቋማት ጠንካራ ሀገር ይፈጥራሉ። በአንጻሩ የተፍረከረኩ ተቋማት ያለባቸው ሀገራት ደግሞ ከራሳቸው አልፈው ለጎረቤቶቻቸውና ለዓለም ራስ ምታት ናቸው።
ኢትዮጵያችን ምዕተ-ዓመታትን የተሻገሩ ጠንካራ ተቋማት ያሏት ሀገር ናት። በሃይማኖት፣ በማኅበራዊ ቁርኝትና በሀገረመንግሥት ግንባታ ሂደት ከሚታወቁ ሀገራት መካከልም ኢትዮጵያ ትጠቀሳለች። ይኽ ሥር የሰደደ ማኅበረ-ፖለቲካዊ ጽናት ሀገራችን በብዙ ችግሮች ውስጥም ኾና ከፈተና በላይ እንድትዘልቅ እንዳደረጋት የፖለቲካ ተንታኞች በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
ይኹን እንጂ፤ የፓርቲ ፖለቲካ ከተዋወቀበት ካለፉት ሀምሳ ዓመታት ወዲህ እነዚህ ሀገራዊ እሴቶች በእጅጉ ተሸርሽረዋል። ከዚያ ቀደምም ቢኾን የሠለጠነና ፖለቲካን በዜግነት መሠረት ላይ ለማቆም የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ አልነበረም። በሂደት ተደራጅቶ መታገልና ፓርቲ ማቋቋም ሲጀመር ዋና ዋና የሀገር ምሶሶዎችንና እሴቶችን ከመጠበቅ ይልቅ አብዮታዊ አመለካከቶች ተስፋፍተዋል። በውጤቱም የተካረረ የጥላቻ ፖለቲካ ባሕል ኾኖ ዛሬም ድረስ ዘልቋል።
ኢዜማ ከምሥረታው ጀምሮ ሀገራችን ያለፈችበትን ታሪካዊ አውዶች በመገንዘብ የሠለጠነ፣ የሰከነ እንዲሁም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የዜግነት ፖለቲካ እንዲሰፍን የሚችለውን ኹሉ እያደረገ ስድስት ዓመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ፓርቲያችን ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዳዲስ ሀሳቦችንና አሠራሮችን አስተዋውቋል። ለአብነትም የድርጅትና የመሪ መዋቅር መለያየት፣ በምርጫ ወረዳ ደረጃ መደራጀት፣ ትይዩ ካቢኔ መሰየም፣ የውስጥ ምርጫን ዴሞክራሲያዊና ግልጽ ማድረግ፣ ትብብርንና ተቃውሞን በሚዛኑ ማከናወን ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢዜማ የአካል ጉዳተኞች መምሪያን ማቋቋሙ፣ በምርጫ 2013 በርካታ አካል ጉዳተኛ ዕጩዎችን ያቀረበ ፓርቲ መኾኑ እና አካል ጉዳተኞችን ብቻ ያሳተፈ የአደባባይ የቅስቀሳ መርሐግብር ያካሄደ ብቸኛ ፓርቲ መኾኑም የፈርቀዳጅነቱ ማሳያዎች ናቸው።
ፓርቲያችን ከምንም ነገር በላይ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በተጓዘባቸው ዓመታት ዳገት ወጥቷል፤ ቁልቁለትም ወርዷል። ተግዳሮቶችን ተጋፍጦ ስኬቶችን አስመዝግቧል፡፡ በዚህ ሂደት ተቋማዊ ጉዳዮችን በአግባቡ ከመምራት አንጻር ግን ጉድለቶች እንደነበሩ የሚካድ አይደለም።
ኢዜማ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዎንታዊ አስተዋጽዖ ለማድረግ እና ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ካለው ቀናኢነት አንፃር ተቋማዊ ጥንካሬውን ጠብቆ መጓዝ በእጅጉ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ይኽንንም እውን ለማድረግ ፓርቲያችን በዚህ ወቅት ለሦስተኛ ጊዜ የአመራሮች የምርጫ ሂደት እያከናወነ ነው። ይኽ የአመራር ምርጫ ኢዜማ በውስጡ ዴሞክራሲያዊነትን እንዲለማመድ ከማድረጉም ባለፈ ለተቋማዊ ጥንካሬ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው። አባላት አቅማቸውን በማሳየት ወደ አመራርነት የሚመጡበትም ስልት ነው።የአመራር ምርጫ ሥርዐቱ የደከመው ትንፋሽ ወስዶ አዲስ ኃይል እንዲመጣ በማድረግ በዱላ ቅብብሎሽ መርሕ ተቋዋሚ ቀጣይነት ዘላቂነት እንዲኖረው ያደርጋል።
በዚህም መሠረት በዘንድሮው የኢዜማ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሊቀመንበርነት፣ አቶ ማዕረጉ ግርማ በምክትል ሊቀመንበርነት፣ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ በዋና ጸሐፊነት እና ወይዘሮ አሰፉ ተረፈ በፋይናንስ (ትሬዠረር) ኃላፊነት በጋራ እንደ አንድ ቡድን ለመመረጥ ተሰባስበናል። ምንም እንኳን ምርጫው በተናጥል ቢኾንም፤ ለፓርቲያችን ያለንን ዕቅድ በማናበብ “ኢዜማን በልኩ!” ብለን በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እነሆ በይፋ መጥተናል።
ውድ የኢዜማ አባላት፤ “ኢዜማን በልኩ!” ብለን የተነሳነውን የአመራሮች ስብስብ መምረጥ ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ስትራቴጂያዊ ተግባራት አዲስ ትውልድ፣ ተራማጅ አስተሳሰብና አዲስ አቅም መፍጠር እንደኾነ ስንገልጽላችሁ በሙሉ መተማመን ነው። እኛ አራት ዕጩዎች ለድርጅታችንና ለሀገራችን ባለን ታማኝነት የምንታወቅ ስንኾን፤ ለድርጅት መዋቅር አመራርነት ከተመረጥን ጠንካራ ጅምሮችን በማስቀጠል፤ ክፍተቶችን ደግሞ በመሙላት ፓርቲያችንን ቅቡልና አስተማማኝ ለማድረግ ያለ እረፍት እንሠራለን።
በዚህ የምርጫ ሂደት ከምንም በላይ ዴሞክራሲ እንደሚያሸንፍ እርግጠኞች ነን። በዕውቀትና በመርሕ ላይ የሚደረግ የውስጥ አመራር ምርጫ በማከናወን እንደተለመደው ድርጅታችንን ተምሳሌት እንድናደርገው በዲሲፕሊን እንድንንቀሳቀስ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች ጥሪ እናቀርባለን።
አዲስ አቅምና ትውልድ ወደ አመራርነት መምጣቱ ለድርጅታችን ብቻ ሳይኾን ለሀገራችንም ተስፋ የሚያጭር ጉዳይ ነው። ሴትና አካል ጉዳተኛን አመራር በማድረግ የተሟላ አካታችነት መተግበርም ተጨማሪ አቅምን ይፈጥራል። በዚህም መነሻነት አባላት የወጠንነውን ዕቅድና አካታች አመራር ማዘጋጀታችንን ከግምት በማስገባት እንድትመርጡንና እንድትደግፉን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
“ኢዜማን በልኩ!” ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ከመረጣችሁ አዲስ ኃይል በተራማጅ አስተሳሰብ እንደምትመርጡ እናምናለን። እኛን ከመረጣችሁ ኢዜማ ስልታዊ በኾነ ቆራጥ አመራር እንዲመራ ፈቀዳችሁ ማለት ነው። እኛን ከመረጣችሁ ለዜግነት ፖለቲካ፣ ለማኅበራዊ ፍትሕና ለዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም መስፈን ተጨማሪ አቅም ፈጠራችሁ ማለት ነው።
ለአመራሮች ምርጫ ያዘጋጀነውን የቃልኪዳን ሰነድ ዛሬ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ከሰዓት ይፋ ስለምናደርግ እንድታነብቡ እየጋበዝን፤ ፓርቲያችን ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሙሉ አቅሙ በመሳተፍ ለዴሞክራሲዊ ተቋማት ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ “ኢዜማን በልኩ!” ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ይምረጡ እንላለን።
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ - ለሊቀመንበርነት
ማዕረጉ ግርማ - ለምክትል ሊቀመንበርነት
ዋሲሁን ተስፋዬ - ለዋና ጸሐፊነት
አሰፉ ተረፈ - ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት
#ኢዜማን_በልኩ!
ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት!
#ኢዜማ_ምን_ያስፈልገዋል ?
👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
ኢዜማ በአማራጭ ኃይልነት ጠንካራ ቁመና ያለው ፓርቲ ሆኖ እንዲወጣ አሁን ላይ “ምን ያስፈልገዋል?” ካልን ተራማጅ አስተሳሰብ ያለው የአዲሱ ትውልድ አካል የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ ቆራጥ እና ትጉህ አመራር ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን።
አሁን የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ኃላፊነትን የሚረከብበት ጊዜ ነው። ይህ ደግሞ ላለፉት 50 ዓመት ደጋግመን በሞከርነው እና ተፈትኖ በወደቀ የፖለቲካ ባሕል ውስጥ ተዘፍቆ ሊሳካ የሚችል አይደለም። አሁናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአዲስ መንፈስ አዲስ ትግል ይፈልጋል። አዲሱ የፖለቲካ ትግል የአዲሱ ትውልድ ኃላፊነት እና መብትም ጭምር ነው። በተለመደው መንገድ ባረጀ አስተሳሰብ ሄደን የተለየ ቦታ መድረስ ካለመቻላችንም በላይ የምንመኘውን ውጤት አናመጣም።
ይህ የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ድምፅ ነው። ይህ ድምፅ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተዘጋጀ፣ ፖለቲካን ተስፋ አስቆራጭ በኾነ ዝግታ አልያም በስሜት እየቸኮለም የማይጋልብ “ኢዜማን በልኩ!” ብሎ የተነሳ ቁርጠኛ አመራር ነው። ላለፉት ስድስት ዓመታት ሀገራችን የነበረችበትን አስጊ የጸጥታ ሁኔታ እና የመበተን ስጋት በቅጡ በመረዳት ኢዜማ በእርጋታ እና በስክነት ሲሠራ እንደቆየ የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ በሀገራችን ያሉትን ተለዋዋጭ ክስተቶች በጥልቀት በመገንዘብ እና በተለይም ሀገራዊ ምክክሩን እና 7 ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ከግምት በማስገባት በተግባር ኢዜማ በልኩ፣ በራሱ መንገድ፣ የራሱን ጉዞ ለማድረግ ተነስቷል።
ይህ ጉዞ ከኹሉም የፖለቲካ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግን ሀቀኛ ትብብር የሚፈልግ እንደኾነ አያጠያይቅም። እኛ እንደምናስበው ኢዜማ በዚህ ሰዓት ጠንካራ መዋቅር መዘርጋት እና ተልዕኮውን መሸከም እና መፈጸም የሚችል ቆራጥ ድርጅታዊ አመራር ያስፈልገዋል። ይህ አመራር የጠራ አረዳድ ያለው፣ እርስ በእርስ የማይጓተት፣ ስለ ዓለምአቀፍ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ እንዲሁም ውስጣዊ ድርጅታዊ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ያለው መኾን አለበት። ኢዜማ የጋራ ግብና ዓላማ ሰንቆ የሚሠራ፣ ኹሌም ለመማር ዝግጁ የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ እውነተኛ የአዲሱ ትውልድ አመራር ለመኾን ቆርጦ የተነሳ አመራር ያስፈልገዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም እኛ አራታችን (ሊቀመንበር፣ ም ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና ፋይናንስ) ተግባብተን ለመመረጥ እየሠራን እንገኛለን።
👉 ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk

የምርጫ ቅስቀሳ
የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎቸ ፓርቲያችን በታሪኩ ለሚያካሔደው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በፋይናንስና ትሬዥረር ለመወዳደር ሳመለክት ፓርቲዬ ኢዜማ የሚያራምደውን ማህበራዊ ፍትህ ጠንቅቄ በመረዳት የዜግነት ፖለቲካን ለማራመድ በማሰብ እና የዜግነት ፖለቲካ ከዘውግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነፃ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በዜግነታቸው ብቻ በእኩልነት ሊስተናገዱበት የሚችል ፓርቲ በመሆኑ ነው፡፡
ፓርቲያችን ኢዜማ በእውቀት /knowledge/ በጥልቅ አሳቢነት /Critical Thinking/ በምክንያታዊነት በመርህ የሚመራ ፓርቲ በመሆኑ በህዝብ ድምፅ እንጂ በጠመንጃ ኃይል መንግስታዊ ስልጣን ለመያዝ ፈፅሞ የማይሳተፍ መሆኑን ጠንቅቄ በመረዳት፣ ስልጣንን በሰላማዊ ትግል መፃኢ የሀገራችንን እድል በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ የስልጣን ባለቤት ሆኖ መራጩ ህዝብ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት ሰላሙ ተጠብቆ የህግ የበላይነት ተከብሮ የሚኖርባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ነው፡፡
በተለይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በ1993 ዓ.ም በነበረው የህዝብ ንቅናቄ የኢዲፓ (የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ) አባልና ተመራጭ በመሆኔ በትግሉ ወቅት በነበረኝ የህዝብ ተቀባይነት ለ3 ወራት በሸዋሮቢት እስር ቤት የመከራ ጊዜያትን አሳልፌአለሁ፡፡ ትግሉ የሚጠይቀውን ሁሉ ከመክፈል በተጨማሪ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ወጋገን ባንክ በመቀጠር የአስራ ሰባት ዓመት የሥራ ለምድ አበርክቶ ያለኝ ሲሆን በተገለፀው የሥራ ጊዜያት ውስጥ ምንም አይነት የዲስፕሊን ግድፈት የሌለብኝ እና በቅንነትና በታማኝነት እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡
በምኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ በርካታ ማህበራዊና ሰብአዊ አገልግሎት በማበርከት ከፍተኛ የሆነ ተቀበይነትና ተደማጭነት አለኝ ከላይ ከገለፅኩት በተጨማሪ እራሴን ለመለወጥ ባደረኩት ጥረት በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን ሁለተኛ ዲግሪ ለመያዝ በቅቻለሁ፡፡ ወደፊትም ሶስተኛ ዲግሪዬን ለመማር በዝግጅት ላይ ነኝ ባለኝ እውቀት በመጠቀም የፓርቲዬን የወደፊት አቅጣጫ ለማሳካት ሀገሬንና ህዝቤን እንዳገለግል ድምፃችሁን እንድትሰጡኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
ታዬ ሽመልስ
የፋይናንስ /ትሬዠረር ተወዳዳሪ/
👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
ተቋማዊ ባሕል በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ አባላት የሚኖራቸው የጋራ አረዳድ፣ ከሌሎች ድርጅቶች አባላት የሚለያቸው እሴት እና ስለተቋማዊ ጉዳዮች የሚኖራቸው ተቀራራቢ አመለካከትን የሚያካትት ነው። ተቋማዊ ባሕል የአንድ ድርጅት አባላት ውሳኔ የመስጠት አቅማቸው፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር ያላቸውን ነፃነት፣ ድርጅታዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የመመልከት ብቃታቸውን፣ ሂደትና ውጤት እንዲተሳሰሩ የማድረግ ችሎታቸውን፣ በጋራ ተናብበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኛነት እንዲሁም ለድርጅቱና ለሥራቸው ያላቸውን ተአማኒነትን የሚመለከት ጉዳይ ነው።
ከዚህ አንፃር ኢዜማ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከተለመደው የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀትና አሠራር የተለዩ ባሕሎችን ተግባራዊ አድርጓል። ኢዜማ ከሌሎች ድርጅቶች የሚለይባቸውን ባሕሎች ለመትከል ተንቀሳቅሷል። ይኹን እንጂ፤ የተጀመሩ በጎ ባሕሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና አዳዲስ ድርጅታዊ ባሕሎችን ለመትከል የሚያስችል ጠንካራ አመራር አልተፈጠረም። በሊቀመንበር ደረጃ የሚመራው የኢዜማ የድርጅት ክንፍ በሚጠበቀው ልክ ለመምራት አለመቻሉ ጅምር ተቋማዊ ባሕሎች በአባላት ዘንድ እንዳይሰርፁ እንዲሁም አዳዲስ የአሠራር ሂደቶች ስላልተፈጠሩ አባላት እምቅ አቅማቸውን አውጥተው እንዳይጠቀሙ ኾኗል። በመኾኑም፤ ተቋማዊ ባሕል ለኢዜማ ውጤታማነት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ እና የአባላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም ያለውን ጠቃሚነት በመገንዘብ፤ አባላት ድምጽ ሰጥተው የሚመርጡን ከኾነ ከተቋማዊ ባሕል አንፃር የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እናደርጋለን።
ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk
#ኢዜማን_በልኩ !!
የዳበረ ተቋማዊ ባሕል