Telegram Web
እንደሚታወቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች በዋናነት የሚደራጁት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ተረክበው ፖሊሲያቸውን ማስፈፀምና ያመኑበት ለመወሰን ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በየምርጫ ውድድሩ የሚከናወኑትን ሂደቶችን በማለፍ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመስረት ነው። እኛም ፓርቲያችን በቀጣይ በሚደረገው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ የየምክር ቤቶችን ወንበር መቆናጠጥ ይጠበቅብናል። ለዚህ ደግሞ የሚጠበቅብን ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ብቻ ሳይ ግዴታችንም ነው። ካለፈው 6ኛው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ በቀሰምነው ልምድና ዕውቀት በቀጣይ ለሚከናወነው ምርጫ ራሱን በአደረጃጀትም ሆነ በፖሊሲ ቁመና የደረጀ ዕጩዎችንና ተመራጮችን ለማዘጋጀት ሲባል በአዲሱ የምርጫ ቦርድ አዋጅ መሠረት ኢዜማም እንደገና ራሱን በመፈተሽ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት።

5, የኢዜማን ህዝባዊ ቅቡልነት ለማደስና አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ

ፓርቲያችን ኢዜማ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደገና ወደ ገናናነቱ መመለስ ስላለበት ኢዜማ እንደገና ራሱን ማቅረብ አለበት የሚል አቋም አለን። የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የህልውናው መሠረት በውስጡ የያዘው ፖሊሲ እና መሪዎቹ ላይ ያለው ህዝባዊ ቅቡልነት ነው። ኢዜማ ተወዳጅ አመራሮች እና የተሻሉ ፖሊሲዎችን በውስጡ ይዞ ህዝባዊ ቅቡልነትን እስካላገኘ ድረስ በቀጣይ ለሚጠብቀን ሀገራዊ ሀላፊነት ዐቢይ ተግዳሮት ይሆንብናል። የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎቹ በፓርቲያቸው አጠቃል አቋም ላይ የመተማመኛ ድምፅ እንዲሰጡ ከተደረገ በኋላ ህዝባዊ ቅቡልነት ያሳጡንን ውሳኔዎቻችን የመቀልበስ ግዴታ አለብን ብለን እናምናለን። ኢዜማ በአባላቱም ይሁን በመራጩ ህዝብ ተቀባይነትንና ቅቡልነት ለማግኘት እስከዛሬ የመጣበትንና የወሰናቸውን ውሳኔዎችን እንደገና በማጤን ወደ ግቡ መድረስ አለበት።

የኢዜማን ማሻሻያ የጠቅላላ ጉባዔው እንዲቀበል የምንጠይቅበት ምክንያቶች በዋናነት ከላይ የጠቅስናቸው ሲሆኑ እኛ በዕጩነት የቀረብነው ተወዳዳሪዎች ኢዜማን እንደገና ማሻሻል አስፈላጊነቱን ያመንበትን ምክንያቶችን አቅረበንላችኋል። የጉባዔ ተሳታፊዎች በሙሉ ድምፅ የኢዜማን እንደገና መሻሻል በመቀበል ለአገልጋይነት እንድትመርጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ዶ/ር ካሣሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሰኔ 28/29 ስለሚያካሒደው የሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን በተለይ በሥራ ሂደት የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል የህገ ደንብ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ ምክትል ሊቀመንበር ማዕረጉ ግርማ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የ #ኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
ማዕረጉ ግርማ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

ኢዜማ የሚታወቅበትን የአካታቸነት መርሕ ዕውን ለማድረግ አካል ጉዳተኞችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ትርጉም ባለው መልኩ ማሳተፍ እዳለበት አምናለሁ፡፡

የኢዜማ ልክ እያንዳንዱን የኅብረተሰብ ክፍል በማካተትና በማሳተፍ በልኅቀትና በትጋት ለድርጅታዊ ጥንካሬ መሥራት ነው፡፡
ኢዜማ በልኩ እንዲኾን ያለኝን የትምህርት፣ የሥራና የፖለቲካ ልምድ በመጠቀም በትጋት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም ዶ/ር ሙሉዓለምን ተገኘወርቅ ለሊቀመንበርነት፣ እኔ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም ወይዘሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ ዋና ጸሐፊ ዋሲሁን ተስፋዬ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
ዋሲሁን ተስፋዬ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለዋና ጸሐፊነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

የኢዜማ ልክ የዳበረ ተቋማዊ ባሕልን መገንባት ነው፡፡ ፓርቲያችን ጠንካራ የሥራ ባሕል ገንብቶ ግብ ተኮር የድርጅት መዋቅር እንዲኖረው ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ያስፈልገዋል፡፡

ድርጅታችን ኹንተናዊ ተግባራቱን በጠንካራ አመራር እንዲያከናውን ያለኝን ልምድ ከስልታዊ ዕቅድ ጋር በማቀናጀት በሳል አመራር ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም ዶ/ር ሙሉዓለምን ተገኘወርቅ ለሊቀመንበርነት፣ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ እኔ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም ወይዘሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
#ኢዜማን_እንደገና
#የምረጡኝ_ቅስቀሳ

ኢዜማ እንደ ፓርቲ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እውነተኛ፣ ተራማጅ፣ ሀገር ወዳድ፣ የበቃ፣ የመምራት አቅም እና ፍላጎት ያለው ወጣት አመራሮችን የምትፈልግበት ወቅት ነው። ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ለመድብለ ፓርቲ ስርዓትና ለዲሞክራሲ ግንባታ ወሳኛ ሚና እንዳለው እሙን ነው። ሕዝባችን እንደ ሕዝብ ከዘረኝነት፣ ከጎሰኝነት: ከኑሮ ውድነት፣ ከጦርነት፣ ከመልካም አስተዳደር ችግር፣ ከፍትህ ዕጦት፣ ከሙስና፣ ከስደት፣ ከረሀብ እና ፍራቻ ነፃ የሚያወጣው የተደራጀ ኃይል የሚፈልግበት ወቅት ነው።

ኢዜማን የዜጎችን ጥያቄ መመለስች የሚችል ለሕዝብ የወገነ ሕዝባዊ ድረጅት በማድረግ የቀደመ ገናናነቱ ሊመልስ በሚችል መልኩ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በማሰባሰብ እና በማደራጀት ለችግሮቻችን መፍትሔ የሚሆኑ ሀሳብ እንዲያቀርቡ እና በሀገራቸው ጉዳይ እንዲሳተፉ በሚያስችል መልኩ የመሪነቱን ድርሻ የሚወጣ ድርጅት እንዲሆን ማድረግ ያሰፈልጋል።

ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ዕውን ለማድረግ ፓርቲያችን ኢዜማን እንደገና በሁሉም መስክ ማጠናከር እና ማደራጀት ተገቢ ነው። የፖለቲካ ምህዳሩ የሰጠንን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የፓርቲያችን ጥንካሬና የሕዝባችን እና የሀገራችን ህልውና ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መጠቀም ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።

ኢዜማን በሕዝብ ዘንድ ታማኝ፣ ተመራጭ፣ እና ተቀዳሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አስፈላጊ ነው። በሕዝብ ዘንድ ያለን ተቀባይነት እንዲላላ ያደረገው የምንከተለው ርዕዮተዓለም ወይም ይዘናቸው የቀረብናቸው አማራጭ ሀሳቦቻችን ሳይሆኑ ሀሳባችንን በሕዝቡ ዘንድ ሰርፀው እንዲገቡ የሚያስችሉ ስራዎች ባለመሰራታቸው ነው። ለዚህ ደግሞ ዋናውን ድርሻ የሚወጣው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው። የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ደካማ መሆን ፓርቲውን ዋጋ አስከፍሎታል ብለን እናምናለን ። ከዚህም በተጨማሪ ፓርቲው በሊቀመንበርነት የመሩ አካለት የፓርቲውን መዋቅሮች የማጠናከሪያ ስራ ባለመስራታቸው ነው የሚል እምነት አለን። ብንመረጥ ኢዜማ ትውልድ ተሻጋሪ ፓርቲ እንዲሆን ከመሪ ክንፍ እና ሌሎች አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር የሚከተሉትን ተግባራት እንሰራለን፡-

1. ድርጅታችን የራሱ ዋና ፅዕፈት ቤት ሕንፃ እንዲኖረው የሚያስችሉ መሠረታዊ ስራዎችን እናስጀምራለን።

2. ከሕዝብ የሚነሱ የልማት እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያስችል መልኩ በሰው ኃይል፣ በፋይናንንስ እና በቴክኖሎጂ የተደራጅ የፖሊሲ ጥናት ክፍል እንዲኖረን እንሰራለን።

3. ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች/በአፍሪካና በሌሎች አሀጉራት ከሚገኙ/ የልማድ ልውውጥ መድረኮችን እናዘጋጃለን

4. የፓርቲውን መዋቅሮች በቴክኖሎጂ የማደራጀት ስራ እንሰራለን።

5. የአባላትን ቁጥር ለማሳደግ በበይነ መረብ የታገዘ የአባላት ምዝገባ ማድረግ የሚያስችል ስራዎችን እንሰራለን

6. የድርጅቱ የሎጅስቲክ እና በምርጫ ወቅት ስራዎችን ለማቀላጠፍ የሚያግዙ ተሽከርካሪዎች እንዲኖሩት የሚያስችሉ ሥራዎችን እንሰራለን።

7. የዜግነት ፖለቲካ እንዲያብብ ከሕዝባችን ጋር በቅርበት እንሰራለን።

8. ወቅታዊ ጎዳዮችን የሀገርን ህልውና በማይጎዳ መልኩ ለፓርቲያችን ጥቅም እንጠቀማለን።

9. የኢዜማ የፓርቲ መዋቅር ባልተዘረጋባቸው አካባቢዎች የማደራጀት ስራዎችን እንሰራለን።

10. የፓርቲውን የገንዘብ አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፈን እንቀሳቀሳለን ። የሀብት አሰባሳቢ መምሪያ በማደራጀት ራሱን የቻለ የሥራ ክፍል እንዘረጋለን። የአባላት መዋጮ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ እናረጋለን።

11. ለጋራ አላማ እና ግብ የቡድን ስራ/team work/ እንዲጎለብት እና በድርጅት ውስጥ ባህል እንዲሆን የሚያስችሉ ስራዎችን እንሰራለን።

12. የምርጫ ወረዳዎች የመስተባበሪያ ቢሮዎች የፈርኒቸር እና የኪራይ ክፍያዎች ችግር በሚፈታበት አግባብ እንሰራለን

13. በኢትዮጵያ 12ክልሎች፣ 70ዞኖች እና 2ከተማ መስተዳድሮች የሚገኙ ሲሆን በሁሉም ከባቢዎች አደረጃጀቶችን እንፈጥራለን።

ንቁ ዜጋ ምቹ ሀገር!
ኢዜማን ኢንደገና!

ጌታቸው ጳውሎስን በሊቀመንበርነት
ኤልሳቤት ሉቃስን በምክትል ሊቀመንበርነት ይምረጡ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ የፋይናንስ/ትሬዠረር አሰፉ ተረፈ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
አሰፉ ተረፈ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

ኢዜማ ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ መልኩ ራሱን የቻለ የሴቶች መምሪያ አለው፡፡ እኔም ፓርቲያችን ለሴቶች በሚሰጠው ልዩ ትኩረት መሠረት ንቁ ተሳትፎ ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡

የኢዜማ ልክ ንቁ የሴቶች ተሳትፎ ነው፡፡ ድርጅታችን አቅም ያላቸውን ሴቶች በመመልመል ብቁ የፖለቲካ አመራር እንዲኾኑ በትጋት መሥራት እንዳለበት አምናለሁ፡፡

ኢዜማ ያለውን የሰው፣ የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የቴክኖሎጂ ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀም እና የፋይናንስ አቅሙ እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሪ ለመኾን ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅን ለሊቀመንበርነት፣ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም እኔ ወ/ሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
2025/07/12 05:15:26
Back to Top
HTML Embed Code: