የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራ ፍትሕ (ኢዜማ) ሰኔ 28 – 29/2017 ዓ.ም ሲያካሂድ የነበረውን ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሰኔ 28 – 29/2017 ዓ.ም ‹‹ በሃሳብ እንፎካከራለን፤ ስለ ሀገር እንተባበራለን!›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የነበረው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን ለመላው የኢዜማ አባላት፣ ደጋፊዎች እና የኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽ እንፈልጋለን፡፡ ከመላ ሃገሪቱ ከሚገኙ የፓርቲው የምርጫ ክልሎች የተወከሉ ከ600 በላይ አባላት በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡
በየሶስት አመቱ የሚከናወነው የኢዜማ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲው ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ሲሆን፣ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የቀረቡለትን የፓርቲውን የሶስት ዓመት የሥራ ክንውን፣ የሂሳብ እና የኦዲት ሪፖርት እንደዚሁም የደንብ ማሻሻያ እና ፓርቲውን ለመጪው ሶስት አመት የሚመሩ አመራሮችን በመምረጥ ጉባዔውን በስኬት አጠናቋል፡፡
ሰኔ 28/2017 ዓ.ም በተከናወነው የመጀመሪያ ቀን መርኃ ግብር መሰረት የፓርቲው ኦዲት እና ኢንስፔክሽን እንደዚሁም የህገ ደንብ ተርጓሚ እና ሥነምግባር ኮሚቴዎች የሥራ ሪፖርታቸውን አቅርበው በጠቅላላ ጉባዔው ጸድቋል፡፡ በመቀጠልም የፓርቲው የድርጅት ክንፍ ሪፖርት በፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ማዕረጉ ግርማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እና ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ ጸድቋል፡፡
በተመሳሳይ የፓርቲው ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሃንስ መኮንን የፓርቲውን የመሪ ክንፍ የሥራ ሪፖርት አቅርበው በአባላት በርካታ ጥያቄዎች እና ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሪፖርቱ ከማሻሻያ ጋር ጸድቋል፡፡
የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ላለፉት በርካታ ወራት የፓርቲውን ደንብ ለማሻሻል በሕግ ባለሙያዎች የተዋቀረው ቡድን ያቀረባቸው የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት እና ገለፃ ከተደረገ በኋላ በአባላት የፀደቀ ሲሆን፣ የተደረገው ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
ሰኔ 29/2017 ዓ.ም በተከናወነው በሁለተኛው ቀን መርኃ ግብር የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለጉባኤተኞች ባስተላለፉት መልዕክት ፓርቲው ከውስጥም ሆነ ከውጪ ሲሰነዘርበት የቆዩትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል እና የዜግነት ፖለቲካ በጽኑ መሰረት ላይ እንዲቆም ጉዞውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ፓርቲው በ2018 ዓ.ም ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ከወዲሁ ዝግጅቱን መጀመር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በየሶስት ዓመቱ የሚከናወነውን የፓርቲውን የድርጅት ክንፍ የአመራር ፣ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን እንዲሁም ህገ ደንብ ተርጓሚ እና ሥነምግባር ኮሚቴ አባላት ምርጫ አከናውኗል::
በዚሁም መሰረት
1. ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን ተመርጠዋል፡፡ አቶ ማዕረጉ ግርማ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
2. አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ በመሆን ሲመረጡ፤
3. ወ/ሮ አሰፉ ተረፈ የፓርቲው ፋይናንስ/ትሬዢረር በመሆን ተመርጠዋል፡፡
በተመሳሳይም ፓርቲውን ለመጪው ለሶስት ዓመት የሚያገለግሉ አምስት አምስት አባላት ያሉት የኦዲት እና ኢንስፔክሽን እንዲሁም ህገ ደንብ ተርጓሚ እና ሥነምግባር ኮሚቴ አባላትም ተመርጠዋል፡፡
በመጨረሻም ፓርቲውን ለቀጣይ ሶስት አመት የሚመሩ አመራሮች ቃለመሃላ በማድረግ ጠቅላላ ጉባዔው በስኬት ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራ ፍትሕ (ኢዜማ)
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
ሰኔ 30 /2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አባላቱን በዲጂታል የአባላት አስተዳደር ሥርዓት መመዝገብ በመጀመሩ አባላትና ደጋፊዎቹን እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሰኔ 28 – 29/2017 ዓ.ም ‹‹ በሃሳብ እንፎካከራለን፤ ስለ ሀገር እንተባበራለን!›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የነበረው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው በስኬት ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
በዚህ ጉባዔ ላይ በሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የአባላት ምዝገባ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አባላትን በዲጂታል አስተዳደር ስርዓት ውስጥ መመዝገብን በይፋ የጀመረ ሲሆን በዕለቱ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሐላፊ የሆኑት አቶ ብስራት ጌታቸው የፓርቲው መሪ የሆኑትን ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን በመመዝገብ የዲጂታል ስርዓቱን በይፋ መጀመር አብስረዋል፡፡
ለዚህ ስኬት የደከማችሁ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ለሰራችሁ አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ፓርቲያችን ኢዜማ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)