Telegram Web
በዚህ ዘመን እያመጣ ያለው ትውልድ
የራሱን ሐገር ቋንቋ የማያውቅ
ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ የሆነ
ሁሉን ነገር በሳይንሳዊ መንገድ ማረጋገጥ የሚፈልግ
ስራ ተኮር የሆነ ጥያቄ የሚያበዛ ያለ አመክንዮ የማይቀበል እሺ ብሎ ተደልድሎ የማያልፍ ገደቡን ሲነኩበት የማይወድ ስለአለም አቀፋዊነት የሚያቀነቅን በአገሩ ተቀምጦ በልቡ ግን የሄደ
በባዕድ ምድር ላይ በሰው ባህል የተዋጠ በመልካምና በስህተት መካከል ያለውን ድንበር መለየት ያልቻለ ኃጢያትን የሚፈታበት መዝገበ ቃላት እንኳ የሌለው
እውነት አንጻራዊ ነው ብሎ የሚያምን ነው።
በፕሮግራም መኖር ጥሩ ነው ። የሰውነትም ልክ ነው ። ዓለም ግን ከፕሮግራም ውጭ የምትሆንበት ጊዜ ብዙ ነው ። መጠንቀቅ መልካም ነው ። እጅግ መጠንቀቅም ቀድሞ የሚገድል ነው ። አንዱን ሞት በየቀኑ እያዩት ፣ ፍርሃት ንጉሥ ሆኖባቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ። ብርሃንና ጨለማ የዕለቱ መቍጠሪያ እንደሆኑ ሁሉ ተራራና ሸለቆ የሕይወት መገለጫ ነው ። ተለዋዋጭና ተነዋዋጭ በሆነው ዓለም ላይ ሁሉም ነገር በአድራሻው አይገኝም ። የትላንት መንገዶች ዛሬ ዝግ ናቸው ፣ ደማቅ መንደሮች ዛሬ ሰው አልባ ሆነዋል ። ታሪክ የትላንቱን የምናይበት መስተዋት ነው ፤
Forwarded from ዕፀ በለስSCAM (𝚆𝚎𝚗𝚍𝚒 |𝚠𝚎𝚗𝚍𝚢𝚏𝚛𝚊𝚠|)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​

​​እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

☞︎︎︎ ልደት

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።

☞︎︎︎ ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።

☞︎︎︎ መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።

☞︎︎︎ አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።

1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።

2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

☞︎︎︎ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።

☞︎︎︎ ስድስት ክንፍ

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።

በዚያም :-
- የብርሃን ዐይን ተቀብለው
- 6 ክንፍ አብቅለው
- የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
- ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
- ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
- ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።

☞︎︎︎ ተዓምራት

የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

☞︎︎︎ ዕረፍት

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።

ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
  
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@ewuntegna
ዘመነ በርዮድ ጳጕሜን
ዓመትን በዘመናት ስንከፋፍለው በ4ት ዘመናት ይከፈላል፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ዘመነ ክረምት (ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25) ነው፤ በዘመነ ክረምት ውስጥ ደግሞ ከሚውሉት መካከል ከነሐሴ 28 እስከ ጳጕሜን ፭ት (በሠግር ዓመት ፮ት) ድረስ ያለው #ዘመነ_በርዮድ_ ይባላል፤ ይህም ወደ አዲስ ዘመን የሚያሻግረን ነው፡፡ በቅዱስ ያሬድ ድጓ መሠረትም ጎሕ (ውጋገን)፣ ነግህ (ንጋት)፣ ጽባሕ (ጥዋት)፣ ብርሃን፣ መዓልት (ዕለት)፣ ጌና (ልደት) ይባላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም (ዘመንን ቀንን በቊጥር ሰጣቸው፣ በውስጧም ያለውን ፍጥረት አስገዛቸው፡፡) እንዲል [ሲራክ 17፥2]
ጳጕሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፤ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት በስድስት መቶ ዓመት አንዴ ደግሞ ሰባት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ ጳጕሜን በአራት ዓመት አንዴ (ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ ቅበላ ስድስት ቀን ትሆናለች)፤ የአለፈውን የ2011 ዓ..ም ወርኀ ጳጕሜን ማስታወስ ግድ ነው፡፡ በዚህም ሃገራችን ኢትዮጵያ የዐሥራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃች፡፡

የጳጕሜን ጾም ጾመ ዮዲት 
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጕሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህ ጾም  በተጨማሪ ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፤ ጾሙ እንደ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ጾመ ዮዲት የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ /እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡/ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉሥ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ፥ ድንበር አስፋ፤ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ፥ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ [ዮዲት 2፥2-7]፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት፤ ከወንድ ርቃ፥ ንጽሕናዋን ጠብቃ፥ በጾም፥ በቀኖና፥ በሐዘን ተወስና የምትኖር ነበረችና፤ በተፈጠረው ጥፋት ሕዝቡ ላይ ለመጣው መከራ፤ ማቅ ለብሳ፥ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክን ሕዝቡ የሚድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለጸላት [ዮዲት 8፥2] ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንንና ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን ለመጎናጸፍ ጳጕሜን በፈቃድ እንጾማለን፡፡

ጳጕሜን የዕለተ ምጽአት መታሰቢያ
የጳጕሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጕሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ፤ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፥ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡

ጠበል በወርኀ ጳጕሜን
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጕሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጠበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጠበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፥ የተቀደስንም ያደርገናል፤ መጪውንም ሕይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ከ/የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

@ewuntegna
@ewuntegna
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (🌼 £itsum 🌼)
🌼+‹‹ ዘመኑን ዋጁ ››+🌼

ዘመናት ያረጃሉ በየዘመን ውስጥ ያለ ሰው እንደሚመላለስበት ጊዜ አርጅቶ በሌላ መተካት መገለጫው ነው እንደ ዓዲስነቱ የሚኖር ጌታችን አምላካችን ወደ እርሱ ከኃጥያት ዘመናችን በንስኅ ተለውጠን እንመለስበት ዘንድ ዘመን ይጨምርልናል ።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን በላከው መልእክቱ እንዴት በዘመን መመላለስ እንደሚገባን ይነግረናል ፦ "እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደ ሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንደ ምትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖቹ ክፍዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ"። (ኤፌ 5፥15-16) መዋጀት ማለት ፦ መፈተሽ ፣ መመርመር ፥ ማወቅ ማለት ነው ። ጥበበኞችስ ስጋውያን ያልሆኑት እንዴት በማን እንደ ሚመላለሱ ፈትሸው የሚያውቁ ናቸው ። በሥነ ምግባር የሚኖሩ እርሱን በህግ "የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔር መፍራት ነው " መዝ 110፥) እንደሚል የሚለወጠን ሰውን ሳይሆን የማይለወጠውን እርሱን እያዩ እንደሚኖሩት ጥበበኞች በተሰጠን ዘመን እንድንመለስ ይጠራናል ።

" የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትን ወደ ጻድቃን ጥበብ " የሚመልስ " ሉቃ (1፥17) አባቶች አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ልጆች የተባሉትም ሐዋርያት ጥበብ ወደተባለው ክርስቶስ የሚመለስ ነው እንደተባለለት ምድራዊው መልአክ ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ወደ ሚነግረን እንመለስ እኛን ወደ ጥበብ ክርስቶሰ ክፍ ቀን ከተባለበት እኛና እግዚአብሔር ከተለያየንበት እንደሞኝ ዘመንን በኃጥያት ካሳለፍንበት ተመለሱ ተውት ይብቃቹሁ ጽድቅን የምትሰሩበት ዘመን ይሁን እያለ የተሰጠን ዘመን ወደ እርሱ መመላሻ መሆኑን የሚያስተምረን ነውና። ሐዋርያት "እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን" 1ኛ ቆሮ 1 ፥16 ይሉ ነበር ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ሐሳብ ስለነበራቸው ዘመናችንን ሰማያዊ ሐሳብ ምናስብበት ወደ ቅዱሳን የሕይወት መንገድ ምንመለስበት ያድርግልን ።


እንኳን አደረሳቹሁ ለአዲሱ ዓመት 2017 ዓ.ም ። 🙏🌼

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
መስከረም 1 2016 ዓ.ም
ዲላ ኢትዮጵያ

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
መስከረም 1 ቀን ለምን የዘመን መለወጫ ሆነ? 
መስከረምና የዓመቱ ወራት ትርጉማቸውስ?

( በከመ ጸሐፎ ጴጥሮስ አሸናፊ )

ዘመን መለወጫ ለምን መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲያትቱም ብርሃናት/ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜን ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ 
ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ ይላልና /ሔኖክ.21.49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድረገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡/ኩፋ.7.1/
በመሠረቱ ዘመን ተለወጠ ሲባል የሚለወጡት ወራቱ ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ የሚከሰቱት/የተከሰቱት/ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር /ገጠመኝ/ ሲሆን ወራቶቹ ግን ያው በየዓመቱ እየተፈራረቁ ይመጣሉ፡፡ ዘመን መለወጫ ላይ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደቀጣዩ ክፍል /ደረጃ/ የሚለወጥበት፣ ገበሬው የክረምቱን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋ ወራት የሚቀበልበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሶ የፀሐይን ወራት የሚቀበልበት ሌላውም እንደዚያ ሆነው ወራቶቹ በዚያ ዘመን ያለው የተፈጥሮ ክስተቶች የሚለወጥበት ዘመን ተለወጠ እየተባለ ይነገራል፡፡

የቀመር መጀመሪያ የሆነው ዕለት ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን ነው።  ነገር ግን የሚያዝያን እንዳንጠቀም መዓልቱና ሌሊቱ እኩል አይደለም፡፡

ይህን ተከትሎ በሚዞር ነገር መስማማት እንጂ ሁሉም መነሻ ሆኖ ማገልገል ይችላሉ፡፡ ለመስማማት ደግሞ በቂ ምክንያት ያስፈልጋል፡፡ሊቃውንት ደግሞ ብዙ ምክንያት ያለው መስከረም ስለሆነ መነሻቸው በመስከረም እንዲሆን አድርገዋል፡፡ የመጻሕፍት መምህራን ሌላ ምክንያት ይጨምራሉ፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡበት የሰባተኛው ወር መባቻ እንደሆነ እግዚአብሔር አዝዟል፡፡ ይኸውም መስከረም ነው ይላሉ፡፡ ክረምት በጨለማ በብሉይ ይመሰላል ፀሐይ የሚወጣበት መስከረም ደግሞ በብርሃን በሐዲስ ኪዳን ይመሰላል፤ ስለዚህ ለዓውደ ዓመት መነሻ ወር መስከረም ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ መስከረም ነው፡፡ መስከረም 1 ቀን ርእሰ ዓውደ ዓመት ተብሎ ይጠራል፡፡ ትርጉሙም ርዕስ የአንድ ጽሑፍ /ንግግር በር እንደሆነ ሁሉ በዓመት ውስጥ ያሉ ዓውደ ዓመቶች /በዓሎች/ እና አጽዋማት ማወቂያ /ማመላከቻው/ መስከረም 1 ቀን የሚውልበት ነውና፡፡ እንዲሁም የዓመቱ በዓላትና አጽዋማት የሚታወጀው መስከረም 1 ቀን ነው፡፡ በዚሁም ዕለት መዓልቱን /በፀሐይ/ ሌሊቱን /በጨረቃ/ በመቁጠር ምሥጋና ለእግዚአብሔር ይቀርባል፡፡

መስከረም ማለት ምን ማለት ነው ? የመስከረም ወር ትርጓሜስ?

መስከረም ማለት ከግእዝ የመጣ ቃል ሲሆን (ከሪም- ወይም ከሪሞት)
(መዝከረ-ውይም -ከረም) ከሚሉ የግእዝ ቋንቋዋች የተገኘ የውህድ አረፍተ ነገሮች ውጤት ነው ።
1️⃣ ከሪም ወይም ከሪሞት ማለት ምን ማለት ነው ?
ከሪም ወይም ከሪሞት ማለት-በግእዝ የከረመ፣ የቆየ የሰነበተ ማለት ሲሆን ይህም የክረምት ቆይታ የሚገልፅ እና የክረምት መገባደጃ እንደሆነ የሚያመለክት ነው በሌላ ፍቺ የከረመው ክረምት ማለቂያ የመፀው መባቻ መጀመሪያ ማለት ነው ።
2️⃣ ሌላው ደሞ መዝከረ - ከረም ከግእዝ ቃል የተገኝ ቃል የተገኝ ውህድ ሲሆን ትርጓሜውም መዝከር ማለት በግእዝ መዘከር፣ ማስታወስ፣ ማሰብ ማለት ነው።
ከረም ማለት ደሞ የቆየ፣ የከረመ፣ የሰነበተ ማለት ሲሆን በአጠቃላይ
መዝከረ ከረም ማለት የከረመን የቆየን መዘከር ማስታወስ ማለት ነው
ለዚህም ሲባል የቆየውን ዓመት የምንዘክርበት አዲሱን ዓመት የምንቀበልበት ወር ለማለት መዝከ ከረም(መስከረም) እንለዋለን። በዚህም ምክንያት አውደ ዓመት አዲስ ዓመት ሆነ የከረመውን የቆየውን አሮጌውን ዓመት ተሸኝ የምንቀበልበት ሰናይ ወር መስከረም ሆነ አሮጌው የቆየው ክረምት ተሸኜ ማለት ነው።
መዝከ ከረም ወደ አማርኛ ሲመለስ አንዱን ከግእዝ በመተው
መስከረም ወደሚል አማርኛ ተቀይሮ ይጠራል። የወራቶች መጀመሪያ የአዲስ ዓመት መባቻ የክረምት መገባደጃ ለማለት መስከረም ተባለ።

13ቱ የኢትዮጵያ ወራት አሰያየም

1️⃣.   መስከረም
የግእዝ ሥርወ ቃሉ  - መስ እና ከረም ሲሆን 
ትርጉሙም መስ፣ አለፈ፤
ከረም፣ ክረምት ማለት ሲሆን፤ መስከረም ማለት ክረምት አለፈ ማለት ነው።

2️⃣. ጥቅምት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ጠቀመ።
ትርጉም ሠራ፣ ጠቃሚ ጊዜ ማለት ነው።

3️⃣. ኅዳር
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ።
ትርጉም አደረ፣ ሰው በወርሃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል።

4️⃣.  ታኅሣሥ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ኀሠሠ።
ትርጉም መረመረ፣ ፈለገ፣ በመኽር ወቅት የሰብል ምርመራ ያመለክታል።

5️⃣.  ጥር
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ነጠረ።
ትርጉም ጠረረ፣ ብልጭ አለ፣ ነጻ በራ የፀሀይን ግለት ወቅት ያሳያል።

6️⃣.  የካቲት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ከቲት።
ትርጉም (የእህልን) መክተቻ ማለት ነው።

7️⃣. መጋቢት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ መገበ።
ትርጉም በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት) ማለት ነው።

8️⃣. ሚያዚያ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ መሐዘ።
ትርጉም ጎረመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ(ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ)

9️⃣. ግንቦት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ገነበ።
ትርጉም ገነባ፣ ሰራ፣ ቆፈረ፣ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል።

1️⃣0️⃣. ሰኔ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ሰነየ።
ትርጉም፣ አማረ ማለት ነው።

1️⃣1️⃣.  ሐምሌ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ ሐመለ።
ትርጉም ለቀመ(ለጎመን)

1️⃣2️⃣. ነሐሴ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ አናህስየ።
ትርጉም አቀለለ፣ ተወ የክረምቱን እያደረ መቅለሉን ያመለክታል።

1️⃣3️⃣.  ጳጉሜን
ሥርወ ቃሉ ግሪክ ሲሆን ኤጳጉሚናስ።
ትርጉም ተጨማሪ ወር ማለት ነው ።

መልካም አዲስ ዓመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

👉
#አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን የሚሆኑ ደቀ መዛሙርትህንና ንጹሓን ሐዋርያትን እንዲህ ያልሃቸው
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌺
#እናንተ የምታዩትን ያዩ ዘንድ ብዙ ነቢያት ጻድቃን ወደዱ #አላዩም

🌺 እናንተ ዛሬ የምትሰሙትንም ይሰሙ ዘንድ ወደዱ
#አልሰሙም

👉
#የእናንተ ያዩ ዓይኖቻችሁና የሰሙ ጆሮቻችሁ ግን #የተመሰገኑ ናቸው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

#ከሌሎቹ ለይቶ ኃጢአት በደላችን ሳይመለከት ቸር አምላክ በቸርነቱ ለዚህች ቀን #ያደረሰን ስሙ የተመሠገነ ይሁን ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


#መልካም አዲስ ዓመት
ርእሰ ዐውደ ዓመት

ዐውደ ዓመት መነሻው ዖደ ከሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ዖደ ዞረ፤ዐውድ ዙርያ፣ ማለት ነው፤ ዐውደ ዓመት የፀሐይ ዐውደ ዓመት ፫፻፷፭ ዕለት ከሩብ ይላል፡፡ (ምንጭ፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰወ ወግስ ወመዘግበ ቃላት ገጽ ፮፻፹፯)፡፡ ወበዐውዱ ለወእቱ መንበር፡፡ ይቀውሙ ዐውዶ፡፡ ዐውደ ጸሓይ፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት (ራእ.፬፡፬፤ አቡሻህር ፳፫)

ዐውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ ይባላል፡፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መፅምቅን ያወሳናል፤ የቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍት (ምትረተ ርእሱ) የሚታሰበው መስከረም ሁለት ቀን ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስን በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ መካከል የነበረ መሸጋገሪያ ነው፡፡ መታሰቢያ በዓሉም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ከሆነው ካለፈው ዓመት የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ወደሚሆነው አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በሆነው በመስከረም አንድ ቀን ይከበራል፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በነቢያት መጨረሻ በሐዋርያት መጀመሪያ ተገኝቶ ዘመነ ሐዲስን እንደሰበከና ከዘመነ ብሉይ ወደ ዘመነ ሐዲስ መሸጋገሪያ ጊዜ ላይ ስለነበረ ያለፈውን ዘመን የምንሸጋገርበት የዘመን መለወጫ ቀን የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ (ማር.፩፥፪-፭)

የዘመን ቆጠራ ከጌታችን ልደት በፊት የነበረው አገልግሎት  የሰው ልጆች ሁሉ በተለይ አበው ነቢያት/ በተስፋ ይጠብቁት የነበረውን የጌታችንን መምጣት የቀረውን ጊዜ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን አጽዋማትና በዓላት ለማወቅ ነበር፡፡ ተስፋው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ የዘመን ቆጠራ ዋና አገልግሎቱ በዓላትና አጽዋማት በዓመቱ የሚወሉበትን ዕለት ለማወቅ ነው፡፡ እነዚህ በዓላት እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት ለሰው ልጆች ያደረጋቸው ድንቅ ነገሮችና ውለታዎች የፈጸመባቸው ስቅለት፣ ትንሣኤ እና ሌሎችም በዓላት የሚታሰቡባቸው ናቸው፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓቱ መሠረት የበዓላቱና የአጽዋማቱ መደብ የሚታወቅበትና የዘመናቱ ሂደት ተቀምሮ የሚታወጅበት ዕለት መስከረም አንድ ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመትን ታከብራለች፡፡ የኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ በዚህ ወር የመጀመሪያው ቀን የተለያዩ መጠሪያዎች አሉት፡፡ እነርሱም ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡

አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን ለምን ይከበራል?

በኢትዮጵያ (ርእሰ ዐውደ ዓመት) ዘመን መለወጫ በመስከረም ወር የሆነበትን ምክንያት ሊቃውንቱ ሲያትቱ ብርሃናት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብት የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ አጠናቀው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ፲፪ ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ ፫፻፰፬ ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና (ሄኖክ. ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው፡፡ (ኩፋሌ. ፯፥፩)፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥን አብራርተው አስቀምጠዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በጽሑፋቸው ዘመኑን በአራቱ ወንጌላውያን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ የጌታን መጠመቅ፣መሰቀልን፣ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ ማውጣትን አራቱ ወንጌላውያን እያወሱ ዘመናትን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ፡፡ ወንጌላዊውን ወይም ዘመኑን ለማወቅ ዓመተ ፍዳ(ኩነኔ) አምስት ሺህ አምስት መቶ  እና ዓመተ ምሕረት (አሁን ያለንበትን ዓመት) በመደመር ውጤቱ ለአራቱ ወንጌላውያን ማለትም ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ በማካፈል የምናገኘው ነው፡፡ ይህም የአንዱ ወንጌላዊ ድርሻ ማለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቀሪው አንድ ከሆነ ዘመኑ ማቴዎስ፣ ሁለት ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣ ሦስት ከሆነ ዘመነ ሉቃስ ምንም ቀሪ ባይኖር ደግሞ ዘመነ ዮሐንስ ነው፡፡ ስሌቱም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ምሳሌ መነሻ አድርጎ ወንጌላዊውን ማን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

አዲስ ዓመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...?

የቅዱስ ዮሐንስ ተግባር በቕዱስ ዮሐንስ አወርቅ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ (ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ ፩-፫)፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡ በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኃጢኣት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን (ሰኮንድን) ሳይቀር እየሰፈሩ(እየቆጠሩ) ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡

ዕንቁጣጣሽ

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በሀገረ ኢትዮጵያ በወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት ዕንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ በመቀጠል የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ንግሥተ ሳባም ከንጉሡ ሰሎሞንም ተገናኝተው ቤተ መንግሥቱንም አስጎበውኝቶ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡

ንግሥቷ ጠቢቡ  ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሔደችበት ወቅት ፀንሳ ቀዳማዊ ምኒልክን በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ እልል እያሉ «አበባ ዕንቁ (አብረቅራቂ ድንጋይ) ጣጣሽ (ገጸ በረከት)» እያለ ገጸ በረከት ለንግሥቲቱ አበረከቱ፡፡ ያ የዘመን መለወጫ በዓልም ልጃገረዶች የአበባ ገጸ በረከት የሚያቀርቡበት ስለሆነ ዕንቁጣጣሽ ተባለ፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ»ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ የዘመን መለወጫ (ርእሰ ዐውደ ዓመት)
ዕንቁጣጣሽ ተብሎም እንደሚጠራ ታሪክ ያወሳናል፡፡  ስያሜውም ለበዓሉ የተሰጠው በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሳብ ዘመን እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የቅደስት ደንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን አሜን፡፡
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼       🌼       🌼      🌼
🌼        🌼      🌼      🌼
🌼🌼🌼         🌼🌼🌼

🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼                   🌼
🌼                   🌼
🌼🌼🌼          🌼
🌼      🌼         🌼
🌼🌼🌼          🌼

🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
    🌼               🌼
     🌼              🌼
                        🌼
                        🌼
                        🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼     🌼     🌼      🌼
🌼     🌼     🌼      🌼
🌼🌼 🌼     🌼🌼🌼
          🌼
        🌼
      🌼

🌼
🌼
🌼🌼
       🌼
         🌼🌼🌼🌼
      🌼             🌼
      🌼             🌼
      🌼             🌼
      🌼              🌼    
   
     🌼🌼🌼🌼
      🌼          🌼
         🌼🌼🌼
           🌼
              🌼
    🌼🌼🌼🌼🌼
    🌼                🌼
     🌼                🌼🌼🌼

            🌼
               🌼
   🌼🌼🌼🌼🌼 🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼

    🌼🌼🌼🌼
    🌼          🌼
    🌼          🌼
    🌼🌼 🌼 🌼🌼
                             🌼
                             🌼
                             🌼
                             🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼      🌼     🌼         🌼
🌼       🌼     🌼        🌼
🌼🌼 🌼      🌼🌼 🌼

          🌼 
          🌼🌼🌼
                      🌼
                      🌼
       🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
                      🌼
                      🌼
                      🌼
                      🌼

                #መልካም #በዓል!

      🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

❝በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።❞
  —መዝሙር 65: 11

የቸርነት አምላክ የረድኤት አምላክ የይቅርታ አምላክ የዘመናት ባለቤት ዘመን ለእሱ የማይነገርለት ዘመን ሳይኖር የነበረ ዘመን መቆጠር ከጀመረ በኋላም ያለ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ከአራቱ አዝማናት አንዱ በሆነው እናም በላም ከሚመሰለው ከዘመነ ሉቃስ በንስር ወደ ሚመሰለው ጌታ ይወደው ወደ ነበረው እና ከስምንት በላይ ስሞች ወደአሉት ወንጌሉን ሲጽፍ ከሥላሴ የጀመረ የክርስቶስን መከራውን ሲያስብ አንድ ቀን እንኳን ላልሳቀ ቁጽረ ገጽ አቡቀለምሲስ ታዖሎጎስ ለተባለ እንዲሁም ወንጌላዊ ወደ ሆነው በስሙ ወደ ተሰየመው ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ።

አመት ሲጨመርልን እድሜ ሲጨመርልን ለንስሐ ነውና አዲሱ አመት ንስሐ የምንገባበት ከሀጥያት የምንርቅበት ወደእግዚአብሔር የምንመለስበት ያድርግልን
👈ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላም ለሕዝቧም እረፍት ከጭንቀት ከመከራ እግዚአብሔር በዚህ በሚመጣው ዘመን ከንስር በሚበልጠው በአምላካዊ አይኑ ተመልክቶ ሰላሙን ያውርድልን አሜን


🌼🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼🌼

@ewuntegna
                       አዲስ ዓመት

አዲስ ዓመት
                                    አዲስ ዓመት

መልካም አዲስ ዓመት ይላል ሁሉም

ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ስልኬ በሚሴጅ ተወጥሯል ምንድንነው ብየ ከፍቼ ሳየው መልካም አዲስ ዓመት ይላል ሁሉም ። ዛሬ ምንድ ነው ቀኑ ስል ለካ መስከረም 1. 2017ነው።  2016 ማለፉነው በቃ ? እሱ ኑሮብን ነው እኛ ኑረንበት ነው ያለፈ?  አይይይ እ <<ተኖረና ተሞተ አለ አሉ አባ ገብረሐና>> ብዬ  እኔም ታድያ እሱ ሳይቀድመኝ ለምን  ጓደኛየን መልካም አዲስ ዓመት አልለውም ብዬ ወደጓደኛየ ደወልኩ እና እኔም እንደ ወጉ መልካም አዲስ ዓመት! አልኩት። እሱም ? ምኑ ነው አዲስ ዓመት ? አለኝ እኔም
ዛሬኮ መስከረም 1 የዘመን መለወጫ ነው አዲስ ዓመት ገብቷል የሚመጣው ዓመት አዲስ ነው እሱም 2017  ነው። 2016 አልፋል። ና ባክህ ፈታ እንበል አዳዲስ ልብሶችን ልበስ ዛሬማ ዘና ስንል ነው እምንውለው ?አቦ ፈጠን በል አልኩት ። ለካ እሱ ተናዷል ። እንኳን ዘና ዘነዘናም መሆን ትችላለክ ። አቦ ተወኝ ልተኛበት አለኝ። ምን ነክቶሃል አንተ ? ይህ ሰው በጤናው ነው ስል። እንደገና መለሰና ስማኝ! አለ።  እሽ አልኩት ።

ለእኔግን አዲስ ዓመት ምኑ ላይ እንደሆነ አልገባኝም
ምንም አዲስ ዓመት አይታየኝም ።
ያየኩት አዲስ ነገር የለም ።
ያው ነው የነበረው ነው ያለው ።
እሱም ሊቀጥል አስቧል
ሊቀጥልም እቅድ ይዟል ስለዚህ ምኑነው አዲስ ዓመት?
2016  ወደ 2017 መዛወሩ ከሆነ እሽ ልቀበልህ ግን
ስድስት ሰአትም ወደ ሰባት ሰአት ይዛወራል
መስከረም አንድ ስለሆነነው ካልከኝ ደግሞ ህዳር አንድም ጥር ወይም የካቲት አንድ ቀን ይሆናል? አለኝ ።
እኔም ግራ ገባኝና እሽ ይሁንልክ ግን አንተ አዲስ ዓመት የምትለው የትኛውን ነው እስኪ አስረዳኝ? ስል ጠየቁት። እሱም ተረጋጋና እንዲህ አለኝ
               እኔ ማውቀው አዲስ ዓመት
ባርነት ቀርቶ ነጻነት
ጦርነት ቀርቶ ሰላም
ልዩነት ቀርቶ አንድነት
የበላይነት ቀርቶ እኩልነት
                         ጥላቻ ቀርቶ ፍቅር ሲመጣ ነው እንጂ ነሐሴ አልፎ መስከረም (2016 አልፎ 2017)።መምጣቱ ለእኔ ፋይዳ የለውም ። የሰላም እና የፍቅር ዘመን ይህ ደግሞ አሁን ላይ የለም እንዳውም እኒህ ነገሮች ሁሉ በሚመጣው ዓመትም እንቀጥላለን ማንም አያስቀረንም ጊዜው የኛነው ብለው ሰሞኑን ሰላማዊ ሰልፍ ወጠዋል። ።መንግስትም እንዲደግፋቸውና በጀትም እንዲለቅላቸው በፓርቲያቸው በኩል ጠይቀዋል ።
ስለዚህ አዲሱ ዓመት ምኑላይ ነው ? በመካከል እኔ ሳቅ ስል  አንተ! እየሰማኸኝ ነው !አለ። አዎ አልኩት ። ቀጠለ ንግግሩን
የነበረው ከነበረ ያለው ካለ ያምናው ዘንድሮም ከኖረ ወደፊትም ከቀጠለ ምኑ ላይ ነው አዲሱ ዓመት ?

እኔ ማቀው አዲስ ዓመት በመጽሐፍም የተገለጸው ግን እንዲህ ይላል የጌታ ዓመት Isaiah 61 (አማ) - ኢሳይያስ
2: የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ የሚያለቅሱትን አጽናና ዘንድ ይላል አሁንግን እንኳን ሊያጽናናህ ቀርቶ ወደፊትም እንዳትጽናና  አድርጎ አስለቅሶህ ተስፋ ነስቶህ ይሄዳል አቁስሎህ ይሄዳል አድምቶህ ይሄዳል ያመንከው ይከዳሃል የያዝከውን ይቀማካል
የአሁኑግን የጌታ አመት አደለም በዚህ በጌታ ዓመትማ  ኦሪት አልፋ ወንጌል ፣ ብሉይ ኪዳን አልፎ ሐዲስ ኪዳን ተገልጧል ። ለድሆች ወንጌል ተሰብኳል
የታሰሩት ተፈተዋል የታወሩትም ማየት ችለዋል
የተጠቁትም ነጻነትን አጊንተዋል የተወደደችው የጌታ አመትም ትሰበካለች ሉቃ.፬፥፩፱  ።  ፍለጠው ቁረጠው በድንጋይ ወግረህ በእሳት አቃጥለህ ግደለው ማለት ቀርቶ ቀኝ ጉንጭህን ቢመታህ ግራህን ጨምርለት ። መጎናጸፊያህን ለወሰደው ቀሚስህን ጨምርለት የሚል ነው ። ያሁኑ ግን ምኑ ላይ  ነው አዲስ ዓመት ?
አሁንም ለእኔግን አዲስ ዓመት ማለት ቤተክርስቲያን ከስደት ስታርፍ ነው
ምእመናኑም በሰላም አስቀድሰው ጸበሉን ጠጥተው ከካህናቱ ተባርከው በሰላም ወጠው በሰላም ሲገቡ ነው
ሕዝቡም ሥራውን በሰላም ሠርቶ ወጥቶ ወርዶ ቤተሰቡን መግቦ አስራት በኲራቱን አውጥቶ ለነዳያን ምጽዋት መጽውቶ ለበዓል ከገዛው ነገር ሁሉ ለተራቡት መሄጃ ለሌላቸው በእየመስመሩ መጠጊያ አጥተው ሰው ሁነው ሰው ለጠላቸው ከውሻና ከድመት ጋር ተኝተው ለሚኖሩት በዓመት በዓል ቀን የሐብታም ጥብስ ሲሸታቸው ለሚውሉት አካፍሎ ሲሰጥ ነው ። ታላቁዋና ገናናዋ ሐገራችንም የሰላም ደሴት ስትሆን ነው አዲስ ዓመት ማለት። ዳሩ ምን ያደርጋል መልካም አዲስ ዓመት እያልን ቴክስት እንልካለን እንመኛለን እንጂ ይህንንም ሰው ምን ይለኛል ብለን ለምን በዐውደ ዓመት አልጠየቅከኝም ተብለን እንዳንወቀስ ሰው ፈርተን ነው ። በውስጣችን የተቀጣጠለ የሰው ፍቅር አንገብግቦን አደለም።

መልካም አዲስ ዓመት
መልካም አዲስ ሕይወት
መልካም አዲስ ሰብአዊነት እንዲመጣ አንጾምም አንጸልይም ይህን ካደረግን ግን ለዘለዓለም ስር ሰደን ቅርንጫፍ አውጥተን በሕይወትና በጤንነት በሰላምና በፍቅር እናብባለን ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ይላል Isaiah 27 (አማ) - ኢሳይያስ
6: በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።
እኛ ከአሮጌው ኃጢአት ወጠን በንስሐ አዲስ ሰው ከሆንን እንኳን ዓመቱ እለቱም አዲስ ነው ። እንኳን እለቱ ሰዓቱም አዲስ ነው እረ ደቂቃውም አዲስ ነው።
ሁሌም ፈጣሪ አዲስ ነገር ያሳየናል ።አዲስ ነገርም ያደርግልና ያውም ያልሰማነውን ያላየነውን ነው እሚያደርግልን። ቃሉም እንዲህ ይላል  Isaiah 43 (አማ) - ኢሳይያስ
19: እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለህ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ። ስለዚህ አዲስ አመት ከመመኘት በፊት መጾም መጸለይና አዲስ ሰው መሆንን መመኘት። አዲስ ሰው ሳንሆን አዲስ ዓመት ብንመኝ ግን የመጣው አዲስ ዓመት የቆየውና የከረመው  ሰቆቃና መከራ የበዛበት አሮጌው ዘመን ነው እሚሆነው ዓመቱን አዲስ የሚያደርገው የእኛ አዲስ መሆን ነው ።

እኛ አሮጌ ሰዎች ሆነን አዲስ ዓመት አናገኝም። ምክንያቱም Matthew 9 (አማ) - ማቴዎስ
17: በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ። ስለዚህ ሁለቱም ለመጠባበቅ አዲስ መሆን ያስፈልጋል
በአዲስ ዓመት አዲስ ሰው ሆነን አዲስ ሥራ ሰርተን በአዲስ ትንሣኤ ለመነሣት ያብቃን ? ብሎ ሲነግረኝ እኔ ፈዝዤ አዳምጠው ነበር ይህን ብሎ ከጨረሰ በኋላ ልተኛበት አትቀስቅሰኝ ብሎ ስልኩን ዘጋ ።
እኔም እውነቱን ነው ምን የታየ አዲስ ነገር አለ
ብዬ አሰብኩና እንደሱ ለሽ ።

አዲስ ዓመት ለማክበር ጠዋት የተነሣችሁ
ለእኔ ግን አዲስ ዓመት ሲመጣ ንገሩኝ ባካችሁ

ሁላችሁንም ፈጣሪ በቸርነቱ እንኳን አደረሳችሁ
                           
                                     Ermi✍️

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
  
@Ewuntegna  
@Ewuntegna
@Ewuntegna            
+ አንገት ተቆርሶ የተከበረ ልደት +

በመጽሐፍ ቅዱስ ልደት ያከበሩት የግብፁ ንጉሥ ፈርዖንና የይሁዳው ገዢ ሄሮድስ ናቸው:: እርግጥ ነው ልደትን ማክበር በአሕዛብ ነገሥታት ቢዘወተርም የሚነቀፍ ነገር አይደለም:: ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም የሚጀምረው የሰማይና የምድርን ልደት በሚተርከው "ኦሪት ዘልደት" ነው::
"እግዚአብሔር አምላክ፥ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ፥ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው" (ዘፍ. 2:4)

ትልቅዋ አፈር መሬት በሰባት ዓመት ማረፍዋን አይተን እኛም በሰባት ቀን እንደምናርፍ የምድርን ልደት መተረክ አይተን ልደታችንን ብናከብር ክፋት የለውም:: (Microcosm /ንዑስ ዓለም/ እንዲል ቴዎሎጂ) የመድኃኔዓለምን ልደት ከፍ አድርገን የብዙ ቅዱሳንን ልደት ደግሞ እንዲሁ በቤተ ክርስቲያን ማክበራችን ልደት አንዱ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ቀን ስለሆነ ነው:: ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንዳንዶቹ ደግሞ የልደቴ ቀን ብለው የሚያከብሩት ለዳግም ልደት ክርስትና የተነሡበትን ቀን ነው::

በዛሬው ዕለት ሔሮድስ ያከበረው ልደት ግን እጅግ የተረገመው ልደት ነበር:: ተጋባዦቹ የንጹሕን ሰው ደም የጠጡበት ልደት ሔሮድያዳ እንደ ታላቂቱ ባቢሎን "በሰማዕቱ ደም ሰክራ" የዋለችበት የልደት ግብዣ ቀን ነበር::

በዚህ ልደት የተቆረሰው ኬክ አይደለም:: በዚህ ልደት እፍ ተብሎ የጠፋው ሻማ አይደለም:: በሰይፍ ተቆርሶ በሰሃን የቀረበው ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚመስለው የሌለ ቅዱስ ሰው አንገት ነበር:: በሻማ ፈንታ የጠፋው ክርስቶስ "እርሱ የሚያበራ መብራት ነበር እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ" ብሎ የተናገረለት መብራት ቅዱስ ዮሐንስ ነበር:: እርግጥ ነው በልደት ሰበብ ብዙ ኃጢአት ይሠራል:: በሔሮድስ ልደት ግን የተሠራው ግፍ ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ ግፍ ነው::

ሔሮድስ የገደለው ማንን ነው? ነቢይን ነውን? እውነት እላችኁዋለሁ ከነቢይ የሚበልጠውን ነው:: ከሴት ከተወለዱት ሁሉ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም:: አንድን ሰው ብቻ የገደለ መስሎታል::
እርሱ የገደለው ዓሥር ሰው ነው:: ከነቢያት የመጨረሻውን ነቢይ ከሐዋርያት የመጀመሪያውን ሐዋርያ ገደለ:: ለብዙዎች የንስሓ ሰባኪያቸውን ለብዙዎች አጥማቂያቸውን ገደለ:: መለኮትን ያጠመቀውን ወደር ያልተገኘለትን አጥማቂ ገደለ::

አንገቱ ተቀልቶ ለሚያይ ወንጀለኛ ይመስለዋል እርሱ ግን ብቻውን በበረሓ የኖረ ባሕታዊ ነበረ:: ጮማ ያቆረጠ ጠጅ ባፉ ያልዞረ በልብስ ያላጌጠ ሰውነቱን በኃጢአት ያላሳደፈው መናኝ በዚያች በተረገመች የልደት ቀን አንገቱ በሰሐን ቀረበ::

የሐዲስ ኪዳኑ ናቡቴ ሕገ እግዚአብሔርን ርስት አድርጎ በኤልዛቤዋ ሔሮድያዳ ምክር በሔሮድስ ትእዛዝ ተገደለ:: የሐዲስ ኪዳኑ ኦርዮ የሔሮድስን አመንዝራነት ለመደበቅ በግፍ ተገደለ:: ዳዊት ኦርዮን ባስገደለ ጊዜ በእጅ አዙር አደረገው እንጂ በፊት ለፊት አላደረገውም:: በኁዋላም ዕድሜውን ሙሉ አልቅሶአል:: ሔሮድስ ግን ኀዘኑ የለበጣ ነበረ::

ቅዱስ ያሬድ “ቢበላው ይሻላል” ባለለት መሐላው አሳብቦ ታላቁን ነቢይ አንገቱን ቀላው:: ቅዱስ ኤፍሬም "አዳምን በጎኑ አጥንት በሔዋን ድል የነሣው ሰይጣን ሔሮድስን በጎኑ አጥንት በሔሮድያዳ ድል አደረገውና ቅዱሱን ዮሐንስ ገደለው" ይላል::

በቤተ መንግሥቱ መካከል የዮሐንስ  አንገት እንደ ምግብ በሳሕን ይዘሽ ለእናትሽ ያቀበልሽ አንቺ ሴት ምንኛ ብትረገሚ ይሆን:: በምድረ በዳ የጮኸ አፉን ክፉ ያላዩ ዓይኖቹን ምላጭ ያልነካው ጠጉሩን በሳሕን ላይ ይዘሽ ስትሔጂ ምን ተሰምቶሽ ይሆን?

መጥምቁን በመግደል ኃጢአትን መሸፈን አይቻልም:: ቅዱስ ኤፍሬም "የዮሐንስ ራስ የገዳዮቹን ኃጢአት አጉልቶ የሚያጋልጥ መብራት ነበረ:: ዮሐንስ በቃሉ ከተናገረው በላይ በሞቱ ኃጢአታቸውን ከፍ አድርጎ አሳየ" ይላል::

ክፋታቸውን ለመደበቅ እንደ ሔሮድስ ንጹሐንን የሚያስሩ : የልባቸውን ሠርተው በሞተ ጊዜ የውሸት  የኀዘን መግለጫ የሚሠጡ ሁሉ መጨረሻቸው ዕብደት ነው:: ከማንም በላይ የሟች ደም የሚጮኸው በገዳይ ሕሊና ውስጥ ነው::
ሔሮድስ ዮሐንስ ገድሎ ተረበሸ:: አይሁድ ጌታ ለመነሣቱ ብዙ ምስክር ቀርቦላቸው ያላመኑትን እርሱ ግን ያለ ማስረጃ "መጥምቁ ዮሐንስ ተነሥቶአል" ብሎ መዘላበድ ጀመረ::

ዮሐንስን በሰይፍ መቅላትና ስብከቱን ዝም ማስባል የሚቻል መስሎት ነበር:: ዮሐንስ ግን ሰማዕት ሲሆን በገዳዩ ሔሮድስ ልብ ውስጥ ስብከት ጀመረ:: እኛ ቆመን ስንለፈልፍ አንሰማም ዮሐንስ ግን ሞቶ ገዳዩን አስጨነቀ:: ነቢዩ ኤርምያስን ጉድጉዋድ የጣለው ንጉሥ ጳስኮርን :- ከእንግዲህ ስምህ ማጎርሚሳቢብ ነው ለራስህና ለወዳጆችህ ፍርሃት አደርግሃለሁ እንዳለው የመጥምቁ ገዳዮች ገድለን አረፍን ሲሉ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ፍርሃት ሆኑ:: ንጹሐንን መግደልና በሞታቸው መሳቅ ይቻላል:: የደማቸውን ድምፅ ግን ከራስ ከሕሊና ማጥፋት አይቻልም:: አሁንም እንላለን ከሟች በላይ ገዳይ ያሳዝናል::

          ( በ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ  )

@ewuntegna
@ewuntegna
እግዚአብሔርን የሚወድ እና በእግዚአብሔር የሚወደድ #መንፈሳዊ_ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ
ነው ። በምንም ሁኔታ ይሁን በምንም እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚሰራለት ይሰማዋል
በእርሱም ስራ ይደሰታል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ሥራውን ባናየውም እንኳ ይሠራል ።
ሥራውን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልናየው እንችላለን በዚህም እንደሰታለን ። ይህን ደስታችንም ማንም አይወስድብንም ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆችየሚደሰቱት በስጦታዎቹ ብቻ ሳይሆን በራሱ በጌታም ነው ።
እግዚአብሔርን የሚወድ እና በእግዚአብሔር የሚወደድ #መንፈሳዊ_ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ
ነው ። በምንም ሁኔታ ይሁን በምንም እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚሰራለት ይሰማዋል
በእርሱም ስራ ይደሰታል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ሥራውን ባናየውም እንኳ ይሠራል ።
ሥራውን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልናየው እንችላለን በዚህም እንደሰታለን ። ይህን ደስታችንም ማንም አይወስድብንም ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆችየሚደሰቱት በስጦታዎቹ ብቻ ሳይሆን በራሱ በጌታም ነው ።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
የኦርየንታል ኦርቶዶክስ እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የነገረ መለኮት ውይይት ከ34 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካይሮ መካሄድ ጀመረ  !
ጉባኤው “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14) በሚል መሪ ቃል በእምነት እና  እና በአገልግሎት እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂደዋል፤ ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ በግብጽ ቅዱስ ቢሾይ ገዳም “ሎጎስ” የስብሰባ ማዕከል መካሄድ የጀመረ ሲሆን በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት እና በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ይፋዊ የነገረ መለኮት ውይይት በዚህ ስብሰባ ተካሂዷል። ዓላማው ከ30 ዓመታት በላይ የተቋረጠውን ይፋዊ የሥነ-መለኮት ንግግር እንደገና ለመቀጠል እና እንደገና ለመገምገም መሆኑን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አስታውቃለች።

ጉባኤው የተከፈተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና በፓትርያርክ አቡነ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ መልእክት ነው።

በስብሰባው ላይ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያናት ቤተሰቦች ላይ የሚነሱ ልዩ ልዩ የአስተምህሮ ጉዳዮች ወደ አንድ ወጥ አቋም ለመድረስ በማለም በዚሁ ልክ ውይይት መደረጉ ነው የተገለጸው።

የምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት ልዑካንን ጨምሮ በጉባኤው  የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (አስተናጋጅ ቤተ ክርስቲያን)፣ የአንጾኪያ እና የመላው ምሥራቅ ፓትርያርክ (ሶርያ )፣ የአርመን ኦርቶዶክስ፣ የኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ የኤርትራ አቢያተ ክርስቲያናት መወከላቸውን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ገልጻለች ።
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ራስን ድል መንሳት 
የስጋ ምኞትንና ፍላጎትን አስመልክቶ ጾምና ድንግልናን ራስን ድል የመንሳት መንገዶች
ናቸው። ነፍስን አስመልክቶ የሚጠቀስም ሌላ መንገድ አለ።ራሱን የሚገዛና እርሱነቱን ወደ
ዓለማዊ ደስታ ከማዘንበል የሚያግድ ሰው ብጹዕ ነው።
ማንነት ልታይ ልታይ ሲል፡ ጉራውን ሊገልጥ ሊተብት ይችላል።በዚህ ሁሉ ግን ልንቃወመው
ይገባናል። ለእኛ #ከእግዚአብሔር ጋር መደሰትና መልካም የሆነው ነገር ለመጪው ህይወት
ብናቆይ የሚሻለን መሆኑን ራሳችንን ልናሳምነው ይገባናል፡፡ በዚህ ዓለም ድስታን ለማግኘት
በሚፈልጉ ሰዎች ላይ #የመድኋኒ_ዓለም ቃል ይመሰክርባቸዋል፡- " . . . እውነት
እላችኋለው፡- ዋጋቸውን ተቀብለዋል።"ማቴ6፡5፡፡
ስለዚህ በምድር ላይ ያሉ መብቶችህን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እግዚአብሔር እያንዳንዱ
ዕንባህን ከዓይኖችህ ላይ የሚጠርግበት በወድያኛው ዓለም ቢሆንልህ ይሻልሃልና።
ማንነትህ ወይም ስጋህ አሁን ላለህበት ዓለም ደስታ የሚያዘም ከሆነ በርትተህ ተከላከላቸው።
በራስህ ወይም በስጋህ ላይ የምይወስደው ይህ እርምጃ ጭካኔ አደለም፡ለእነርሱ ዘላለማዊ
ሕይወትን ማረጋገጫ እንጂ!
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚንከባከባት ያጠፋታል። ራሱን በጥብቅ ከመቆጣጠር ችላ የሚል
ሰው በእርሱ ላይ ኋይል እንዲኖረው ያደርጋል።ሰለሆነም ራሱን ለጽድቅ ከሚያለማምደውና
#የእግዚአብሔር መንገድ ከሚተገብረው ሰው በተለየ ሁኔታ በመንፈሳዊ ጠባዩ ላይ
እንዲያምጽ ያደርገዋል።
ራስን ድል መንሳት የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ከስጋ ደስታ ጋር እንደማይነጻጸር እርግጠኛ
ሁን። ከሁሉ በጣም የሚያስደንቀው የራስ ጉራ ሙሉ ለሙሉ መጥፋት በሚገባው በመንፈሳዊ
አገልግሎት ውስጥ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው።
#ቅድስነታቸው_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
(መንፈሳዊ ውግያዎች ከሚል መጽሓፋቸው የተወሰደ ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
2025/01/06 02:41:03
Back to Top
HTML Embed Code: