Telegram Web
ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ጥራልያን፣ ምዕ. 10

👉የማምነውና ተስፋ የማደርገው በምትሐት ወይም በማስመሰል ሳይሆን ስለ እኔ በእውነት ሰው በሆነውና በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

👉ሐሰት የሆነ ነገር ለእውነት አስጸያፊ ነውና፡፡ ስለሆነም የማምነው ድንግል ማርያም የፀነሰችውና የወለደችው እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደውን ሥግው ቃልን ነው፡፡

👉 የእግዚአብሔር ቃልም የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ በእውነት ከድንግል ማርያም ተወልዷል፡፡

👉ሰዎችን ሁሉ በማኅፀን የሚፈጥረውና የሚቀርጸው እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በድንግልና በማኀፀኗ ተፀንሶ ኖሯልና፡፡

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ኢየሱስ ክርስቶስ፡-

“ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ኃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

“ለሁሉ ያስባል፤ ሁሉንም ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡

“ከክንፍህ የጽድቅ ፀሐይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የጽድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ አሜን፡፡”

(ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
"መከራችሁ እንደማያልቅ በማሰብ ራሳችሁን አታስጨንቁ! እግዚአብሔር መጽናናትን ይልካል።"

[ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖ]


@Ewuntdgna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡

ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"

(ቅዱስ ኤፍሬም)
(ትንቢተ አሞጽ ምዕራፍ 5)
----------
13፤ ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።

14፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።

15፤ ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
ለእግዚአብሔር የምትገዛው ስለአራት ነገሮች ነው

1 ስለ ፈጠረህ ስለመገበህ ለጌትነቱ ለመገዛት ለቃሉ በመታዘዝ አምላካዊ ባሕርይን ለማስደሰት ነው።

2 በደሙ ገዝቶ በጥምቀት ወልዶ በቸርነቱ የሰጠህን ባባትነቱ የተከለህን ሰማያዊ ርስትህን እንዳትነቀል ለመገበር ነው።

3 ለእግዚአብሔር አልገዛም አልገብርም እያለ ለገዛ ባሕርዩ የሚገዛ ባሕርየሥጋን ከክፉ ምኞት እስኪመለስ በትሩፋት ለመቅጣት ነው።

4 ጌታችን ስለኛ ኃጢአት ስለተሰዋልን በሌላ ስጦታ የማይመለስ ትልቅ ወሮታ አለብንና ፍቅሩን ለመሻት በሱ ፍቅር ነደን የትሩፋት ሥራችንን ለመሰዋት ነውና ።

❤️❤️❤️❤️
(ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ)
[ፍኖተ አእምሮ]
ትንቢተ አሞጽ.3
4: እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤
Forwarded from የአባቶች ሃይማኖት (አደመ የአዳም ዘር)
ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ (፻፳፰፥፭)
(በዲ/ን ናትናኤል ግርማ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ  ደቀመዝሙር) ኅዳር 20ቀን 2017 ዓ.ም

እስራኤል ከግብፅ ከባርነት ከወጡ በኋላ ጸልየው እንዲድኑባት ሰውተው እንዲከብሩባት ታቦተ ጽዮንን ሰጥቶቸዋል:: በታቦተ ጽዮን እየተማፀኑ አርባ ዘመን ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ዐለት እየሰነጠቀ ውኃ ከጭንጫ እያፈለቀ በሰላም ተንከባክቦ መግቦ ምድረ ርስት አግብቷቸዋል። ከዚህም በኋላ መስፍን ሲሞት መስፍን ካህን ሲሞት ካህን እየተተካ ሥርዓቱ ሳይጓደል ከዔሊ ደረሰ። ዔሊም ክህነት ከምስፍና አስተባብሮ ይዞ ዐርባ ዘመን ካስተዳደረ በኋላ  አፍኒንና ፊንሐስ የሚባሉ ልጆቹን ከበታቹ ሾማቸው። ጌታን የሚያስቆጣ ሦስት ዐበይት ኀጣውእ ሠርተዋል:: ነህ ፱ ፥ ፳፩፣ የሐዋ ሥራ ፲፫ ፥ ፲፰

አባታቸው ዔሊ ይህን ሰምቶ ‹‹ደቂቅየ እኮ ሠናይ ዘእሰምዕ ብክሙ ለእመ አበስ ሰብእ ላዕለ ቢጹ አምኃበ እግዚአብሔር ይጼልዩ ሎቱ:: ልጆቼ ስለእናንተ የምሰማው ደግ አይደለም፣ ሰው ሰውን ቢበድለው በእግዚአብሔር ያስታርቁታል፤ ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል ግን በማን ያስታርቁታል? ተዉ አይሆንም አላቸው:: ዳሩ ግን ከጌታው ይልቅ ለልጆቹ አድልቶ ልሻራቸው ሳይል ቀረ። ፩ኛ ሳሙ ፪ ፥ ፳፭

ታቦተ ጽዮንን እያገለገለ የሚኖር ሳሙኤል በዚያች ሌሊት ተኝቶ ሳለ ጌታ ‹‹ሳሙኤል ሳሙኤል›› ብሎ ጠራው። ዔሊ የጠራው መስሎት ሄዶ ‹‹ነየ ገብርከ ዘጸውዐከኒ›› እነሆኝ  የጠራከኝ አለ፡፡ አልጠራሁህም ሔደህ ተኛ አለው፤ ኹለተኛ ጠራው፤ ከዔሊ ቀረበ ዒሊ ይህ ብላቴና ራእይ ተገልጾለት ይሆናል ብሎ እንግዲህ ወዲህ ቢጠራህ ተነሥተህ ታጥቀህ እጅ ነሥተህ ቁምና እነሆ ባርያህ እሰማለሁ ተናገር በል አለው። ሦስተኛ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ተነሥቶ ታጥቆ እጅ ነሥቶ ቆመና ባሪያህ እሰማለሁና ተናገር አለ፡፡ ልጆቹን ከመበደል አልከላከላቸውምና እንድፈርድበት የተናገሩኩትን በዔሊ እፈጽምበታለሁ ብሎ የእስራኤልን መመታት የታቦተ ጽዮንን መማረክ የአፍኒን ፊንሐስን የዔሊን ሞት ነገረው፡፡ ሲነጋ ዔሊ እግዚአብሔር የነገረህን አንዳችም ሳታስቀር ንገረኝ አለው፤ ነገረው። ዔሊም ‹‹ለይግበር እግዘአብሐር ዘአደሞ›› እርሱ እግዚአብሔር ነው የወደደውን ያድርግ አለ፡፡

ጌታ የማያደርገውን አይናገርም የተናገረውን አያስቀርምና እስራኤል በኢሎፍላውያን ዘምተው በአንድ ጊዜ አራት ሺህ ሰው አለቀባቸው። ይህ ነገር የሆነብን ታቦተ ጽዮንን ባለመያዛችን ነውና ታቦተ ጽዮንን ላክልን ብለው ወደ ዔሊ ላኩ። አፍኒን ፊንሐስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሄዱ። በእስራኤል ጦር ሰፈር ታላቅ ደስታ ተደረገ ዕልልታው ደመቀ:: ኢሎፍላውያን ድል ያደረግን እኛ ነን እነሱ ምን አግኝተው ነው የሚደሰቱት አሉ፤ በታቦተ ጽዮን ምክንያት መሆኑን ሲያውቁ በግብጻውያን የሆነውን ሰምተዋልና ወዮልን ወዮልን አሉ።

ኋላ ግን ተጽናንተው ገጠሙ። እስራኤል ተመቱ አፍኒን ፊንሐንስ ሞቱ ታቦተ ጽዮንም ተማረከች፤ አንድ ብንያማዊ ልብሱን ቀዶ አመድ ነስንሶ ወደ ከተማ ተመለሰ። የኀዘን ምልክት ነው፤ ከዚያም ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች፤ ካህናቱም እንደሞቱ፤ ሕዝቡም እንደተሸነፉና ብዙ ሕዝብ እንዳለቀ ለከተማው ሁሉ አወራ፤ ከተማዋ በልቅሶና በዋይታ ተናወጸች፣ በዚህ ጊዜ ዔሊ የዘጠና ዓመት ሽማግሌ ነበርና የሆነውን ሰምቶ ደንግጦ ከመንበሩ ወድቆ የጎድን አጥንቱ ታጥፎ ሆዱን ወግቶት ሞቷል። ፩ኛ ሳሙ ፬ ፥ ፱

ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን አዛጦን ወስደው በቤተ ጣዖታቸው ከዳጎን ጋር አስቀመጧት። በማግሥቱ ሊያጥኑት ቢገቡ ዳጎን በታቦተ ጽዮን ፊት በግምባሩ ወድቆ አገኙት፤ ከቦታው መልሰውት ሄዱ። በማግስቱ ሲመለሱ እጅ አግሩ ተቆራርጦ ደረቱ ለብቻው ቀርቶ አገኙት፣ ሰዎቹም በአባጭ ተመቱ። መቅሠፍቱ ቢጸናባቸው ወደ ጌት ወስዷት፤ የጌት ሰዎችም እንዲሁ በመቅሠፍት ተመቱ ወደ አስቀሎና ቢወስዷት ልታስፈጁን ነውና መልሱልን አሏቸው፡፡ ከሰባት ወር በኋላ ወደ ሀገሯ ትመለስ ብለው ቀንበር ባልተጫነባቸው በሚጠቡ ላሞች በሚሳብ አዲስ ጋሪ አድርገው የበደል መስዋእት እንዲሆን በአምስቱ ከተሞቻቸው አምሳል አምስት የወርቅ አይጦች አድርገው ሰደዷት። ላሞቹም ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሳይሉ ቤተ ሳሚስ ከኢያሱ እርሻ ደርሰው ቆመዋል። ታቦተ ጽዮንን ከሐውልተ ስምዕ አኑረው ሠረገላውን ፈልጠው ላሞቹን አርደው አወራርደው መስዋዕት አቀረቡ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ታቦተ ጽዮንን በድፍረት በማየታቸው ከመካከላቸው አምስት ሺህ ያህሉ ተቀሰፉ፤ ፈርተው ታቦተ ጽዮን መጥታለችና ውሰዱ ብለው መልእክተኛ ላኩ:: ወስደው በአሚናዳብ ቤት አድርገዋት ልጁ አልዓዛር ኻያ ዓመት አገልግሏታል። ፩ኛ ሳሙ ፯ ፥ ፪ እስራኤል ታቦት ጽዮንን ከጠላት ሲታደጉባት ከአባር ከቸነፈር ሲድኑባት ከእግዚአብሔር ጋር ሲታረቁባት በረከትና ረድኤት ሲቀበሉባት እስከ ሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ድረስ ኖረዋል። በሰሎሞን ዘመነ መንሥት እስራኤል ወደ ፊት ጠፍ እንደምትሆን እግዚአብሔር ስለሚያውቅ በእርሱ ቸርነት በሰሎሞን አስረካቢነት በቀዳማዊ ምኒልክ ተረካቢነት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ችላለች:: እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በአክሱም ትገኛለች። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ጽዮን የሚለው ቃል ለዐምስት ነገሮች ይቀጸላል! ጽዮን የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ፀወን አምባ መጠጊያ ጥላ ከለላ ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ቃል ለዐምስት ነገሮች መጠሪያ ሆኗል። እነዚህም፦

፩. ሙሴ በደብረ ሲና ከእግዚአብሔር የተቀበለው ጽላተ ሕግ፤ ጽላተ ሙሴ ወይም ታቦት  ጽዮን ትባላለች። ፩ኛ ሳሙ ፪ ፥ ፲፱  
፪. የአብርሃም ርስት የኾነችው ኢየሩሳሌም ጽዮን ትባላለች! ፪ኛ ሳሙ ፭ ፥ ፮

፫. ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጽዮን ቅድስት ትባላለች፤ ‹‹ነያ ሠናይት ሰላማዊት ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አፍላገ ሕይወት በየማና ወበጸጋማ አዕፁቀ ዘይት ኵለንታሃ ወርቅ ወያክንት ሀገሮሙ ለሰማዕት᎓᎓›› የሰማዕታት ሀገራቸው ሁለንተናዋ በወርቅና በዕንቍ የተሸለመች በቀኟ   የሕይወት ወንዞችን በግራዋ የዘይት ልምላሜዎችን የያዘች ሰላማዊት አምባ መጠጊያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እነሆ ያማረች የተወደደች ናት።› ብሏል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ።

፬. መንግሥተ ሰማያት ደብረ ጽዮን ትባላለች አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው መንግሥተ ሰማያት ደብረ ጽዮን ተብለ እንደምትጠራ ‹‹ኦ አንትሙ ሕዝበ ክርስቲያን እለ ተጋባእክሙ በዛቲ ዕለት ከማሁ ያስተጋባእክሙ በደብረ ጽዮን ቅድስት ወበኢየሩሳሌም አግዐዚት በሰማያት᎓᎓›› የክርስቲያን ወገኖች በዚች ዕለት እንደተሰበሰባችሁ፤ ነጻ በምታወጣ በደብረ ጽዮን በመንግሥተ ሰማያት ይሰብስባችሁ በማለት ይመሰክራል።

፭ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም፤ ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ‹‹አብርሂ ጽዮን ዕንቁ ዘጳዝዮን ዘአጥረየኪ ሰሎሞን። ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ የዓውዳ ስብሐት።›› ሰሎሞን ጳዝዮን በሚባል ዕንቊ የተወዳጀሽ ጽዮን ሆይ አብሪ፣ ዕዝራም ምስጋና የሚከባት የክርስቲያን ማደሪያ የሆነች ቅድስት ጽዮንን በሴት አርአያ አያት። በማለት ሰሎሞንና ዕዝራ በአንድ መንፈስ ሆነው ስለ እመቤታችን ተቀኝተዋል።  ጽዮን የሚለውን ቃል ከእመቤታችን ጋር ያለውን ተዛምዶ በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡ የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የኾነችው በወርቅ የተለበጠችው ይቺ የእግዚአብሔር ታቦት፣ በንጽሕና በቅድስና የተጌጠችው የእግዚአብሔር ወልድ እናት የኾነችው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡
Forwarded from የአባቶች ሃይማኖት (አደመ የአዳም ዘር)
ኢትዮጵያዊው ሊቅ በሰቈቃወ ድንግል መጽሐፋቸው ላይ የአምላክ ማደሪያ የኾነችው ታቦት ወደ ፍልስጥኤም ሀገር ሄዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ኹሉ፣ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ መውደቃቸውን ያስረዳል፡፡

ይህን አባ አርከ ሥሉስ የተባሉ ሊቅ ሲያስረዱ እንዲል ብለዋል፤
ታቦተ አምላክ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኀን ማኅጎሊ
አመ ነገደት ቍስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ
ወተንፍሩ ኵሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ

‹‹ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የኼደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታቦተ ጽዮንን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው በዚች ታቦት የተመሰለች ድንግል ማርያምም ኹሉን ማድረግ ከሚችል ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል አገር በኼደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የኾኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ኹሉ ዐፈሩ።›› በማለት አነጻጽራል። ይኸም ለጊዜው ቢደረግም ለኋላው ግን ምሳሌ ነበር፡፡ ላሞቹ የሰማዕታት፤ ልጆች የልጆቻችው፤ ሠረገላ የመስቀል፤ ልጆቻቸውን ከወደ ኋላ እንዳስተሩ፤ ስማዕታትም የልጅ የገንዘብ ፍቅር አያስቀራቸውምና፤ ሠረገላውን ፈልጠው እንደ ሠዋቸው ራሳቸውን በመስቀል ይሠዋሉና በማለት የብሉይ ኪዳን መተርጕማን ያመሰጥሩታል፡፡

የመልክአ ማርያም ደራሲ ታላቁ ንጉሥ ቃላት የተጻፉባቸው ጽላት የተቀመጡባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ጊደሮቹ ከልጆቻቸው ይልቅ በማስበለጥና በመውደድ ይዘዋት ወደፊት እንደነጎዱ፤ እርሱም የልዑል ማደሪያ ለኾነችው ለድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር በድርስቱ ሲገልጥ እንዲህ አለ
ማርያም ጽዮን ታቦት ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ
ዕጐላት እምዕጕሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ
‹‹የሃያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ማደሪያ ጽዮን ማርያም ሆይ፤ ጊደሮች ከጥጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደእፈቀሩ፤ እኔም ወድጄሻለሁና ከዛሬ ጀምሮ ፈጽሞ ውደጅኝ›› በማለት ገልጦታል፡፡

የሃያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ሲል ዐሥሩን ቃላት መናገሩ ነው፡፡ ያቺ ታቦተ ጸዮን የማይታይ ረቂቅ ቃል በጽሑፍ እንደገዘፈባት በአማናዊት ጽዮን በእመቤታችን ረቂቅ መለኮት አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ገዝፎባታልና፣ ያቺ የዐሥሩ ቃላት ማደሪያ እንደሆነች እመቤታችንም የዐሥሩ ቃላት ባለቤት የኢየሱስ ክርስቶስ ማደሪያ ናትና፣ በዚያች አምልኮት እንደጸና በእመቤታችንም አምልኮተ እግዚአብሔር ጸንቷልና፣ ያቺ አራት ማዕዘን እንደሆነች እመቤታችንም ቃል ኪዳንዋ በአራቱ ማዕዘን ይደርሳልና፤ አንድም በአራቱ ማዕዘን ያሉ ክርስቲያኖች ሰአሊ ለነ ቅድስት እያሉ ይማፀኗታልና፡፡ ያቺ መማሪያ ፊደል የረቂቅ ቃል መገለጫ እንደሆች እመቤታችንም የአካላዊ ቃል መገለጫ የኀጥኣን መማሪያ ፊደል ናትና።

አባ ጊዮርጊስ ‹‹ትመስሊ ፊደለ ወትወልዲ ወንጌለ ወታገምሪ መስቀለ፡፡›› ፊደልን ትመስያለሽ፤ ወንገልን ተወልጃለሽ መስቀልን ትወስኛለሽ ሲል ይነግረናል፡፡
ዳግመኛም ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በምሥጢር ሲራቀቅ ‹‹አንቲ ውእቱ  ጽዮን ታቦተ አምላከ እስራኤል እንተ ነገደት ምድረ ኢሎፍሊ ወበህየ አውደቀቶ ለዳጎን፡፡›› ወደ አሎፍሊ ምድር የሄደች የእስራኤል አምላክ ማደሪያ ጽዮን አንቺ ነሽ፤ በዚያም ዳጎንን የጣለችው ጣዖት አምላኪዎቹንም የቀሠፈቻቸው በአመጣጧም ከአዛጦን ሰዎች ካሳን የተቀበለች: ከካሳዋም ጋር እንቦሳ ባላቸው ላሞች አስጭነው የሸኟት ከርሷም ጋር የወርቅ ሳጥኖችን በጐኗም የበድን ሣጥን ሥርዐትን አልሠሩም፣ ነገር ግን በእርሷ ዘንድ ካለ ከወርቅ መሣሪያና ከሣጥን ጋራ ላኳት፤ በእንግድነቷ ወቅትም በአሳደራት ጊዜ ወደ ቤቱ በመግባቷ እግዚአብሔር የአብዱራን ቤት ባረከ በማለት የምሳሌዋን እሙንነት በሰፊው ገልጧል፡

ይኽቺም የእግዚአብሔር ታቦት በቤተ ዐሚናዳብ ኻያ ዓመት ተቀምጣለች፤ ከዚያም የሳኦል ዘመን አልፎ የእግዚአብሔር ወዳጅ ዳዊት በነገሠ ጊዜ በአዲስ ሠረገላ አድርገው ከቤተ ዐሚናዳብ አውጥተው በበገና፣ በመሰንቆ፤ በከበሮ፤ በነጋሪት በጸናጽል እግዚአብሔርን እያመሰገነ ይዘዋት ሲመጡ የእግዚአብሔርን ታቦት ዖዛ በድፍረት በመያዙ እግዚአብሔር ቀሥፎት ወዲያውኑ በታቦቷ አጠገብ ሕይወቱ አልፏል፤ ያን ጊዜ ነቢዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ያደረገችውን ተአምራት ተመልክቶ፤ እግዚአብሔር በእርሷ እንዳደረ በማመን የፍርሃት ተውጦ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?› በማለት ለታቦቷ ያለው ክብር ገልጧል፡፡ ፪ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፱

በዘመነ ሐዲስም በተመሳሳይ መልኩ ጌታን በማኅፀኗ የተሸከመች የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ አማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ ኤልሳቤጥ ልክ እንደ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ መልቶባት፤ የጌታ ታቦት (ማደሪያው) መሆኗን ተረድታ፤ ድምፅዋን አሰምታ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል?›› በማለት ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላትን ታላቅ አክብሮት እንደ ዳዊት ገልጣለች። ሉቃ ፩ ፥ ፵፫ ከዚያም ዳዊት ይኽነን ታላቅ ቃል ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት በአቢዳራ ቤት ለሦስት ወር ያኽል እንደተቀመጠች ፪ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፲፩ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክ ማደሪያ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በካህኑ በዘካርያስ ቤት ለሦስት ወር ተቀምጣለች። ሉቃ ፩ ፥ ፶፮ ዖዛ ተቀሥፎ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቢዳራ ቤት ገብታ ቤቱ ለሦስት ወር በበረከት እንደተመላ ኹሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ ዘካርያስም የመልአኩን ቃል ባለመቀበሉ ከተረገመ በኋላ እውነተኛዪቱ የአምላክ ታቦት ድንግል ማርያም በቤቱ ለሦስት ወር ያህል ተቀምጣ ቤቱን ባርካለታለች፡፡ ሉቃ ፩ ፥ ፳

እግዚአብሔር በታቦቷ ምክንያት የአቢዳራን ቤት እንደባረከ ኹሉ የዘካርያስንም ቤት በእመቤታችን ምክንያት የባረከው መኾኑን ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሲገልጥ ‹‹ድንግል በምሥጢር የተመላ ታቦትን ኾና ትኖራለች፣ የካህናት ወገኖችም ደስ ይላቸዋል፣ ያከብሯታልም›› በማለት ታቦትነቷን አጕልቶ አስተምሯል፡፡

በተጨማሪም የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተ አቢዳራ ወደ ዳዊት ከተማ ስትገባ፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከደስታው ብዛት የተነሣ የጌታ የክብሩ መገለጫ በኾነችው በታቦቷ ፊት እየዘለለ እንዳመሰገነ ኹሉ ፪ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፲፪  አካላዊ ቃልን በማኅፀኗ የተሸከመች የአምላክ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ታላቁ ነቢይ መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማኅፀን ኾኖ ከደስታው ብዛት የተነሣ እየዘለለ አመስግኗል። ሉቃ ፩ይኽነን ምሥጢር ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሲያብራራ ‹‹ንጉሡ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ይዘል ነበር፤ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለንጉሣውያኑ ደንብ አልታዘዘም፤ እንዲኹ ዮሐንስ ደግሞ ገና ፅንስ ሣለ ከደስታው የተነሣ ከዳዊትም በላቀ ኹኔታ ዘለለ፣ ፅንስ ቢኾንም የእርሱ ባልኾነው በዚኽ ዕድሜ አልተገታም፣ ድንግል እና ቡርክት የኾነችው እናት የእግዚአብሔር ቤት ምስጢራት ከመሉባት ታቦትም በላይ ውብ ነበረች፤ ዳዊትም በአክብሮት በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ ይኽም ዮሐንስ በማርያም ፊት ሊዘል እንዳለ አስቀድሞ ያሳይ ነበርና፤ ከዳዊት በቀር ንጉሥ መዝለሉ ተሰምቶ አይታወቅም፤ ሕፃን መዝለሉም እንዲኹ ነቢያት ካህናት የእግዚአብሔርን ልጅ መንገድ አስቀድመው አመለከቱ፤ እርሱም በመጣ ጊዜ ይሹት የነበሩትን ምልክቶች ፈጸማቸው፤ የጌታውን የንጉሡን ምልክት ይጠቁም ዘንድ፤ ዳዊት
Forwarded from የአባቶች ሃይማኖት (አደመ የአዳም ዘር)
በደስታ በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ ዮሐንስ በማርያም ፊት የሚያደርገውን ነገር ምሳሌ በመኾን አሳየ፤ ያቺም ብላቴና እንዲኹ የእግዚአብሔር ታቦት ነበረችና የምሥጢራት ጌታ በርሷ ዐደረ፤ ከዚኽም የተነሣ ልክ እንደዚያ ጀግና ንጉሥ ሕፃኑ በርሷ ፊት በደስታ ዘለለ፣ እርሷ በቅዱስ ቃል እንደተመላ ታቦት የተሸከሟት ነበረች፤ የትንቢት ምስጢራት ፍቺ በርሷ ዐደረ›› በማለት ይኽ ምሁር ቅድስት ድንግል ማርያ በምሥጢር የተመላች የአምላክ ታቦት መኾኗን በማብራራት ገልጦታል፡፡

ዳግመኛም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በደስታ ሲያመሰግን አይታ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብትንቀው እግዚአብሔር ተቈጥቷት በሕይወቷ ዘመን ኹሉ የልጅ ጸጋ እንዳታገኝ በመካንነት ቀጥቷታል፡፡ ፪ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፳ ይኸውም ማደሪያው የኾነች ታቦቷን በድፍረት ሊነካት የሞከረውን ዖዛን የቀሠፈ፤ ዳግመኛ የጌትነቱ መገለጫ በኾነች በታቦቷ ፊት ያመሰገነ ዳዊትን የናቀች ሜልኮልን በምክነት የቀጣ አምላክ፤ ዛሬም ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን፤ የድንግልና ጡቶቿን የመገበችውን፤ _ በጀርባዋ ያዘለችውና በደረቷ የታቀፈችውን ቅድስት እናቱን በድፍረት የሚነቅፉ፤ ሔዋንን ያሳተ እባብ መርዝ ክሕደቱን በአፋቸው የረጨባቸው በልቡናቸው ያሳደረባቸው፤ ነቢያት ሐዋርያት ያስተማሩትን የሚያጣምሙ ጸረ ማርያሞች ለዚኽ ድፍረታቸው ንስሓ ካልገቡ የዘለዓለም ቅጣትና፤ በዚኽ ዓለምም ከድንግል ማርያም አማላጅነት የሚገኘውን ታላቅ በረከት በማጣት እንደ ሜልኮል የበረከትና የጸጋ ምክነት ያጋጥማቸዋል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ ፻፳፰ ፥ ፭ ላይ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም›› በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቃወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው።

ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግል ሲያስጠነቅቁ፡-
እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቍርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ‹‹አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለሁ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን›› በማለት ገልጿል፡፡

ከእመቤታችን ረድዔት በረከት ይክፈለን አማላጅነቷ አይለየን 🙏

@yeabewu
@yeabewu
@yeabewu
በቤትህ እኖር ዘንድ እኔን ከጥፋት ጠብቀኝ!!

''ጌታ ሆይ ይቅርታ በዚያ አለና ከደጅህ አልራቅ። ፍቅርህና ቸርነትህም የሚገኝበት መጠጊያ የሚሆነኝን ቤትህን አልተው። ከቆሰልኩበት የኃጢአት ቁስል ድህነትን ሳላገኝ የስንፍና በሽታ ደምፁን አጥፍቶ እንዳያጠቃኝ። ኤሳው ብኩርናውን እንዳጣ በፍላጎቴ ቤትህን እንዳልተው የችለተኝነት ፍሬ የሚያፈራ ሥራ በውስጤ አይግባ።"

    [ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
#ማርያም_ሆይ

#እኔ ገደሉን ለማለፍ ወደ ብርሃን
ሥፍራ ለመድረስ የቸኮልሁ ነኝ ፡፡
#አንቺ የመድኃኒት ድልድይ ነሽ ፡፡
#ልጅሽም ለተገፉት መጠጊያ የተድላ ደስታ ሥፍራ ነው ፡፡

የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት
#እኔ ነጋዴ ነኝ ፡፡
#አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ ፡፡
#ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው ፡፡

#እኔ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የምፈልግ ደሃ ነኝ ፡፡
#አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ ፡፡ #ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው ፡፡

#እኔ የታረዝሁ የብርሃን ልብስ የምሻ ነኝ ፡፡
#አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ ፡፡
#ልጅሽም የማያልቅ የማያረጅ የሃይማኖት ልብስ ነው ፡፡

#እኔ ቁስለኛ ነኝ #አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ ፡፡ #ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡

#የፍቅሯ_ኃይል ያረፈበት የስም አጠራሯ ከአንደበቱ የማይለየው #አባ_ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

        
#_ሰናይ_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@ewuntegna
@ewuntegna
2025/01/01 02:43:25
Back to Top
HTML Embed Code: