Telegram Web
እንኳን አደረሳችሁ የሚካኤል ወዳጆች

@ewuntegna
Audio
+ ማር ሚካኤል + " አዲስ ዝማሬ "

ማር ሚካኤል ልበል ማር ሚካኤል ልበልህ (2)
ባርከህ አሳደከኝ በቅኔ በዜማ
መዝሙር አልሰስትም አባቴ ለአንተማ


ጀርባዬ ታናሽ ያልበቃሁ ብሆን
እንድፀና አውቃለሁ ከፊቴ ስትቀድም
ፍጻሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ
አበረታኝ ልበርታ አፅናኝ ልፅና ልጅህ

ባሕሩን ክፈለው በደረቅ እንዳልፈው
እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በጅህ ያዘው

ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደውል
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል
በሄድኩበት ሁሉ ከአፌ አትነጠል
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም

ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለ አፌ
ውልድህ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ

በሞቱ ቀጠሮ ሰርግ የደገስክለት
ምን አለ ባህራን ስታተርፈው ከሞት
ዛሬም ታምርህን ትድግናህን አይተው
ብዙዎች ይሉሀል ሚካኤል ሙት አንሳው

ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ
ከክፋ ከልለህ በድል አሳላፈ

አለቱን ከፍለህው በበትረ መስቀልህ
ከጭንጫው ሰጠህኝ ማርና ፀበል
ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው
ያኔ የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው

የብርሃኑን አምድ ፍና ተከትለን
ከቅዱሳን ስፍራ ሚካኤል ደረሰን


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

@ewuntegna
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ  / ዘጸ 20 /

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ትዕዛዝ በሚያነቡበት ወይም በሚሰሙበት ጊዜ "ይህ ከእኔ ጋር ምን ግንኙነት አለው ? ይህ ሊነገር የሚገባው ለከሐድያንና ለመናፍቃን ወይም ከሥጋዊ ዕውቀታቸው የተነሳ አለበለዚያም ከፍልስፍና በመነጨ ሁኔታ ከሃይማኖት ያፈነገጡትን ነው ። እኔ ግን በሳምንት ይህን ያህል ቀን እጾማለሁ አሥራት አወጣለሁ  በየሰዓቱ እጸልያለሁ ከልብ ሆኜ እዘምራለሁ  ፤ የቤተ ክርስቲያን መርሃ ግብሮችን  ያለማቋረጥ እከታተላለሁ ስለሆነም ይህ ትእዛዝ አይመለከተኝም " ይሉ ይሆናል ።

ነገር ግን ይህ ትእዛዝ ሁሉንም የሚመለከት ነው ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ " ተብሎ መነገሩ በሰው ልጅ እጅ የተጠረቡትንና የለዘቡትን ሰው ያቆማቸውንና በባሕር ወይም በፀሐይ ወይም በእሳት ወዘተ  የተመሰሉትንና በተለያዩ ስያሜዎች የሚታወቁትን ጣኦታትን ብቻ ማለት አይደለም ።
በዚህ አንጻር ሰዎች ሀይላቸውን ያመልካሉ ፤ ገንዘባቸውን፤ ውበታቸውን  ፤ ዝናቸውን ወዘተ  ያመልካሉ ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች በየፊናቸው የየራሳቸው ጣዖታትና አማልክት አሏቸው ማለት ነው ። እንደዚህም ሆነው እየኖሩ ደግሞ እነዚህ ሁሉ " በእውነት እግዚአብሔርን እናመልካለን በእርሱም እናምናለን ።" ሲሉ ይደመጣሉ ። በእነርሱ ዘንድ  ግን እውነትም ሃይማኖትም ፈጽሞ የለም ። 

[ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ]
የሞቱት ሞቱ

👉 የሚሞቱትም እየሞቱ ነው

👉 የሞቱትን መግደል

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ምድር እየተስፋፋ የመጣ ነገር ቢኖር ምእመናንን አባት አልባ ማስቀረት ነው። ሁሉንም ምእመን መበተን ማጥፋት ስለማይቻል፦ እረኛውን ምታ መንጎቹ ይበተናሉ ነው ነገሩ።ዋናው አላማም ምእመናን የሚጸልይላቸው የሚጮህላቸው እኔ አለሁላችሁ የሚል አባት እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው። ይህም በሰፊው በሁለት መንገድ እየተሠራበት ያለ ኦርቶዶክስን የማጥፋት ትልቁ ፕሮጀክት ነው።

በሩቁ በሐሩሩ ፣በበረሃው፣ በገዳሙ ጤዛ ልሰው ፣ድንጋይ ተንተርሰው ፣ይህን አለም ንቀው በመኖራቸው ብቻ ተጠሉ። ስለዚህም ምክንያት በሌለው ምክንያት ተገደሉ። የሞቱ ግን እነርሱ ሳይሆኑ እኛው ነን። ተዋረድን ትላንትም ዛሬም ቁመን አባቶቻችንን ስናሳርድ ቀረን። እስኪ በሌሎች ቤተ እምነቶች እዩ እንኳን ትልቅ ያውም ከአስራአምስት በላይ ተገድሎ ይቅርና አንድ ተራ አማኛቸው እንኳ ተነክቶ እንዴት እንደሚሆኑ?

ስንት ወንበዴ በሐገሪቶ ሞልቶ አላስወጣ አላስገባ ብሎ ሳል መነኮሳት ይገደሉ? መነኮሳትኮ ሚኖሩ ከሰው እርቀው በበረሃ ነው። ሰው አላስቸገሩ መንግስት ላይ አላመጹ ተቃውሞ አላስነሱ።ቢፈተሹም በእጃቸው መስቀል እንጂ ሰይፍ የለም።በማገቻቸውም ጠመንጃ የለም ዳዊት ነው ያለ።ቢጠየቁም መልሳቸው እኛ የእከሌ ደጋፊ ነን የእከሌ ዘር ነን አይሉም። ይልቁንምመልሳቸው እንዲህ ነው ፦

የማን ደጋፊ ናችሁ ሲባሉ" ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?"(የማቴዎስ ወንጌል 16:26) በማለት ሲመልሱ፦ ከማን ዘር ናችሁ ሲባሉ ደግሞ ከመልካሙ ዘር ይላሉ። መልካሙ ዘር ማነው ሲባሉ ደግሞ " መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤"
(የማቴዎስ ወንጌል 13:38) ይላሉ። የመንግስት ልጆች እነማን ናቸው ሲባሉ ደግሞ፦ ከማይጠፋው ዘር የተወለዱት ናቸው ይላሉ ።እንደ ሕያው ቃሉ ፦1ኛ,ጴጥሮስ1፥23: ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

እና ለምን ወደዚህ መጣችሁ ሲባሉ ጌታ እንዲህ ብሎናል ፦" ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 19:29) ይህ ነበር መልሳቸው። ዳሩ ምን ያደርጋል ዘር የሌላቸው መልካም ዘሮች ታጨዱ።

እና እንደዚህ በማለት የሚናገሩትን እንደነዚህ ያሉትን አባቶች ማፈን፣ ማሳፈን፣ መግደል እና በተከታታይ መልኩ በጦርነት ሰበብ መጨፍጨፍ ሲሆን፦ በከተማ ያሉትን ደግሞ ስማቸውን ማጥፋት በፖለቲካ በዘር ምክንያት ማሰቃየት በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራቸውም የጥላቻ ስም በመደረብ ማሳደድ ነው።

ይህም የተፈለገው አንደኛ ኦርቶዶክስን ማጥፋት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሐገሪቱን ለ........አሳልፎ ለመስጠት የታቀደ እቅድ ስለሆነ ነው።ሀገሪቱ እንድጠፋ ደግሞ መጀመርያ ኦርቶዶክስ እስከ አባቶች መጥፋት አለባት ነው ነገሩ። ለዚህ ነው በተደጋጋሚ ምክንያት ገዳማውያኑ መነኮሳት አባቶች ሚገደሉት። ታፍነው ሚወሰዱት። በእየገዳማቱ የሚረሸኑት። ገዳማት ሚዘረፉት ሚቃጠሉት። በከተማ ያሉትም በብሔር ምክንያት ከስራ ሚፈናቀሉት፣ ስማቸውም በእየ አደባባዩ በእየ ሚድያው ሲተች ሚውለው። በቃ አባቶች ካለቁ ልጆች አይቆዩም ነው። ሁሌም በአንዱ ችግር አዝነን ኀዘናችንን እንኳ የመጨረስ እድል የለንም። ሳንጨርስም ሌላ አጀንዳ ይሰጠናል። በኀዘን ላይ ኀዘን እረ ያማል ጎበዝ?

ሰሞኑን አንድ አባት ታፍነው ተወሰዱ፡ ታሰሩ ተባለ። ምንድን ነው ጉዳዩ ብለን አጣርተን ሳንጨርስ እንኳን ማሰር፦ መግደል ማጥፋት መብቴነው በሚመስል መልኩ በዝቋላ ከ15 በላይ መነኮሳት እና በቦታው የሚገኙ አገልጋዮች ተገደሉ ታፍነውም ተወሰዱ ተባለ። አሁን ምን ይባላል ስለማን፣ ይጮሃል ለማን ይጮሃል፣ ወደማንስ ይጮሃል? እሁሁሁሁሁሁሁሁሁሁሁ ኧረ....
ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል አዶናይ ?
አሉ የምንላቸው አባቶችም፦ እንኳን ችግሩን በዘላቂ መልኩ ሊፈቱት ቀርቶ፡ በምእመናኑ ላይ በእየጊዜ ችግር ከመፍጠር አላረፉም። እንደ ፖለቲከኛ ችግር እየፈጠሩ ችግር ሆኑ እንጂ።

ሁሉም ቢሆን ነገሩን በሚድያ ከማራገብ በቀር ያመጣው ለውጥ የለም። ሚድያ ላይ ከሆነ ከዚህ በፊትም ተንጫጭተን አይተነዋል። ሞቱ አሉ፡ ተገደሉ አሉ፡ ታፈኑ አሉ !ተጨፈጨፉ አሉ? አንዳንዱማ ሲኖዶሱ ምን አለ! ምን መግለጫ ሰጠ ነው የሚል። ሲኖዶስኮ አንተ ምእመኑ ነህ። እኔም ነኝ እንዳንተ ከአንተ ጋር።
ሚዛን ማይደፋ ጫጫታ። ሁሉም ያው ነው ሲኖዶሱም መግለጫ ከመስጠት ያለፈ የሚያደርገው ዘላቂ ነገር ስሌለው ወይ አንድላይ እንሙት ወይ ታጥቀን እንመክት ከዛ ውጪ ማሕበራዊ ሚድያ ላይ ብንጫጫ በአንድ ሞቀጫ ነን ብሮ ይሰማሃል?
ቤተክርስቲያን ማለት አሁን ላይ አንዱ ስድስት መቶ ብር ደሞዝ ሲበላ
ሁለተኛው ስድስት መቶ ሺህ ብር ደሞዝ ሚበላባት ሆናለች።
ከዛ ውጪ እንደበግ ኑሪ ተብዬ እያልህ አታላዝን
መቶ ሃምሳ ጥቅስ አትደርድር
ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት እንደ አጼ ካሌብ




የሞቱት ሞቱ
መናንያን

የሚሞቱት እየሞቱ
ምእመናን

🕊 🕊
#እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤

ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።

(ትንቢተ ኤርምያስ 9; 23-24)
ወዳጄ

ማንም ሞትህን አይመቀኝም
ብቻ አንተ ሙት እንጂ ሁሉም ይወድሃል

ሞተህ ማንም አያማህም ፡ አይተችህምም : አይወቅስህም

ሙት መውቀስ ድንጋይ መንከስ ይባልላሀል
ከሞትህ እንደገና አያዩህምና

ፎቶህን በትልቁ አሰርተው
ለኔ ትልቅ ሰው ነበረ እያሉ ያዜሙልሀል

ከዚህ በኋላ መጥተህ ቁመት አትለካካቸውምና
ወደ ታች ይቀብሩሃል
ሽቷቸውን አትጋፋምና አፈር ይበትኑብሃል
አንተን ደስ አይልህምና ኮርማ የሚያህል አበባ ያመጡልሃል
እንዳትወጣ ሰግነው በሲሚንቶ ይደፍኑብሃል

ግማሽ ቀን ብቻ ነው እርስ የምትሆነው
ከዚያም ለዘላለም ይረሱሃል

ስምህን ሲያጠልሹህ ከረመው መድረሻ እና መግቢያ እንዳላሳጡህ
ቅድስና የሞለበትን የህይወትህን ታሪክ ያነቡልሃል

ታመህ ያልፀለየልህ አዝነህ ያላፅናናህ የሃይማኖት አባት
ለሸክም የሚከብድ መፅሐፍ ይዘው ቀብርህን ያሰምሩልሃል
ብቻ ሙትላቸው እንጂ ያኔ በጣም ይወዱሃል።

በዚህ አለም ላይ ደሀውንና  ታማሚውን  ወዳጅና ዘመድ ይክደዋል
የተሳካለትን ደሞ ሁሉን ነገር  ሀረግ ሰርቶ ዘመዴ ነህ ይለዋል

በልጅነታቸው የኛ ዘር አይደሉም ተብለው ተጥለው ያደጉ ልጆች
ዛሬ ባለጠጋ እና ሀብታም ሲሆኑ የካዷቸው ያምኗቸዋል

ባለፀጋ ዘመድ የሌለው ደሀ የለም
ሁሉም ባለ ፀጋ የራሱን ደሀ ቢሸከም ያአለም ችግር ይቀንስ ነበር።

ደሀ ሁሉ ደሀ የሆነው ባለ ፀጋ ዘመድ ስለሌለው አይደለም
ብዙ ጊዜ ባለፀጋ ዘመድ ቀብር አሳማሪ እንጂ ኑሮ አሳማሪ አይደለም
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከማድረግ የዘለለ ለሟቹ ምንም ትርፍ የለውም፡፡

ባለፀጋ ለስሙ እና እሱን ብሎ ለሚመጣ 
እኩያ የሚደረግ ግብዣ እንጂ ለሟቹ ምንም ጥቅም የለውም

እኛ ጋር ብቻ ይመስለኛል እርቦት ለሞተ ሰዉ
ቀብሩ ላይ በሬ የሚታረደው

ጎዳና ለኖረው ብዙ ድንኳን ይጣልለታል
ብቸኝነት እንዳለጠቃው ሺዎች ሊቀብሩት ይመጣሉ

ስለዚህ    ተወዳጆች

ሞት ለማንም አይቀርምና ሳትኖሩ አትሙቱ
መኖር ማለት ራስን መሆን ለአላማ መቆም ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የውሸት ዘመን፣ የመብያ ቤተ ክርስቲያን ናት እንብላባት"

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዘባሌ!!
" እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 6:11)
የኔታ ሊቀ ብርሃናት ይባቤ በላይ በዛሬው ዕለት ተፈትተዋል። እርሳቸውን ለማስፈታት የተባበራችሁ ብፁዓን አበው ጳጳሳት (ሁለት ጳጳሳት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንደደከሙ መረጃው ስላለኝ ነው)፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ይስጥልን።

ሊቃውንት የሀገር ሀብቶች ናቸው። በተለይ እንደየኔታ ይባቤ ዓይነት ሁለገብ ሊቃውንት ደግሞ እንደ ዓይን ብሌን የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች ወደላይ አያዳልጣችሁ። ትልቅን ሰው መሳደብ ውርደቱ ለራሳችሁ ነው። ትልቅን ሰው ማክበር ይልመድብን።
ጻዴ
ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤
የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፤
ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፤ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ።😭
                19: ቆፍ።
ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥
በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤
በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።🤲

             [ሰቆ ኤር.2፥18-20]
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 21-ለአዳም ዘር ሁሉ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚሀች ዕለት እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ከተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ከነገረችው በኋላ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገች፡፡
+ አስቀድሞ ከከሃዲውና ከጨካኑ መኮንን ከአርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ አንዱ የነበረው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጢሞቴዎስ ተጋድሎውን በድል ፈጸመ፡፡
+ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረዷት ሴት ላይ ላደረገው ታላቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ፡፡
+ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ያጠመቀውና በኋላም ዲቁናና ቅስና የሾመው አባ ከላድያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም አባ ሜልዮስ ባረፈ ጊዜ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 4ኛ የሆነ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፡- ይህም ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከምስር የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ እርሱም አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ጣዖትን እንዲያመልክ የሚያዝ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ በግዛቱ ሁሉ በተነበበ ጊዜ ይህ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን የአዋጅ ደብዳቤ ቀደደው፡፡ ደብዳቤውን ከቀደደው በኋላ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ‹‹ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም›› ብሎ መሰከረ፡፡
የንጉሡ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል የሆነው መኰንን ይህንን የቅዱስ ጢሞቲዎስን ድፍረት በተመለከተ ጊዜ ይዞ ክፉኛ አስደበደበው፡፡ ዳግመኛም ሰውነቱ ሁሉ እስኪደቅ ድረስ እንዲደበድቡት አዘዘ ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ ፈውሰው፡፡ ከሥቃዩም ድኑ ፍጹም ጤነኛ ሆኖ አደረና በቀጣዩ ቀን ወደ መኰንኑ ቀርቦ አሁንም በድጋሚ ‹‹ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ ሰውነቱንም በመጋዝ ቆራርጦና ሰነጣጥቆ ሰቀለው፡፡ በብረት ምጣድም አድርጎ ሥጋው እንደ ሰም እስኪቀልጥ ድረስ በእሳት አበሰለው፡፡ ከከተማ ውጪም አውጥቶ ጣለው፡፡ አሁንም ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ ፈወሰውና ወደ መኰንኑ ተመልሶ ሄዶ ‹‹ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ ድጋሚ መሰከረ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው በዙያው የነበሩ በጣም ብዙ አሕዛብ በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀዳጅ አደረገው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + ++ + ++ + ++ + ++ + +
የእመቤታችን ዓመታዊ በዓልና በዓለም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ስለመታነጻቸው፡- ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፡፡
እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው፡፡ አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ፡፡ ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ፡፡
ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው፡፡ ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው፡፡ የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት፡፡›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14፡፡ እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡ እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡ ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፡፡ እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸው ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር፡፡
ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
ዳግመኛም በዚህች ዕለት በቂሣርያው በቅዱስ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ፡- ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም ‹‹የልጆቼ ነው አልሰጥም›› አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡
የእመቤታችን ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ባስልዮስ ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሏም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ የከበረች ሥዕሏ ከተቀመጠበት ምሰሶ ሥር ጸበል ፈለቀና በዚኽም ብዙዎች ተፈወሱ፡፡ ይህም የተፈጸመው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት ዕለት በሰኔ 21 ቀን ነው፡፡ የብርሃን እናቱ የእመቤታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
+ የመከራ ጉዞ +

አምኖባት ለተሳፈረባት ሁሉ ሚቀርበት አይደለም አይነቱ ይለያይ እንደሆነ እንጂ ሁሉ በዛ ውስጥ እንዲያልፍ ይሆናል ላጡት የማስተዋል ዕውቀት ከሷ ይወለዳል ባተሌነት እንዲቀር እርሱ ብልህ መምህር ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው ፦" እንደ ብልህ አሰልጣኝ ኹሉንም ነገር እንዲያዩ እያደረገ ያለማምዳቸው ነበር ። መከራ ሲገጥማቸው እንዳይፈሩ ፈተናዎችን መቋቋም እንዲችሉ ክብር ሲያገኙ እንዳይመኩ "። ሰጥታ ባለባት መርክብ ሳይሆን እረፍት ባልሆነባት መርከብ እንዲጓዙ አደረጋቸው ሐዋርያቱን ።

ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ ። ማቴ 3፥23 ተከተሉት ወደ መስቀል በወጣ ጊዜ ሰማዕታት በመከራ መሰሉት መከተላቸው እስከሞት መታመናቸው ነውና ።

የእርሱ እስከሆነ መነኮስነቱ ከመከራ ሚያስመልጠው አይደለም መከራው ለዓለማዊው እንጂ ለእነርሱ እንደማይገባ አድርጎ መረዳት ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች የተገባ እንደሆነ ማሰብ መከተላቸው ከእርሱ መከራ ተሳትፈው ከክብሩ ይሳተፍ ዘንድ ፈቃዱ ሆኗልና ።

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሰኔ 22 2017 ዓ.ም

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
2025/06/30 00:51:24
Back to Top
HTML Embed Code: