Telegram Web
"የውሸት ዘመን፣ የመብያ ቤተ ክርስቲያን ናት እንብላባት"

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዘባሌ!!
4
" እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 6:11)
የኔታ ሊቀ ብርሃናት ይባቤ በላይ በዛሬው ዕለት ተፈትተዋል። እርሳቸውን ለማስፈታት የተባበራችሁ ብፁዓን አበው ጳጳሳት (ሁለት ጳጳሳት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንደደከሙ መረጃው ስላለኝ ነው)፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ይስጥልን።

ሊቃውንት የሀገር ሀብቶች ናቸው። በተለይ እንደየኔታ ይባቤ ዓይነት ሁለገብ ሊቃውንት ደግሞ እንደ ዓይን ብሌን የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች ወደላይ አያዳልጣችሁ። ትልቅን ሰው መሳደብ ውርደቱ ለራሳችሁ ነው። ትልቅን ሰው ማክበር ይልመድብን።
🙏6
ጻዴ
ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤
የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፤
ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፤ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ።😭
                19: ቆፍ።
ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥
በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤
በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።🤲

             [ሰቆ ኤር.2፥18-20]
3
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 21-ለአዳም ዘር ሁሉ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚሀች ዕለት እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ከተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ከነገረችው በኋላ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገች፡፡
+ አስቀድሞ ከከሃዲውና ከጨካኑ መኮንን ከአርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ አንዱ የነበረው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጢሞቴዎስ ተጋድሎውን በድል ፈጸመ፡፡
+ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረዷት ሴት ላይ ላደረገው ታላቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ፡፡
+ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ያጠመቀውና በኋላም ዲቁናና ቅስና የሾመው አባ ከላድያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም አባ ሜልዮስ ባረፈ ጊዜ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 4ኛ የሆነ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፡- ይህም ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከምስር የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ እርሱም አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ጣዖትን እንዲያመልክ የሚያዝ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ በግዛቱ ሁሉ በተነበበ ጊዜ ይህ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን የአዋጅ ደብዳቤ ቀደደው፡፡ ደብዳቤውን ከቀደደው በኋላ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ‹‹ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም›› ብሎ መሰከረ፡፡
የንጉሡ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል የሆነው መኰንን ይህንን የቅዱስ ጢሞቲዎስን ድፍረት በተመለከተ ጊዜ ይዞ ክፉኛ አስደበደበው፡፡ ዳግመኛም ሰውነቱ ሁሉ እስኪደቅ ድረስ እንዲደበድቡት አዘዘ ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ ፈውሰው፡፡ ከሥቃዩም ድኑ ፍጹም ጤነኛ ሆኖ አደረና በቀጣዩ ቀን ወደ መኰንኑ ቀርቦ አሁንም በድጋሚ ‹‹ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ ሰውነቱንም በመጋዝ ቆራርጦና ሰነጣጥቆ ሰቀለው፡፡ በብረት ምጣድም አድርጎ ሥጋው እንደ ሰም እስኪቀልጥ ድረስ በእሳት አበሰለው፡፡ ከከተማ ውጪም አውጥቶ ጣለው፡፡ አሁንም ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ ፈወሰውና ወደ መኰንኑ ተመልሶ ሄዶ ‹‹ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ ድጋሚ መሰከረ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው በዙያው የነበሩ በጣም ብዙ አሕዛብ በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀዳጅ አደረገው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + ++ + ++ + ++ + ++ + +
የእመቤታችን ዓመታዊ በዓልና በዓለም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ስለመታነጻቸው፡- ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፡፡
እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው፡፡ አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ፡፡ ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ፡፡
ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው፡፡ ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው፡፡ የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት፡፡›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14፡፡ እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡ እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡ ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፡፡ እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸው ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር፡፡
ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
6
ዳግመኛም በዚህች ዕለት በቂሣርያው በቅዱስ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ፡- ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም ‹‹የልጆቼ ነው አልሰጥም›› አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡
የእመቤታችን ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ባስልዮስ ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሏም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ የከበረች ሥዕሏ ከተቀመጠበት ምሰሶ ሥር ጸበል ፈለቀና በዚኽም ብዙዎች ተፈወሱ፡፡ ይህም የተፈጸመው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት ዕለት በሰኔ 21 ቀን ነው፡፡ የብርሃን እናቱ የእመቤታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
4🙏2
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
+ የመከራ ጉዞ +

አምኖባት ለተሳፈረባት ሁሉ ሚቀርበት አይደለም አይነቱ ይለያይ እንደሆነ እንጂ ሁሉ በዛ ውስጥ እንዲያልፍ ይሆናል ላጡት የማስተዋል ዕውቀት ከሷ ይወለዳል ባተሌነት እንዲቀር እርሱ ብልህ መምህር ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው ፦" እንደ ብልህ አሰልጣኝ ኹሉንም ነገር እንዲያዩ እያደረገ ያለማምዳቸው ነበር ። መከራ ሲገጥማቸው እንዳይፈሩ ፈተናዎችን መቋቋም እንዲችሉ ክብር ሲያገኙ እንዳይመኩ "። ሰጥታ ባለባት መርክብ ሳይሆን እረፍት ባልሆነባት መርከብ እንዲጓዙ አደረጋቸው ሐዋርያቱን ።

ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ ። ማቴ 3፥23 ተከተሉት ወደ መስቀል በወጣ ጊዜ ሰማዕታት በመከራ መሰሉት መከተላቸው እስከሞት መታመናቸው ነውና ።

የእርሱ እስከሆነ መነኮስነቱ ከመከራ ሚያስመልጠው አይደለም መከራው ለዓለማዊው እንጂ ለእነርሱ እንደማይገባ አድርጎ መረዳት ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች የተገባ እንደሆነ ማሰብ መከተላቸው ከእርሱ መከራ ተሳትፈው ከክብሩ ይሳተፍ ዘንድ ፈቃዱ ሆኗልና ።

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሰኔ 22 2017 ዓ.ም

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ቅዱስ ቁርባን"
...
✍️ቁርባን ምንድነው? ቁርባን ማለት፦
1.  አምሃ (መንፈሳዊ ስጦታ) ማለት ነው::
2. ቁርባን የክርስቶስ እውነተኛ ስጋ እና እውነተኛ ደሙ ነው። (ዮሐ.6÷55) ክርስቶስ ለእኛ ያለውን ፍቅር የገለፀልን ቅዱስ ቁርባኑን በመስጠት ነው።
3. ቁርባን ማለት "መቅረብ" ወደ ክርስቶስ መቅረብ ነው
4. ቁርባን ማለት አንድነት ማለት ነው። ጌታ ከእኛ ጋር እንዲኖር እኛም ከጌታ ጋር እንድንኖር የምናደርገው ነው። "ሥጋዬን የሚበላ፡ ደሜንም የሚጠጣ፡ በእኔ ይኖራል፡ እኔም በእርሱ እኖራለሁ" (ዮሐ. 6÷56)
5. ቁርባን መስዋዕት ነው። መስዋዕቱም መስዋዕቱን አቅራቢውም ራሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
6. ቅዱስ ስጋና ክቡር ደሙ መድኀኒት ነው።

==//==
👉ከመቁረብ በፊት ምን ያስፈልገናል:-
1. ንስኀ መግባት
2. ቅዳሴ ሲጀመር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያልነበረ ሰው መቁረብ የለበትም። (ህፃናትንም ጨምሮ)
3. በትዳር ላይ ላሉት ሶስት ቀን ከቁርባን በፊት እንዲሁም ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ ለሁለት ቀን ከፈቃደ ስጋ መራቅ አለባቸው።
4. ንጹህ ልብስ መልበስ (ከተቻለ ነጭ ልብስ)
5. ለአዋቂ ሰው ከመቁረብ በፊት ለ18ሰዓት መጾም ይገባል

✍️በመቁረብ ጊዜ ምን እናድርግ?
1. ድርገት ሲወርዱ ማለትም ካህናት ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ይዘው ወደ እኛ ሲቀርቡ እጅ እንነሳለን(እንሰግዳለን)
2. "ቅዱስ ስሉስ'ን" መድገም ያስፈልጋል (እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለም ዓለም።)
3. ቅዱስ ስጋውን ስትቀበሉ አንድ ጊዜ "አሜን" በሉ። ክቡር ደሙን ስትቀበሉ "ሁለት" ጊዜ አሜን በሉ። ጌታ ሁለት ጊዜ ደሙ ፈሷል (ከመሞቱ በፊትና ከሞተ በኋላ ጎኑን በጦር በወጉት ጊዜ)
4.ሴቶች ክንንቡን ያውርዱ
5.ቅደም ተከተል ጠብቆ መሰለፍ ከ40ቀን ህጻን ጀምሮ እስከ ሽማግሌ...

✍️ከቁርባን በኋላ በዕለቱ :-
1. እጅንና እግርን መታጠብ አይገባም
2. ልብስን መገላለጥ አይገባም
3. ምራቅን መትፋት አይገባም
4. ስግደት አይገባም
5. ሩቅ መንገድ መሄድ አይገባም

✍️የቆረበ ሰው:-
1.ካልቆረበ ሰው ጋር ሰላምታ መለዋወጥ÷ መሳሳም  ይቻላል።
2. ካልቆረበ ሰው ጋር መብላት ይችላል።
3. ምግብ ማስተረፍ ይችላል።
4. የቆረበ ሰው ብቻውን መሄድ (ብቻውን መሆን) ይችላል።
5. የቆረበ ሰው "በቁርባን" ማግባት ይችላል።
///
✍️ቁርባን ከ40 እና 80 ቀን ህፃን ጀምሮ በሁሉም እድሜ ላሉና ንስኀ ለገቡ÷ በክርስቶስ ላመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ  የቀረበ የዘለዓለምን ህይወትን የሚያስገኝ (ዮሐ.6÷54) በእግዚአብሔር የተዘጋጀ ሰማያዊ ግብዣ ነው።

"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።" (ኢሳ. 25÷ 6)
///
"ኑ! ጊዜያችን ሳያልቅብን ንስኀ እንግባ÷ የጌታን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም እንቀበል፤ ወደ እግዚአብሔር ህብረት እንግባ ፤ የዘላዓለምን ሕይወትም እንውረስ::"

(የቅድስት ቤተክርስቲያን የዘወትር ጥሪ)
12🔥1
ሁሉም ለገንዘብ ይገዛል ።
(ምሳሌ 10፥19)

በእኛ ዘመን፦
ለጥበብ ሳይሆን ለገንዘብ
ለዕውቀት ሳይሆን ለሀብት
ለጽድቅ ሳይሆን ለወርቅ
ለሕይወት ሳይሆን ለውበት
ለፍቅር ሳይሆን ለነገር
ለሰላም ሳይሆን ለሕመም
ለክብር ሳይሆን ለነውር
ለመንፈሳዊው ሳይሆን ለሥጋዊው
ለማያልፈው ሳይሆን ለሚያልፈው
ለኗሪው ሳይሆን ለቀሪው
የሰው ዘር ተገዝቷል ።

ለገንዘብ ከመገዛት ይልቅ ለእግዚአብሔር መገዛት እጅግ ክብር ነው።
ምክያቱም ለእግዚአብሔር ከተገዙ ከእግዚአብሔር ዕቅፍ ሥር ካልወጡ እግዚአብሔር ከሀብት ሁሉ ባለቤት ነውና የሚጠቅመንን ይሰጠናልና ነው ።
ለገንዘብ ስንገዛ ግን እግዚአብሔርን እንተዋለንና
ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል የተናገረ፦
" ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።"
(የማቴዎስ ወንጌል 6:24)
Forwarded from Ei Du 💃 via @Quality_Move_Bot
🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️🀄️ሉን!👇

https://www.tgoop.com/+UqU8zCoHqyw2NzQ0
Forwarded from 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
Forwarded from 🔥አረፍ አሪፍ folder disk channel🔥
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

በቤቲንግ ብር እየተበላችሁ የምትገኙ በሙሉ ይሄ ቻናል ለናንተ ነው ምርጥ ቲፕ የምታገኙበትን ቻናል ይዘን መጥተናል

ማየት ማመን ነው
🏆👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እግዚአብሔርን_መምሰል!!!

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሰው ከሆነ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል የጸጋ አማልክት ልንሆን ይገባል!!!
(ዮሐ.10:35::መዝ.ዳዊ.81:6፡፡)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ትሑት ከሆነ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ልዑላን ልንሆን ይገባል!!! (ዮሕ.12:32::ማቴ.11:29::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ድሃ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ሀብታሞች ልንሆን ይገባል!!!
                (2ኛ ቆሮ.8:9::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ምድራዊ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ሰማያውያን ልንሆን ይገባል!!!
          (1ኛ ቆሮ.15:48::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ግዙፍ ከሆነ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ረቂቃን ልንሆን ይገባል!!!
            (ዮሐ.1:14::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል አላዋቂ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል አዋቆች ልንሆን ይገባል!!!
(ዮሐ.11:34::ዮሐ.5:6::1ኛ ቆሮ.2:16)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሀገር ከለለው እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ባለ ሀገሮች ልንሆን ይገባል!!!
(ማቴ.2:13::ኤፌ.2:19::ዕብ.12:22::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ቤት የለለው ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ባለቤቶች ልንሆን ይገባል
(ዮሐ.14:3::ማቴ.8:22::ፊልጵ.3:20::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ርሑብ ከተባለ እኛ ለእግዚአብሔር ስንል በሥጋ ወደሙ ልንጠገብ ይገባል!!!
(ማቴ.4:2::ዮሐ.6:54::1ኛ ቆሮ.11:26 ማቴ.26:)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ስደተኛ ከተባለ እኛ ለእገዚአብሔር ስንል ከስደት ልንመለስ ይገባል!!!
                 (ማቴ.2፡20::ኤፌ.2:19::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ወደዮርዳኖስ ከሄደ እኛ ለእግዚአብሔር ስንል ወደማየገቦ ልንሔድ ይገባል!!!
            (ማቴ.3:13፡፡ዮሐ.3:5::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ወደምድረ በዳ ከሔደ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ከምድር በዳ ልንመለስ ይገባል!!!
                  (ሉቃ.4:2::ያዕ.4:8::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ከጾመ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ከክፉ ነገር ልንጾም ይገባል!!(ማቴ.4:2::ሉቃ.4:3::ማቴ.9:15::ማር.2፡19::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ባሕታዊ ከሆነ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል አንድ ልንሆን ይገባል!!!
(ዮሐ.8:1::1ኛ ቆሮ.10:17::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ድንግል ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ደናግላነ ሥጋ ወነፍስ ልንሆን ይገባል!!!
(2ኛ ቆሮ.11:2::1ኛ ቆሮ.7:32::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል በሰይጣን ከተፈተነ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ሰይጣንን ድል ልንነሳ ይገባል!!!
(ሉቃ.4:13::ሉቃ.10:17::ማር.16:17::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ከአስተማረ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ልንማር ይገባል!!!
(ማቴ.5:2::ማቴ.7:24::ዮሐ.6:45::ኢሳ.54:13::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሐረገ ወይን ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ቅርንጫፎች ልንሆን ይገባል!!!
                  (ዮሐ.15:1::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ኖላዊ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል አባግዕ ልንሆን ይገባል!!!
(ዮሐ.10:14::1ኛ ጴጥ.5:4::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል አንቀጽ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ወደበሩ ልንገባ ይገባል!!!
              (ዮሐ.10:9::ዮሐ.14:6::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሙሽራ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ሙሽሪት ልንሆን ይገባል!!!(ኤፌ.5:32::ዮሐ.3:29፡፡2ኛ ቆሮ.11:2፡፡)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሐዋርያ ከተባለ እኛም ለእርሱ ስንል ደቀመዛሙርት ልንሆን ይገባል!!!
(ዕብ.3:1::ዕብ.6:20::ዮሐ.13:35::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሊቀካህናት ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ካህናት ልንሆን ይገባል!!!
(ዕብ.4:14::ዕብ.5:10:1ኛ ጴጥ.2፡5:ራእ.20:6)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ተኛ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ንቁዎች ልንሆን ይገባናል!!!
             (ማቴ.8:24:፡2ኛ ጢሞ.4:5::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሕይወት ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ልድን ይገባል!!!
(ዮሐ.11:25::1ኛ ቆሮ.1:18-24::1ኛ ጴጥ.4:::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ትንሳኤ ከተባለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል ትንሳኤ ልቡና ልንነሳ ይገባል!!!
                  (ዮሐ.6:40::)
#እገዚአብሔር ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ ከዋለ እኛም ለእርሱ ስንል መስቀል ልንሸከም ይገባል!!!
(ማቴ.10:38፡፡ገላ.6:14::2ኛ ቆሮ.4:10::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ሐሞት ከጠጣ እኛም ለእርሱ ስንል ደሙን ልንጠጣ ይገባል!!!
                        (ዮሐ.6:54)
#እግዚአብሔር ለኛ ሲል አምላኪየ ካለ እኛም ለእግዚአብሔር ስንል አቡነ ልንለው ይገባል!!!
(ማቴ.27:47::ዮሐ.20:17::ሮሜ 8:16::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ሲል እናቴን አደራ ብሎ ከሰጠን እኛም ለእግዚአብሔር ስንል እመቤታችንን እናቴ ብለን ልንቀበል ይገባል!!!
                 (ዮሐ.19:26::)
#እግዚአብሔር ለእኛ ብሎ ከሞተ እኛም ለእግዚአብሔር ብለን ሞትን ልናሸንፍ ይገባል!!!
(2ኛ ጢሞ.2:1::1ኛ ቆሮ.15:54::2ኛ ቆሮ.2:16::)

#እግዚአብሔር ለእኛ ብሎ ከተቀበረ እኛም ለእግዚአብሔር ብለን መቃብርን ልናሸንፍ ይገባል!!!

#እግዚአብሔር ለእኛ ብሎ ጎኑን ከተወጋ እኛም ለእግዚአብሔር ብለን በማየ ገቦ ልንጠመቅ ይገባል!!!
(ቲቶ 3:5::ኤፌ.5:26::ማር.16:16::ዮሐ.19:34)

#እግዚአብሔር_ከእኛ_በእኛ_ለእኛ_ስለእኛ_እንደእኛ ሁሉን ሆነ!!!

#እግዚአብሔር ከእኛ ተወልዶ ለእኛ ለመካሥ በእኛ ሰቃይነት እንደእኛ ወንጀለኛ ተብሎ ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ሁሉን ሆነ!!!

❖እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው እንላለን!!!
             ❖አ.ዘ.ያዕቆብ፡፡
   ©ጌዴዎን ዘለዓለም::
2
🌷💒ክርስትና ለተቀጠቀጠው ሸንበቆና ለሚጨሰው ጧፍ ተስፋ ሰጥቷል።እግዚአብሔር
የተቀጠቀጠ ሸንበቆን ሰብስቦ በአንድ ለማሰርና የሚጨስ ጧፍን ለማቀጣጠል
አይሳነውም።ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ለሰዎች ተስፋን ይሰጥ ዘንድ "የደከሙትን
እጆች አበርቱ" (ኢሳ.35:3) በማለት ተናግሯል።ይህን በማለቱም ለደከሙት እጆችና
ለላሉት ጉልበቶች ተስፋ ሰጥቷል።
 በክርስትና ተስፋ የተሰጠው ለሁሉም ነው።ለግለሰቦች : ለተቋሞች : ለአብያተ
ክርስቲያናት : ለሀገሮችና ለመላው ዓለም ነው።እግዚአብሔር በማንኛውም ዘመን
ሰውን ስለሚፈልገው በዚህ ሁላችንም ተስፋ አለን።ይህ በአማኞች ዘንድ ያለ ተስፋ
ነገሮች ቢወሳሰቡና ከባድ ቢመስሉም እንኳ በጭራሽ አይላላም።
ነቢዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ተስፋ ነበረው። (ዮና. 2:5)
የማይድን በሽታን በማዳን ውስጥ ተስፋ አለ። (ዮሐ. 5:8)
ልጅ ባለመውለድ ውስጥ ተስፋ አለ።(ኢሳ. 54:1-3)
ነገሮች ከባድ የማይቻሉና አስቸጋሪ ቢመስሉም እንኳን ከእግዚአብሔር የተሰጡ
ተስፋዎች አሉን። (ማር. 10:27 ; 9:23 ፊልጵ.4:13)
በክርስትና ተስፋ ወሰን ስለሌለው አንድ ክርስቲያን በችግር በመከራና በጭንቅ
ውስጥ ወድቆ ወይም ለፈተናዎቹ መፍትሔ ያጣላቸው ሲመስል የተስፋ ጸጋ
እንዳለውና እንደሌለው ለማወቅ ራሱን ይፈትሻል።በዚህ ጊዜ በተስፋው ውስጥ
እግዚአብሔር ለችግሮቹ ሁሉ ብዙ መፍትሔዎች እንዳሉትና ሰዎች ዘግይቷል ብለው
በሚያስቡበት ሰዓት በእርግጥ እንደሚመጣ ይታወቀዋል።
 በሕይወት ካሉት ጋር ኀብረት እንዳለን ሁሉ በሞት ከተለዩት ጋርም ኀብረት አለን
!!ሞት ከሌሎቹ የክርስቶስ ብልቶች ጋር አይለየንም እነርሱን በግልና በጉባኤ
ጸሎታችን ውስጥ እናስባቸዋለንና ። እነርሱም በምድር ላይ የሚኖሩንን የቆይታ ቀናት
በሰላም አጠናቀን ከእነርሱ ጋር እንድንገናኝ አጥብቀው ይጸልዩልናል ።ሐዋርያው
ቅዱስ ዮሐንስ የአማኞችን ኀብረት አስመልክቶ የተናገረው ቃል እንዲህ ይላል ፦ "
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን #ኅብረት_አለን
። የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ። 1ኛ ዮሐ 1*7
 እምነት ባህርን ከፍሎ ያሻግራል፣በበረሃ መካከል ከሚገኝ ዓለትም ውኃ አፍልቆ
ያጠጣል። በዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለው።
 "በማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ እግዚአብሔርን ማንሣትና በችግር ውሥጥ ሥሙን መጥራት
ተማር፡፡ በራሥህ ማስተዋል ተደግፈህ ችግሮችን ለመጋፈጥ አትሞክር፡፡

         አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
3
መልሰኝ

ጌታ ሆይ እንድትወደኝ እለምንሃለሁ ብዬ በፍጹም አልጠይቅህም እንደ ምታፈቅረኝ  እስከ ኃጢአቴ እንደ ተሸከምከኝ ጠንቅቄ አውቃለሁና። አባቴ ሆይ እኔ የምለምንህ አንተ ማፍቀር የሚችል ልብ እንድታድለኝ ብቻ ነው። ጌታ ሆይ አንተን መውደድ ልቤን በፍቅርህ መሙላት እፈልጋለሁ። ከንቱ ነገሮች የሞሉትን ልቤን አጽድተህ የፍቅርህ ዙፋን አንተን በመውደድ እንድታስጌጠው እማጸንሃለሁ።

ጌታ ሆይ ለአንተ ምኑን እደብቅሃለሁ ከአንተ ይልቅ የምወዳቸው ብዙ ኃጢአቶች አሉ። ሕይወቴን የተቆጣጠረው ዓለማዊነት በእርኩሰት ፍቅር ጥሎኛል። ኃጢአት ሰላሜን ቢነሳኝም እርሱን ከመስራት ግን ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም። በአመጽ መንገድ እርቄ ከመሄዴ የተነሳ በነውሬ የማጌጥ ደንዳና የዲያብሎስ ባሪያ ሁኛለሁ። ኃጢአቴ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ የበዛብኝ እኔ እጅጉን እፈራለሁ። በደሌን ባሰብኩ ጊዜ ልቦናዬ ይደነግጥብኛል። ወደ አንተም እማጸናለሁ። ተንበርክኬም እለምንሃለሁ ። የነጻነት ሕይወት ወደ ሚሰጥ ወደ ፍቅርህ ሙላት ከፍታ አውጣኝ። በኃጢአት ጨለማ የጠቆረ ልቤን በፍቅርህ ብርሃን አስጌጠኝ።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ እንካ እጄን ያዘኝ እኔ አቅም አጥቻለሁ በራሴ ጉልበት ከኃጢአት መውጣት አልችልም እባክህን ጎትተኝ። ለዓለማዊነት የተሰነፈውን እኔነቴን ፈውስ። ወደ ከፍታ ልወጣባቸው የተሰጡኝን ግን በኃጢአት የተሰበሩ ክንፎቼን ጠግን። ለምን እንደወደድከኝ በእድሜዬ ላይ ይችን ቀን ለምን እንደ ጨመርከኝ ሳስበው በጣም እገረማለሁ ይመለሳል ብለህ በትዕግሥት እኔን መጠበቅን ሳስብ እደነቃለሁ። ፍቅርህ ለእኔ ያለህ ውድ ከአእምሮ በላይ ነው። ለፍቅርህ የምመልሰው ጥቂት መልካም ምግባር የሌለኝ ከንቱ መሆኔን ሳስብ በራሴ እናደዳለሁ።

ጌታ ሆይ እባክህ ተመለስ አትበለኝ ። እኔ በራሴ ከኃጢአት መመለስ የምችልበት አቅም የለኝምና ። በኃጢአት የደከምኩ ልምዝምዝ መሆኔን አንተ ታውቀለህ። ግን እንዲህ እልሃለሁ “ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።” ኤርምያስ 31፥18

    
          
7
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን "

ሃይማኖተ አበው
እንቁ መምህራችን የሆኑት እዮብ ይመኑ ትምህርቶች ለማግኘት ከታች ናለድ ሊንክ ይግቡ❤️


የይቱብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ
      👇👇👇
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
1
2025/07/12 06:03:54
Back to Top
HTML Embed Code: